ዐብይ አህመድ፡ በማንነቱ ምክኒያት እኩይ አዟሪት ውስጥ የገባ የወያኔና የኦነግ ድቃይ አውሬ – መስፍን አረጋ

በዐብይ አሕመድ ላይ አሁንም ድረስ ተስፋ ያልቆረጥክ አማራ ካለህ ተስፋህን ቁረጥና ራስህን የራስህ ተሰፋ ለማድረግ ቆርጠህ ተነሳ፣ ተነሳሳ፡፡  የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ወይም ኦነግ ሳይሆኑ፣ ወያኔ ከኦነግ የደቀለው ዐብይ አሕመድ የሚባል በሽተኛ ግለሰብ መሆኑን ያልተረዳህ አማራ ካለህ ደግሞ እርምህን አውጣና፣ በቀንደኛው ጠላትህ ላይ አስቀድመህ ዝመት፡፡    

—————————-

ሰካራም ባል ሚስቱን አድንቆ እንደማይጠግብ የታወቀ ነው፡፡  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሚያወራው ስለሷ ወደርየለሽነት ነው፡፡  ይህን የሚያደርገው ደግሞ በሰካራምነቱ ሳቢያ በሚስቱ ላይ የሚደርሰው ዘርፈብዙ ጉስቁልና ሕሊናውን ስለሚሸነቁጠው ነው፡፡  እንዲህ ዓይነቱን ባሕሪ ልቦናሲነኛወች (psychologists) ማካካስ (compensation) ይሉታል፡፡  ባጠቃላይ አነጋገር ማካካስ ማለት ያንድን ዘርፍ ደካማነት በሌላ ዘርፍ ጠንካራነት ለመዋጥ (ለመሸፋፈን ወይም ለማድበስበስ) ሲባል በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚደረግ ያላሰለሰ ጥረት ማለት ነው፡፡

የዐብይ አህመድ ድርጊቶች ሁሉም የሚጠቁሙት ግለሰቡ በሥርሰደድ (chronic) የማካካስ በሽታ በጽኑ የታመመ  የልቦናሲን (psychology) በሽተኛ ሳይሆን እንደማይቀር ነው፡፡  ዐብይ አህመድ የልቦናሲን በሽተኛ መሆኑን ለመጠርጠር ደግሞ ልቦናሲነኛ (psychologist) መሆን አያስፈልግም፡፡  አኳኋኑ ግልጽ ስለሆነ፣ ምንነቱን ለመረዳት ልቦናሕግ  (ሕገ ልቦና፣ common sense) ብቻ በቂ ነው፡፡

ስለ ሰላምና ስለ ፍቅር አውርቶ የማይታክተው ዐብይ አህመድ፣ የሰላምና የፍቅር ቀንደኛ ጠላት ስለሆነ ይሆናል፡፡    ነጋ፣ ጠባ ጦቢያ አትፈርስም የሚለው፣ ቀን ከሌት የሚያስበው ጦቢያን ስለሚያፈራርስባቸው መንገዶች ስለሆነ ይሆናል፡፡  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ መግደል መሸነፍ ነው የሚለው ደግሞ ማሸነፍ መግደል ነው በሚል መርሕ የሚመራ ደም ጠማሽ ስለሆነ ይሆናል፡፡  ደም ጠማሽ መሆኑን ደግሞ በግልጽ የሚያሳዩ አያሌ ምሳሌወችን መጥቀስ ይቻላል፡፡  እኔን ብትነኩ ባንድ ጀምበር መቶ ሺወቻችሁ ትታረዳላችሁ በማለት ሳይሰቀጥጠው በኩራት የሚናገር ግለሰብ፣ የቆሪጥ ጭራቃዊ መንፈስ የተጠናወተው፣ የሰው ደም ጥሙ መቸም የማይረካ፣ ደም ጠማሽ ካልተባለ በስተቀር ሌላ ምንም ሊባል አይችልም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አደባበዬቻችን እና መንገዶቻችን መሉሱልን ? !!!

በልጅነቱ ጫካ ገብቶ ሐይማኖትና ምግባር ከሌላቸው፣ በነውር ከተጨማለቁ፣ በጎጠኝነት ከታወሩ፣ በጥላቻ ካበዱ፣ በስቃይ ከሚደሰቱ፣ በደም ከሚታጠቡ ከወያኔ ጉምቱወች ጉያ ሥር ያደገ ግለሰብ በኣካልም ሆነ በመንፈስ ጤነኛ የመሆኑ ዕድል እጅግ የመነመነ ነው፡፡  በዚያው መጠን ደግሞ ከባድ ወንጀለኛ የመሆኑ ዕድል በጣም ከፍተኛ ነው፡፡  ስለዚህም ዐብይ አሕመድ እንዳይታወቁበት የሚፈራቸው አያሌ ጉዶች ሊኖሩት ይችላሉ ማለት ነው፣ አሉትም ተብሎ ይጠረጠራል፡፡  ጉደኛ ከሆነ ደግሞ ጉዱን የሚያውቁበት ሰወች በመረጃቸው እያስፈራሩት (black mail) አድርግ ያሉትን ሁሉ እንዲያደርግ ሊያስገድዱት ይችላሉ፡፡

ዐብይ አህመድ ጃዋር ሙሐመድንና ለማ መገርሳን አለቅጥ የሚፈራቸው ወዶ ሳይሆን በጉዱ ምክኒያት በግድ ተገዶ ሊሆን ይችላል፡፡  ጦቢያ ከኦሮሚያ ትውጣ (Ethiopia out of Oromia) የሚለው ጃዋር ሙሐመድ ያገኘውን ክፍተት የሚበረግድ ወንበዴ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ሱሴ የሚለው ለማ መገርሳ ደግሞ ባገኘው ቀዳዳ የሚገባ ሸለመጥማጥ ነው፡፡  ወያኔወች ደግሞ ዐብይ አሕመድን እናጋልጥኻለን እያሉ ዘወትር የሚዝቱበት የያዙትን ቢይዙበት ነው፡፡  እስካሁንም ያላጋለጡት ደግሞ ዐብይ አሕመድ ባጸፋው እንዳያጋልጣቸው ስለሚፈሩ ነው፡፡  እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ፡፡

አያሌ አገር ወዳድ ጦቢያውያን የዐብይ አህመድ ወላጅ እናት አልኦሮሞ (non-oromo) መሆን የዐብይን የኦሮሞ ጎጠኝነት ስሜት ያለዝበዋል የሚል እምነት ነበራቸው፡  ታሪክ የሚመሰክረው ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፡፡ ያንድ ብሔር አባል አለመሆኑ የሚጠረጠር ግለሰብ የዚያ ብሔር ጽንፈኛ ከሆነ፣ በብሔር አባልነቱ ሊጠረጠር እንደማይገባው በግልጽ ለማስመስከር ሲል ያማያደርገው ድርጊት የለም፡፡  ሂትለር ይሁዳወችን ያለ ርኅራኄ የጨፈጨፈበት አንዱ ምክኒያት የይሁዳ ደም አለበት የሚባለውን ጭምጭምታ ለማስተባበል ነበር፡፡  አብዛኞቹ ያሜሪቃ ነጭ ልዕለኛወች (white supremacists) አንግሎ-ሳክሶኖች ከነጭ የማይቆጥሯቸው የደቡብና የምሥራቅ አውሮጳ መደዴወች ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወንጀል እና ህግ ፣ እውነት እና ውሸት በብሄረሰቦች ነፃነት ዘመን (ታሪኩ አባዳማ)

በወያኔ በኩል ደግሞ ኤርትሬውን በረከት ስምዖንን መጥቀስ ይቻላል፡፡  የወያኔን ፀራማራ አጀንዳ በማራመድ ረገድ ከራሱ ከመለስ ዜናዊ በላይ ትልቁን ሚና የተጫወተው በረከት ስምዖን ነው፡፡  እነ አዲሱ ለገሰን፣ ተፈራ ዋልዋን፣ አለምነው መኮንንን፣ ከበደ ጫኔን፣ ተመስገን ጥሩነህንደመቀ መኮንንን፣ … የመሳሰሉትን አማራ ነኝ ባይ ፀራማሮች፣ በብአዴን ቁልፍ፣ ቁልፍ ቦታወች ላይ አስቀምጦ፣  በአማራ ሕዝብ ላይ መርገምት ያወረደው፣ ይህ ጎንደር ተወልዶ ያደገ፣ የበላበትን ወጭት ሰባሪ እኩይ ግለሰብ ነው፡፡  በረከት ስምዖን ደግሞ ከወያኔወች በላይ ፀራማራ የሆነበት አንዱ ምክኒያት፣ ተጋሩ ባለመሆኑ ተጋሩወች እንዳይጠረጥሩት ነው፡፡

ጌታቸው አሰፋ በላኤአማራ የሆነበት አንዱ ምክኒያት አባቱ አማራ ቢሆኑም ‹‹ከሙሉ ትግሬወች›› በላይ አማራጠል መሆኑን ለማስመስከር ነበር፡፡  ጌታቸው ረዳ ደግሞ ከአማራ ጋር ሒሳብ እናወራርዳለን አለበለዚያ ሲኦል እንወርዳለን እያለ የሚቅለበለበው ወዶ ሳይሆን፣ ባማራነቱ እንደሚጠረጠር ስለሚያውቅ ጥርጣሬውን ለማስወገድ ነው፡፡

ዐብይ አሕመድ ደግሞ በአማራ ጥላቸው ወደር የሌለው ኦነጋዊ አውሬ መሆኑን በስካሁን ድርጊቶቹ በግልጽ አስመስክሯል፡፡  ኦነጋውያን በመቶ ዓመታት እንፈጽመዋልን ብለው ሊያስቡት ቀርቶ ሊያልሙት የማይችሉትን፣ በረቀቀ የሽንገላ ክሂሎቱ በሦስት ዓመታት ብቻ በመፈጸም ኢትዮጵያን የኬኛ፣ በኬኛ ለኬኛ አድርጓታል፡፡  ባጭሩ ለመናገር  ዐብይ አሕመድ ማለት የሦስት ሺ ዓመት አገር በሦስት ዓመት ያፈራረሰ የሉባወች ሉባ ነው፡፡    

ለኦነጋውያን የዋለው ውለታ ወደርየለሽ ቢሆንም፣ በኦነጋውያን የዘር እሳቤ መሠረት ሙሉ ኦሮሞ አይደለም ስለሚባል ግን፣ ኦነጋውያን መቸም ቢሆን አያምኑትም፡፡  እሱም ራሱ ቢሆን፣ በማንነቱ ምክኒያት በኦነጋውያን እንደሚጠረጠርና ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቅ፣  እያንዳንዷ ድርጊቱ በዘር መነጽር እንደምትመረመር፣ ትንሽ ቢሳሳት ግዙፍ ውለታው መና ቀርቶ ከሃዲ ተብሎ ተዘቅዝቆ እንደሚሰቀል ወይም ደግሞ ከነነፍሱ ቆዳው እንደሚገፈፍ ነጋሪ አያስፈልገውም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሙስና ምርመራ እየተወሳሰበ ነው! "መበላላት እንዳይጀመር ስጋት አለ"

ስለዚህም ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት ከፈለገ ትናንት ካደረገው የከፋ ዛሬ ማድረግ አለበት፡፡  ይህ ማለት ደግሞ ዐብይ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የበለጠ እና የበለጠ እያረመነ (አረመኔ እየሆነ) ይሄዳል ማለት ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ዐብይ አህመድ ማለት በማንነቱና በምንነቱ ምክኒያት እኩይ አዟሪት (vicious circle) ውስጥ የገባ የኦነግ አውሬ ነው፡፡  ካዟሪቱ ነጻ የሚያወጣው ደግሞ ዳግም ምጽአት ብቻ ነው፡፡

በዐብይ አሕመድ ላይ አሁንም ድረስ ተስፋ ያልቆረጥክ አማራ ካለህ ተስፋህን ቁረጥና ራስህን የራስህ ተሰፋ ለማድረግ ቆርጠህ ተነሳ፣ ተነሳሳ፡፡  የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ወይም ኦነግ ሳይሆኑ፣ ወያኔ ከኦነግ የደቀለው ዐብይ አሕመድ የሚባል በሽተኛ ግለሰብ መሆኑን ያልተረዳህ አማራ ካለህ ደግሞ እርምህን አውጣና፣ በቀንደኛው ጠላትህ ላይ አስቀድመህ ዝመት፡፡

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

9 Comments

  1. It is simply puzzling for physics professor Mesfin Arega Woldeyohannes teaching at an American university to speak so vilely of Prime Minister Abiy Ahmed as ድቃይ አውሬ cross-bred beast on account of the latter’s ethnic origin. It is obvious he has issues with the prime minister. What is scary and goes beyond the pale is for the professor to incite the Amhara to rise up and do in “enemy no. 1”, the “cross-bred beast” Abiy (who happened to be Oromo)! The professor’s behavior is unacceptable and to be condemned in no uncertain terms. Mesfin has been posting similar articles in Zehabesha for quite a while now.

  2. አቶ መስፍን፦
    እጅግ ወቅታዊና እውነትን በእጂጉ የተላበሰ ወቅታዊ መካሪና አንቂ ጽሁፍ አቅርበህልናል፡፡ቀጥልበት ብለናል፡፡ ከአብይ አህመድ መርህ የለሽነት ባሻገር የተዳቀለ ማንነቱ ክፉኛ የተጠናወተው ስለሆነ በጽሁፉ እንደተገለጸው በተረኝነት ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ለመሆን የአማራ ሆድ አደር ሹመኞችን በምርኩዝነት ይዞ አያሌ መቅሰፍቶችን እያደረሰብን ነው፡፡ ከጀርባ አብይ አህመድን የሚያሾረው ለህዝብ ይፋ ያልሆነ የኦሮሙማ ካውንስል አለ፡፡ በካውንስሉ ውስጥም እነ አባዱላ ገመዳ፣ ግርማ ነገዎ፣ ሁለቱ ሌንጮወች፣ ምርጦቹ አባገዳወች…ወዘተ በቋሚነት ያሉበት ስብስብ ያለ ሲሆን በየዘርፉም ለማ መገርሳ ዳውድ ኢብሳ፣ ጃዋርና መራራ ጉድና ወዘተ ሌሎችም የኦሮሞ አክራሪወችን ያሉበት አሰራርተዘርግቷል፡፡ተሳትፏቸውም በደረጃው ይለያያል፡፡ በምክር፣ በውሳኔ ሰጭነት፣ በአስተያየት አቅራቢነትና በእርምጃ አወሳሰድ ወዘተ በተለያዩ አሰላለፎች በየደረጃው ሁሉንም አካትቶ ይዟል፡፡ ይህ ካውንስል ነው የተወካዮች ምክርቤትንም ሆነ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ጉልቶች በአብይ አማካይነት ትአእዛ እያሰጠ የሚያሾራቸው፡፡ ከዘረፋውና ጭፍጨፋው ባሻገር የካውንስሉ ዋና ግብ ኢትዮጵያዊነትን ነቅሎ አገሪቱን ኦሮማዊት ማድረግ ነው፡፡
    አብይ የግል ማንነቱና ያለበት የኋላ ታሪኩ፣ተጨምሮበት ለጥፋት ወደኋላ እንደማይል ሶስት አመታት ሙሉ ያየናቸው እጅግ አሳፋሪ ድርጊቶቹ እጋግጠውልናል፡፡ አማራው ዘግይቶም ቢሆን አሁን ላይ ነቅቶ በፋኖ ዙሪያ ራሱን ማደራጀት ጀምሯል፡፡ አፋሩም ይሄው የአብይ አህመድ ሴራ የተገለጠለት ይመስላል፡፤ ሱማሌውም ቢሆን ኦሮሙማ ድጋሜ እንዳያጠቃው ህዝቡን ማንቃት አለበት፡፤ ተረኛው ኦሮሙማ የወያኔ ልቅምቃሚወች ጋር ሆኖ በድብቅ እየተናበበ ብዙ ጉድና መካራ ሳያመጣብን በፊት ሴራውን ማስቆምና ማስወገድ አለብን፡፡ በቅርቡ ወራሪው የወያኔ ሰራዊት ባደረሰው ወረራ ላይ በተደረገው ጦርነት በየአውደ ዉጊያወቹ ፋኖ፣ የአማራ ልዩ ሀይልና የአፋር ልዩ ሀይል ክንድ ምን ያህል ብርቱና የማይቀመስ እንደሆነ ወያኔ በሚገባ ተገንዝቦታል፡፤ የአማራንም የአፋሩንም ክንድ ገና ያልቀመሰው 31 ዙር የሰለጠነው ከ100ሽህ በላይ ቁጥር ያለው ባለ ልዩ ትጥቁ የአብይ አህመድ የኦሮሞ ልዩ ሀይል ነው፡፡ ነገሩ ልብ እንጅ ቁጥር፤ ወኔ እንጅ ትጥቅ በዉጊያ ላይ እምብዛም ወሳኝነት ስለሌላቸው ዉጤቱ በማይቀረው በመጪው የአብይ አህመድ ኦሮሙማ የመስፋፋትና የወረራ ወቅት ይታያል፡፡ አብይ በፊታውራሪነት የሚመራው የኦሮሙማ መስፋፋትና የጥፋት ወረራ አፍጥጦም አግጥጦም እየመጣ ነው፡፡ ስለሆነም የኦሮሙማን መስፋፋትና ወረራ የማትቀበል ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለማይቀረው ትንቅንቅ ተነሳ!! ሁሉም በዚህ መልኩ ነቅቶና ተደራጅቶ እራሱን ካዘጋጀና ራሱን ከተከላከለ በድምር ውጤቱ አገሩን ከወያኔ ሙታቾችና ከኦሮሙማ ኬኛወች አዳነ ማለት ስለሚሆን ሁላችንም ለዚሁ እንዘጋጅ፡፡
    አማራ ሆይ ይበልጥ ንቃ፡፤ ወደተግባር ስትገባም መጀመሪያ ውስጥህን አጥርተህ ሆዳም የአብይ ፈረሶችን በቅድሚያ አስወግደህ መሆን አለበት፡፡ ህብረትህንም አጠንክረህ በያለህበት በጎበዝ አለቃ እየተደራጀህ የነጻነት ተጋድሎህን ዛሬዉኑ ጀምር!!

  3. ወንድሜ መስፍን – ከአርዕስቱ እስከ ይዘቱ ሃሳብህ መንገድ ለቋል። ሲጀመር ነገርህ በስድብ መጀመር አልነበረበትም። ጠ/ሚሩ እንደ መልአክ ክንፍ አውጥተው በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ይበራሉ ብሎ የሚያምን ማንም የለም። እንደ እኔና አንተ ሰው ናቸው። ያጠፋሉ፤ ያለማሉ። በዓለም ላይ ያሉ የቱም መንግስታት ቢሆኑ በሥራቸው ሙሉዕ የሆኑ የለም። ግን ሰው የሚመዘነው በሥራው እንጂ በቃሉ ጋጋታ አይደለምና የሃበሻን ህዝብ ለማስተዳደር እጅግ እጅግ ከባድ ነው። አንድ ጋ ረጋ ስትል ሌላ ጋ ይበረግጋል። በተለይም ደግሞ ባለፉት 30 ዓመታት በተዘራው የጥላቻ ፓለቲካ የተነሳ የዘረኝነት ፈረስ ሰውን ሁሉ ሲጋልበው ማየት ምንኛ ያሳዝናል። ግን ሆን ብሎ ጠ/ሚሩ በዘር ተሰልፎ ሃገር ያፈርሳል ብየ እኔ በግሌ አላምንም። በዙሪያው ያሉ የዘር ጡሩንባ ነፊዎች ግን በዚህም በዚያም ሃገሪቱን ደማስቆን ሊያስመስሏት ቀርጠው እንደተነሱ እያየን ነው። በዚህ ሁሉ ግን አንድም ሰው አትራፊ አይኖርም። በተለይ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ሰቆቃ ሊገታ አለመቻሉ የቱን ያህል የሃገሪቱ የፓለቲካ የክፋት ጆንያ አሁንም የሚያከፋፍለው በለውና በላት ብቻ መሆኑን ነው።
    የአማራ ህዝብ ራሱን በራሱ አስተባብሮ፤ ሽዋ፤ ጎንደር፤ ጎጃም ወይም ወሎ ሳይል በተቻለ መጠን በመሰልጠን፤ በመታጠቅ፤ ራስን ለህግና ለሃገሪቱ የጸጥታ መዋቅር ጋር በማዛመድ ራሱን በራሱ መመከት እስካልቻለ ድረስ ይህ ሃይል ይደርስልኛል ያ ይረዳኛል የሚለው አይሰራም። ለዛ ነው በወያኔ የግፍ ወረራ የወደመውን መልሶ ለማቋቋም ከመሯሯጥ ይልቅ ወያኔ ዳግም ወረራ መፈጸም እንዳይችል ስልታዊ በሆነ መንገድ ራስን ማደራጀት ቀዳሚ የሚሆነው። ለዚህም ፋኖና የአማራ ልዪ ሃይል እንዲሁም የገጠር ገበሬዎች ሚሊሻ ቅንጅት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ውጊያው የህልውና ነው። የመኖርና ያለመኖር። ይህ በየትኛውም ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። እሳትን በእሳት ለመመለስ መታጠቅ፤ የጠላትን ትጥቅና የስልጠና ስልት ቀድሞ ማወቅ፤ የጠላትን ስሪት አምካኝ የሆኑ ነገሮችን ከአሁኑ ማሰብና መታጠቅ አስፈላጊ ነው። በእኔ እምነት ወያኔ ለዳግም ወረራ አሁንም ታላቅ ዝግጅት እያደረገ ስለሆነ በየከተማው ያለፈን እያነሱ ከመፎከር ይልቅ ለቀጣዪ ፍልሚያ ራስን ማዘጋጀት ይገባል ባይ ነኝ። ዶ/ር አብይ ስልጣን ላይ ቆየ አልቆዬ የአማራው መከራ ራሱ አማራው እስካልገታው ድረስ ይቀጥላል። ሰው በዘሩ እየተመረጠ የሚገደልባት የሃበሻ ምድር ሙታኖችን እየቀበረች እስከ መቼ ትቀጥላለች?
    ግራም ነፈሰ ቀኝ የአቶ መስፍን አረጋ ሃሳብ እንደገና ሊሰለቅ የሚገባው ይመስለኛል። ዓለሙን ሁሉ አግምቶ የት መኖር ይቻላል? የትም። የሃበሻው ትልቁ ችግር ሌላውን የራሱ ጉዳይ አስፈጻሚ ማድረጉ ነው። የሰው ልጅ ለፈተና የተፈጠረ ፍጡር ነው። መከራው ተፈጥሮአዊም ሰው ሰራሽ ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን ባለቸው ኢትዮጵያ የችግራችን ሁሉ ምንጭ ራሳችን ነን። መፍትሄውም ከዚሁ ይመጣል ብዬ አምናለሁ። ነጩ/አረቡ/ሌላው የጥቁሩ ዓለም የእኛን እርስ በርስ መተራረድ የዜና ማሟያና የዪቱቭ ገንዘብ ማግኛ ነው የሚያረጉት። ዝንተ ዓለም ስንቧቀስ ብንኖር ደስ ይላቸዋል። የእኛ ረሃብ ዜናቸው ነው። የእኛ ሞት ደግሞ ለወሬም አይገባም። አንድ ነጭ የወያኔ ደጋፊዎችን በለንደን ሰብስቦ እንዲህ ነው ያለው (ቪዲዪውን ይመልከቱ). የኤርትራ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሂዶ መሰለፍ ዜና አይደለም። ግን የኤርትራን ኤምባሲ ማቃጠል ዜና ሊሆን ይችላል በማለት ነው ቅስቀሳ ያካሄደው። ዛሬ በትግራይ መሬት ከወያኔ ጎን ተሰልፈው ይህንና ያን አርጉ የሚሉ፤ በሩቅ እጃቸውን ዘርግተው በሏቸው የሚሏቸው ለትግራይ ህዝብና በጦርነቱ ለሚያልቁት ቅንጣት አይገዳቸውም። ሃበሻው ይህ ግልጽ ሆኖ ሊገባው በተገባ ነበር። ግን ከሃበሻ ዶክተር የነጭ ድሬሰር ያክመኝ የሚል ስብዕና ከነጭና ከአረብ ተንኮል ይወጣል ብሎ መቀበል ይከብዳል። መለወጥ ያለብን እኛ ነን። መስፍን አረጋ ራሱን አይቶ ከራሱ ጋር እርቅ ማድረግ ተገቢ ነው። ማንም ሰው ድቃይ አውሬ ሊሆን አይችልም። የሰው ልጅ ባህሪ ግን ሰው መሆኑ ቀርቶ የአራዊት መሆኑን በተግባር እያየን ነው። ያን አስተሳሰብ ነው መዋጋት ያለብን። በስድብ መዘናጠሉ ለራስም ለሃገርም አይጠቅምም። በቃኝ!

    • ተስፋ ነገሩ ላንተ ቀልሎ የታየህ የነገሩ ክብደት የመስፍንን ያህል ከብዶ ስላልታየህ ነውና በመስፍን ልክ እንዲህ ይህ እውቀትና ቀጥታ እይታ ያስፈልጋል ከብዙ ጥቅሻዎችህ እንደማየው ከአርእስት በዘለለ የምታነብ አይመስለኝም አንዳንዴም ጎንደር የተወለድክ ሻቢያ ወይም ትግሬ ትመስለኛለህ።

      • በሃሳብ ተላልፈናል ወገኔ። የዘርና የፓለቲካ ፍረጃውን አሰርተህ ልበሰው። እኔን አንተ ከምትለው ጋር የሚያገናኘኝ ቅንጣት ነገር የለም። እንዳልከው ለእኔ ችግሩ ቀሎ ታይቶኝም አይደለም። የሆነውንና የሚሆነውን የመከራ ክምር ጠንቅቄ እረዳለሁ። ግራም ነፈሰ ቀኝ እንደተመቸህ ተራመድ።

  4. Dear Prof. Mesfin Arega, I often follow your articles on zehabesha.
    and I got all of them very true. Yes there is no doubt Abiy is cruel.
    He killed so many Amharas by his evil deeds. I want to thank you very
    much for your integrity and honesty for exposing this wild animal. I
    also have too much respect for your writing skill . I am very proud
    that we have such a wonderful man. please keep it up.

    You are the true son of Ethiopia!

    Regards!

  5. ተስፋ ብዙ ታግሼ ቢብስብኝ ነው እግዜር ያሳይህ ተለይተህ የወጣህ አንተ ብቻ ነህ ምን አድርግ ትለኛለህ ለእኛ የታየን ላንተ አልታየህም ያልኩህ አይቼ ነው እኛ አንድ ሀገር ብቻ ነው ያለን እናንተ አንድም ሁለትም ሶስትም ይኖራችኋል።

  6. ተስፋ እና አለም የተባላችሁት አስተያየት ሰጪወች፦ በጣም ትገርማላችሁ፡፡ ሁልጊዜ አብይ አህመድን ሸንቆጥ የሚያደርግ አስተያየት ሲቀርብ አፋችሁንም ብእራችሁንም አሹላችሁ እርሱን ተጠያቂ ላለማድረግ ትውረገረጋላችሁ፡፤ ትሟገቱለታላችሁ፡፡ ጽሁፉን መስፍን አረጋም ይጻፈው ማላጅ ወይንም ሌላ ማንም ጽሀፊ እናንተ ብቻ አብይ የተነካ፣ የተወቀሰ በመሰላችሁ ጊዜዜ የክፍያ ጉዳይ ነውና ስራችሁን በስድብ ትጀምራላችሁ፡፤ ስታጻሳዝኑ! አብይ ሁሉንም መሆን ሲመኝና ሲያወናብድ አንዱንም በቅጡ መሆን ሳይችል በመቅረቱ ወደጉድጓዱ ሊገባ እየተቃረበ ነው፡፤ ያን ጊዜስ ማን ይከፍላችሁ ይሆን?? ከንቱወች!!!

  7. ጥላቻ ላበገናቸው የወያኔ አጀንዳ ፈጣሪዎች የሚሰጥ ሀሳብ የባከነ ሀብት ስለሚሆን አይገባቸውም። መስፍን በርግጥ ተምሮ እንደዚህ ከሆነ ወደ አዕምሮ ሕክምና ይግባና ኢትዮጵያዊነትን ለዜጎች ይተው። አሳፋሪ የጥላቻ ወሬ ስለሆነ ይብቃው!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share