January 13, 2022
28 mins read

ኢትዮጵያዊነት  እና ፋኖን  ለያይቶ ማየት እንዴት..? –  ማላጂ

ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት እና ገናናነት አብዝተዉ የሚናገሩ ግን ደብቅ ፀረ ኅዝብ እና ዓማራ አስተሳሰብ ያላቸዉ ከራሳቸዉ የግል እና ቡድን ጥቅም ዉጭ ሌላ እንዲጣስቡ መጠበቅ ከንቱነት ነዉ ፡፡

ይህን አለማሰብም ሆነ አስቀድሞ ከታሪክ አለመረዳት እና በአገር እና በትዉልድ ሞት እና ቁስል እና መቃብር  መሳለቅ ነዉ ፡፡

የአማራ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ዕድገት እና መፃኢ ዘመን ወሳኝ እና ግንባር ቀደም ባለዉለታ ህዝብ መሆኑን ከአገረ  መንግስት ምስረታ ጅምር አስካሁን ያለዉን ፤የነበረዉን ለመረዳት የሚያስፈልገዉ ሠዉ እና ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊ መሆን በቂ እና በቂ ነዉ ፡፡

በታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማንበርከክ ይጠቀሙበት ከነበረዉ አንዱ እና ዋናዉ የኢትዮጵያዉያንን በተለይም ዓማራ  ማንነት ፣ ታሪክ ፣ የዘመናት ብሄራዊ አገር ግንባታ የነበረዉን መስተጋብር እና መተባበር የሚያስፈራቸዉ ናቸዉ ፡፡

ኢትዮጵያ በታሪክ በዉጭ እና በዉስጥ ጠላቶች በተደፈረች ወቅት የደረሱለት እና የሞቱላት ዕዉነተኛ እና ቁርጠኛ የቁርጥ ቀን ልጆች እንጂ በየጊዜዉ የነበሩ እና ያሉ መንግስታት እና ፖለቲከኞች አልነበሩም ሆነዉም አይታዩም ፡፡

ነገሩ በተለያየ ታሪክ አጋጣሚ ያለዉ እና ባለጊዜ ሁሉ ከኋላ ከመቆም ፤ ኋላ መንሸራተት እና ሽሽት  ታይቷል ፡፡

ከዚህ በተቃራኒ ለአገር ከፍተኛ የህይወት ዋጋ ከፍለዉ ነጻ አገር እና ህዝብ ያቆዩ ጀግኞች  በፓለቲካ ሴራ እንዲጠለፉ ፣እንዲጠፉ እና እንዲወገዱ ሆኗል፡፡

በዘመናችንም ኢትዮጵያ ብሄራዊ መንግስት ከፈረሰባት 1983 ዓ.ም. ጀምሮ አስካሁን በጥቅል ጥላቻ እና አገርን የመካድ ዘመቻ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ተቋማት የብሄራዊ አንድነት ምልክቶች እና ህዝባዊ መሠርት የነበራቸዉ  ተቋማት ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱ መቶ ፹፫ ዓ.ም. ጀምሮ እንዲከስሙ ሲደረግ ይህም ዛሬ አገሪቷን ለማዳከም የጥፋት እና ክህደት ጥንስስ የተጣለበት  ነበር ፡፡

ከብሄራዊ ተቋማት ማፈራረስ በተጓዳኝ ኢትዮጵያዊነት ማዛባት የመጀመሪያዉ እና መጨረሻዉ  ኢትዮጵያዊነት ብሎ ማንነት  ሲተረተር እና ሲመረመር  ዓማራ፤ አገር ሲባል ታላቋ  ኢትዮጵያ ብሎ አገር  አይኖሩም  ብሎ የተነሳ ኢትዮጵያ …..ኢትዮጵያ…..የሚሉ እና የነበሩ የአዞ  ዕንባ  የሚያሰኛቸዉ ትናትም ፤ጥንትም ፤ዛሬም ጥርሳቸዉ እንጂ ልባቸዉ የሚመኘዉ  ጥፋት እና ሞት ነዉ፡፡ የዚህ አድር ባይ ተሸካሚዎችም ትናትም ዛሬም የኢትዮጵያ ፣ኢትዮጵያዉያን  እና በተለይም ዓማራ  ጠል  ይቅር የማይባሉ  ናቸዉ ፡፡

ዓማራ የአገር ዋልታ እና መከታ መሆኑን ክዶ ለ፴ ዓመት በመላ አገሪቷ በጂምላ  እያታደኑ ሲገለሉ እና ሲገደሉ ኢትዮጵያ አገሬ ማለታቸዉ በጠላትነት እንዲታዩ ሲያደርግ ነገሩ በአንድነት እና ህብረት ጠላትን ለመለየት አለመቻል የኢትዮጵያን እና ህዝቧ የመከራ ዘመን  ከማራዘም ፤ የኢትዮጵያ አንድነት ዉድቀት  የሚያፋጥን ነዉ ፡፡

የቡድን እና የግለሰብ ርዕዮተዓለም እና የጥቅም ዓለም ለማስቀጠል አገር እና ህዝብ የሚጎዳ የትኛዉም አስተሳሰብ እና ድርጊት በቃ መባል ያለበት ጊዜዉ አሁን እና አሁን ብቻ ነዉ ፡፡

የዉስጥ ጠላትን በአድር ባይነት እና በስንፍና ብዛት እያለባበሱ የሩቅ እና የማይመለከተዉን ጠላት “በቃ ” እያሉ መጮህ  ለ፴ ዓመታት የነበረዉን የመከራ ዘመን  በማድበስበስ ፣ ማደስ እና በማለባበስ  በዓነት እና ብዛት ከማስቀጠል  ያለፈ ፋይዳ አይኖረዉም፡፡

ኢትዮጵያም ሆነ ኢትዮጵያዉያን እየተጎሳቆሉ  ስደት እና ሞት እየደረሰባቸዉ ያሉት  በዉስጥ እና ቅርብ አስመሳይ ጠላቶች እንጂ በየትኛዉም የዉጭ አገር መንግስት ወይም ዜጋ አይደለም ፤አልነበረም፡፡

ለዚህ ነዉ  ኢትዮጵያ ዉስጥ  ቁርጠኝነት እና ታማኝነት ያለዉ  አሰራር ባለመኖሩ እና ለዚህም ተጠያቂነት ያለዉ አካል መንግስት አስካሁን ፶ ዓመት ሙሉ ዜጎች በማንነታቸዉ በጅምላ እንዲሞቱ ፤በአገራቸዉ እንዲሰደዱ  መሰረቱ ህገ መንግስት እና አስተዳደራዊ መዋቅር (ፌደራሊዝም)  ዋነኛ የአሳዳጂ እና ተሳዳጂ ምንጭ ሳይደርቅ  እንዴት “በአገር ህዝብ  ሞት እና ስደት ” በቃ ሳንል ሞት እና ስደት ይቀጥል  ብሎ ማይመለከተዉን እና ሩቁን መማፀን ከንቱ ድካም ነዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ በደሙ እና በአጥንቱ የሠራትን ፣የመሰረታትን አገር  እየሞተ ያኖራትን ታላቅ ህዝብ ማግለል፣ ማስገደል እና ማታለል በይፋ ለዘመናት እንዲያስተናግድ ሲሆን ለምን ብሎ በቃ ያላለ  ዛሬ የዓማራ ህዝብ በህብረት እና በአንድነት ራሱን ፣ አገሩን እና ህዝቡን ለመታደግ የሚያደረግዉን  ትንቅንቅ  መፍራት ወይም ማጥላላት ከታሪካዊ እና ብሄራዊ ክህደት እና ፍርሃት ነዉ፡፡

የዓማራ ህዝብ ዛሬ ታሪካዊ የኢትዮጵያ የዉስጥ ጠላቶች  ከኋላ እና ፊት ሆነዉ  ሞት በይፋ ሲያዉጁበት  በአልሞት ባይ ተጋዳይ ተዋርዶ ሞት በቃ ሲል ተዋርዶ፣ተሰዶ እና ነፃነት አጥጦ መኖር  ከ ፷ (ስድሳ) ዓመት አስቀድሞ “በቃ ” ቢል ኖሮ ዛሬ አገሪቷን እና ህዝቧ የደረሰባቸዉን የዘመናት ዉርደት እና ሞት ባላስተናገዱ ነበር ፡፡

ዛሬ የኢትዮጵያዊነት ህብረት እና አንድነት በአንደበታቸዉ  የሚለፍፉት  ትናንት ኢትዮጵያዊነት እና ዓማራነት  ዉጉዝ  ሲሉ የነበሩ ስለመሆናቸዉ ከራሳቸዉ በላይ ማንም ሊነግራቸዉ ፤ ሊያዉቅላቸዉ አይችልም፡፡

ሆኖም በተለይም  በምንኖርበት ዘመን በየትኛዉም ዓለም ፣ጊዜ እና ታሪክ በኢትዮያ ህዝብላይ በተለይም በዓማራ መበአፋር…ህዝብ ላይ የደረሰዉ ዕልቆ መሳፍርት የማይገኝለት ሰቆቃ በኢትዮጵያ ዉስጥ እና በኢትዮጵያዊነት ካባ በተጀቦኑ የዉስጥ  ግፈኞች እንጂ ከሌላ ዓለም በመጡ ቅጥረኞች እና ምንደኞች አይደለም፡፡

ለሠባዊ እና ብሄራዊ አንድነት ፣ ዕድገት እና ሁለንተናዊ ነፃነት   “  በቃ”  ስንል  በራስ አገር ምድር  ሞት ፣ ስደት፣ ዉርደት ፣ ባርነት ፣ አድርባይነት …ከእነ መሰረታቸዉ መንቀል መሆን አለበት የምንለዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ እና ከአብራኩ የተገኙ ወጣቶች ከአንድ ዓመት አስቀድሞ  በዚሁ ስርዓት ተወልደዉ ያደጉ ስደት እና ሞት በቃ  ሲሉ  የስልጣን  ፍላጎት እና ሞኞት አድርጎ መዉሰድ  ለህዝብ እና ለዕዉነተኛ ሀሳብ አፈንጋጭ  ስለመሆናችን ዛሬ ህዝብ ያነሳዉ ዕዉነተኛ እና ወቅታዊ ጥያቄ ትክክል መሆኑን ለመቀበል ዛሬም እያንዉ እና የመከራ ዶፍ እየጠረገን አልገባንም፡፡

የዓማራ ህዝብ የትኛዉም አለሁ የሚል አካል  ጥሪ እና ጥያቄ ሳያቀርብለት  ኢትዮጵያን እና ራሱን ከህልዉና ጥፋት ለመታደግ  ዘብ የቆመዉ ከ ፴ ዓመታት ጀምሮ ቢሆንም  በህሊና ቢስ እና በአድር ባይ የዉስጥ ጠላቶች ሲጠለፍ ቢቆይም በአሁነ ጊዜ ያለዉ በህብረት እና በአንድነት የመቆም ጉዳይ ከምንጊዜዉም በላይ ምርጫ ሳይሆን  የራሱን እና የአገሪቷን ትንሳዔ  ዕዉን የማድረግ በህይወት የመኖር ፤አለመኖር  ፩(አንድ ) በመሆኑ በአንድነት እና በህብረት ለመቆም የማንንም ፈቃድ እና መዉደድ  የሚጠይቀበት አይደለም፡፡

የራስም ሆነ የአገር ክብር  ከተሟላ ነፃነት ጋር ዕዉን የሚሆነዉ  በራስ እንጂ በማንም አይደለም ፡፡

ኢትዮጵያ ተዳክማለች፣ ዓማራ እና አፋር  በሁሉ የግፍ ሠለባ እንዲሆኑ ተፈልጎ እና ታቅዶ በዓለም ያልሆ ሠባዊ ፣ ቁሳዊ እና በህይወት የመኖር ተፈጥሯዊ ነፃነት እናመብት እንዲያጡ ሆኗል፡፡

የሞተ ባይመለስም የሞተን እስካልረሳን ፣ ለአገር ዋጋ የከፈለን ዕዉቅና እና አድናቆት አስከሰጠን ከሰዉ ህይዎት ዉጭ እንደ ህዝብ  በግፈኞች የተዘረፈ እና የጠፋ ሀብት ለማስመለስ  ጠላቶች እንደሚሉት ፴(ሠላሳ ) ዓመት ሳይሆን ሶስት ዓመት እንደማይወስድብን የአማራ እና የአፋር ህዝብ የትግራይ ህዝብ ወረራ እና ምዝበራ ለመቀልበስ ያሳዩት አንድነት ፣ህብረት እና ቁርጠኝነት የፈረሰ መሰረተ ልማት ለማስተካከል ከሚየይቃቸዉ በላይ መስዋዕት ከፍለዋል፡፡

ይህን ያደረገ የአማራ እና አፋር ህዝብ ራሱን እና አከባቢዉን ብሎም አገሩን ከነበረበት ከፍ ለማድረግ የሚሳነዉ ህዝብ አለመሆኑ የተደገሰለት ሆነ የደረሰበት ግፍ እና ጦርነት ብቻ ሳይሆን ዓለም የሚመሰክረዉ ፣ጠላት የሚያዉቀዉ ግን የሚፈራዉ ነዉ ፡፡

ለዚህ ነዉ ፀረ ኢትዮጵያዉያን በቀኝ ይቁሙ በግራ የአፋር እና የዓማራ ህዝብ አንድነት ፣ ህብረት እና ነፃነት በተለያየ ህዝባዊ አደረጃጀት የሚያስፈራቸዉ፣ የሚያተኩሳቸዉ ፡፡

የአፍር ሆነ የኣማራ ህዝብ በሞት እና በህይወት ሆኖ ለራሱ እና ለአገሩ መሪር ዋጋ የከፈለዉ የግል ፣ቡድን እና የየትኛዉንም የፖለቲካ ጥቅም ለማስጠበቅ አልነበረም ፡፡

ከእኔ በላይ ለሳር ሲል የነበር አስተዳደርዋለሁ የሚለዉን ህዝብ እና አካባቢ ትቶ ….ሲሸሸ በማንነታቸዉ እና ኢትዮጵያ ላይ ድርድር አይታሰብም ያሉት የህይወት መስዋዕት ከፍለዋል፡፡

ለእነዚህ የቁርጥ ቀን ኢትዮጵያዉያን ዕዉቅና ፣ዕድገት እና ሽልማት ለመስጠት ባንፈልግ እንኳን ለአገር እና ለህዝብ ከብር እና ዳር ድንበር በማለት አገር ለማፍረስ ፤አንድነት እና ነጻነት ለማፋለስ ከመጣ ጠላት የማረኩትን ፣የነጠቁትን  ዛሬ ምንደር ለመንደር በጥላ የቆየ አይኑ ሲቀላ ክላ ከማለት ይልቅ የአድርባይ እና ፈሪ ምቀኛ መናጆ መሆን ሌላዉ ሊቆም የሚገባ ነዉ፡፡

ወደ ዓማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ስንመለስ  ፋኖ የኢትዮጵያ በተለይም የዓማራ ህዝብ የስጋም፤ የመንፈስም አካል ነዉ ፡፡ በአማራ ህዝብ ማንነት እና ነፃነት ላይ ባለቤቱ የዓማራ ህዝብ እንጂ ማንም ምንም ቢሆን በየትኛዉም መመዘኛ የሚመለከተዉ አይሆንም ፡፡

የዓማራ ህዝብ በአንድነት እና ህብረት አለመደራጀት እና አለመሰናኘት ለኢትዮጵያ ህልዎት ሆነ ሞት  ወይም ትንሳዔ ሆነ ዉድቀት ኃላፊነትም ፤ተጠያቂነትም አለበት ፡፡

የዓማራ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ የፓለቲካ ስልጣን ፍላጎት ኖሮት አያዉቅም ነገር ግን በማንነቱ ፣ በአገሩ እና በነፃነቱ ላይ የማይደራደር ስለመሆኑ  ከምንም  እና ከማንም በላይ  ኢትዮ-ዓማራ ጠል  እና ግትልትል አካላት የማይክዱት ሀቅ ነዉ ፡፡

በአማራ ማንነት እና ነፃነት ላይ ተረማምዶ የስልጣን ትሩፋት እና ከንቱ ዉዳሴ ለማግኘት የሚደረገዉ የቆየ ሠይጣናዊ ብልጠት ፀረ ኢትዮጵያዊነት በግልፅ ከሚያስተጋቡት ብሶ የአገሪቷን አንድነት ፣ የህዝብ ዕንባ እና ደም እንዲፈስ በማድረግ ስዉር ደባ የሚራምዱ ወዳጂ አሳዳጂ  ጠላቶች ፍላጎት ነዉ  ፡፡

የአማራ አንድነት እና ህብረት ለማንነት እና ለነፃነት መደራጀት የሚያቅረዉ በአማራ ማንነት እና ነጻነት ለስልጣን እና ለግል ጥቅም መኖር የሚፈለግ የኢትዮጵያዊነት ጥላቻ የነበረዉ የሚያገረሽበት ፀረ ኢትዮጵያ እና ዓማራ ነዉ ፡፡

ለዓመታት በእናት አገር  ምድር በቅለዉ  ኢትዮጵያ ብለዉ ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያዉያን አስኳል የሆነዉ ብዙኃን  ህዝብ -ዓማራ -የመደብ ጠላት ያደረጉት ኢህአዴግ አምላኪ እና ምልኪዎች ኢትዮጵያን ለማዳከም ኢትዮጵያዊነትን ከነስረ መሰረቱ ማንኮታኮት የታዩ የዓመታት የማንነት ጅምላ ጥላቻ ፣ ማሳደድ እና ግድያ መቀጠል ቱባ ማንነት እና ታሪካዊ በጎ ትሩፋትን ለማዛባት እና ለማጥፋት የሚያስችል የማንነት ጥቃት ዘመቻ መቀጠል ከወል ይልቅ መነጣጠል እንዳያመጣ ሊታሰብበት ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያን በመዳፋቸዉ ለማድረግ ለዘመናት የተጠቀሙበትን የአንድን ህዝብ እና ማህበረሰብ ተፈጥሯዊ፣ መልካ ምድራዊ ፣ሠባዊ ፣ማህበራዊ ፣ ታሪካዊ እና ማንነታዊ ማዛባት ( ማወናከር ፣ማደናገር ….) በጆርጂ ኦርኤል አበባል “The most effective way to destroy people is to deny and obliterate their own understanding of their own history.” ለ ፴ ዓመት በኢትዮጵያ ምድር በኢትዮጵያዉያን እና በተለይም በዓማራ ህዝብ ላይ ከቤተ ሙከራነት አልፎ በህዘብ መከራነት አስካሁን ቢዘልቅም ኢትዮጵያን የሚል ኢትዮጵያዊ በዋናነት የዚህ የጥፋት ቤተ ሙከራ ሰለባ ባለቤት -ዓማራ-  ራሱን እና አገሩን ከጥፋት እና ሞት ለመታደግ ለነጻነቱ እና ለማንነቱ መደራጀት፣ ህብረት እና የጋራ አንድነት እጂ ለእጂ ተያይዞ ለመሄድ ፈቃድ የሚጠብቅ መሆን የለበትም፡፡

ጠላት የዓማራን እና አፋርን ህዝብ ለማጥቃት የማንንም ፈቃድ እና ይሁንታ እንዳልጠየቀ ሁሉ እነኝህ ህዝቦች ራሳቸዉን እና አገራቸዉን ለመታደግ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ይሁንታ ከፍተኛዉን መስዋዕት እንደከፈሉ ሁሉ አሁንም ሆነ ለወደፊት በብሄራዊ የአንድነት ፍቅር እና መከባበር ማወቅ፣ መጠንቀቅ እና መታጠቅ  የራሳቸዉ የማይገሰስ አንጡራ መብት መሆኑን እየመረረን ቢሆን መቀበል አለብን፡፡

ሲወረሩ  ፣ሲመዘበሩ እና እንደ ዱር አራዊት ሲባረሩ  ያልደረሰ ዛሬ ለህልዉናቸዉ ዘብ መቆማቸዉ የሚያመዉ በህዝብ እና አገር ኪሳራ ትርፍ የሚያምረዉ ሰይጣን ወይም ጠላት ብቻ ነዉ ፡፡

ከዚህ አኳያ ፋኖ የ፻( አንድ መቶ) ዓመት እና ከዚያ በላይ ኢትዮጵያዊነት ጋር  የማይነጠል እና ድር እና ማግ ስለመሆናቸዉ ወዳጂ ቀርቶ ጠላት የማይክደዉ ዕዉነታ መሆኑን ኢትዮጵያ ጠል ክህደት የሚሟሸዉ በአማራ እና በአማራ ጥንካሬ ሊሆን ይችላል የሚል አንድነት እና ህብረት ዕንቅልፍ ይነሰዋል፡፡

በዓማራ ነጻነት እና በአገር ህልዉና መካከል አነዲት አንከን እና መለያየት የለም ዳሩ ግን አገርን እና ህዝብን በአገር ሀብት እና ንብረት ተደራጂተዉ አገር ለማፍረስ እና ህዝብ ለማክሰም ለአለፉት ፴ ዓመት እና ከዚያ በላይ በማን አለብኝነት መግደል እና በማንኛዉም መንገድ ከማንኛዉም ብሄራዊ እና ተፈጥሯዊ መብት ሲገፉ፣ሲያጠፉት ኖረውል ፤እየኖሩ ስለመሆኑ ይኸዉና ቀጥሏል፡፡

የማንነት እና የህልዉና ጉዳይ በህይወት መኖር ፤አለመኖር ጉዳይ ለይተዉ ሊነግሩን ለሚሹ በብዙኃን ሞት እና ስቃይ ዘመናቸዉን የሚያራዝሙ የሚመስላቸዉ ከጠላትነት የሚለዩበት አንዳች ምክነያት ሊኖር አይችልም፡፡

የማንነት እና የወሰን ጉዳይ ከግለሰብ እና ከማህበረሰብ ነፃነት የማይለይ እንደመሆኑ የአማራን ህዝብ ያለምንም ታሪካዊ እና ህጋዊ መሰረት የተነፈገዉን በተፈጥሮ የመኖር ማንነት ፣ህልዉና እና ይህን ዕዉን ለማድረግ የሚያስችል ህብረት እና አንድነት ለመመስረት የጠላቶችን ይሁንታ እና ፈቃድ መጠበቅ ይበቃል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ አግላይ እና በዳይ የህግ ማዕቀፍ -ህገ መንግስት- በልዩነት ስራ ላይ በማዋል ከአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት አስከ አሁን ድረስ በራሱ አገር እና ምድር ስደት እና ሞት የተፈረደበት ህዝብ በዓለም ኖሯል ከተባለ አማራ ስለመሆኑ እና ለዚህም ለአለፉት ሁለት አሰርተ ዓመታት በላይ ለህልዉናዉ (ማንነት እና ነፃነት) ሲታገል ኖሯል፡፡

ሆኖም የዚህ ህዝብ መደራጀት ኢትዮጵያ ትንሳኤ መሆኑን መረዳት የሚያዳግታቸዉ ዳተኞች ለግል እና ለቡድን ጥቅም እና ስልጣን ስስታቸዉ ስለሚልቅባቸዉ በጊዜዉ ከመመለስ ማድበስበስ ለዚህ አሁን ላለንበት አድርሶናል፡፡

ከዚያ በኋላ ለቀረቡ የወሰን ፣ማንነት እና አስተዳደር ጥያቄ መልስ ሲያገኝ (ሲሰጥበት) ለዓማራ እና ኢትዮጵያ ትንሳዔ  ጉዳይ መዳፈን  የዓማራ ህዝብ አለመደራጀት ከህግ እና ታሪካዊ አግባብ ዉጭ ለሆኑ ሠባዊ እና ተፈጥሯዊ የህልዉና ጉዳት መፍትሄዉ በህብረት እና በአንድነት (ኃይል  ) መቆም ብቻ ስለነበር ነዉ፡፡

በዛሬ ጊዜ የዓማራ ህዝብ እና ወገን የአፋር ህዝብ የደረሰበትን  አሳኝ እና ዘግናኝ በደል አይቶ እና ሰምቶ ከነዚህ ህዝቦች ህብረት እና አንድነት አለመቆም ኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት መከበር  በተቃራኒ ስለመገኘት  ብቻ ሳይሆን ሰባዊነት እና ዕምነት ጥያቄ ዉስጥ የሚወድቁበት ነዉ፡፡

ጠላት የትግራይ ወራሪ በ8 ወር ከተመደበለት 100 ቢሊዮን ብር በላይ በተለያየ መንገድ ዘርፎ የታጠቀዉን መሳሪያ በምድረ ኢትዮጵያ -ሰሜን ምዕራብ ፣ሰሜን  ህይወት ያለዉን ብቻ ሳይሆን ግዑዝ  እና መሬት ሳይቀር የደበደበበትን እና  ያመከነበትን ተጠያቂ ከመሆን ይልቅ ጠያቂ መሆን አይቶ እንዳላዩ ማለፍ የኢትዮጵያን በተለይም የዓማራ እና የአፋር ህዝብን መከራ እና ሰቆቃ የሚያሽር ሊሆን አይችልም፡፡

በነዚህ ህዝቦች የደረሰዉ በመላ አገሪቷ እና ህዝቦች የደረሰ እንደመሆኑ ለደረሰባቸዉ የዘመናት መከራ ዕዉቅና፣ ካሳ እና መታሰቢያ ሊደረግ ሲገባ ራሳቸዉን እና አገራቸዉን ቤዛ ሆነዉ ለተገኙ ጀግና ህዝቦች የታደጉት አገር እና ህዝብ ብቻ ሳይሆን መንግስትም ጭምር በመሆኑ በማንኛዉም ሁኔታ ወደ ፊት በህዝብ ፍላጎት እና አንድነት ከጠላት ራስን ሆነ አገርን ለመታደግ ለሚያደርጉት ማንኛዉም አደረጃጀት እና ህብረት ህዝብ እና መንግስት ብዙ ርቀት ሄዶ በሚገባዉ እና በሚችለዉ ሊደግፍ  ይገባል፡፡ ከዚህ ዉጭ የህዝብን መደራጀት የሚነቅፍ በህዝብ እና በአገር ብሶት እና ጩኸት  እንደመቀለድ ይሆናል፡፡ ለአገር አንድነት እና ሉዓላዊነት የህይወት ቤዛ ለከፈለ ሁሉ ከህዝብ እና ለህዝብ ለሚቆም ኃይል አደረጃጀት ባለቤትነቱ ለህዝብ መሰጠት አለበት፡፡ ለህዝብ እና ለአገር ከመኖር በህዝብ እና አገር መኖር ለለመደ የሕዝብ ችግር ላይሰማዉ ይችላል የችግሩ ባለቤት ህዝብ ግን ህመሙንም፤ሞቱንም ስላየዉ ከህመም እና ሞት ለመዳን ብቸኛዉ መንገድ መደራጀት እና በአንድነት ለዘላለማዊ ትንሳዔ መቆም ግድ የሚልበት ጊዜ አሁን ነዉ፡፡

 

 

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop