ስለ ግል እና ተቋማት ስያሜ ወይም መጠሪያ መለዋወጥ ከአልፎ ሂያጂ የፖለቲካ ስም ጋር ለማጣጣም የሚደረግ ትንቅንቅ ዕዉነት እና ታሪክን ለመጨፍለቅ እና ለማስጨነቅ ካልሆነ በቀር ምድር ላይ ወርዶ ስር የሰደደ ትርጉም ይዞ አይገኝም፡፡
የእኛ አገር ህዝባዊ መንግስት እና ስርዓት (ዲሞክራሲ) አዋላጂ እና ኃዋርያ የሚሉት ፖለቲከኞችም ሆኑ የፖለቲካ አመራሮች የዓለም መጠሪያቸዉን ትተዉ የድብቅ ስማቸዉን ይዘዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ በታማኝነት እና ኃላፊነት ስሜት ለማገልገል አለመቻላቸዉ በተግባር የመታየቱ ሚስጥር ከራሳቸዉ ያለመስማማት እግር ዉጤት መሆኑን መረዳት የሚቻል ነዉ ፡፡
ለህዝብ እና አገር ጥልቅ ፍቅር እና ከብር ያለዉ ለህዝብ ለሚያደርገዉ ማናቸዉም አገልግሎት ከህዝብ ለመደበቅ የኋላ ታሪኩን ለመሸፈን ስያሜ የሚቀይርበት ምክነያት የለም ፡፡
ከነበሩት የፖለቲካ አመራሮች እና መሪዎች ዕዉነተኛ ስማቸዉ ከዕዉነተኛ ምግባር እና ተግባር ጋር ከነበሩት እና ካሉት እነ ከሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም፣ ኮ/ል አጥናፉ አባተ……ለማኑበት ፣ለተነሱለት እና ለቆሙለት ህዝባዊ እና ብሄራዊ የህዝቦች አንድነት እና ነጻነት በትክክል ሰርተዉ የሚገኙ እና ያለፉትን መጥቀስ ከብዙ በጥቂቱ ለማመሳከር እንደሆነ ይታወቅ ፡፡
ከዚህ በተቃርኖ ልማታዊ እና ዲሞክራቲክ የሚለዉ “ ህወኃት /ኢሀዴግ” ከጥዋት አስከ አስከ ሞት ምሽት ያለፉትን እና የኢትዮጵያነት አብነት እና ኩራት የሆኑትን መታሰቢያዎች፣ መጠሪያወች እና ዕንቁ ብሄራዊ እና ዓለማቀፋዊ ታሪኮችን በማጥላላት እና በማሳሳት የጥላቻ ስብከት (ፕሮፖጋንዳ) በስያሜ እና በንግግር ሲያደናግር የመሸበት መሆኑን ዓለም የሚገነዘበዉ ገሀድ ነዉ ፡፡
የጥላቻ ፖለቲካ ልክፍት የህዝብን እና አገርን ዕዉነተኛ ገፅታ የመጥላት አባዜ የሚነሳዉ ስለ ራስ የቤተሰብ ስም ጥላቻ እና ለዉጥ ፍለጋ ነዉ ፡፡
አብዛኞች የኢህዴግ የፖለተካ አመራሮች የሽፍታ ስያሜቸዉን አስከ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት ይዘዉ መዝለቃቸዉ ለህዝብ እና ላአገር የነበራቸዉ ንቀት እና ጥላቻ ለራሳቸዉ ስያሜ እና ማንነት ከነበራቸዉ አስተሳሰብ የተቀዳ እንደነበር በስራ ዘመናቸዉ የተከሉት የጥላቻ እና ምቀኝነት አደረጃጀት እና ሀዉልት የሚገለፅ ነዉ፡፡
ለአብነትም የሆለታ የመኮንኖችን ማሰልጠኛ ት/ት ቤት ጀነራል ሙሉጌታ በኃየሎም ፣ መንግሰቱ ኃ/ማርያም ሆ/ል(ሆስዓና ) መቀየር፣ የመለስ(ለገሰ ) ዜናዊ አካዳሚ መባል፣ ሁሉም ግንቦት 20….. በራስ ያለመተማመን የጥላቻ እና የክፋት/ ምቀኝነት ፖለቲካ አርቆ ካለማየት የሁሉንም ነገር መሰረት በተግባር የሚለካ ምግባር መሆኑን ካለመረዳት መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
ይህ የዘመናት ታሪክ እና ዕዉነት የመፋቅ በቁም ያለምግባር እና ተግባር የራስን ሀዉልት ለማቆም የመሽቀዳደም አባዜ ዛሬም ከ27 ዓመት በኋላ መቀጠሉ ግን ህዝባዊ ብሶት ያስገኘዉን የለዉጥ ጭላጭል እንዳያጨልመዉ የሚመለከተዉ ሁሉ ልብ ቢለዉ ይገባል፡፡
ብሄራዊ እና ዓለማቀፋዊ ቅርስነት ያላቸዉን ፣ ታሪካዊ እና ዕዉነተኛ ስያሜ የተሰጣቸዉን፣ በዕንቁ እና ዘመን አይሽሬ ተጋድሏቸዉ ጀግኖች ቀደምት ኢትዮጵያዉያን በደም ብዕር እና በህይዎት ዋጋ የዋጇትን አንድ አገራችንን እና ህዝቧን የማይመጥን ጊዜያዊ ስያሜ /መጠሪያ ለማስገኘት፣ለማግኘት ወይም በዉሸት ዕዉነትን መፋቅ ትርፉ ትዝብት፣ ክህደት እና ታሪካዊ ሞት ከመሆን አይዘልቅም፡፡
የነበረዉን እና የኋላዉን የማያገናዝብ እና የማያገኛኝ የለዉጥ ምዕራፍ መደነቃቀፍ እና መለላጥ ስለሚሆን ቀደምት ዋኖችን ተግባር ስንዘክር እና በዕዉነት ስንኖር ብቻ ዘመን ተሸጋሪ እና ትዉልድ አስተማሪ ስም እና መታሰቢያ ሲዘከር እና ሲከበር የሚኖረዉ ፡፡
ትናንት በቁም ሲመለኩ እና በፈራሽ ሀዉልት ሲመኩ የነበሩት በአድር ባዮች ጭብጨባ ተደናቀረዉ እና አደንቁረዉ ማስተዋል የራቃቸዉ ፤ሠባዊነት በህይወት ሳሉ የከዳቸዉ ፤የራቃቸዉ እነ የሊቢያዉ ሙዓመር ጋዳፊ ፣ የኢራቁ ሳዳም ሁሴን፣ የሶሪያዉ በሽር አሳድ፣ የቱኒዚያዉ ቤኒ ዓሊ፣ የሱዳኑ ዑመር አልበሽር፣ የመከረኛዋ አገር እና ህዝብ / ኢትዮጵያ መለስ ዜናዊ ፣ የኡጋንዳዉ ኢዲ ……መታሰቢያቸዉ መቅረት እና መፍረስ ቀርቶ ህዝባቸዉ ፣አገሮቻቸዉ ፣ ቤተሰባቸዉ ሳይቀር በፈፀሙት ጥፋት እና ክህደት አይከፍሉት ዋጋ እየከፈለ እና እየተገለለ ነዉ ፡፡
ዕዉነተኛ ለዉጥ በተግባር የሚታጀብ እና በመጠሪያ እና ስያሜ መቀያየር የሚገኝ ባለመሆኑ ተግባር ሳይኖር በስም መኖር ከሰሞነኛነት ስለማያልፍ ከምግባር እና ተግባር የሚከሰት ስም ለመትከል እንደማይተሰብ በዝርዝር እና በምክነያት እንነጋገር ፤እንተግብር ፡፡
“ ስም የበጎ ምግባር እና ተግባር የምንጊዜም መታሰቢያ ሲሆን መጠሪያ ብርሃን እንደሚሸሽ ጥላ በምሽት የሚሸሽ ፤ንጋት እንደረፋድ ጤዛ የሚጠፋ የባዶ ምኞት ቅዠት ነዉ ፡፡”
“እየናዱ መካብ ከታሪክ አለመማር ብቻ ሳይሆን በዕዉነት ላይ የሚደረግ አመፅ እና ክህደት ነዉ ፡፡”
ማላጂ
”
“አንድነት ኃይል ነዉ !! ”