የ፭ ዓመት የነፃነት ዘመን ያላትን አገር ለማጥፋት ሰታትሩ የነበሩትን አሰባስቦ ኢትዮጵያን እና ዜጎቿን በጠላትነት የሚፈርጂ የፖለቲካ ጉድጓድ ቆፋሪዎች የተሰባሰቡት በ1983 ግንቦት 20 ቀን ነበር፡፡
ያኔ ነበር የኢትዮጵያ ጠላቶች በመሰባሰብ የኢትዮጵያን ጣራ ለማፍረስ አንድ ብሎ መምዘዝ የተጀመረዉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ኢትዮጵያዊ ማሳያዎችን ዳብዛ ማጥፋት እንደሆነ ሴራዉ ተጎነጎነ ፡፡
ኢትዮጵያን እና ማንነትን ለማጥፋት የመጀመሪያ የሉዓላዊነት እና የአንድነት ማፍረስ ሀ…..ሀ…. የጥፋት እና ሞት አዋጂ በአስመሳዮች እና ኢትዮ ጠሎች ዕዉን ሆኗል፡፡
የጥፋት ጉዞዉ አንዱን ማህበረሰብብ እና ማንነት መገለጫ ማጥላላት እንደ አረም ተዘርቷል ፤ ተስፋፍቷል ፡፡
ኢትዮጵያ እንደ አገር ፣ ዓማራን እንደ ህዝብ ፣ ክርስትናን እንደ ኃይማኖት ፣ ባንዲራን እንደ ብሄራዊ መለያ አድርጎ መቀበል አይደለም ማሰብ እና ማሳሰብ ወንጀል ሆኖ እነኝህን ብሄራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ፀጋ ከስር ለመንቀል ከ፴ ዓመት ዕንቅልፍ በማጣት የሚሰሩት በኢትዮጵያ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸዉን እያወቅን ኢትዮጵያን የሚሉ ኢትዮጵያዉያን የዜግነት መብታቸዉን ተነፍገዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን እንደ አለቀ ጨርቅ የጣሉትን ለራሳቸዉ ጥቅም እና ስልጣን (ድሎት) ሲፈልጉ የሚነግሩለት እና ድረስልን የሚሉት ካለፈ መማር አለባቸዉ ፡፡
የቀድሞዉ የሕወሀት መስራች እና ሊቀመንበር የነበሩት ለገሠ ዜናዊ በአንድ ወቅት ዓማራ የሚታሰር ቢሆን ዕስር ቤት አይበቃንም ፤ ባንዲራ ጨርቅ ነዉ በማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ የነበራቸዉን ጥላቻ የወለደዉ ንቀት ለሚያስታዉስ የማይረሳ ዕዉነታ ነዉ ፡፡
ሆኖም ያን ባሉበት ለፖለቲካ ስልጣን ማጣፈጫ እና መረጋገጫ ሲባል በፈጠሩት የኢትዮጵያ እና አርትራ ጦርነት አገር እና ሠንደቅ ዓላማዉን ከምንም በላይ የሚያይ ኢትዮጵያዊ በተለይም ዓማራ እና የዓማራ ባንዲራ የሚሉት በግንባር ቀደምትነት ታድጓቸዋል፡፡
ዛሬም ከዓመታት በኋላ በተነሳ ረጋ ሰራሽ ጦርነት ኢትዮጵያንም ሆነ ስልጣን ላይ ያለዉን መንግስት የታደገዉ ያ የሚጠሉት እና የሚያጥላሉት እና የዚህ የጥላቻ ፈለግ ተካታዮች በማይወዱት ኢትዮጵያዊ እና ሶስቱ ቀለማት -የኢትዮጵያ ባንዲራ ናቸዉ ፡፡
የሚገርመዉ ጦርነቱ ሳይጀመር በከተማ የኢትዮጵያን ባንዲራ ለኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ኢትዮጵያዉያን ለዕገዛ ሲፈለጉ (ሲታሙ) የሚያነሱት እንጂ ከዚህ ዉጭ በከተማ እና ገጠር ማየት የማይፈልጉ ኢትዮጵያዉያን በጠላትነት የሚፈርጁ እንዴት ኢትዮጵያዊ ሆነዉ አስከ መቸ በኢትዮጵያ እና ዜጎች አንጡራ መብት እየገፈፉ ይኖራሉ ፡፡
በኢትዮጵያዊነት እና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመክር እና ሊወስን የሚችለዉ ኢትዮጵያዊ ህዝብ እንጂ ኢትዮጵያዊነትን ለራሱ ከንቱ ዉዳሴ እና ጥቅም ለሚያዉል መሆን የለበትም፡፡
ከዚህ ዉጭ ከኃዲነት በመትከል ኢትዮጵያዊነት መንቀል ኢትዮጵያዊነት ሊሆን የሚስችል ሳይሆን የብልጠት ምኞት “ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ” ሲደጋገም ሆድ ያበዉን …..መሆኑን ስናዉቅ ሉላችን የሆነችዉን አገር በጋራ እና አንድነት እንጠብቅ ፡፡
ማላጂ
“አንድነት ኃይል ነዉ ”