አልረሳውም! እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ!!
ክፍል 2
የፍርድ ቀን ዘመቻ!!
‹‹ኢትዮጵያ! ያጎረሰ እጇ! ያጠባ ጡቶቿ! ተነክሷል!!››
(የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር በወቅቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጡት አስቸኳይ መግለጫ)
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትሩ! ይህን ድንገተኛ መግለጫ እየሰጡ ባሉበት ጊዜ፤ ከሄዝቦላው የሽብር እልቂትና አፈና የተረፈው የሀገር መከላከያ ሠራዊት! ከአሸባሪው ቡድን ራስን የመከላከል ትንቅንቅ እያደረገ ነበር፡፡ የኢትዮጵያው ሄዝቦላ ሽብር የመፈፀሙ ነገር አይቀሬ መሆኑን የተረዳው! የአማራ ልዩ ኃይል ሠራዊት፤ የሄዝቦላውን የሽብር ጥቃት ለመከላከል ወትሮም ዝግጁ ስለነበር! ፈጥኖ ተንቀሳቀሰ!! የአማራ ልዩ ኃይል ያከናወነው ይህ ፈጣን የመከላከል እንቅስቃሴ! በአሸባሪው ሄዝቦላ ላይ የሚካሄደውን ‹‹የፍርድ ቀን ዘመቻ›› በይፋ ያበሰረ ነበር!!
ለሀገሩና ለክብሩ ቀናኢ የሆነው የተከበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በበኩሉ! ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ስማኝ! ሀገርህ ባበላቻቸው እና ባጠጣቻቸው ስግብግብ ቡድኖች ተደፍራለች! ሀገር እንዲጠብቁ መርቀህ የላካቸው ልጆችህን አርደውብሀል! ሕገ-መንግስቱን ጥሰውብሀል! በዚህም ሕልውናህን አደጋ ላይ ጥለውታል!!›› የሚል ይዘት ያለው መግለጫ! ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሰማ! ድንጋጤ ውስጥ ወደቀ! ቀጥሎም መራር የመጠቃት ስሜት ከበበው! ይህ ስሜትም በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጣ ግን! ተቆጥቶ የሚያበቃ አልነበረም! የኢትዮጵያን ህልውና እንዲታደግ! ልጁን መርቆ ከመላክ እና ቤቱ ያፈራውን ያለስስት ከመቸር ባሻገር! ደሙን በመለገስ ጭምር! የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ን መከላከያ ሠራዊት ሞራሉንና ተቋሙን በቅፅበት መልሶ ገነባለት!!
ፍርዱ ቀጠለ!! የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መከላከያ ሠራዊት! ለሰከንዶች ማሰብ ቅንጦት በሚሆንበት እሣት! ፋታ በማይሰጥ የእሣት ዝናብ! አሸባሪውን ሄዝቦላ ሲቀጣው ውሎ ሲቀጣው አደረ!! የኢትዮጵያው ሄዝቦላ ራሱ በለኮሰው ብርቱ ጥፋት ምክንያት! ተራራን በሚንደው! ብረትን በሚያቀልጠው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መከላከያ ሠራዊት ብርቱ ክንድ! በፍርድ እሣት ሲለበለብ! ከነበልባሉ ለመውጣት ተመኘ!! ነገር ግን ‹‹ብርቱ ጥፋት›› አንዴ ከለኮሱ በዃላ ‹‹መውጣትና መግባት›› እሚሉት ተአምር በጭራሽ አይገኝም!! በሁመራ ቢል ተዘጋ!! አሸባሪው ሄዝቦላ ከሚለበልበው ‹‹የፍርድ እሣት›› ለመትረፍ በአፋር እድሉን ሞከረ! ነገር ግን የኢትዮጵያ ጥቃት የሚያንገበግበው! ኩሩው ኢትዮጵያዊ የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ! ‹‹በኢትዮጵያ ላይ ብርቱ ጥፋት ለኩሰህ መውጣትማ አይታሰብም›› እያለ! ፍርዱን ይሰጠው ጀመር!!
የፍርድ ቀን ዘመቻው! በዚህ የሚያበቃ አይደለም! ምክንያቱም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. አየር ኃይል ‹‹ፍርዱን›› ማስተላለፍ ነበረበት!! ስለዚህ የአየር ኃይሉ ሱፐር ሶኒክና ‹‹አርድ-አንቀጥቅጥ›› የሆነው ‹‹እሣታዊ ፍርድ›› ቀጠለ!! በኢትዮጵያው ሄዝቦላ ላይ የሚተላለፈው የአየር ኃይሉ ፍርድ! አሸባሪው ቡድን ‹‹በብርቱ ጥፋት ድግስ›› ውስጥ እያለ ይሰማው ከነበረው የስካር ድምፅ! በእጅጉ ይለያል!!
የኢትዮጵያው ሄዝቦላ ‹‹በብርቱ ጥፋት ድግስ›› ውስጥ እያለ የሰማው ድምፅ! በሳለው ካራ! ጥይት ባጎረሰው ክላሽ! ላንቃውን ለመክፈት ባዘጋጀው መድፍ! ብርቱ ጥፋቱን እንዲለኩስ፣ ንፁህ የሰው ልጅ ደም እንዲያፈስ፣ እንዲያሸብርና ዝርፊያ /ሌብነት/ እንዲፈፅም! ድፍረትና የፈራጅነት ሥልጣን ሰጥቶት ነበር!!
ይህ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሱፐር ሶኒክና ‹‹አርድ-አንቀጥቅጥ›› የሆነው ‹‹እሣታዊ ፍርድ›› ግን፤ አሸባሪ ቡድኑ አሰቃቂ ወንጀል በመፈፀም! ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የዘረፋቸውን ከባድ የጦር መሣሪያዎች! በቅፅበት አስጣለው!! እንዲያሸብርና ብርቱ ጥፋቱን እንዲለኩስ ታጥቆት የነበረውን ‹‹ደም ጠማሽ›› ድፍረቱንም! ከልቡ ውስጥ ሰልቦ! ደመነፍሳዊ የመትረፍ ሽሽት ውስጥ እንዲገባ አደረገው!!
በመንፈሳዊ እምነቶች ላይ ላሳየው ንቀት የተሰጠው ፍርድ!
የፍርድ ቀን ዘመቻው! በዘመናዊው የውጊያ ቴክኖሎጂ ቀጠለ!! በዚህ ዘመናዊ የውጊያ ቴክኖሎጂ! አሸባሪው የኢትዮጵያ ሄዝቦላህ የሆነውን መስማት! ማየትና ማወቅ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ላደገበት ጨዋነትና ቁጥብነት የማይመጥን ቢሆንም! ራሱ አሸባሪው ቡድን ያዋጣኛል ብሎ በፈፀመው የሽብር ተግባር፤ በራሱ ያመጣው ጦስ በመሆኑ ደግሞ! ሳይነገርና ሳይታወቅ መታለፍ የለበትም!!
አሸባሪው የኢትዮጵያ ሄዝቦላ! ሀቀኛ የእስልምናን መንገድ የሚከተሉ ዜጎችን! የአሸባሪነት ስዕል በመስጠት!! የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነትን አና ተቋሙን! እንደጨቋኝ እና ዃላ-ቀር አድርጎ በማሳየት!! ‹‹እምነት የለሽነቱን›› እንደእውቀት! ‹‹ኮሚኒስትነቱን›› እንደተራማጅነት ቢቆጥረውም!! ፍርድ ማስተላለፊያና የአሸባሪ መቅጫ በሆነው! በዘመናዊው የድሮን-ቴክኖሎጂ ውጊያ! የሽብር ቡድኑ በፍርድ እሣት ሲለበለብ!! የደመነፍስ ማምለጫው ያደረገው! እነዚህ ሁለት ታላላቅ እምነቶች በሚጠቀሙበት! ዶግማዊ አለባበስ በመልበስና በማምለኪያ ቦታዎቻቸው በመደበቅ ነው!!
በሴቶች እኩልነት ላይ ላሳየው ንቀት የተሰጠው ፍርድ!
አሸባሪው የኢትዮጵያ ሄዝቦላ!! የሴቶችን እኩልነት በተግባር አለመቀበልን እንደትክክልና እንደወንድነት ቢቆጥረውም!! የፍርድ ማስተላለፊያና የአሸባሪ መቅጫ በሆነው! በዘመናዊው የድሮን-ቴክኖሎጂ ውጊያ! ይህ የሽብር ቡድን በፍርድ እሳት ሲንገበገብ!! ‹‹ጦርነት ብትገጥም ታሸንፋለህ›› ብለው ያሳሳቱትት የውጭ ኃይሎች! ባስቸኳይ ደርሰው ፆታውን ቢቀይሩለት ቢወድም!! ከዚህ ፋታ ከማይሰጠው ‹‹እሣታዊ ፍርድ›› ለጊዜው ማምለጫ ያደረገው! እኩልነቷን በተግባር ያልተቀበለላትን! የሴቷን ተለምዷዊ አለባበስ! ቀሚስ በመልበስ ነው!!
ማን-አህሎኝነትን ላሳየበት የተሰጠው ፍርድ!
አሸባሪው የኢትዮጵያ ሄዝቦላ! ! ሊያበርረው ያልቻለውን የጦር ጄት በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ (በሎቤድ) አስጭኖ! የሀገር ህልውናን በሚፈታተን መልኩ! የሽብር ሠራዊትና ትጥቅ አስከትሎ! ሕዝብ በተሰበሰበበት ስቴዲየም ዛቻ መፈፀምን እንደጀግንነት ቢቆጥረውም!! በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘው ውጊያ እና የፍርድ አሰጣጡ ሲለበልበው! እጅግ ሲያንገበግበውና መፈጠሩን ሲያስጠላው! እብሪት ያሳየበትን ወታደራዊ ዩኒፎርሙን ጠቅልሎ እየሸጎጠና አወላልቆ እየጣለ! ደመ-ነፍሱን ሸሸ!!
ከዚህ ቀደም ሠላማዊውን የትግራይ ማሕበረሰብ!! ‹‹በአደባባይ የጦር ትርኢት ላሳይህ ነውና ከቤትህ ውጣ›› እያለ! በግዳጅ ከቤቱ ሲያስወጣው የነበረው ይህ አሸባሪ ቡድን! ያላሰበው ‹‹የፍርድ ቀን ዘመቻ›› ሲጠናበት!! ‹‹እባክህ ከቤትህ ደብቀኝ›› እያለ ይማፀነው ገባ!!
አሸባሪው ቡድን እነኚህን ትልልቅ እሴቶቻችንን የማምለጫ ስልቶች አድርጎ የተጠቀመው! የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት በጦርነት ውስጥም ቢሆን ኃላፊነት የሚሰማው! ሴት፣ ሕፃናትን እና አረጋውያንን እንደማያጠቃ በግልፅ ስለሚታወቅ!! የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት ለመንፈሳውያንና ለማምለኪያ ቦታዎቻቸው! እንዲሁም ለየትኛውም ሠላማዊ ማህበረሰብ ክብር እንዳለው በተጨባጭ ያሳየ በመሆኑ ነው!!
አሸባሪው የኢትዮጵያ ሄዝቦላ! በኦሮሞ የገዳ ባህሉ ላይ! በኢሬቻ ሥነ-ስርዓት ማክበሪያ ቦታዎቹ ላይ! በእምነት እሴቶቹ ላይ! የማጣጣል እና የማናናቅ ተግባር ሲፈፅም! ከዚያም አልፎ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ሲያስተላልፍበት የቆየ ቢሆንም!! አሸባሪው ቡድን ላይ የፍርድ ቀን ዘመቻው የተካሄደው! በዚህ ማህበረሰብ አካባቢ ቢሆን ኖሮ! የናቀውን ይህን የኦሮሞ ቅዱስ ስፍራና ባህላዊ አለባበሱን! ከፍርድ እሳቱ ማምለጫው እና መደበቂያው ያደርገው እንደነበር አያጠራጥርም!!
በኢትዮጵያ ውስጥ! እንደሊባኖሱ ሄዝቦላህ ለመሆን አምሮት! የሌባኖሱን ሄዝቦላህ አይነት አደረጃጀት፣ የሌባኖሱን ሄዝቦላህ አይነት ወታደራዊ ክንፍ፣ የሌባኖሱን ሄዝቦላህ አይነት የሽብር ስልት የተከተለው! የኢትዮጵያው ሄዝቦላ!! በእግረኛ፣ በሜካናይዝድና በአየር ኃይል በተቀናበረው የሶስት ሣምንት ‹‹የፍርድ ቀን ዘመቻ›› ተንኮታኮተ!!
ለአሸባሪው የተላለፈው መልዕክት!
በዚህ ‹‹የፍርድ ቀን ዘመቻ››! ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መከላከያ ሠራዊት፣ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. አየር ኃይል፣ ከአማራ መደበኛ ልዩ ኃይልና ሀገር ወዳድ ታጣቂዎች፣ ከአፋር መደበኛ ልዩ ኃይልና ሀገር ወዳድ ታጣቂዎች፤ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ!! ለአሸባሪው የኢትዮጵያ ሄዝቦላ! ሁለት መልዕክቶች ተላለፉለት!! ይህ! የሊባኖስ መደበኛ ጦር አይደለም!! የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መከላከያ ሠራዊት ነው!! ይህ! የሊባኖስ መንግስት አይደለም!! የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት ነው!! የሚሉ ሁለት ብርቱ መልዕክቶች!! እነዚህ ሁለት ብርቱ መልዕክቶችም! ከኢትዮጵያ ሕዝብ መተላለፋቸውን ያረጋገጠ! የኢትዮጵያን ምድር ከዳር እስከ ዳር ያካለለ! የአድናቆትና የምስጋና ጭብጨባ አስተጋባ!!
የተንኮታኮተው መግለጫ!
አሸባሪው የኢትዮጵያ ሄዝቦላ! ከዚህ ሁለንተናዊ መንኮታኮቱ በዃላ የሰጠው መግለጫ፤ የሊባኖሱ ሄዝቦላህ የእሥራኤል ወታደሮችን በማገት የፈፀመው የሽብር ተግባር፤ በሊባኖስ ሕዝብ ላይ ሰብአዊ እልቂትና ቁሳዊ ውድመት ካስከተለ በዃላ፤ ዋና ፀሐፊው ነስራላ ከሰጠው መግለጫ ጋር አንድ አይነት ነው!!
ነስራላ! ‹‹እሥራኤል በታገቱት አምስት ወታደሮቿ ምክንያት፤ በተሟላ ዘመቻ ጦርነት ትከፍታለች ብዬ ባስብ፤ ወታደሮቹ እንዲታገቱ ትዕዛዝ አልሰጥም ነበር›› ሲሉ! መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም ማወጁን ተከትሎ ከተደበቀበት የወጣው! የኢትዮጵያው ሄዝቦላ የሽብር ስልት ነዳፊው ፃድቃን ገ/ተንሳይ! ለሚዲያ በሰጠው ቃለ-ምልልስ ደግሞ! ‹‹ባልጠበቅነው መንገድ ተመተናል፤ እኛ መንግስት እንዲህ ያለ የጦር ቴክኖሎጂ ይታጠቃል ብለን አልገመትንም ነበር›› የሚል ነው!! የኢትዮጵያው ሄዝቦላ ይህን የተረዳው! ባልተገባ ጥጋብ፣ በእብሪትና በድንቁርና የፈፀመው የሽብር ተገባር! ካስከተለበት የመንኮታኮት አደጋ በዃላ ነው!!
በአይናችን ያየነው! በጆሯችን የሰማነው! በፅሁፍም ያነበብነው! ይህን መሰሉ የአሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. መንኮታኮት! የመጨረሻው ሳይሆን! ‹‹የመጀመሪያው መንኮታኮት›› ነው!!
በመሆኑም ይህ የሽብር ቡድን! ከመጀመሪያው መንኮታኮት ሳያገግም፤ በቀድሞው የሽብር ስልቱ ላይ የአረዌነት /Barbarism/ የሽብር ስልት አክሎበት! ‹‹ወርሮ ሰፋሪነት››፣ ‹‹ነጥቆ በሊታነት›› እና ‹‹ገድሎ ኗሪነት›› ላይ የተመሠረተ፤ የሽብር ተግባሩን አስቀጥሎታል፡፡
ስለዚህ አሸባሪው የህ.ወ.ሓ.ት. ቡድን! ለዚህ ‹‹አርቅ-የለሽ›› የሽብር ስልቱና ተግባሩ! ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መከላከያ ሠራዊትና አየር ኃይል የሚሰጠውን! ‹‹የመጨረሻ ፍርድ›› እና ‹‹የመጨረሻውን መንኮታኮት›› እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡
ሳይቃጠል በቅጠል!
መነጋገርና መደራደር አዋጭ ስትራቴጂ አይደለም በሚል! በሰይፍ መወራረድን አማራጭ አድርጎ! በመሀከለኛው ምሥራቅ ዘወትር ለማጥቃት በሚንቀሳቀሰው የሊባኖሱ ሄዝቦላ! ከዓመት ዓመት በደህንነት ስጋትና ጭንቀት መኖር፤ በመካከለኛው ምሥራቅ የተለመደ ከባቢ ሆኗል፤ በዚህ የስጋትና ጭንቀት ከባቢ ውስጥ ከሚገኙ ሀገራት ውስጥ ሳዑዲ አረቢያ፣ ዓረብ ኤመሬቶችና እሥራኤል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከሄዝቦላህ ጋር ችግሮችን ተነጋግሮ የመፍቻው በር ዝግ በመሆኑ፤ ለሄዝቦላህ ጥቃትና ትንኮሳ የአፀፋ እርምጃ በመውሰድ መቋቋምን! ቀጠናው ብቸኛው የሠላም አማራጭ እንዲያደርገው አስገድዶታል!!
የኢትዮጵያው ሄዝቦላህ! የመንኮታኮት አደጋ ውስጥ ቢሆንም! አሁንም የሊባኖሱን ሄዝቦላ አደረጃጀት! አካሄድና የሽብር ስልት መከተሉንና ተፈፃሚ ማድረጉን! ባልተወበትና አባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ! ‹‹ከእሥራኤል ጋር ጥብቅ ግንኙነት እመሠርታለሁ›› እያለ ይገኛል!! የኢትዮጵያው ሄዝቦላ ከነሽብር አደረጃጀቱ፣ ከነሽብር አስተሳሰቡ፣ ከነሽብር ስልቱና ከነሽብር ተግባሩ! ከእሥራኤል ጋር ጥብቅ ግንኙነት የመመሥረት ሀሳቡ! የእሥራኤልን መንግስትና ሕዝብ ክብር የሚነካ ብቻ ሳይሆን! እሥራኤልን በዓለም-አቀፉ ማህበረሰብ ፊት፤ የአሸባሪ ቡድን አድናቂና ደጋፊ አድርጎ ለማሳየት! የሽብር ቡድኑ አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝ ማሳያ ነው፡፡
ህ.ወ.ሐ.ት. እየተባለ የሚጠራው! አሁን ደግሞ ለሽብር ተግባር ያስታጠቃቸውን ቡድኖች ‹‹ትግራይ መከላከያ ኃይል›› /TDF/ እያለ በመጥራት፤ ሀገራትን እያደናገረ የሚገኘው፤ ይህ አሸባሪ ቡድን!! እሥራኤልን ብቻ ሳይሆን ሳኡዲ አረቢያን፣ አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባውያንን፤ የሽብር ተግባሩ አድናቂዎችና ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ እያደረገ ያለው ጥረት!! በሀገራቱ ላይ ዓለም-አቀፍ ‹‹አስከፊ የዲፕሎማሲ ኪሣራ›› እና የሞራል ውድቀት ከማስከተሉ በፊት!! የአሸባሪ ቡድኑን ትክክለኛ ማንነት መርምረው! ተገቢ የፀረ-ሽብር ውሳኔ የሚያሳልፉበት ጊዜው! አሁን ብቻ ነው፡፡
ማስታወሻ፡ ደራሲው በቅርቡ ከሚያሳትመው አነስተኛ የመጽሐፍ ክፍል የተወሰደ ነው፡፡
ሠላም ለኢትዮጵያ ሠላም ለአፍሪካ
ቴዎድሮስ ጌታቸው
/ደራሲና የፖለቲካ ተመልካች/