ለእኛ ለባርነት ሆድ :ለነፃነት ክንድ  –  ማላጂ

በአገራችንም ሆነ በዓለም የነፃነት ታጋዮች ለዘመናት ከየትኛዉም የገዥ ክፍል መደብ ያልነበሩ እንዲያዉም በስርዓቱ ከፍተኛ ጭቆና እና ግፍ የተቀበሉ ነበሩ ናቸዉ ፡፡

እንደ እኛ አገር ሁሉ ሌሎች አገሮች እና ዓለማት የነፃነት ፋና ወጊዎች( ፋኖ) በኪዩባ አብዮት ወቅት ፊደል ካስትሮ፣ ቸኮ ቬራ ፣ ሮል ካስትሮ ፣ በደበቡብ አፍሪካ ኔልሰን ማንዴላ ፣ በዚምበብዌ ሮበርት ሙጋቤ በዓለማችን በግንባር ቀደምትመት የየአገራቸዉን ክብር እና የህዝብ ፍቅር እና አጋርነት ይዘዉ የህዝብ ልጂነታቸዉን በደም እና አጥንት ያረጋገጡ የባለደማቅ ታሪክ ባለቤት ፋኖዎች ነበሩ ፡፡

ሁሉም በየዘመናት በነበሩ ሆድ አደሮች እና የስልጣን ጥመኞች ተሳደዋል ሞተዋል፡፡ ሁሉም ከራሳቸዉ አልፈዉ ለሌላ የሚሆን አቅም እና ስም ነበራቸዉ ነገር ግን በህዝባቸዉ እና በአገራቸዉ ላይ ይደርስ የነበረዉ የአገዛዝ ብልሽት እና አድር ባይነት ከግል ድሎት እና ምኞት ለወገን ኖሮ ማለፍን መርጠዋል፡፡

በዚህም በሠነፎች እና በአዉርቶ አደር ሆድ አምላኮች ቸኮ ቬራ እና ብዙ የኩዩባ አብዮት አራማጂ ፋኖች በጊዜዉ በነበሩ የስልጣን ጥመኞች ተገድለዋል፡፡ ሆኖም በዓላማ አንድነት እና ፅናት የተጀመረ የነፃነት ጉዞ በክንድ ማረጋገጥ የዘመኑ አቻ የማይገኝለት አማራጭ መሆኑን ተረድተዉ የነፃነት ፋና ወጊ ፋኖዎችን አርማ ያነገቡት ተወዳጆች ፤ፊደል ካስትሮ፣ ሮበርት ሙጋቤ ፣ ኔልሰን ማንዴላ ፣ ሮል ካስትሮ….ለአገራቸዉ እና ለዓለም የማይረሳ የነፃነት ተጋድሎ ገድል ፈፅመዋል፡፡

ወደ እና አገር የነፃነት ትግል ስንመጣ ለአገር ህልዉና እና ህዝብ ተፈጥሯዊ በነፃነት የመኖር ሠባዊ መብት ለመከላከል እና ለማስቀጠል ፋኖ በሚል የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ ከ፪ ክ/ዘመን የሚሻገር ዕድሜ እንዳለዉ ቢያንስ እንጂ የሚቀነስ አይደለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወያኔ ትግሬዎች በጉንደት፤በጉራዕ፤በዶጋሊ፤….ጦርነቶች የሚዋሹት ውሸት ሲመረመር

የኢትዮጵያ የነፃነት ፋና ወጊዎች እና ብርሃን ፈንጣቂዎች “ ፋኖስ ” ሆነዉ ከዐለማ አገዛዝ ወደ ብርኃን፤ ሻማ ሆነዉ በመቅለጥ ለህዝብ አርነት እና ለአገር አንድነት መሰረት ጥለዉ አልፈዋል፡፡

ይህም ከቅርብ ዘመናት እንኳን ከአደዋ አስከ ሸዋ ምድር በሆነዉ  የዉጭ እና የዉስጥ የዕብሪተኞች ወረራ በግንባር ጠላትን መዉጫ መግቢያ ያሳጡት በነዲድ የአገር እና ህዝብ ፍቅር ተወልደዉ እና ተኮትኩተዉ ያደጉት የብዙኃኑ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ፋኖች ነበሩ ፤ናቸዉ ፡፡

ፋኖ እና ኢትዮጵያዊነት ማግ እና ክር ሆነዉ የሚታዩ እንጂ ኢትዮጵያዊነት ፋኖነት የማይለይ ጭራ መሰንጠቅ የክፋት አባዜ ምልክት ነዉ ፡፡

በኢትዮጵያችን በአደዋ የነፃነት ተጋድሎ፣ በ1928 ዓ.ም የኢጣሊያ ዳግም ወረራ ፣ ከ1983 ዓ.ም.አስካሁን ለነፃነት እና ለአገር ሉዓላዊነት ክብር እየተደረገ ለነበረዉ እና ላለዉ ተጋድሎ  ትልቁን ሚና የሚይዙት፤ አገር እና ህዝብ የሚታደጉት የህዝብ ልጂ የነበሩት እና ያሉት የነጻነት አርበኞች ፋኖዎች ነበሩ ፤ ናቸዉ ፡፡

ታላቁ መፅሀፍ እግዚያብሄር የሾመዉን ማን ይሽረዋል ….አንዲል የህዝብ የሆነዉን እና ከህዝብ አብራክ ወጥቶ ለአገር እና ህዝብ ህይወቱን ቤዛ ለሚያደርግ ከህዝብ በላይ ማን ሊሾምም ሆነ ሊሽር አይቻለዉም፡፡

ማንም አገሩን እና ራሱን የሚያከብር ወገኑ ፤ ህዝቡን እና ብዙኃንን ያከብራል፡፡

እነ ደጃች በላይ ዘለቀ፣ ራስ አበበ አረጋይ፣ደጃች ባልቻ አባነፍሶ……የነጻነት አርበኞች / ፋኖ ነበሩ ፡፡

ለዕዉነተኛ ዘላቂ ነፃነት እና ብሄራዊ  አንድነት የችግር ጊዜ ደራሽ የቁርጥ ቀን ህዝብ ልጆችን በነበረዉ እና በሚያኮራ የነፃነት ትግድሎ መጠሪያ እና መኩሪያ በሆነዉ  የነጻነት እና ህልዉና ኃይሎች አርማ  ፋኖ መጥራትም ሆነ መጠራት  ዕዉነት እንጂ ሀፍረት ሊሆን እንደማይችል መረዳት አለብን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢህአዲግ ከ70 ዓመት በፊት በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን በተገነባ ስታዲዮም ውስጥ ሆኖ ግንቦት 20 እያከበረ ኢትዮጵያ አድጋለች ይላል

ጀግኖች በሞቱለት የእናት አገር ህልዉና መረጋገጥ እና የህዝቦች ነፃነት መከበር ቀና ብለን እንድንቆም ላደረጉን ክብር እና ፍቅር እንጂ  ማለባበስ ከየትም እንደማያደርስ  ከኋላ ታሪካችን ልንማር ይገባል፡፡

በየዘመኑ ክፉ ቀን ያወጣ ክፉ ቀን ይ መስላል እያልን  እነ ዐፄ ቴወድሮስን ፣  ደጃች በላይ ዘለቀን ፣ ንግስት ዘዉዲቱን ፣ ኮ/ል አጥናፉን እና ጓዶቻቸዉን ፣ በዘመነ ጥልመት (ህወኃት/አህዴግ) በጅምላ ፍጂት እና ስደት እና ብሄራዊ ክህደት  የአገራቸዉ እና የህዝባቸዉ ጥቃት  ሠላም የነሳቸዉ   ብዙዎች ነፃነት ወይም ሞት ያሉትን  ( ፐ/ር. አስራት፣ አስማረ ዳኜ፣ ሳሙኤል አወቀ  …..) ይህም በህይዎት የሚገኙትን  ህዝብ የሚያዉቃቸዉን እና የሚያደንቃቸዉን የህዝብ ልጆችን በክፉ የሚመለከቱ ሆድ አደሮች ለዓመታት ለኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ እንወክለዋለን ለሚሉት ህዝብ ያተረፉለት ባርነት፣ ሞት ፣ ድህነት እና ስደት ነዉ፡፡

አበዉ ሆዱን የወደደ ማዕረጉን ይጥላል፣ ሆዱን ያለ ፤ሆዱን አኃለ…. እንዲሉ ባርነት እና ድህነት  በሆድ እንደሚንሰራፉ ፤ ነጻነት በክንድ ብቻ ሊረጋገጥ እንደሚችል የዘመናችን ፋኖ ተጋድሎ ከሚመሰክርልን ዉጭ ሌላ እማኝ አያስፈልገንም፡፡

እዉነተኞች ሠዎች እና ኢትዮጵያዉን ከሆን በየትኛዉም ዘመን እና ዓለም ነፃነት ለማጠበቅ ፣ ለማስከበር እና ለማስቀጠል ከክንድ(ኃይል) ዉጭ በዉድ እና በሆድ  ባርነት መሆኑን ልናዉቅ እና ከክፉዎች ማደንዘዣ ልንጠበቅ ይገባል፡፡

 

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share