የምዕራባውያን ፍላጎት ሁሌም እንደምንሰማው እና እንደምናወራው የራስቸውን ጥቅም ለማመቻቸት ነው ይባላል። እውነት ነው ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል ይባል የለ። ወዳጅ ተብዬው ለሞፈርነት የተመያትን ዛፍ ለማግኘት አንድም በብልጠቱ አለዛም በክፋቱ ካልሆነም በሃብቱ ይደራደርባታል። ሁልግዜ የሚያያት ዛፍ የሱ አላማው ነች ቆርጦ ለመውሰድ። የማረሻ ሞፈር ችግርም ላይኖርበት ቢችልም ለነገ ተጨማሪ አስፈልጎታል ለእራሱ ማድረግ አለበት። እያየ የጎመጀበትን እድሜ አስተውሉ የአንድ አመት እይታው እንዳልሆነ ይታወቅ። የሞፈሩን እንጨት ቆርጦ የእሱ ለማድረግ የተለያዩ ሙከራዎችን ማድረጉ አይቀሪ ነው ። ሃሳቡን ከፍ ላድርገውና ያዛን ሞኝ ገበሬ ለዛች ዛፍ ሲል መሬትህን ሽጥልኝ ሳይለው ይቀራል፣ በተለይ ትንሽ ቸገር ብሎ ካገኘውማ ለድፍረቱ ከልካይ የለውም። የተመኘውን ማግኘት አለበት የመቆረጫው ጊዜ ማለፍ የለበትም ለአገልግሎት በምትውልበት ሰአት ማግኘት ያስፈልገዋልና መስዋትነት ማድረግ ይጠብቅበታል።
ሁላችንንም በምዕራባውያኑ ላይ ያለንን ስሜት ማንሳቱ ተገቢ ነው። ያገኘነው የተሻለ ሁኔታ አለመኖሩ ከቀደም ስራዎቻቸው እና ፍላጎቶቻቸው በመነሳት ግምቶቻችንን አንድ ያደርገዋል። አብዛኞቻችን መመልከት ያልቻልናቸው የተደበቀው የምዕራባውያን አስተሳሰቦች እና የሚፈልጉትን ለማግኘት የሚሄድበትን መንገድ አለመረዳችን ይሆናል። ከስሜቶቻችን ተነስተን የምሰጣቸው መላምቶች በደንብ ያልበሰሉና ነጥረው ያልወጡ ሃሳቦች መሆናቸው ልዩነትን ከመፍጠር አያልፉም። የአንድ ወቅት ትርክት በሌላ እየተተካ ሲሄድ መሰራት ያለበቸውን ስራዎች እና የመዕራባውያኑ ሃሳብ የተረዳውን አስተሳሰብ ለማዳመጥ እና ለመረዳት ይቸግረናል። ምዕራባውኖቹ ጥቅም ፈላጊዎች ናቸው ሃይላቸውን ገንዘባቸውን አውጥተው ሲሰሩ ለሚተገብሩት ስራ የግዜ ገደብ እንዳለው ለመረዳት የተለየ ጥበብ አያስፈልግም በተለያየ አጋጣሚዎች የሚገለፁ ናቸውና አስተዋይ ልቦና ብቻ ነው የሚያስፈልገው።
የአለማችን የተፈጥሮ ሃብት እየመነመነ እና ያላትንም በመለገስ ሂደት ወስጥ የተዛባ እየሆነ መምጣት፣ በፍላጎቶቻችን ላይ ውስንነት እና እጥረት ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብ ቁጥር የሚጨምርባቸው አካባቤዎች ትኩረት የሚያስፈልጋቸው እየሆነ መጥቶል። በማደግ ላይ የሚገኙ አገራት ተብለን የተፈረጅነው አፍሪካያን በተለይ ደግሞ የተፍጥሮ ሃብት ባለቤት መሆኖ በምዕራባውያን ትኩረት የተሰጠን የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገራት የህዝብ ቁጥራችን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ከመሄዱ በተጨማሪ የስራ አጡ ቁጥር አሳሳቢ ነው ። በምዕራባውያን የሚደረግለትን ምፅዋት የሚጠብቅ ትውልድ እንዲሆን ሆኖል። ያለንን የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ ለመሆን የአገራቱ ኢኮኖሚ ዝቅተኛ በመሆኑ የተሻለ አሰራሮችን አደራጅቶ ከተመፅዋችነት ለመውጣት እንደማንችል በምዕራባውያኑ ታሳቢ ከሆነ ውሎ አድራል።የህዝብ ቁጥሩ መጨመር በአካባቢው ሰላም አለመኖርን ተከትሎ የተነሱት እሳቤዎች አገራቱ በጋራ ሊለሙ የሚችሉበትን ሃሳብ በመንደርደርያነት በማስቀመጥ ህዝቦች በአንድነት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለመፍጠር የታሰበ ነው። ከግብፅም የሚያገኙትንም ጥቅም ለማስቀጠል እና አስተማማኝ ማድረግ የሚያሳስባቸው ሲሆን የነበረው የምስራቁ አዲኦሎጂም ከአፍሪካ ቀንድ ማራቅ ግድ ይላቸዋል።በዘመናችንም የቻይና በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉት የሃብት ፍሰት ለዘመናት የቆጠቧትን አፍሪካ ሊያስነጥቃቸው እንደሆነ ከማሰብ አልቦዘኑም።
የዚህ ሃሳብ የመጀመርያ ሰልባ ያደረገው ዋንኛው አገራችን ስትሆን ለአላማቸው ግብ አስቀምጠው በከፍተኛ ሁኔታ የውስጥ ደባ የጀመሩት በኢትዮጵያ ላይ ነው። ቀደም ብለን ባነሳነው ሃሳብ ምዕራባውያን የሚፈልጉን ለጥቅማቸው ነው በሚለው አመለካከት ብንስማማም በአካሄዳቸው እውቀቶቻችን ይለያዩና ለችግሮቻችን ምክንያት በመስጠት እንዳንስማማ እየተደረገ ሳናውቅና ሳይገባን እንቀራለን።
አንዳንዴ ምዕራባውያን ለምን እርዳታ ያደርጉልናል ብለን እንጠይቃለን ። ይህ ሃሳብ በሁላችን ውስጥ የሚያቃጭል ሃሳብ ከሆነ ጥሩ አመለካከቶች ማንሳት ቻልን ያስብላል። ችግሩ ጥያቄውም የሚነሳው ከችግሩ ተካፋይ ወይም መፍትሄ ከሚፈልገው አካል አለመሆኑ ነው። የአገራችንን የተፈጥሮ ሃብት አብቃቅተን የህዝብ ቁጥራችንን መጥነን መኖር መቻላችን ቀድመን የምንሰራው የቤት ስራዎች ይጠበቅብናል። የሰው ልጅ በተሰጠው እኩል የሰውነት መብት በህይወት እስካለ ድረስ ከሚያስፈልጉት የመጨረሻዎች ፍላጎት መብላት ፣መጠለያ እና ልብሱ መሞላታቸው ግድ ይላልና ነው።
የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገራት በኢኮኖሚ እራሳቸው መቻል ሳይችሉ ስለእድገት ማሰቡ የማይፈታ ህልም ሲሆንባቸው፣ የህዝቦቻቸውን ችግር ለመወጣት ለተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች የይድረሱልን ጥያቄ እያቀረቡ ልመናቸውን ተገን አድርገው እንደአገር ለመቀጠል አመታዊ ባጀት ሲያዘጋጁ ይታያል ።እርዳታው ይቁም የሚለው ጥያቄ አያሳስበን ይሆናል ። በእድገቴ ላይ ተፅእኖ አድርጎብኛል እና አልፈልግም ብለን ስናስብ ነው አሳሳቢ የሚሆነው። ወደድንም ጣላን አንድ ወቅት ላጋሾቻችን ምፅዋታቸውን ማቆማቸው አይቀርም። ለዚህ ደግሞ ምዕራባውያን ያስቀመጡት የግዜ ገደብ እንዳለ መዘንጋት የለበትም።
የህዝብ ቁጥራችንን መጥነን የተፈጥሮ ሃብታችንን የማብቃቃት ሃላፊነት ለራሳችን የተተወ ሲሆን በማውቅም ይሁን ባለማወቅ ጦርነትም ይሁን ሌሎች አማራጮቻችን እየተገበርን ያለነው የቤት ስራዎቻችን እንደሆኑ ማስታወስ ግድ ይላል ።
አገራችንን የተመለከትን እንደሆነ ምዕራባውያን የሄዱበትን የህብረተሰብ ግንባታ ቀርቶ በምዕራባውያኑ ይተገበር የነበረውን 19 ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ ያላስወገድን ነን ። እርስ በርስ ጣርነት ውስጥ የተዘፈቅን ነን ። በጎሳ የበለፀገ ማንነታችን በሃይማኖታዊ ጥያቄዎች እየተከበበ ለልዩነቶች እየዳረገን ግለስባዊ ፍላጎቶች እያደጉ አገራዊ ማንነትን እያስጠፋን ይገኛል።
ሰዎች በአለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራቸው ትስስር እየጎለበተ መምጣቱ በሰውነት ቀለም የነበረው ልዩነት መሰረት የሌለው ሆኖል፣በጋራ ለመራመድ የሚያግባባው የአገራት ኢኮኖሚ ነው ። የአገራት ተቀራራቢነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት በቀላሉ ውህደት ሲፈጥር ይታያል ። ለዚህም ነው ብል መረጥኩ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገራት ኢኮኖሚ በጣም ዝቅ ማለቱ ከምዕራባውያኖቹ ጋር አብሮ የመሄድ አቅም ያጣው። ያላንን እምቅ ሃብት ለመጠቀም ብድር ወይም ስጦታ ያስፈልገናል ። ለዚህ ደግሞ የሚያበቃ ዝግጅት መደረግ አለበት። በተለያየ ግዜ የቀረቡልን ከአለም ባንክ ይሁን ከሌሎች አለም አቀፍ አበዳሪዎች የሚቀርቡት ጥያቄዎች መሰረታቸው በህብረተሰቡ ላይ ያተኮሩ ናቸው። እርዳታ ሰጭዎቻችንም በቀጥታ የህዝብ ቁጥራችሁን እንቀንስ ባይሉንም በተለያያ ሁኔታ ሙከራዎች አድርገዋል ።በተለይ በአለፍናቸው 30 አመታት ምዕራባውያኖቹ ስርተውብናል የሚፈልጉት ላይ ለመድረስ የመጨረሻ ምእራፍ ላይ እንደሆንን መታወቅ አለበት። ጊዜው ካላለፈብን የሚሉንን በብልጥነት ማለፍ መታሰብ ያለበት ጉዳይ ነው። በተለይ መሪዎቻችን እውነታውን ለህዝቡ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ግልፅ በሆነ አነጋገር የምዕራባያኑን ፍላጎት ለማስጠበቅ እስካሁን የተሳተፉባቸውን ድርጌቶች አካተው ቢሆን ጥሩ ነው እላለሁ።
የምዕራባውያኑ አስተሳሰብ በኢትዮጵያን እና በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ
የቀደምት የሕወሃት መሪዎች አሰራር ብንመለከት የምእራብያውያኑን ፍላጎት የሚተገብሩበት መንገድ ስር የሰደደው በአለም አቀፍ ደረጃ የታመነበት አስራር የተከተለ ነበር። የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ የተፈጠረው አመራር ምስጥር ያልገባቸውና በጊዜዎች ቆይታም አስተሳሰባቸው በማርጀቱ ቀጣይነት ያለው ስራን ሊያሰራቸው አልቻለም።
አቶ ኃይለማርያምን ብናነሳ የመለስ የቅርብ ወዳጅና በደህንነት ውስጥ የነበራቸው የምሥጥር አዋቂነት ቦታ ነበር ለስልጣን እንዲበቁ ያደረጋቸው፣ ስልጣናቸውን ለማቆየት ብልጥ መሆናቸው ከሕወሃቶቹ በተሻለ የምዕራብያኑን ፍላጎት እንደሚተገብሩ ታምኖባቸው ነበር። በዙሪያቸው የነበሩት የግል ሃብት በመሰብሰብ ላይ የነበሩት ትልልቆቹ ሕወሃቶች አመራራቸው እና ማንነታቸው ቦታ የሚደፋ እንዲሆን አላስደረጋቸውም።
ዛሪም ስልጣንን በመፈለግ የተገለፁት ማንነቶች በምእራብያኑ እምነት ማጣታቸው የልዩነቶች መሰረት ሆነዋል።እየተመለከትን ላለው የተዘባራረቀ አስተሳሰቦች መሰረት የሆነው ለስልጣን ያበቃቸው በምዕራብያኑ ተቀባይነት የነበረው ማንነታቸው ነው። ማስተካከል የሚቻልባቸው ሁኔታዎች የሉም ማለት አይደለም፣ አንዳንዴም እኩል ማሰብ ተገቢ ነው በጊዜዎች ተበልጠናል። አማራጮችን ለመመልከት የሚያስፈራ ነገር እንዳለ ማስተዋሉ ካላስፈላጊ ጥፋት ያድነን ይሆናል እንጂ መሸነፍን አያመጣም። ሉአላዊት ኢትዮጵያ የግላችን የህዝቦቿ ስትሆን ምዕራብያኑ ደንታ እንደሌላቸው መመልከት ይጠበቅብናል።
በምዕራባውያኑ የተሰጠው የጊዜ ገደብ የሚያበቃበት ደውል እየተደወለ ነው።በአለፍናቸው አመታት ብዙ ተሰቃይተናል አሁን ነገሮች መቆም አለባቸው ። ጦርነት ብዙ መስዋትነት ያስከፍላል የአገራችንን መዳከም የህዝብን መበታተን የሚፈልጉ ጠላቶች እንዳሉን ማስተዋል ተገቢ ነው።ሁላችንም በአንድነት የምንቆመው ለአገራችን እድገት መሆን ይገባዋል፣ በጦርነት የተዳከመን ኢኮኖሚ ለመገንባት ለቀጣዩ ትውልድ መተው የለበትም ።
አማራጩ ሁለት ናቸው አዲሱ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገራቱ አስተሳስብ ያገራቱን ሉአላዊነትን ባልተጋፋ መልኩ ስለአብሮ መቀጠል እና ማደግ ያነሳሉ። ሌላው ምዕራባውያኑ ያስቀመጡት አምስት ወይም ስድስቱን ምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገራት አንድ አድርጎ የማስተዳደር አላማ ነው።የሁለቱም ግብ አንድ ቢሆንም ምዕራባውያኖቹ ከእኛ ጋር ተባብሮ የሚሉንን መስማት የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገራቱ ሉአላዊነታችንን ይጋፋል የሚለውን እዲያስቡ አድርጓቸዋል ።ራእይ ማድረግ የሚገባን ለቀጣዩ ትውልድ መሆን አለበት ከጎሳ፣ ከሃይማኖት ነፃ የሆነ የትልቋ የበለፀገች ምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገር እንዲኖረው ይታሰብ እላለሁ ።
በዚህ ዘመን የተፈጥሮ ሃብታችን ብቻውን የበለፀገ አገር ይፈጥራል የሚለውን አስተሳሰብ የምጋራው አይደለም ። ለመተባበር አብሮ ለመቀጠል ሊኖረን የሚገባው የጠነከረ ኢኮኖሚ ትስስር ነው እላለሁ። የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገራት የጋራ ራእይ ትልቅ ባጀት የሚያስፈልገው መሆኑ አይቀሪ ነው፣ አማራጮችን አዘጋጅቶ ለፍልሚያው መዘጋጀት ጠለቅ ብሎ መታስብ አለበት።
የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገራትን በአንድ ላይ ለማደግ ይችላሉ የሚለው የምዕራባውያኑ አስተሳሰብ እና አመለካከት ለአገራቱ ይበጃል ተብሎ እሳቤ መሆኑ የሚያስፈራ አይደለም። ዋንኛው ያተመጣጠነ የህዝብ ቁጥር መኖሩ ትኩረት የተሰጠው መሆን የእርስ በርስ የጎሳ ፣ የሃይማኖት ልዩነቶች በአካባቤው ላይ አለመረጋጋት አያስወግድም የሚል አስተሳሰብ ሲጨመርበት ውስብስብ ያደርገዋል። አገራችንን ኢትዮጵያ እንደ ምሳሌ ብንወስድ የቆየ የማንነት ጥያቄ የምታስተናግድ አገር ይዞ ትልቅ የጋር የሆነ አስተሳሰብን ለማራመድ ማስቸገሩ አይቀሬ ነው። ኩሩ ህዝብ የቀኝ ግዛትን ያልቀመሰ ሲሆን ፣ህብረተሰብ የእኔ የሚለው ማንነቱን የበላይ አድርጎ ስለሚያስቀምጥ የግዛዊ ማስተካከያ ሳይሆን መሰረታዊ ማንነቱን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ስራዎች የሚያስፈልገው እንደሆነ በመዕራብያኑ የታመነበት ነው።
የአፍሪካን ቀንድ አገራት የትብብር ስራዎች ቀድሞ ከነበራቸው የድንበር የህዝብ ለህዝብ ትስስር በላይ ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ከሱማልያ፣ከጅቡቲ እና ከኤርትራ ጋር እየገነባች ያለችው ዘመናዊ የሆነ የትራንስፖርት መስመሮች መኖራቸው የበለጠ ሁኔታዎችን ሊያበረታት ይችላል ። ከኬንያም ጋር ይህ ነው የሚባል የጋራ ስራዎች ባይታዩም በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር ሞያሌ ሊሰራ ታቅዶ የነበረው ዘማናዊ እና ትልቁ የንግድ ከተማ አንድ ምእራፍ የምስራቅ አፍሪካን አገራት የሚያደርሳቸው ነበር። በኤርትራም ሊገነባ የታቀደው ትልቁ የጋራ ከተማ ከዱባዩ ተወዳዳሪ የሚያደርግ ነበር።
ምዕራባውያን በተለይ አሜሪካ የኢትዮጵያ ሃይል በማዳከም ወደተነሱበት አላማ ለመድረስ የሄዱባቸውን መንገዶች በግልፅ አሁንም ምላሽ ለማግኘት ቢያስቸግረንም በአለፈው ሳምንት ጄፍሪ ፍሊት ማን የገለፁትን መንደርደርያ በማድረግ የቀድሞ ስውር ደባዎችን ሲተገብሩ የተከተሉትን አማራጮች እና ስራዎቻቸውን በአጭሩ ብንመለከት።
የኤርትራን መገንጠል ያስተናገደው አስተሳሰብ ለምን የተሰጠውን የቤት ስራዎች መስራት አልቻለም
በአንድ ላይ ሆነው የሴሜኑን ኢትዮጵያ ችግር ለመፍታት በትግል ላይ የነበሩት አካላት ምላሽ ያገኙበት ወቅት ነበር ። ሻቢያም ኤርትራን ሲይዝ ሕወሃትም በአጠበቀው ሁኔታ ኢትዮጵያን ተቋጣጠረ ። በቀጣይም በሻቢያው እና በሕወሃት መካከል ያለው የዘር ማንነት አስተሳሰብ በምራባውያኑ ሊተገበር የሚፈለገውን አስራር ለማስፈፀም እንደማይችል ይታወቃል።ስለዚህም አንድ ላይ አድርገህ ጠብብተኝነትን ወደ አላስፈለገ ግጭት ከመውሰድ ሁለቱን መለያየቱ ተገቢ ነበር። ኤርትራም በህዝብ ፍላጎት አሳቦ እንድትገነጠል ሲደረግ ፣ በጫካም እንበለው በአውሮፓ ከተሞች የተነደፉት ሃሳቦች አብሮ የመግዛት መንፈስ ታሪክ ሲሆን መከዳዳትን ፈጠረ። ሕወሃት ደብቆ የያዘውን ክፋት ተጠቅሞበት ለምዕራባውያንን እራሱን አስገዛ። በሁለቱ ወንድማማች መካከል ጦርነት ተደረገ ። ይህ ነው የማይባል ህዝብ በማያውቀው ሁኔታ ለምዕራብያኑ አላማ መስዋት ሆነ። ኤርትራውያንም በተገቢው ሁኔታ የተሰጣቸውን የቤት ስራዎች መስራት ባለመቻላቸው በአለም አቀፍ ማዕቀብ ተወጥራ ምንም የማያደርግ መሪዋን ይዛ መቀጠል ግድ ሆነ። ህዝቡም የጠነከረ እምነቱን እንዲያጣ ሲደረግ በአዳዲስ ሃይማኖቶች ሰበብ ፣በኑሮ ውድነት ማንነቱን መሸርሸር ተሰራበት ።
የሕወሃት ህልውና በምዕራባውያን በኩል ያስገኘው ተቀባይነት ከምን የመጣ ነው
ምዕራባውያን ኢትዮጵያን ከደርግ አጋዛዝ ሲያለያዩ የኤርትራን መገንጠል ብዙ አላሰቡበትም ቀድሞውኑ ኢትዮጵያን አጠቃልሎ የመግዛት ሃላፊነቱ የተሰጠው ለአቶ ለኢሳያስ በመሆኑ በሁለቱም ቦታዎች የበላይነት ይዞ አገሪቷን መቆጣጠር ችሎ ነበር ። ሆኖም ግን ለብልጦቹ ሕወሃቶች አመቼን ሁኔታ አልፈጠረም፣ በጥረታቸው ባልልም በብልሃታቸው የበላይነት ለመያዝ የአቶ ኢሳያስን ግትርነት ተጠቅመውበታል። በአንድ በኩልም በምዕራባውያን የታቀደው የኤርትራን የመገንባት ስራዎች እንቅፋት ሲሆኑ የኢሳያስ ትምክተኝነት እና አልታዘዝም ባይነት ምዕራባውያንን መረዳት ሳያስከፋ አልቀረም። በሌላ በኩል እንደአማራጭ የወሰዱት አቶ መለስን በማቅራብ ታዣዥ እንዲሆን ማድረግ ነበር። ደጎም ያለ የዶላር ማዕበል ሲያናውጠው ተራማጅ አስተሳሰብ ያላቸውን ወዳጆቹን አይን መጋረድ ብዙ አላስቸገረውም። ለስራው እንቅፋት የሆኑትን ስኳር እያለ ከአካባቢው ሲያርቅ በሌሎቹም እንዲፈራ ሆነ። ከአገራቸው ላይ በመስረቅ እንዲበለፅጉ ሲደረጉ ስብእናቸውን አሳልፈው መስጠታቸውን እረሱት ። አቶ መለስም ኤርትራን ካስገነጠለ በኃላ የሚባሉትን የሚሰሩ ካድሪዎች በመፍጠር በህዝቦች መካከል የዘር ፣የሃይማኖት ልዩነት በከፍተኛ ሁኔት እንዲያድግ ተደረገ። ሌላውም ህዝብ ምዕራባውያኑ የሚሰሩት ስራዎች የሚገቡን አልሆኑም የፖለቲካው፣የአስተሳሰብ ልዩነቶች በአደገበት ሁኔታ በአገር ውስጥ ይሁን በውጭው አለም የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በአንድነት ተስማምቶ መደማመጥ የማይችል ሆነ።
ቀጥሎም በሕወሃቶቹም ዙርያ የመሪያቸው የአቶ መለስ ሞት ተከትሎ ተቆጪ ፣የሚፈሩት የሌለው ሆነና ትቢት ከማን አለብኝነት ጋር አዳምሮ ድብቅ አላማቸው ለመተግበር ይቸኩል ጀመር። ትልቋን ትግራይ የመመስረት ጠባብ አስተሳሰባቸው ከምዕራብያኑ አላማ ጋር እንደማይታረቅ ማወቅ እንኳን አላስቻላቸውም። በአማራው አካባቢዎች ላይ
የተካናወኑት የዘር ማጥፋት የግዛት ማስፋፋት መሰረት ይኑረው እንጂ ማህበረሰቡን በማፈናቀል ማንነት ማሳጣት፣ የህዝብ ቁጥር መቀነስ የነበረው የምዕራባውያኑ አስተሳሰብ የታከለበት ነበር ።
በቲም ለማ የተመራው የለውጥ ሂደት የተከተለው አላማ ለምን መስመሩን ሳተ!!!
የኢትዮጵያውያን ህዝቦች የዘር ፣የሃይማኖት ልዩነታቸውን አስወግደው እመነታቸውን ለመሪዎቻቸው ስጥተው በአንድነት እና በመተባበር ታዛዥነታቸውን ያሳዩበት ወቅት ነበር። ለምዕራብያኑም ቀጣይ ስራዎች ምን መምሰል እንዳለበት ግንዛቤ ሰጥቷል። ጥያቄ የሆነው ግን በአገሪቱ ወስጥ በሰፊው ተሰራጭቶ የነበረው የዘር፣ የሃይማኖት ልዩነት መፍትሄ ማግኘት ዋንኛው ተግባር ነበር። አቦ ለማ ሆነ የአማራውን ህዝብ ይመሩት የነበረው የለውጡ አካላት የዘር ጥያቄዎቻቸው ከምዕራብያኑም አላማ ጋር ተስማሚ ስለማይሆን መወገድ ግድ አለ። ችግሩን የፈጠረው የአስተሳሰብ ልዩነታቸው ብቻ ሳይሆን የመረጃ እጥረት ነበር። ወዳጃቸው ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከእነሱ አልፎ ለሁላችን ሊያስረዳ የሞከረባቸው ጊዜያት የሚገባው አልተገኘም ። በምዕራባውያኑ የተሰጣቸው ግንዛቤ ተመሳሳይ ቢሆንም እውቀት አወሳሰዳቸው ለየቅል ነበር፣ በአብዛኛው የገባው ሰሙን ብቻ ሆኖ የቅኔው ሚስጥር ሳይገባው ይቀራል። ዶክተር አብይ የሆነው እንዲሁ ነው የቅኔው ሚስጥር ገብቶታል የምዕራባውያንን ፍላጎት በተገቢው ተረድቷል አስፈፃሚ እንደሚሆን በምዕራብያኑ ተስፋ ተጥሎበታል።
ሕወሃቶቹም ቀጣይ ስራዎችን መስራት እንደማይችሉ ሲታወቅ ስልጣን ከእነሱ ቢሄድም አልተከፉም በቆይታዎች የምዕራብያኑን አላማ የተረዱ ሆነውል፣ በቅርብ በመሆን ህልውናቸው እና ጥቅሞቻቸው ተጠብቆላቸው መኖርን መርጠዋል። ለዋስትና እንዲሆናቸውም የደህንነቱ ቦታ መፈለጋቸው አልቀረም ምኞትም ብቻ ሳይሆን ቃል የተገባላቸው ሁኔታዎች እንደነበር የሚያሳዩ ሁኔታዎችን ነበር። አስተዋይነታቸው የሸፈነው እና ቅጥ ያጣው የተንደላቀቀው ኑሮ ሁኔታዎችን መከታተል አልቻለም የስልጣን ድልድሉ ነበር ከእንቅልፋቸው ያነቃቸው። በሌላ በኩል ተስፋ ይዞ የነበረው እና በምዕራባውያን ክትትል ውስጥ የነበረው የግብፅ እጅ የተመኘውን የድህንነቱን ስልጣን ማጣቱ እነ ለማን አስከፍቶ ከተነሱበት አላማ ውጭ አደረገ። ጅሃርን እና ሌሎቹን ጠባብ ፖለቲከኞች አካቶ ለግዜውም ቢሆን ለእስር እንዲዳረጉ ሲደረግ ውጥረቱን ትንሽ ተንፈስ ያደረገው መሰለ።
የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚለው አስተሳሰብ ይሰራ የለ ሕወሃቶቹ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ የቀድሞ የጥቅም ተካፋዮቻቸውን በማስገደድም ይሁን በፍቅር አብረው እንዲቆሙ አደረገ። በደህንነቱ ዝርያ ይሰሩ የነበረው የኢህአደግ አብዛኛው አባላት፣ከፍተኛ የመከላከያው ባለስልጣናት፣ ከኦነግ ጋር የተጣመደው ኦፒድዮ ፣ የአማራው ባንዳ፣ እስከ ደቡብ ህዝቦች የተበተነው የኢህአደግ ባለጥቅም እና ሌሎችንም አካቶ በጠ/ሚ ዶክተር አብይ ላይ ክተት ሰራዊት ማለት ግድ ሆነ ።
የአሻግራችሁ አስተሳሰቦች ወስጥ ያለው ውጥረት
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ የተረጋጋ ህይወቱን የሚያጣጥምበት እና እርካታ የሚሰጠውን መንፈስ የሚያገኝበት እና ወደ ህዝብ የሚቀርብበት መንገድ የተለየ ያደርገዋል ። ስራ መስራቱን የሚነግረን ሳይሆን የምናያቸው ስራዎች መሰረቶች ናቸው።እድለኛ ቢሆንም ብልጥ መሪነቱ ያሳያል። የተከበበባቸው ወጣቶች እንደልብ የሚሆኑበት አሰራር ሲደራጅላቸው እና የዘመኑን ምርጥ አውቶሞቢሎች ሞሾፈርም የሚያስችል ደሞዝ ባይኖራቸውም ከሌላው የመንግስት ተከፋዮች የተሻሉ መሆናቸው የሚያኩራራ ስለሆነ ለምን ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ስራዎችን ቶሎ ስርተው እውቅናን ማግኘት የሚተጉ፣ ከቢሮክራሲ ነፃ የሆነ አስራር የተላበሱም እንዲሆኑ በጥንቃቄ የተመረጡ ናቸው። ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በጠዋት ተነስቶ ዛፍ ለመትከል የሚኖረው ተነሳሽነት የሚሸሽው፣ የሚፈታተነው ማንነቱ እንዳለ ቢያሳይም ስሜቱን ሙሉ ለማድረግ ይጠቀምበታል ። ከፖለቲካ ስራዎች እራሱን ሊያሳርፍ ከቢሮው ይወጣባቸውል፣ ሊታዩ በሚችሉ ስራዎች እራሱን ይመለከትበታል የባከነ ጊዜ የለውም ። አዲስ አበባን መለወጡ እኔም አገር አለኝ ብሎ ለመዝፈን ለሁላችን አግዞን እንደሆነ የገባን ይመስለኛል። ለስራው ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከዘፈን ያለፈ እርካታው አግኝቶበታል፣ ለትውልድ የሚቀርለት ማስታወሻዎች ዋጋው ከፍ ያለ መሆኑ ሌላ ለመስራት ያበረታታዋል ። ለማወዳደር ባይሆንም የቀደሙ መሪዎቻችን በዘመናቸው የተክሏቸው ሃውልቶች ማስታወሻዎቻቸው አይደሉ። የጠ/ሚ ስራዎች ደግሞ የሁላችን ሃብቶች ሲሆኑ የአገርም ኢኮኖሚ መደገፋቸው ምን ያህል በአመለካከት እንደበለጠን ያሳያል ።
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በህዝብ እውቅና በአገኘባቸው የመጀመርያ አመታት ስራዎችን በፍጥነት አልመስራቱ ቢያስጠይቀውም ፣የግለሰባዊ ስሜት የፈጠረ አመለካከት ሊሆን ይችላል ብሎ ማለፍ ይበጃል፣ በሚሊተሪ በኩል ያሳለፈቸው ተሞክሮዎች በትግራይ የተገነባውን የጦር ሃይል የተረዳ ነበር። የሰው ልጅ በላስፈላጊ ሁኔታ እንዲጠፋ አልፈለገም። የምዕራብያኑን የግዜ ሰሌዳ ታሳቢ በማድረግ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኘውን የወጣት ሃይል ለመጠቀም ያሰበበት በቂ መረጃ እንዳለው የሚያሳይ ነበር።
የሰው ሃይል እንደሌሎች የተፈጥሮ ሃብት የአንድ አገር የእድገት መሰረቶች ነው የሚለው አስተሳሰቡ የግል ጥሩ እይታዎቹ ናቸው። ሆኖም ግን ይህ የሆነው የምርት ሃይሉ የሰው ሃይል ሲያንቀሳቅሰው ነው ብዬ አምናለሁ። በኢንድስትሪ ዘመን ይሰራል ለማለት ቢያስቸግርም፣ አለም ሰፊ በመሆና አሁንም በተለያየ ሁኔታ የሚሰራን ሰው ትፈልጋለች ።መስራት የሚችሉትን የሚያስተናድግ አቅም አላት የተማረ የሰው ሃይል በሚለው ሃሳብ መስተካከል አለበት ። በትክክል መገመት ባልችልም ከ60 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ወጣት መሆኑ አበረታታች ቢሆንም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱ ያጠናቀቀ በተገቢው ሁኔታ የተከታተል ምን ያህሉ ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። በየከተማው እየፈለሰ የምናገኘው የሰው ሃይል ነው ብለን ካሰብን ለስህተት ይዳርገናልና ።
የምዕራብያኑ አላማ ለእራስ ጥቅም ያደላ ቢሆንም ለአገራቱ እድገት ያመጣል የሚለው እራይ በጠ/ሚ ዶክተር አብይ ውስጥ በትንሹም ቢሆን መመልከት ይቻላል ። የተነሳበትን አመለካከት ጠለቅ ብለን ስንመለከት በቂ የሆነ የተፈትሮ ሃብት ያለው የህዝብ ቁጥር ችግር አይደለም ብሎ ያስባል ።
የተማረ ህብረተሰብ ከእገር ልማት አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ መስራት መቻላቸው የስራ እድልን ሲያሰፋ ፣ ባላስፈላጊ ስደት የሚጠፋው የተማረ ሃይል አገራቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ። ህዝቦች ከኖሩበት ቦታ ማፈናቀል ፣ርሃብን እና ጦርነት የህዝብ ቁጥርን ይቀንሳል የሚለው አስተሳሰብ የሚያስታርቅበት መንገድ በአንድ እጅ ማጨንጨብ እደሆነባቸው ይታያል፣ አገሪቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥያቄ ውስጥ ውድቃለችና።
የጠ/ሚ ዶክተር አብይ አሻግራችሃለው አስተሳሰብ ከርሃብ ከድህነት ወደ ብልፅና እንደሆነ በወረቀት ላይ ተሞክሯል ወደተግባር የሚለውጠው የምስራቅ አፍሪካውን አስተሳሰብ ተግባራዊ ሲያደርግ ይሆን ፍኖተ ካርተው በቅርብ ምን ያመጣ ይሆን።
የአገራችን ቀጣይ ተስፋ ከምዕራብያኑ ጋር ይሄዳል ወይስ ሊሎች አማራጮችን መመልከት ይጠበቅበታል
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ስራዎችን እየሰራ ነው ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትለምልም በሚለውን ሃሳብ የፀና ይሆን ብላችሁ ነው። ምዕራባውያኖቹም ማስገደዳቸውን አልተዉም ከጎኑ ቆመው እየረዱት ባይሆንም በዝምታ ማዝገሙ ግድ ነው አላየሁም ብሎ ማለፍ ያዋጣቸዋል።በጦርነት ብዙ ህዝብ ያልቃል ተብሎ ይገመታል ያም ብቻ ሳይሆን የእኔ ዘር እና ክልል የሚለው የትግራይ እና የአማራው አካባቤ ያለምንም ዋጋ በወጣቶቹ ደም መስዋት የሚሆነው ለምዕራብያኑ አላማ ብቻ ነው አያስብልም ክፋትም ያለበት ይመስላል ።
ጦርነቱ ግድ እየሆነ መጥቷል አገር በደም ትቀጥላለች የተረፈው ተርፎ ማለቴ ነው ወታደርነትም አገርን ከባላንጣ መጠበቅ ብቻ አይደለም የስራ መስክ በመሆን ለአንዳንድ አገራት በኢኮኖሚያቸው እድገት ውስጥ ተሳታፊ ስለሚያደርግ ለትውልዱ ጥሩ ይሆናል።
ምዕራባውያኑ በማደግ ላይ ባለነው አገራት የሚያደርጉት ጫና መላ እንደማይፈጥር መረዳት የቻሉ ይመስላል። ሰብዊነት በሚለው አስተሳሰቦች የሚፈልጉትን ማግኘትን በአማራጭነት ይዘዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በፈለጉት ሁኔታ በአንድ አገር ውስጥ እራሳቸውን በማስገባት የኢኮኖሚ ወይም የፖለቲካ አማካሪ በመሆን ስውር አላማቸውን ማከናወን አላስቻላቸውም። የአፍሪኪያኑ አስተሳሰብ እየበለፅገ ስውር ደባቸው እየገባው የመጣ ትውልድ ከእኔ ይልቅ አገሪ የሚለው እየተበራከተ መምጣቱን አስተውለዋል። ለዚህም ነው የቤት ስራዎቻችን እኛው እንድንሰራ የተውኑ። ምዕራብያኑ በተለይ አሜሪካን ግብታዊ የነበረው አመለካከት አዋጭ እንዳልሆነ የተረዱት ይመስላል። የህዝብ ቁጥር ጥያቄዎቻቸውን መመለስ ከቻልን ቀድመው ይዘውት የነበረው የአፍሪካን ቀንድ አገራት በአንድ ላይ ማስተዳደር ከሚለው ይልቅ በየአገራቱን ላይ የግል ጥቅማቸውን ማሳደጉ የተሻለ አማራች ሲሆን የአፍሪካው ቀንድ አገራት አብሮ ለማሳደግ ጥርጊያ መንገድ ይሆናል ።
የአገራቱ የኢኮኖሚ ትስስሮች ሉአላዊነታቸውን ማስቀደማቸው አንዱ ማሳያ ነው። የበለፅጉት አገራትም ቢሆኑ የቀድሞው አመለካከታቸው በጋራ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ለማስገኘት በስምምነት እንደሚሰሩ ግንዛቤ ነበር ። አሁን ያለው የአለማችን የበለፀጉት አገራት ፍላጎት በትንሹም ቢሆን ሁሉንም ይዞ መገኘት የተሻለ እንደሆነ ይታያል። እንደ ቻይና ያሉ ብልጥ አገራት ደግሞ አስተሳሰባቸው የሚታወቅ አልሆነም። አለም መጥፋት ካለባትም ከጥቅማቸው አንፃር በመሆኑ ለማንም ግድ የላቸውም። የራሽያዎቹም አጋር አገራት ኢኮኖሚያቸውን ጠብቆ መቆየት የመረጡ መሆናቸው ለታቀደው የአፍሪካ ቀንድ እድገት አሉታዊ ተፈፃሚነት ጥያቄ ያመጣል። ስራዎችን በአገራቱ ለመተግበር የሚያስፈልገው ኢንቨስትመት ከበለፀጉት ምዕራብያን አገራት የሚሰበሰብ ሲሆን የአለማችን በተለያየ ሁኔታ የገጠማትን ልዩንቶች ስንመለከት በጋር የሚለው አስተሳሰብ ቦታ ያጣ ይመስላል። አማራጩ አንድና አንድ እየሆነ ይመጣል ብዬ አስባለሁ በአንድ ላይ የሚለውን አስተሳሰብ መተዋቸው የማይቀር ነው ። የአፍሪካን ቀንድ አገራትም በአንድነት ስለእድገታቸው የሚያመጡት አምራጭ መፍጠር እንዳለባቸው የሚያሳዩ አስተሳሰቦች እየተስተዋለ ነው። ለሁሉም ግን የአፍሪካን ቀንድ ከዘር ከሃይሞኖት የፀዳ መሆን ይጠበቅባቸዋል ።
አገራችንን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅልን
በቀለ