November 11, 2021
14 mins read

የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ዕጣ ፋንታ ለኢትዮጵያን ወይስ ? “

የኢትዮጵያን ጉዳይ በየዘመናቱ ለመጣ እና ለሄደ በክህደት እና በአድር ባይነት አረንቋ ለተዘፈቁት መተዉ አስከ መቸ ይሆን…..የሚል ጥያቄወች በህሊናችን እየተርመሰመሱ ነዉ
ethiopia
ethiopia

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማፍረስ ከግማሽ ክ/ዘመን ዓመታት በፊት ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፈዉ ሰጥተዋል ፡፡

ከዚህም ኢትዮጵያን የባህር በር ማሳጣት እንዲሁም ነባር እና ለአገር ግንባታ እና ባለቤትነት የማይታመነዉን ህዝብ በጠላትነት በመፈረጂ ለ አለፉት ፴ ዓመታት በማንነት ምክነያት እና ፍረጃ ጅምላ ፍጂት ተካሂዷል ፡፡

ይሁንና እንደ ትህነግ እና ሌሎች ግብረ አበር ከኃዲዎች ጥቅማቸዉ ሲረጋገጥ መግዛት ፤ጥቅማቸዉ ሲነጥፍ ነፃ አዉጭነት ቆብ ደፊዎች የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ በእነርሱ እንዲዘወር እና ህዝብ በአጥፍቶ ጠፊዎች እንዲወረር ተደርጓል ፤እየተደረገ ነዉ ፡፡

በኢትዮጵያ እና ህዝቧ ላይ የጠላት አገልጋይ እና ጌኞች የጠላት ያደሩ ፍላጎት እና ምኞት ለማሳካት ሲባል የኢትዮጵያን ጉዳይ ለጠላት አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገዉ የጠላት ተደጋጋሚ ሙከራ የኢትዮጵያን መከራ ለማራዘም ከመሞከር ዉጭ ጉዳዩን ለኢትዮጵያዉን መስጠት ያስፈልጋል ፡፡

በፀረ ኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያዉያን መካከል ያለዉን ምልክት እና መስመር መለየት እና በዜጎች ህመም እና ቁስል ላይ የሚደረገዉን ዕንቆቅልሽ ለአንዴ እና መጨረሻ መቆም አለበት ፡፡

የትናንት ጠላትን ከዳሚ የዛሬ ተቃዋሚ ሲሆን የፀሀይን ብርሃን መፍዘዝ እያየ እንደሚለይ ጥላ መሆኑን መገመት እና መገንዘብ አቅቶን ዛሬም ከነፈሰዉ መንፈስ ልማድ አድርገንዋል ፡፡

በኢትዮጵያ እና የኢትዮያ ዳር ድንበር እና ግዛት ጉዳይ ላይ ከሩቅ እና ከዉጭ የቅኝ ግዛት ናፋቂዎች እና ባሮች፤ ከዉስጥ እና ከቅርብ “ሞት ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ” እያሉ ቅጠል ሲበጥሱ ፤ አፈር ሲምሱ ለኖሩት ቦታ እንሰጣለን ፡፡

ከነርሱ ከንቱ ቡራኬ እና ዉዳሴ መጠበቃችን ሳያንሰን ተሸፈኑ እናሞኛችሁ ሲሉን አሜን እንላለን ፡፡ ለኢትዮጵያ እና ዜጎች መፃኢ ዘመን ፍስኃ እና ዕድገት በነፃነት ለማረጋገጥ በዱር በገደሉ አንድኛ ነፍሱን ለሚሰጥ ኃይል ትጥቅ እና ስንቅ ማቅረብ ቀርቶ ዕዉቅና ለማስጠት እንኳን ከግል አስከ ከፍተኛዉ የመንግስት መዋቅር እንደ ሰማይ የከበደን ብዙዎች መሆናችንን ለሚገነዘብ ኢትዮጵያ ለኢትዮያዉያን የምትሆንበት ጊዜ አብዝቶ ይናፍቀናል ፡፡

የዕዉቁ እና ስመ ጥር ባለቅኔ እና ጥበብ ሠዉ ዮፍታሄ ንጉሴ ትንቢት አይሉት ንግርት “ ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ ፣የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ” ለኢትዮጵያዉያን ፤በኢትዮጵያ ምድር ሰማይ ስር እንደ ሀረግ ተስቦ እንደ ሠንጋ ደልቦ ፤እንደ ሠማይ ከዋክብት በዝቶ አሁን በዕኛ ዘመን የማቅቀናል ፡፡

ዛሬ በዉስጥ እና ዉጭ እንደ መዥገር ህዝቡን እና አገሪቷን በነጭ ባርነት እና በዘወርዋራ ግዞት ደሙን ከዉስጥ ፤ላቡን ከዉጭ የሚመጡት በህዝብ እና አገር ሀብት በተገኘ የጥፋት መሳሪያ ( ጦር መሳሪያ) መልሰዉ ህዝብ እና አገር ለማስገበር እና ለማክሰም ሲሰሩ በተቃራኒዉ ለኢትዮጵያ ከጥንት አስካሁን ሳይታክቱ ለሚሰሩት እና ለሚዋደቁት ሳይኖሩ በሞት ላይ ሞት አሜን ብለዉ እንዲቀበሉ እጅ እግራቸዉ እንዳይላወስ እንዳይንቀሳቀስ ዕግር ከወርች ታስረዉ መገኘታቸዉ ከላይ ለተባለዉ ዘመን ጠገብ ትንቢት እና ትንግርት ዋቢ ነዉ ፡፡

ለሩብ ምዕተ ዓመት ሠፊዉ ህዝብ እና ጥቂት ልበ ብርሀን ሰዎች የነበረዉን ካለዉ እና ከሚሆነዉ ጋር የነበራቸዉን ምልከታ እና ስጋት በመጥቀስ የዝግጂት ጥያቄ በተደጋጋሚ አቅርበዉ ሲገፋ የነበር የማንነት ፣ ፍትዊነት፣ ነፃነት እና በህይዎት የመኖር የመብት ጥያቄ ቀርቧል፡፡

እንደ ኢትዮጵያዉያን የዘመን አቆጣጠር በ፪ ሽ ፲፫ ዓ.ም. በመላዉ የሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ(ሰም-ኢትዮጵያ) ኢትዮጵያ የተካሄደዉ ታላቅ እና ደማቅ ህዝባዊ ጥያቄ “ዉርደት እና ሞት/ የሞት ሞት ” በቃ ጉዳዩ የዓማራ እና ኢትዮጵያዊነት ህልዉና እንዲሁም እንደ ሠዉ በህይወት የመኖር እና አለመኖር የተፈጥሮ መብት እንጂ በማንም በምንም ሊቸር እና ሊቀር ማይችል መሆኑን በህይወት የመኖር ጥያቄ ድምፆች ፤ ብሶቶች እና ቀለማት ወቅቱን የዋጁ ስለመሆናቸዉ ዛሬ ላይ በአገራችን ሰሜን ምዕራብ ግዛቶች እና ነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ያለዉ የፈርጂ ጥቃት የዘመናት የጥላቻ እና የበታችነት ሰንኮፍ ያስከተለዉ የመጨረሻዉ የአጥፍቶ መጥፋት ግርሻት መሆኑን ትናንትን ያለመኖር ምልክት ነዉ ፡፡

የዉስጥ ቀንደኛ የብሄራዊ አንድነት እና ደህንነት ስጋት የሆኑት የጠላት ወዳጆች እና አገልጋዮች አስከ አፍንጫቸዉ ያስታጠቀች አገር እና ህዝብ ኢትዮጵያን እንዲሞቱ ተጨፈኑ ላሞኛችሁ የሚሉን ምዕራባዉያን ስህተት ናቸዉ ማለት ከራስ ያለመነሳት ታሪካዊ እና ደጋገም ስህተት ነዉ ፡፡

ትናንት አንድ የአሜረካ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ፍሊት ማን …. የኢትዮጵያ ህዝብ ራሱን እና የአገሩን ሉዓላዊ ግዛት ለመከላከል መታጠቅ የለበትም ቢል ምኑ ላይ ነዉ ስህተቱ ፡፡

ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን በማሳከር እና እንደ አገር ላለመኖር ዓማራን የማክሰም “የጥፋት መጨረሻ መነሻ እና መዳረሻ” በማድረግ ፀረ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ህልዉና ማስቀጠል የተሸረበ ጥላቻ እና በታችነት የፀነሰዉ ሴራ ከ18 ኛዉ ክ/ዘመን ሲነሳ ዛሬ ላይ ሆኖ ስለ ጠላት ከአሰልች ታካች መግለጫ ወጥተን ትናንት ራስን እና አገርን ለመታደግ በህብረት እና አንድነት ተደራጂተን ፣ታትቀን እና ነቅተን ዘብ እንቁም ያለዉን ኢትዮጵያዊ ጆሮ ዳባ ልበስ ያልነዉን በይቅርታ እና በሙሉ አለኝታነት በሁሉም መስክ ተገቢዉን እና ወቅታዊ ድጋፍ እና ማእቀፍ ልናደርግ ይገባል፡፡

በኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት እንዲሁም የህዝቧ በነፃነት በህይወት የመኖር ተፈጥሯዊ ማንነት ሙሉ ኃላፊነት እና ባለቤት የኢትዮጵያዉያን እና ዜጎች ብቻ እንጂ የሌላ የማንም የዉስጥ ሆነ የዉጭ ጠላት ፍላጎት እና ምኞት ሲባል በማንም የሚቀለስ ፤የሚመለስ የምንም ጉዳይ ሊሆን አይችልም ፤አይገባም፡፡

የዉጭም ሆኑ የዉጭ የጭቃ እሾክ ታሪካዊ የትዉልድ እና የአገር ሰለሊቶች ሊረሱት የማይገባዉ ዕዉነተኞች ኢትዮጵያዉያን በዕዉነት ኖረዉ ወደማይቀረዉ ዕዉነተኛ የተፈጥሮ ምዕራፍ ለሄዱት እና ስማቸዉ ከማቀብር በላይ በተግበራቸዉ እና በበጎ ምግባራቸዉ በትዉልድ ቅብብሎሽ ሲከበሩ እና ሲዘከሩ ለሚኖሩ ህያዋን ልጆች መሆናችንን ነዉ ፡፡ በተለያየ አሰላለፉ በተለያየ ካባ ተጀቡነዉ እናሞኛችሁ ባይ የቀበሮ ቀዳሽ እና አወዳሾች ዕዉነተኛ ወዳጂ እና ጠላት ከምንም ከማንም በፊት መረዳት የቻልን መሆናችንን ….ቆሞ የሚቀበለን ….ሁሉ አክባሪ እንዳልሆነ ቁጭ ብሎ ለሚቀበለንም ሁሉ ክፉ አሳቢ አለመሆኑን ከዓለም በፊት በነበር “ቁሞ የሚንቀንን ፤ ቁጭ ብሎ የሚከብረንን ” የምናዉቅ የ፭ ሽ ፭ ዓመት የነፃነት እና ማንነት ባለ አገሮች ነበርን ፤ ነን፤ እንሆናለን ፡፡

ትናንት በቅኝ ግዛት እና ባርነት ሲማቅቁ ለነበሩት ህዝቦች እና አገራት የቅኝ ግዛት ፣ የግዛት መስፋፋት እና ባርነትን ከረጅም ክ/ዘመን በፊት በማዉገዝ ለነጻነት እና ርዕት ማገዝ የጥቁር ዓለም የነጻነት ቀደምት ኢትዮጵያዉያን ዋኖች ተጋድሎ በእንግሊዝ እና አባሪ ተስፋፊዎች እጅ መዳፍ ለባርነት እና ግዞት ወድቀዉ ለነበሩ ነጮችም ከቅኝ ግዛት ቀንበር ሸክም ያዳኑ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ እና ስለእኛ ነጻነት እና የግዛት አንድነት …ለእኛ ለኢትዮጵያዉያን ሁላችሁም ስሙን እና ተዉት ፡፡ ነገሩ ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ ነዉ እና ……የሰሞኑ ከዓመት እና በፊት ከነበረዉ የጅብ ስምምነት የማይለይ ነዉ ፡፡ አበዉ አባ ጂቦ ሳታመሃኝ ብላኝ እንዳለችዉ …እንድንል ጠላት ሆይ አትጠብቅ ይህ የጂብ ስምምነት እና ማህበር ነዉ ፡፡

አያ ጅቦ ከወንዙ አናት ሆኖ ከታች ያለቸዋን አህያ ዉኃዉን አደፈረስሽ ነይ ወደ ላይ ……ዓይነት ተነሱ ፤ተመለሱ ፣ አርደርሱ……የማንም ሳይሆን ለኢትዮጵያ እና በግዛቷ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጉዳይ ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያዉያን እንጂ ለጠላት አሳልፎ የመስጠት ሴራ እና ትንቅንቅ የፀረ ኢትዮጵያዊነት ፍላጎት እንጂ ኢትዮጵያዊነትም ወዳጂነት አይደለም ፡፡

በምስራቅ ካራ ማራ ፤በሰሜን አስከ ማይካድራ ፣ ከየትኛዉም የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን ከቀበሌ አስከ መቀሌ እና ባሌ ….የኢትዮጵያነት ዋጋ የተከፈለበት በኢትዮጵያዉያን የህይወት ቤዛ እንጂ በባዶ ተስፋ እና ለፈፋ አልነበረም ፡፡

 

 

ማላጂ

 

“የ ኢትዮጵያዉያን ህልዉና ዕጣ ፋንታ የሚገኘዉ አገር ወዳድ ልጆች ክንድ እና መዳፍ ብቻ ነዉ ፡፡ ”

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop