February 11, 2022
16 mins read

ኦሮሚያ የሰው ቄራ!?-ከቴዎድሮስ ሐይሌ

273700792 1561919317526240 765613491810836887 nየዋህና ደጉ የኦሮሞ ሕዝብ ከአብራኩ ወጣን በሚሉ 1 ፐርሰንት በማይሞሉ  ጽንፈኛ ሞት ነጋዴ ፖለቲከኞችክብሩ ተገፎ ስሙ እረክሶ እንዲታይ እያደረጉት ነው:: ኦሮሚያ ለውጥ የተባለው ከመጣ ወዲህ ሰው ወጥቶ የማይገባበት ስራ መስራት የከበደበት የፖለቲካ ምህዳሩ የጨለመበት ልማት የሚወድምበት ሰው የሚታረድበት ቄራ ሆኗል:: እርግጥ ነው አብዛኛውን ኦሮሞ እንደ ሕዝብ ባይወክልም የፖለቲካ ኤሊቱና የመንግስት አመራሩ ከዚህ የሞት ንግድ የለበትም አይባልም::

ከተጎጂዎቹ አንደበት እንደምንሰማውና የጽንፈኛ ኦሮሞ ፖለቲከኞችን ስሜት በግልጽ እንደምናውቀው የሚፈጸመው ሰቆቃ የዘፈቅደ ሳይሆን በእቅድና በፕላን የሚካሄድ ነው::  የምናባዊቷ ኦሮሚያ አላሚዎች የጥላቻጠማቂ ጎምቱ ፖለቲከኞች ለዘመናት ያካሄዱት በተዛባ ትርክት ላይ የተመሰረተ ታሪክ ሳያላምጥ የሚውጥ ትውልድን ፈጥሯል:: ትውልዱም የተጋተውን የጥላቻ ሂሳብ በበቀል ለማወራረድ ተግቶ ሕፃን ከአዋቂ ሳይመርጥ እንደ ፍሪዳ እያረደ ነው::

የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቀዳሚና ዋና ፍላጎቱ ሰላም ልማትና እድገት እንጂ ሁከትና ብጥብጥ አይደለም:: ኢትዮጵያ እንደ ሃገር በየዘመኑ የተጋረጠባትን አደጋ ተቋቁማ ዛሬ የደረሰችበት ደረጃ እንድትደርስ የኦሮሞ ሕዝብ ተሳትፎ እጅግ የላቀ ነው:: ተማርን ባይ ደንቆሮዎች ይህንን ታሪክ ክደው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በልማቱም በጉዳቱም እኩል ተሳትፎ የነበረውን የኦሮሞ ሕዝብ በተዛባ የሃሰት ትርክት ፈጥረው ተበዳይ ሆኖ እንደኖረ የሚያቀርቡት ውንጀላ ሕዝቡን ቅንጣት ባይጠቅምም ስልጣንና ጥቅምን አስልቶ ለተነሳው የፖለቲካ ነጋዴ  በግርግር ግዜያዊ ውጤት አስገኝቶለታል::

በዚህ ድንበር አልባ የግሎባላይዜሽን ዘመን ንግድና ሸቀጥ ያለገደብ በሚንቀሳቅስበት አለም ውስጥ የኦሮሞ ኤሊት በፈጠረው የጥንታዊ ጋርዮሽ ባርቤሪክ ርዕዮት ብዙ ኢንቨስትመቶች በኦሮሚያ እንዲወድሙ ባልሃብቶችም ፈርተው እንዲሸሹ ተደርገዋል:: በዛሬው አለም እንኳን በድሃ ሃገር አይደለም በበለጸጉት ሁሉ ነገር የተትረፈልቸው ሃገራት አምራቾችና ነጋዴዎች ወደ ሃገራቸው እንዲመጡ ከማግባባት አልፈው ድጎማ በሚሰጡበት የኢኮነሚ አለም ኦነጋዊው አራዊታዊ አስተምሮ ልማትን ማውደምና አልሚን ማሳደድ ስኬታማ የፖለቲካ መንገድ አድርጎታል::

ኦሮሞው ጠቅላይ ሚንስትር መሪነቱን ከጨበጠ ወዲህ በታሪክ ታይቶ የማያውቅ ብሄር ተኮር የመከራና ጭፍጨፉ ጽልመት ውስጥ  ሃገራችን ገብታለች:: በኦሮሚያ ከሐረር እስከ ባሌ ከሻሸመኔ እስክ ወለጋ ሰው ታረደ በቁሙ ተሰቀለ ሃብት ወደመ በርካቶች ሞተው በሺዎች ተፈናቀሉ:: አጥፊዎች ሲቀጡ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮች ሲጠየቁ አላየንም አልሰማንም::

የሁሉም ምክንያት በሃገሪቱ የቆየው የዘር ፖለቲካ የፈጠረው ፖለቲካ ነው ያሉትን ሕዝብ አምኖ በትግዕስት ተቀበለ::  የጥላቻ ምንጭ የሆነው ሕወሃት ጥሎት የሄደው መርገምት በሂደት ይጠራል በሚል ጊዜ ቢሰጠውም ዛሬም ከጽልመቱ ልንወጣ ቀርቶ እየባሰ ከመሄድ አልተገታም::

በተለይ በወለጋ የተሰማራው አራጅ የጭራቅ መንጋ የሚፈጽመው ሰቆቃ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ይፈጸማል ተብሎ ለማመን የሚከብድ ሆኗል:: ወለጋ ጎርፍ ሆኖ ሊውጣት እስኪቃረብ በንጹሃን ምስኪን አርሶ አደር የአማራ ተወላጆች እንባና ደም ተሞልታለች:: ድሆችን በመግደል አርሶ አደርችን በማፈናቀል ለኦሮሞ ሕዝብ ሊያተርፉለት የፈለጉት ከቶስ ምንድን ነው? በፈጠራ ትርክት ተመስርቶ አንድን ሕዝብ ጠላት አድርጎ በጅምላ ለመፍጀት ይቻላልስ ወይ? የወለጋው የሰው እርድ ማን ነው የሚያቆመው? ኦሮሚያስ የሰው ቄራ ሆና የምትቀጥለው እስከመቼ ነው::

ትግራይ ሽምግልና ተቃሎ  መካሪ ተንቆ ከትዕቢት ወጥቶ አስተውሎት ኖሮት የሚያስብ ምሁርና  ቅንነት ያለው አባት በማጣቷ ትውልዷን አስጨርሳ ወደ ድንጋይ ዘመን ተረማምዳለች:: በሸፍጥ የዶለደመ በቁስ ሰቀቀን የጠውለገና በጀብደኝነት ቅራሬ በሰከረ የፖለቲካ አመራር ዙሪያው ካሉ ጎረቤት ወንድሞቹ የትግራይን ሕዝብን አቃቅረውታል:: ከእንግዲህም  የትግራይ ሕዝብ  ትከሻው ላይ የሰፈረውን የወያኔ መንፈስ ከጫንቃው አውርዶ እውነታውን ተቀብሎ ከወገኑ የኢትዮጵይ ሕዝብ ጋር እስካልተስማማ  ድረስ መቼም ቢሆን ሰላሙን እያገኝም:: ጥቂት ሌቦችንና ወንጀለኞችን ለመሸሸግ ሲባል በትግራይ እንደ ሆነው ሁሉ ቦቅቧቃ ኦነጋውያንን የጨነገፈ ሕልም ለማሳካት የኦሮሞ ሕዝብ የትግራዩን ስህተት እንደማይደግም ብዙዎች እምነታችን የጸና ነው::

ብልህ ከሰው፣ ሞኝ ከራሱ ይማራል›› እንደሚባለው ከትግራይ ልሂቃን ስህተት የኦሮሞ ሕዝብ ሊማር ይገባል:: የኦሮሞ ህዝብ በግዜ ሊነቃ በስሙ የሚነግዱትን አትመጥኑኝም ይበል:: ጥቂት በማንነት ቀውስ የጠወለጉ በቅልውጥ ርዕዮት የቋመጡና በበታችነት ስነልቦና የታወሩ ፖለቲከኞች  ከንቱ ፕሮፓጋንዳ ዙሪያህን ካሉ ህዝቦች አባልተው መንደርህን የጦርነት አውድማ ሳያደርጉት በፊት አይሆንም በላቸው:: ሕውሃት በትግራይ ላይ ውድመትን እንዳመጣ የማይረቡ ፖለቲከኞች መንደርህ የጦር አውድማ ሳያደርጉት በፊት ነቅተህ ቁም::

አካባቢህ የልማት መዋያ እንዳይሆን በቅዬህ  ኢንቨስተር እንዳይመጣ ባለፈው የተሰራብህ መጥፎ ሴራ እንዳይደገም በቃኝ በል:: የኦሮሞ ሕዝብ ዙሪያው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ብሄሮች የተጋመደና በጉርብትናም ለዘመናት በሰላም አብሮ የኖረ ማህበረሰብ ነው:: በኦሮሞ ስም የሚቀነቀነው ጽንፈኛና ሴጣናዊ ዘመቻ ምንም በዋናነት አማራውና ጋሞው ላይ ቢያተኩርም የአብዛኛውን ብሄሮች ደህንነት ጥያቄ ላይ የጣለና ስጋት ውስጥ የከተተ ሁኔታን ፈጥሯል:: በኦሮሚያ ውስጥ ያለው የሰው እርድ ቁጣን ቀስቅሶ ወደለየለት ግጭት ካመራ ኦሮሞው ዙሪያውን ካሉ ሕዝቦች ጋር ጭምር የከፉ ደም መፉሰስ ውስጥ ሊገባ እንደሚችል አስተዋይ ኦሮሞዎች ሊገነዘቡት ይገባል::

በተለይ በወለጋ ትላንት በሕወሃቶች እናት ልጇ እሬሳ ላይ እንድትቀመጥ የጭካኔ ድርጊት የተፈጸመባት ሴት ታሪክ ከማንም ሕሊና የማይጠፉ በደል ነበር:: ወለጋ ያዋረዳትን ልጆቿን በግፍ የገደለባትን ሕወሃት መርጣ መጠጊያ የለሽ ምስኪን የአማራ ተወላጆች አንገት ላይ ቢላ ማሳረፏ ታሪኳን ከማቆሸሹ ትውልዷን አንገት ከማስደፉቱም በላይ ቢዘገይም ከሰውም ይሁን ከፈጣሪ የእጇን ማግኘቷ ፍጹም አይቀሬ ነው::

ክልሉን የሚመራው የኦዴፓ ኦነግ አመራር ቀን ደማሪ ሌሊት ቀናሽ የአፈናቃይነት የፖለቲካ ሂሳብ ይቀምራል:: ሲመቸው በግላጭ ሸኔን ያስታጥቃል ምልምሎቹን ቆሞ ያስመርቃል:: ሳይሆንለት ሰራዊት ያሰማራል :: ውስጣዊ ችግር ሲንጠው ቀውስ ያከፉፍላል የጦስ ዶሮ ይፈልጋል:: አዲስ አበባ ሃገር ይመራል:: ወለጋ እና ጉጂ ላይ ሃገር ያፈርሳል:: ኦዴፓ ሃገር እየመራ ሌላ ሃገር ይመኛል:: ዙፉን ላይ ቁጭ ብሎ የምድጃ ዳር ሃሳብ ያራምዳል:: ጮማ እየቆረጠ ደረቅ ቂጣ በሚበሉት ይቀናል:: በ21 ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ቆሞ በስብስቴ ዘመን ትርክት ይቆዝማል:: ግራ የተጋባ ምን እንደሚፈልግ ወዴት መሄድ እንዳለበት የማያውቅ ድንጉጥና መንፈሰ ሰባራ ጥርቅም በታሪክ አጋጣሚ ያገኘውን ሃገር የመምራት እድል መጠቀም አቅቶታል::

ኦዴፓና የኦሮሞ ልሂቅ ሃገር የመምራት እድሉን ያገኘው ሕዝብን የሚማርክ አጀንዳ ወይም  ተጽዕኖ ማሳደር የሚችል ወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ ቁመና ኖሮት ሳይሆን በአንድ ዶር አብይ መልካም ቃልና ስብዕና በሌሎች የኢህአዴግ ድርጅቶች  ትብብር  ዛሬ ላሉበት ደረሱ እንጂ እንኳን ሃገር ለመምራት እድል ሊያገኙ ከመንደራቸውም ባልወጡ ነበር:: ሽመልስ አብዲሳን ከንግግሩ እስከ ቀፈቱ አስቀያሚነት ኦሮሞውን ጨምሮ እጅግ የሚንቀው ሕዝብ ዶር አብይን ሲል እንዲቀበለው ግድ ብሎት እንጂ ለመሪነት ብቁ ሆኖ አይደለም:: የዳውድ ኢብሳ ጉራ የሌንጮ ለታ መቀማጠል ሃምሳ አመት ተሸክምውት እላያቸው ላይ ዝጎ በቀረው ጠመንጃ ድል ነስተው ሳይሆን በመላው ሕዝብ ትግል በተገኘ ለውጥ ነው ሃገር ቤት መግባት የቻሉት::ኦነግ ሃምሳ አመት ሙሉ ከምርኮና  አንድም ቀን ጀግኖች የዋሉበት ቦታ ያልዋለ ወኔ በሚጠይቅ ግንባር መሳተፍ ያልቻለ አሮጊት ገዳይ እሬሳ በላችና ባልታጠቀ ህዝብ ላይ የሚያቅራራ ቦቅቧቃ እንኳን ህዝቡን እራሱንም አያድንም:: ኦነግ ሸኔ (ሸሌ) እያለ ድሆችን መግደሉ በዚህ አይቀጥልም::

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ መግደል መሸነፍ ነው በሚል መሪ ቃሉ ሰላማዊ መሪ እንዳልመሰለ መግደል አይደለምሰው ማረድን ድርጅቱ ኦዴፓ ስፖንሰር ማድረጉን አላውቅም ሊል አይችልም::  +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++እንደ ባልቴት ወሬ እያሳመረ ሕዝብን እያወናበዱ መምራት ለግዜው እንጂ ለዘለቄታው የሚበጅ አይደለም:: ጠቅላዩ ከአጉል ብልጣ ብልጥነት ወጥቶ የሃቀ መስመር ይዞ መፍትሄ መሻቱ ለሱም ለድርጅቱም ለሃገሪቱም የሚበጅ መሆኑን በግዜ ቢረዳው መልካምነው:: ኦነግ ሆነ ሸኔ ቁርጠኝነቱ ካለ በሳምንት ዘመቻ ከስሩ መንቀል የሚከብድ አይደለም:: ከሺህ ቃላትና ከደርዘን ተረት አንዲት አነስተኛ ተግባር እንደሚበልጥ ጠቅላዪ ሊረዳ ይገባዋል:: ዶር አብይ ዛሬ ላይ ድርሪቶ ንግግሩም ሆነ የማይጨበጥ ተስፉው ሃገሪቱ እየሰመጠችበት ካለው የቀውስ ባህር ሊታደጋት አይችልም:: እውነት ቅንነት ቆራጥነትና ተግባር ብቻ ነው መዳኛችን::

ኢትዮጵያ በላዪ ላይ ሕወሃት የቀበረው ፈንጂ በየግዜው እያቆሰላት መቀጠል አትችልም:: ወይ ተያይዘን እንድናለን አለያም እንጠፉለን:: ኦሮሚያ የአፈና ቀጠና የሰው ማረጃ ቄራ ሆኖ ፈጽሞ ሊቀጥል አይችልም:: የኦዴፓ ቁማሩም ማደናገሩም የመሪውም የተስፉ ቃል ሕዝብን ሊታደግ አልቻለም:: ጽዋው እየሞላ የህዝብም ትዕግስት ወደ ማለቁ ተቃርቧል:: በሰላም ህዝብ መፍትሄ ካላገኘ ተገዶ እራሱን ወደ መከላከል ይገባል:: እጣችን ሞት ከሆነ አበው እንደሚሉት ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉ አንዱን ግባ በለው እንዳለው በዚህ አያያዙ የትግራዩ ጦርነት በኦሮሚያም እንዳይደገም ሁሉም ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል::

ኢትዮጵያ ዛሬም ለዘላለም በክብር ትኑር!!!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop