October 29, 2021
18 mins read

ከዱቄት እስከ ሰብዓዊ አንበጣነት!! (የኢትዮጵያ ‹‹ሰብዓዊ ድሮኖች›› መነሳት) መነሻ! – ቴዎድሮስ ጌታቸው

ከአንድ የሕይወት ተመክሮ ካለው እና በእድሜውም አባቴ ከሚሆን ሰው ጋር፤ ድሬዳዋ ከተማ ከዚራ ውስጥ! በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሀሳብ ተለዋወጥን፡፡ ይህ ሰው ቀደም ሲል የሚያውቀኝ በመሆኑ ‹‹በሀገራዊ ጉዳይ አንድ ግልፅ ያልሆነልኝ ነገር አለ፤ እባክ እንድ ጊዜ ቁጭ ብለን ብናወራበት?›› አለኝ፤ እኔም የማከብረው ሰው ስለሆነ፤ በተጨማሪም ሀገራዊ ጉዳይ በመሆኑ ጥያቄውን ተቀብዬ አጠገቡ ተቀመጥኩ፡፡ ቢራ አዘዘልኝ! ይህንንም አመስኜ ተቀበልኩ፡፡

ሰውየው መረር ብሎ ጥያቄውን ጀመረ! ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወያኔን ቡድን ዱቄት ሆኗል ብለው ነበር፤ ኢኸው እንደምታየው ወሎ ድረስ ገብቷል፤ ወሎ ድረስ የሚገባ ቡድን እንዴት ዱቄት ሆኗል ይባላል?›› አለኝ፤ እኔም በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን መረዳት መዛባቱ ሁሌ ስለሚያበሳጨኝ፤ ብስጭቴ ወደውጭ እንዳይወጣ በተጋበዝኩት ቢራ እያወራረድኩ፤ ማብራሪያ መስጠት ጀመርኩ፤ ‹‹ጉዳዩ የወያኔ ዱቄት አለመሆን ሳይሆን፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ በአግባቡ ያለማብራራት ያመጣው ችግር ነው›› አልኩት፡፡  ሰውየው ግን በቢራ የሚወራረድ ብስጭት አልነበረውም! ቆጣ ብሎ ‹‹ምን ለማለት ፈልገህ ነው?›› አለኝ፤ ይህን ሰው ያበሳጨው ሌላ ሳይሆን ‹‹የወያኔ ዱቄት አለመሆን ሳይሆን…›› የሚለው አረፍተ-ነገር በመግባቱ ነበር፡፡

ብዙ ጊዜ እንዳስተዋልነው፤ አሸባሪው የህ.ወ.ሓ.ት. ቡድን ጥቃት በፈፀመ እና ወታደራዊ ባልሆነ መንገድ /ስልት/ አካባቢ በተቆጣጠረ ቁጥር፤ ‹‹የዱቄት ጉዳይ›› በተደጋጋሚ ይነሳል! አሁንም እየተነሳ ይገኛል፡፡ የዚህ ጥያቄ መነሳት ለየት የሚያደርገው! ማብራሪያ የማፈላለግ እና ለሕዝብ አጥጋቢ መልስ የመስጠት ኃላፊነት ያለባቸው፤ የፖለቲካ አመራሮች ጭምር ‹‹የዱቄቱ ነገር›› ያልገባቸው፤ ከሕዝቡ ባልተናነሰ ‹‹አስረዱኝ›› በማለት የሚያፋጥጡ መሆናቸው ነው፡፡

በሌላ በኩል /ሐቅ የማይጠላ ከሆነ/፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ፤ ራሳቸው በዐይናቸው አይተው በተግባር ያረጋገጡትን ‹‹ዱቄት››፤ በቃል ሊያብራሩት አለመቻላቸው፤ የማብራራት እዳው በፖለቲካ ተመልካቾች፣ ተንታኞችና ፀሐፊዎች ትከሻ ላይ መውደቁን አረጋግጦልናል፡፡ በመሆኑም እውነታውን በጥቂቱ እንቃኛለን፡፡ እነሆ፤

ቅድመ ዱቄት!

የመጋቢት 24/2010 ሕዝባዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ለውጥ ማዕበል! ህ.ወ.ሓ.ት.ን አያንከባለለ ወስዶ አፋርና አማራን አሻግሮ፤ ትግራይ ክልል ሲያላትመው፤ እንደመጨረሻ ድል የቆጠርነው ጥቂቶች አይደለንም፡፡ ግን ስህተት ነበር! ይህን የምንረዳው የመጋቢት 24ቱ ድንገተኛ ማዕበል ለህ.ወ.ሓ.ት. የፈጠረለትን ምቹ እድል ስንቃኝ ነው፡፡ ምቹ እድል ስንል! ህ.ወ.ሓ.ት. በትግራይ ክልል እንደአዲስና ያለከልካይ፤ ራሱን በወታደራዊና በፖለቲካ ቁማር አጠናክሮ የወጣበት ‹‹ኩነት›› ማለታችን ነው፡፡

ሌላውን አቆይተን አንዱን ብቻ ብንመለከት፤ በብር ያስፈፀመው የፖለቲካ ቁማር /ወንጀል/ ተጠቃሽ ነው፤ የብር ጉዳይ ስናነሳ ‹‹ብር በጆንያ›› አይደለም! ‹‹ብር በጆንያ›› እኮ የኦ.ነ.ግ. ሸኔ ነው፤ የህ.ወ.ሓ.ት. ግን! ‹‹ብር በእህል መጋዘን›› ነው›፡፡ እናም የህ.ወ.ሓ.ት. ቡድን ብሩን ከመጋዘን እየዛቀ፤ ከጥፋት ፕሮጀክት ጋር በየክልሉ በመበተን! የለውጡን ቀጣይነት ገና ከጅምሩ ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አደረገ፤ በለውጥ አመራሩ ተአማኒነት ላይ ጥርጣሬ አሰፈነ፤ በሕዝብ ወጥቶ የመግባት ዋስትናው ላይም ስጋት ደቀነ፡፡ ህ.ወ.ሓ.ት. በጊዜው ይህን እኩይ-ስልት ተጠቅሞ! በለውጥ አመራሩ ላይ የፖለቲካ የበላይነቱን አሳይቷል፡፡

የዱቄቱ ምስጢር ሲገለጥ!

አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. ዱቄት የመሆኑ እውነታ የሚገለጥልን፤ ጠንካራ አቅም የገነባበትን ምስጢር በሚገባ ስንረዳ ነው፡፡ አቅም የገነባባቸው ምስጢሮችም እነዚህ ናቸው፡-

  1. አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. በጦር ዝግጅቱ! ከምዕራባውያን ሳይቀር የአሸናፊነት ቅድመ ግምት ያገኘበትን አቅም የገነባው፤ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› በሚለው መርህ በመመራት ነው፡፡
  2. አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. በትግራይ ክልል ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት፤ ከመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የሚፈልጋቸውን አባላት አስወጥቶ፤ የክልሉን ልዩ ኃይል ቁጥሩን ጨምሮ፣ ከሚገባው በላይ ወታደራዊ ሥልጠና ሰጥቶና አስታጥቆ ያዘጋጀው፤ የኢ.ፌ.ዴ.ሪን መከላከያ ሰራዊት ለመገዳደር አይደለም!! በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መንፈስ ለመደምሰስና ለመተካት ነው፡፡
  3. አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. ብሩን፣ ዶላሩንና ሕዝባዊ ድጋፉን ያሰባሰበው፤ አብዮታዊ ዴሞክራሲን መልሶ ለመታደግ እልህ አስጨራሽ ትግል ለማድረግ ነው፡፡

እንግዲህ በዚህ መልኩ ተጠናክሮ የተዘጋጀ የህ.ወ.ሓ.ት. ኃይል ነው! በምዕራባውያን የማሸነፍ ቡራኬ የተቸረው የህ.ወ.ሓ.ት. ኃይል ነው! አብዮታዊ ዴሞክራሲን አንግቦ ሀገር ሲገዛ የነበረ የህ.ወ.ሓ.ት. ኃይል ነው! የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መከላከያ ሠራዊት ላይ ‹‹መብረቃዊ ጥቃት›› ፈፅሞ! የሠራዊት አመራሩን! አባላቱን! ታንኩንም! መድፉንም! ሚሳኤሉንም የማረከ የህ.ወ.ሓ.ት. ኃይል ነው! አብዮታዊ ዴሞክራሲው እንዳይቀለበስበት፤ ያለ-የሌለ አቅሙን የተጠቀመ የህ.ወ.ሓ.ት. ኃይል ነው!! በሦስት (3) ሣምንታት ‹‹የህልውና ዘመቻ›› የተንኮታኮተው!!

መንኮታኮት ብቻ ግን አልነበረም! አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. አብዮታዊ ዴሞክራሲን ‹‹መስመሬ እና መታገያዬ›› ማለቱ ሳያንስ! አብዮቱን ከማምለኩ የተነሳ ‹‹የሚቃወሙኝን የምገድልበት መመሪያዬ ነው›› እያለ የሚምልበትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ!! ዳግመኛ አንግቦ እንዳይንቀሳቀስ እና እርግፍ አድርጎ እንዲተው! ዳግመኛም ‹‹የአቢዮት ሥም እንዳይጠራ›› ተደርጓል፡፡ ይህ! ምን ማለት ነው?

የአሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. አብዮታዊ ኃይል፤ ዳግመኛ ተሰብስቦ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ኃይል መሆን አይችልም ማለት ነው፡፡ ይህን በዱቄት መንዝር! አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. በተካሄደበት ‹‹የህልውና ዘመቻ›› እኩይ ዓላማው ተጨናግፎበት፤ በንፋስ እንደተበተነ ዱቄት ሆኗል፡፡ ዳግመኛም እኩይ ዓላማውን በሚያሳካበት ደረጃ ‹‹የሚሰበሰብ ዱቄት›› ሊሆን አይችልም!! በአጭሩ ‹‹የዱቄት ብናኝ›› ሆኗል፡፡ እባካችሁ? ይህን እንደያዝን ወደአሁናዊ ኩነት እንዝለቅ!

አንበጣነት!

አሁን በአፋር፣ በወሎ እና በጎንደር እያጋጠመ ያለው ወረራ! የተበተነው ዱቄት ተሰብስቦ በድጋሚ የጦርና የፖለቲካ ቁመና በመያዙ አይደለም፤ በርግጥ አሁን የሚገኘው ወራሪ ኃይል፤ ቀደም ሲል በተበተነው ‹‹የዱቄት ብናኝ›› የሚመራ ኃይል ነው፡፡ ነገር ግን ‹‹በዱቄቱ ብናኝ›› የሚመራው ይህ ወራሪ ኃይል፤ ከጥፋት ውጪ የወረራውን ግብ ያልተረዳ! ‹‹ስብስብ የጥፋት መንጋ›› ወይም ‹‹ሰብዓዊ አንበጣ›› መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ለዚህም ነው ይህ ወራሪ ኃይል ወርሮ በያዘበት ቦታ ሁሉ፤ በዱቄት ዝርፊያ! በተቦካ ሊጥ ማሰባሰብ! ዶሮ አባሮ በመያዝ እና ያልደከመበትን አዝመራ ወርሮ በማጨድ /በሰብአዊ አንበጣነት/ ጊዜውን የሚያጠፋው፡፡

ይህን የምንለው ወራሪው ኃይል ወርሮ በያዛቸው አካባቢዎች፤ እያደረሰ ያለውን ጥፋት ለማሳነስ! ወይም በዜጎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ‹‹ሽብር ተኮር ግድያ›› እና ‹‹ከቀዬ ማፈናቀል›› በመዘንጋት አይደለም፡፡ ይህ ‹‹ስብስብ የጥፋት መንጋ›› እያካሄደ የሚገኘው ወረራ፤ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልትን ያልተከተለ! ‹‹ዘለቄታ የሌለው እና ራዕይ አልባ ወረራ›› መሆኑን ለማመላከት ነው፡፡ ይህ በመርህ ደረጃ የሚያግባባን ከሆነ፤ ወደመራሩ እውነት እናምራ!

ከክህደት እስከ ቀብድ!

በሀምሌ 7/2013 በመንግስት ለቀረበው ‹‹ሀገራዊ ህልውናን የመታደግ›› ጥሪ፤ በሞያ ምላሽ ለመስጠት ባሕር-ዳር ነበርኩ፤ በወቅቱ በዱቄቱ ብናኝ የሚመራው ኃይል የወሎና የጎንደርን ውስን ቀበሌዎች በወረራ ያዘ፤ በንጋታው ለዚህ ወረራ ግብረመልስ የተደረገው! ‹‹ተክደናል›› የሚል ወራሪውን የሚያጠናክር ወሬ ነበር፡፡ ይህ የተክደናል ወሬ ነው ራሱን በውሸት አጎርምሶና አበልፅጎ! አሁን ወደ ‹‹ወሎ ቀብድ›› ያደገው፡፡

በእውነቱ ከሆነ እንኳን ‹‹የተካፍለን እንብላ›› እና ‹‹የመተሳሰብ›› ተምሣሌት የሆነውን ማህበረሰብ /ወሎ ገራገሩን/ ይቅርና! በአሸባሪው ወያኔ እብደትና የተላላኪነት ቅዠት ምክንያት፤ በችግር የሚጠበሰውን ወገናችንን የትግራይ ማሕበረሰብ የሚከዳ!! ተጨባጭ መረጃ በኢትዮጵያ ምድር አይገኝም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ወገኖቻችን መረዳት ያለባቸው! ይህ ትውልድ ለሀገር አንድነት እና ህልውና መዋደቅን እንጂ፤ ክህደትም! ቀብድም! ቀልድም! አያውቅም!! እናም እባካችሁ ለጠላት መሿለኪያ የሆነችውን ኢቺን ክፍተት በማስተዋል እንድፈናት፡፡

ቀጭን መጠቅለያ!

በአፋር እና በአማራ ክልል ‹‹በአሸባሪው የዱቄት ብናኝ›› አመራር ሰጪነት፤ ተግባራዊ የሆነውን ‹‹በሕዝባዊ ማዕበል ወረራን የማስፈፀም ስልት››፤ ምንነቱን፣ ምክንያቱን እና የሚያስከትለውን ውጤት ግልፅ ማድረግ! ሰፊ ጊዜ የሚወስድ ሊሆን አይገባም!! አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. ‹‹የዱቄት ብናኝ›› ከሆነ በዃላ እየተከተለ ያለው ስልት፤ የትግራይ ክልል ማሕበረሰብን ከሁለቱ ክልሎች ማሕበረሰቦች ጋር ‹‹ደም የማቃባት ስልት›› ነው፡፡

አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት› ይህን ስልት ‹‹እንደአዋጭ ስልት›› የተከተለው፤ በግልፅ የሚታየው! በአፋር በኩል የሚሌን በአማራ በኩል የሁመራን አካባቢ በመቆጣጠር፤ በኢትዮጵያ የገቢና ወጪ መስመሮች ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር ሲሆን፤ በግልፅ የማይታየው ደግሞ! በድጋሚ ተሰብስቦ ‹‹ዱቄት›› ወይም ‹‹አብዮታዊ ኃይል›› መሆን እንደማይችል በመረዳቱ እና ‹‹የዱቄቱ ብናኝ›› እድሜውን ለማራዘም ካለው ምኞት የመነጨ ነው፡፡

አሸባሪው ህ.ወ.ሓ.ት. እየተጠቀመበት ያለው ይህ ‹‹ደም የማቃባት ስልት››፤ የሚያስከትለው ውጤት አሉታዊ መሆኑ ባያከራክርም፤ አሁን ላይ የተሟላ ትንታኔ ለማቅረብ አያስችልም፤ ምክንያቱም አሸባሪውና ውስን ምዕራባውያኑ ‹‹ደም የማቃባቱን ስልት›› ነገ ለምን ዓላማ ሊጠቀሙበት ይችላሉ? በሚለው ‹‹ተጠየቅ እና የሤራ ትንታኔ›› ላይ የሚመሠረት በመሆኑ ነው፡፡

መዘንጋት የሌለበት! አሸባሪው ቡድን ‹‹ደም የማቃባቱን ስልት›› ያራመደው! ‹‹የዱቄት ብናኝ›› ከሆነ እና አብዮተኛነቱን እርግፍ አርጎ ትቶ ‹‹ኒዮ ሊበራሊዝምን በመርህ ደረጃ ተቀብያለሁ›› ካለ በዃላ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ‹‹የዱቄት ብናኝ›› ፈጥኖ ማክሰም የሚቻለው በ ‹‹ለይቶ መምታት ስልት›› ሲሆን፤ ለሰብዓዊ አንበጣው ‹‹ተገቢ ቅጣት›› ልንሰጠው የምንችለው ደግሞ! በተቀናጀ አሰላለፍ ‹‹ሰብዓዊ ድሮን›› በመሆን ነው፡፡

tedሠላም ለኢትዮጵያ ሠላም ለአፍሪካ

ቴዎድሮስ ጌታቸው

/ደራሲና የፖለቲካ ተመልካች/

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop