January 9, 2022
11 mins read

ፍትሕን እራሳቸዉ አልከሰከሷት!-መኮንን ብሩ(ዶ/ር)

abiy 1

ከክርስቶስ ዉልደት አንድ መቶ ሰባ ዓመታት በኋላ የተወለደዉ ሮማዊዉ ዳኛ ዮፒያን “ፍትህ ማለት ሁሉም የድርሻዉን ይቀበል ዘንድ የሚያደርግ ሚዛን ነዉ” ሲል ይገልፃል። አርስጣጣሊስ በበኩሉ “የሰዉ ልጅ ከሕግ እና ፍትህ ዉጪ ከሁሉም አዉሬዎች የከፋ አደገኛ ፍጡር ነዉ” ሲል የሕግና ፍትህን አስፈላጊነት ያሰምርበታል።

ያለ ሕግ እና ያለ ፍትህ ሀገር ሊኖር ቢችልም ሰላምና ዲሞክራሲ ግን ፈፅሞ አይታሰብም። እንግሊዛዊዉ ፈላስፋ እና ፖለቲከኛ ፍራንሲስ ቢከን “ፍትሕን መጠበቅ ያልቻለ ሕብረተሰብ ወይም ሀገር እራሱን መጠበቅ አይችልም” ሲል ፅፏል። ፍትህ ለሰዉ ልጆች በመከባበር አብሮ ለመኖር ወሳኝ ነዉ። ያለ ፍትህ ጭቆና ወይንም አምባገነን የትዉልድ ነቀርሳ ሆኖ ይንሰራፋል። “ፍትህ ባለበት ማንኛዉም እዉነት አይጎዳም” ይሉ ነበር ጋንዲ፤ ያለ ፍትህ ግን ሁሉም ይጎረብጣል።

ከአንድ ቀን በፊት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የእራሳቸዉን መንግስት በተለያየ ፈርጁ አምርረዉ ሲወቅሱ ተደምጠዋል። በተለይም የፍትህ ስርሃቱን የዘቀጠና የተጨመላለቀ ሲሉ ገልፀዉት ነበር። ይሁን እንጂ እስከ ገና ባዕል ምሽት ድረስ ጠቅላዩ ሊሉ የፈለጉት በትክክል የተገለፀለት ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ለፍትህ የሚታገል ግን ፍትህን የተራበ ሕዝብ በመሆኑ የጠቅላዩን “የዘቀጠ የፍትህ ስርሃት” ንግግርን ያዳመጠዉ የነገን የፍትህ ዘመን ተስፋ በመናፈቅ እንጂ ሰዉዬዉ በኢፍታዊነት ቆስለዉ አመርቅዘዋል ብሎ አልነበረም።ይሁን እንጂ የሕመማቸዉ ዱብዳ በጌታ ልደት ምሽቱ ተገለጠ። በርካቶችን ለሞትና ለስቃይ የዳረጉትን ፋሺስቶች በቀጭን ትህዛዝ ከእስር እስኪለቁ ድረስ በእዉነትም አብዝተዉ የተጨማለቁ ብቻ ሳይሆን በኢፍታዊነት ነቀርሳ የቆሰሉና የሚያጣጥሩ በሽተኛ መሆናቸዉን ያልጠረጠሩ ሁሉ ዕጢ አስጣሉ። አዎን ጠቅላዩ በኢፍታዊነት በፀና ታመዋል። አመርቅዘዋልም።

በአንድ ወቅት እራሳቸዉ ሲናገሩ “ከዉጪ ሀገራት ለምኜ ያመጣሁትን ፍራንክ ምንም ላደርገዉ እችላለሁ፤ …… ፓርላማዉም ሊጠይቀኝ አይገባም” ብለዉ ሲመፃደቁ ብዙዎቻችን ሰምተን እንዳልሰማ ያለፍነዉ ሰዉዬዉ በለመኑት ሳንቲም እየሰሩ ያሉት ለሀገር ሊጠቅሙ የሚችሉ ፓርኮችና መዝናኛ ቦታዎች በመሆናቸዉ እንጂ የመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ፣ በሕዝብ ጊዜና ገንዘብ ከሀገር ሀገር እየበረሩ፤ በትረ ስልጣኑንም ሆነ ማዕረጉን ተላብሰዉ በየሄዱበት ዕቅፍ አበባ እየታቀፉበት ልትጠይቁኝ አትችሉም የሚለዉ አባባላቸዉ ዉሃ የማይቋጥር ተላላ አባባል መሆኑ ሊገባቸዉ እንዲት እንዳልቻለ ተገርመን ትተነዋል። ምናልባት ያኔ የሕመማቸዉ ሁኔታ ቀላል ቁስል ቢጤ በመሆኑ እያደር ይደርቃል ያሉ በርካቶች ሳይሆኑ አይቀሩም። አሁን አሁን ግን ቁስሉ ዉስጥ ዉስጡን ሳያመረቅዝ የቀረ አይመስለኝም። ይህ ደግሞ አደገኛ ነዉ። አሜሪካዊዉ ገጣሚ እና ፀሐፊ ተዉኔት ጀምስ ባልድዊን እንደሚለዉ “አለማወቅ ከስልጣን ጋር ከተጣመረ በጣም አደገኛ ነዉ”። ጠቅላዩ የኢፍትሃዊነታቸዉን ጥልቀትና ንቅዘት አለማወቃቸዉ ከድርጊታቸዉ በላይ አደገኝነቱ አስፈርቶኛል።

ማርክስ ኤንግልስ እና ሌኒን የሶሻሊዝም መገለጫዎች የሆኑትን ያህል ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ እና ደብረፂሆን የሽብርተኛዉ ትህነግ ማዕተሞች ናቸዉ።እነዚህ ፋሺስቶች  የሃያ ሰባቱ ዓመታት የኢትዮጵያዊያን ስቃይ እና እንግልት፣ ለብዙ ሺዎች ከሀገር መሰደድ፣ ለበርካቶች አካለ ስንኩል መሆን፣ ለመቶ ሺዎች ያለ ወላጅ አልያም ያለ ልጅ ባዶ መቅረት ተጠያቂ ናቸዉ። በተጨማሪም ላለፉት አንድና ሁለት ዓመት በተኙበት ለተረሸኑ፣ ከወላጆቻቸዉ ተመንጭቀዉ ተወስደዉ ለተደፈሩ፣ ቅዬቸዉ በትግራይ ወራሪዎች ተወሮ በቁማቸዉ ለተቃጠሉ ወገኖቻችንም ኃላፊነቱ በእነሱ ጫንቃ ላይ ነዉ። ታዲያ አንድ ቀን ለፍርድ ሳይቆሙና ሳይጠየቁ መለቀቃቸዉ የማያበሳጨዉ ካለ እሱ ገዳዩና ደፋሪዉን መሆን አለበት። ለዚህም ወንጀል ፍትህን የማይሻ እርሱ በሽተኛ ነዉ። ጊዜ ይፈጃል እንጂ ፍትህ ደግሞ ሁሉም ላይ መፋረዷ አይቀርም። ፍትህ ያጎደለም፣ ፍትህ ያዛባም ሁሉም በጊዜ ዉስጥ ዋጋዉን ከፍትህ ያገኛል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ የቀድሞ ነገስታትንና መሪዎችን በመጠቃቀስ የሚመስለኝን ፁሑፍ ለአንባቢዎቼ አቅርቤ ነበር። መይሳዉ ካሳን በጀግንነቱ፣ እምዬ ሚኒሊክን በብልሃተኝነታቸዉ፣ ኮረኔል መንግስቱን በሀገር ፍቅር ስሜታቸዉ፣ እንዲሁም ዶክተር አብይን ከፕሬዘዳንት ሊንከን ጋር በማመሳሰል ኢትዮጵያን በዚህ ወቅትም ለማስቀጠል መቻላቸዉን በመተረክ የእኛዉ ሊንከን ብያቸዉ ነበር። በዚያ ፁሑፌ አልፀፀትም፤ እንደዉም አሁንም ቢሆን ያ ዕምነት እና አመለካከት በእሳቸዉ ላይ አለኝ። ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በሆነ መልኩ ብቅ ብለዉ የተዋጋሁት ለኢትዮጵያ አንድነት ስል አልነበረም እስኪሉ ድረስ (የሚሉ ከሆነ) እኔ ለኢትዮጵያ መዝመታቸዉን አደንቃለሁ። እቀበላለሁ። ይሁን እንጂ ይህን ያህል ጭፍን እና ኢፍትሃዊ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ መቼም ገምቼ አላዉቅም ነበር። ይህ ብቻ አይደለም፤ መዋሸትም እንደሚችሉ ታዝቢያለሁ፣ በመሆኑም ዳግም ላምናቸዉ እቸገራለሁ። “ሽማግሌ ከፍርድ በፊት አትላኩ እኔ ይህን ማድረግ አልችልም” ያሉትን ዘንግተዉ በቀጭን ትህዛዝ ፋሺስቶችን ከእስር ቤት በመፍታት ዋሽተዋል። የዋሸ ደግሞ ዉሸታም ነዉ። ስለሁሉም አዝናለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

መኮንን ብሩ (ዶ/ር)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop