አገራዊ ወይም ብሔራዊ ምክክር እንደ ኢትዮጵያ ላለ የፓለቲካ ”ኮምፓሱ” ለጠፋብን፤ ከአንድነት- ልዮነትን፣ ከትልቅነት – ትንሽነትን፣ ከሰላም -ጦርነትን፣ክውቅያኖስ-ኩሬ ለመረጥን አይደልም፤ ከተቻለ የዓልም አገሮችም ቢወያዩ ጠቃሚነቱ አያጠራጥርም። በርግጥም ይወያያሉ፤ ውይይቱ ግን ኃያላን አገራት እንዴት ደሃ አገራትን እንድሚበዘብዙበትና እንደሚቆጣጣሩበት የሚዘይድ ነው።
የሥልጣኔ ጣራ የነኩ አገሮች ትላንትም ሆነ ዛሬ በአፍሪካ ላይ ጥባጥቤ የሚጫዎቱበት ሚስጢር፣ ከሥልጣናቸውና ከግላዊ ጥቅማቸው ይልቅ ፤ አገርንና ህዝብን በማስቀደም ፤ ፓለቲካቸውን በምክከር፣ በውይይትና በሃሳብ የበላይነት ላይ መሰረታቸውን ስለ ጣሉ ነው። ብዙ አገሮችም ብሔራዊ ውይይት እንበለው ምክክር በማድራግ ችግሮቻቸውን በከፊልም ቢሆን የፈቱ አሉ። በአንጻሩ ደግሞ ችግራቸውን ያባባሱም አሉ።
ይህ ብሔራዊ ምክክር የሚለው ሃሳብ ምን አልባትም ከደርግ ጀምሮ፣ የወያኔን ዘመን ተሻግሮ፤ በሃሳብ ደረጃ ሲነሳና ሲወድቅ፣ ሲንከባለል ከዚህ የደረስ ነው።
የጠ/ሚ አብይ አገዛዝ መምበሩን እንደተፈናጠጠ ፤” የአገራችን ውስብስብስብ ችግር ለመፍታት ከሁሉም በፊት አገራዊ ምክክር ወይም አገረዊ መግባባት ይቅደም።” የወያኔ መወገድና ወደ መቀሌ መሄድ፣ የሥረዓት ለወጥ አያመጥም፣ እየተደረግ ያለውም ”በአሮጌ እቁማዳ እዲስ ወይነ ጠጅ ” እንደሚባለው ስለሆነ፤ ሌላው ቢቀር ሁሉንም ኃይል ያሳተፈ ውይይት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን የሚያስፈልጋት ሥር-ነቀል ለውጥ ነው።” ብለው የጠየቁና የተየቡ ነበሩ፤ ግን ስሜ አልበረም። እንድሚባለው እኛ ”መንቀል እንጅ መትከል” እንችልም።
ስልጣኑን የያዙት ትኩረታቸው ሥልጣናቸውን ማጠናከርና ማደላደል ላይ ስለነበር፤ አገሪቱ ከአንዱ ችግር ወደ ሌላ ችግር ብትላጋምና ህዝብም ቢያልቅ ፤ በሥልጣናቸው እስከ አልመጣ ድራስና የነርሱን የጎሳ የበላይነት የሚያመቻች እስከሆነ ድረስ ደንታም አልነበራቸውም።ዓልማቸው ነውና ”ለምን” ብሎ መጠየቅይ ቂልነት ነው።
አሁንም ከወያኔ ጋር ያለው ጦርነት ሳይጠናቀቅ፣ ሚሊዮኖች በተፈናቀሉበትና ቁስላቸው ባልሻረበት፣ የገዥው አካል የሆነውና የዳቦ ስም የተሰጠው ኦነግ-ሸኔ አሁንም ከወያኔ ባልተናነስ የሰውን ልጅ በማንነቱ ብቻ በሚያርድበትና ከተማን በሚያወድምበት ሰዓት፡ ሰንት ቅድሚያ የሚሰጠው የውስጥና የውጭ ፋታ የማይሰጡ ችግሮች እያሉ፤ ያኔ በሚያስፈልግበት ግዜ አሻፍረኝ ብለው፤ ለምን አሁን በግርግር ገዥዎቻችን ”አገራዊ ምክክሩን ፈለጉት?” የሚለውን ብቻ ሳይሆን፤ እነማንና ለነማን ነው አገራዊ ምክክር የሚደረገው? ብለን መጠየቅ አልበን።
እስከ መቼ ነው ገዥዎች ወደ ፈለጉት አቅጣጫ የሚነዱን? የዲሞክራሲ መዋቅር በሌለበትና የጎሳ ህግ-መንግሥት ባለበት አገር ምንም ዓይነት ዲሞክራሲያዊ ምርጭ ቢካሄድ ፍታዊ እንደማይሆን እያወቅን ተሳትፍን ውጤቱ ምን ሆነ? ውጤቱን በዓይናችን የምናየው በእጃችን የምዳብሰው፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እያጠፋን የኦሮሙማን የበላይነት ማረጋገጥ ነው። በርግጥ አፈቀላጤዋችና ተጠቃሚዎች ልባቸው እያወቅ ቢሆንም ይህን ሃቅ እንዲነግሩን መጠበቅ የለብንም።
ብዙዋቻችን ህዝብ ገና በጦርነት ላይ እያለና በየቀኑ እየተገደል፤ የእልቂቱ ፈጣሪዎችና አድራጊዎች ከሥር ተለቀው ለባሰ እልቂት በሚዘጋጁበት፤ ኦሮሙማ የኢትዮጵያን ባንዲራ በያዘ ታቦትና ምዕመናና ላይ ተኩሶ እየገደለ፤ መንግሥታዊ ኦነግ ሸኔ በየቀኑ ዜጎችን በማንነታቸው እይረደ፡ በአጠቃላይ ከወከባና ከጭብጨባ ገና ያልወጣን ብቻ ሳንሆን ፣በትክክል በአገራችን ላይ ምን እየተደረገ ነው? ብለን ለመጠየቅም ሆነ የጠይቁትንም ለማደመጥ ዝግጁዎች አይደለንም። ለዚህ ደግሞ አሁን ‘’የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ጉባኤ’’ እየተባለ የሚናፈሰው አዲሱ አጀንዳ ምስክር ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ጉባኤ ሳይረግዝ መጨንገፋን የምናየው ”ተጠሪነቱ ለፓርላማው ነው።” ሲባል ነው። ብልጽግና – ኦሮሙማ- ብቻውን ተወዳድሮ ባሸነፈበትና በሚቆጣጠረው ፤ ለይስሙላ የስልጣን ጥቅመኞች ብቻ ባሉበት ፓርላማ፤ አገልግሎቱና አዳሪነቱ ለማን እንደሆነ እያወቅን ” ብሔራዊ ምክክር ” ብለን ሰይመን ፤ እንደገና ተጠሪነቱን ለፓርላማው ስናደርግ፤ ይህንም ተከትሎ ተቃውሚ ነኝ የሚሉ ክፍ -ዝቅ ሲሉ፤ የህዝባችን መከራ ካለፈው በባሰ በአዲስ ዙር እየተጅመረ ነው ያስብላል።
ለትዝብት ፓርላማው ውስጥ ያለውን አቶ ሃንጋሳ ህብራህም የሚባል ሰው ምን እንዳለና እስቲ ያልሰማችሁ ሊንኩን በጫን ስሙት፤
ነገ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ጉባኤ ከሚወስኑት ሰዎች አንዱ መሆኑን ስናስብ ፤
”ኢትዮጵያ አገሪ ሞኝነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” ማለት ሳይሆን ፤ ለኢትዮጵያዊነታቸው የተሰው ዜጎች የተዳሉ ብቻ ሳይሆን ፣ የቁም ሞታችንን ሳያዩ እንኳንም ሞቱ ያሰኛል።
ሌላው አስቂኝና ማን አለብኝነት፡ የወያኔን የኦሮሙማው ብልጽግና ፍጹም ወራሽነት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ጉባኤ ለዕጩነት የሚቀርቡ ማሟላት ከሚገባቸውን መስፈርቶች ውስጥ በተረ ቁጥር 2 ያለውን እንመልከት፤
2/ ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ የተለያዩ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን በእኩል ዐይን የሚያይ፤
ልብ አድርጉ ‘ርግጥ ነው ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩል ዓይን ማይት አይደልም፤ ማክበርና እንደራሱ አድርጎ መክባከብ አለብት። ይሁን እንጂ ”ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦች በእኩል ዐይን የሚያይ” የሚለው ወያኔ ሲጠቀምበት የኖረውን፤ የዛሬዎቹም ተረኞች ”ትርጉሙን አስረዱን”ቢባሉ ማስረዳት ዓይደለም በትክክል የማይጠሩ ፤ ስለ ብሔራዊ ምክክር እየሰበኩ፤ እንደ ገና ”ተለያዩ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን እያሉ ” በግብዝነት ያደነቁሩናል። የግብዝናውና የድንቁርናው ስር መስደድ የሚያሳየው ደግሞ፤ በአገሪቱ ውስጥ ተስፋ የሚደረግባቸውና የሚከበሩም ዜጎች፤ ከተረኛው ኦሮሙማ ጋር ሆነው በመከረኝውን ህዝብ፤ ለረሃቡና ለመገደሉ ስይናገሩለትና ሳይደርሱለት ዛሬ ”ብሔራዊ ምክክር ተቀበል ” እያሉ ሊሰብኩት መሞከራቸው ነው።ይህ “‘ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦች ” የሚለው የሚያሳየን ”አገራዊ ምክክሩ ” ዜጋንም ሆነ ኢትዮጵያያን እንደማያውቃት ነው።
ግልጽ መሆን ያለበት አገራዊ ምክክር ወይም ውይይት አያስፈልግነም የሚል ያለ አይመስለኝ። የተሳካ የህዝብን ችግር ለመፍታት ከተፈለግ ፍጹም ነጻና ገለለተኛ፤ ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጣና ሁሉንም ዜጋ ያካተተ መሆን አለበት። መንግሥት ነኝ የሚለውም አካል የሚወያየው እንደ አንደ እንደማንኛውም በአገሪቱ ውስጥ እንዳለ ቡድን እንጅ፣ ከዚያ ያለፍ ስልጣንም ሆነ የሚዲያ ተጠቃሚነት ሊኖረው አይገባም ።
ከዚህም በተጨማሪ ሁሉም ዜጋ ከገጠር እስከ ከተማ ሊወከል የሚግባው ሰላም ፤ የተረጋጋ ማህበራዊ እንቅስቃሴ በህዝቡና በአገሪቱ ውስጥ ሲኖር ነው። በአጠቅላይ አሁን የተነሳው አገራዊ ምክክር ከመነሻውም እውነተኛ ሰላም ለማምጣትና የአገሪቱን መሰረታዊ ችግር ለመፍታት የታሰበ ሳይሆን ፤ ”ምርጫው ችግራችን ሁሉ ይፈታል፤ ብቻ ምረጡን ” እያሉ እንደ አወናበዱት ሁሉ፤ አሁንም ህዝብን በማደናገርና አጀንዳ በመስጠት ፤ ስለጦርነቱም ሆነ ስለ ወያኔ መጨረሻ ህዝብ ጥያቄ እንዳያነስ የአፍ ማዘጊያ ዓላማ መሆኑን መገንዘብ ያሻል።
”ይሁንላቸው፣ እንያቸው ምን አማራጭ አለን” ቢባል እንኳን ” ከጋሪው ፈርሱን ማስቀደም ” ይሆናል። የአንድ አገዛዝ የመጀመሪያው ተግባር የሆነውን የዜጎቹን ደህንነት ማስከበር ደግም ኦሮሙማ ሲያልፍም አይነከውም።
ስለዚህ ማጨብጨቡንና ማስጨብጨቡን አቁመን ፤ ሳይጸነስ ለተጨነገፈው አገራዊ ምክክርም ሆነ፤ ነገ-ከነገ ወዲያም ለሚፈበረክ አጀንዳ ጅሮ ሳንሰጥ፤
1/የወያኔንና ገዥው ኃይል በኦነግ ሸኔ ስም የሚያካሄደን የዘር ማጥፋትና የህዝብ ማፈናቀል በጋራ እንታገል።እንደምናየው ጦርነቱ በኦሮሙማ ተፈላጊ መሆኑን በተግባር አሳይተውናል፤ ምክንያቱም የሚሞተው አማራና አፋር ነውና። የሚገደለው ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ነውና።
-2/በአሁኑ ግዜ አገራችን የኦሮም፣ የትግሬና የአማራ ህዝብ ብቻ እየመሰልች መጥታለች። ይህ ሌሎች ዜጎችን ያገለለ አካሄድ ከጥፋት ውጭ የትም አያደስምና፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት የምንታገል ፤ ትግሉን የሁላችን በመሆኑ ፣ ለሁሉም አገር ወዳደ ህዝብ እንዲዳራረስና የትግሉ ተካፋያ እንዲሆን መቀሰቀስና ትኩርት መስጠትን አንዘንጋ። ከኦሮም፣ ከትግሬና ከአማራ ውጭ ነን ብለን የምናስብ ዜጎችም ፤ ኢትዮጵያ የጋራችን ብቻ ሳትሆን የሁላችንም መዳኛ ናትና ፤ እንደ ሰጎን ጭንቅላታችን አሸዋ ውስጥ በመክተተ የምናመልጠው ትግል አይኖርም፤ የትግሉ አካል እንሁን። የማንንም የበላይነት ሆነ ተረኝነትን እንደማንቀበል፤ ለገዝዎቻችን በሚገባቸው ቋንቋ ማናገር አለበን።
3/ በአሁን ሰዓት በአገራችን በማንኛውም ውይይት ይባል ድርድር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የሚወክል ኃይል የለም ። ያለፍውን በማውገዝ ወይም ገዥዎቻችንን በመለማመጥ የሚከበር እንደነትም ሆነ ኢትዮጵያዊነት አልነበረም፤ አይኖርምም። ስለዚህ ራሳችን ለራሳችን ኃላፊነት መውሰድና ኢትዮጵያን መታደግ የህልውና ጥያቄ ነውና፤
1ኛ / እንደራጅ
2ኛ/ እንደራጅ
3ኛ / እንደራጅ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!
——//——–ፊልጶስ
ጥር/2014