ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY
ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)
የአሜሪካ ፕሬዤዳንት ጆባይደን፣ የግብጽ ፕሬዤዳንት አብዱል ፈታ አል ሲሲ፣ የሱዳን ፕሬዤዳንት አብደላ ሃምዶክ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ፣ የቻይና ፕሬዤዳንት ዥ ጂንፒንግ፣ የራሲያ ፕሬዤዳንት ቭላድሜር ፑቲን፣ የቱርክ ፕሬዤዳንት ኤርዶጋን
‹‹ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፣ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፣ የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ ይወድቃሉ ብዛትዋንም ይወሰዳሉ፣ መሠረትዋም ይፈርሳል፡፡ ኢትዮጵያና፣ ፋጥ፣ ሉድም የተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ግብጽን የሚደግፋ ይወድቃሉ፣የኃይልዋም ትዕቢት ይወርዳል ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፡፡›› ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 30 ከ4 እስከ 5
BIBLICAL PROPHESY: “A sword shall come on Egypt, and anguish shall be in Ethiopia, when the slain shall fall in Egypt; and they shall take away her multitude, and her foundations shall be broken down…” (Ezekiel 30:4).
አዲሱ የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ ሁለት ረድፎች፡-
‹‹ጦርነት ማን ትክክል እንደሆነ ሳይሆን ማን እንደተረፈ ነው የሚያረጋግጠው፡፡›› “War does not determine who is right, only who is remaining.” የፊንላንዶች አባባል፡፡
- ትህነግ ለሃያ ሰባት አመታት ኢትዮጵያን በአንባገነን አገዛዝ በመምራት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በፈጸመው የስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት፣ በእስረኞች ኢስብዓዊ አያያዝ በግድያ በቶርቸር ጥሰት፣ በስብዕና ላይ ሰለፈጸማቸው ወንጀሎች በዘር ማፅዳት በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በሱማሌ፣ በኦሮሞ፣ ወዘተ ህዝብ ላይ የፈጸመው ህግ ጥሰት፣ ህዝብ በማፈናቀል፣ በማስደድ ወዘተ አገዛዙ የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብን በዘር ፌዴራሊዝም ከፋፍሎ በመግዛት ጸረ-ህዝብ ሽብርተኛ ድርጅት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ በመቆም ፀረ-ትህነግ ጦርነት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያዊ ሃገር ፍቅርና በህብረ-ብሄር አንድነት ሁሉም ዘብ ቆሞል፡፡
- ምዕራባዊያን አገራት ትህነግን በመደገፍና ለማዳን አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአረብ ሊግ ፣ ግብፅ፣ ሱዳን ወዘተ በአንድ ረድፍ ቆመዋል፡፡ ምዕራባዊያን አገራት ለትህነግ በሱዳን በኩል ኮሪደር ለማስከፈት፣ በእህል እርዳታ ማቅረብ ስም የጦር መሣሪያ ለማስታጠቅ፣ የመገናኛ ሳተላይት ስልኮችና ዘመናዊ የመገናኛ ሬዲዩን ለማቅረብ፣ መድኃኒቶች ለማድረስ፣ ከሱዳን ያሉ አርባ ሽህ የትህነግ ሠራዊትን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ወዘተ ኢትዮፕያን ለማፍረስ የማይፈነቅሉት ድንጊያ የለም፡፡
- በሌላው ረድፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን በመደገፍ አቆማቸውን በፅናት የገለፁ የቻይና መንግሥት፣ የራሽያ መንግሥት፣ የቱርክ መንግሥት፣ የህንድ መንግሥት፣ የአፍሪካ ህብረት ወዘተ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመደገፍና የትግራይ ጉዳይ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ ምዕራባዊያን አገሮች ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው በማውገዝ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል፡፡
‹‹ማንም ሰው ወደ ጦርነት እንዲሄድ ወይም ሚስት እንዲያገባ አትምከር፡፡ ›› “Never advise anyone to go to war or to marry.” የስፔኖች አባባል፡፡
አዲሱ የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ ሁለት ረድፎች አቌም፡-
‹‹ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ!!!›› ግድቡ ለመቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ አገራችን በዓለም የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሴራ የግብፅ፣ ሱዳን፣ የአረብ ሊግ፣ እስራኤል፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት ወዘተ አገራቶች በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግብፅና ሱዳንን መንግሥት በመደገፍ ጸረ- ኢትዮጵያ አቌም ወስደዋል፡፡
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብአራት የኒውክለር ማብላያ እምቅ ኃይል ያላት አገር ሆናለች፡፡ የህዳሴ ግድቡን ለማስቆም በባዕዳን ኃይሎች ከሃገር ውስጥ የትህነግ ሽብር ኃይሎች ጋር የውክልና ጦርነት ከተለያየ አቅጣጫ ጦር የሚወረወርባት፡፡ ኢትዮጵያን የነካ!….ግድቡን የነካ!.. የውኃ ጥፋት ዘመን … የኖህ ዘመን ያሸጋግራቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሆኖ ጠላቶቹን በመመከት የሚቀጥለውን ዘመን መሻገር የህልውና ጉዳይ ነው፡፡
የቻይና ልዕለ ኃያል መንግሥትነት
ቻይና መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ አገሮች የኢኮኖሚ ግንባታና የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ግንባታ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጅ፣ የፋይናንስና ባንኪንግ ዘርፍ ለአፍሪካ አገራት፣ የባንክ ብድር አገልግሎት በመስጠት ለአፍሪካ ህዝብ ተደራሽ በመሆናቸው የቻይና ልዕለ ኃያልነት በአፍሪካ ተመራጭ ለመሆን ችለዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ባንክ፣ አይ ኤም ኤፍ ወዘተ የበሰበሰ ሥርዓት ለመገርሰስ ታዳጊ አገራቶች ከቻይና፣ ሶብየት ህብረት፣ ህንድ፣ ወዘተ ጋር ህብረት ፈጥሮ የዓለም አቀፍ ሥርዓት መለወጫው ጊዜ በአሜሪካ የውሸት ዴሞክራሲ በአፍሪካ አገራቶች የቻይና መንግሥት የልማት አቅጣጫ ደጋፊ መሆናቸው ምዕራባዊ አገሮችን ስጋት ላይ ጥሎቸዋል፡፡ ምዕራባዊ አገሮችና አሜሪካ በኢራቅ ህዝብ፣ በሲሪያ ህዝብ ላይ፣ በየመን ህዝብ ላይ፣ በሊቢያ ህዝብ ላይ የፈጸሙት የመንግሥት ለውጥ ‹‹régime Change ›› የአሜሪካ ልዕለ ኃያል መንግሥት አገዛዝ ታሪክ ይቅር ማይለው፡፡ አሜሪካ በኢትዮጵያ ‹የመንግሥት ለውጥ› ለማድረግ ትህነግን በመደገፍ የምታራምደው የፖለቲካ ሴራ እውን አይሆንም፡፡
የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ አሻጥር በኢትዮጵያ
#{1}የአግዋ (AGOA) የንግድ ስምምነት፡- የትህነግ አሸባሪ ቡድን የአፍሪካን እድገትና የተመቻቸ ንግድ አክት፡- Africa Growth and Opportunity Act (AGOA) ኢትዮጵያ ለማስወጣትና ከንግዱ እድል ተጠቃሚ እንዳትሆን የትህነግ ዲያስፖራዎች የኢኮኖሚ አሻጥር (Economic sabotage) በማድረግ ላይ ስለሉ የኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች በፓብሊክ ዲፕሎማሲው መስክ እንዲመክቱ ጥሪ ቀርቦል፣ተባበሩ፡፡ በአሜሪካና በአፍሪካ ሀገራት መኃል የተፈጠረ የንግድ ግንኙነት ከታክስ ነጻ የሆነ በውጭ ንግድ ወደ አሜሪካ ምርትና ሸቀጦች የማስገባት ስምምነት ነው፡፡ በዚህ ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ሁለት መቶ ሚሊዮነን ዶላር በውጭ ንግድ ገቢ በ2012ዓ/ም አግኝታለች፡፡ በአግዋ ስምምነት ሀገር ውስጥ የገቡ ኢንቨስተሮች በኢንዱስትሪያል ፓርኮች መቶ ሽህ ሠራተኞች ቀጥረው በማሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት አራት ቢሊዮን ዶላር በ2013ዓ/ም ተመዝግቦል፡፡
Ethiopia’s exports to US under Africa Growth and Opportunity Act (AGOA) increasing:- Ethiopia’s export under AGOA has jumped by 62 percent between October 2017 and September 2018. The country experienced the largest increase exports in the period under review, according to USAID East Africa Trade and Investment Hub. “If this growth continues, Ethiopia may quickly become the second or third largest exporter under AGOA in East Africa,” the Hub said. East African countries supported by the USAID-Hub reached nearly one billion… (02 January 2019)
#{2} የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ፡– የትህነግ አሸባሪ ድርጅት የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ድርጅትን የኢትጵያ መከላከያ ሠራዊትን ወደ ትግራይ ለጦርነት አመላልሶል በማለት ስም በማጥፋት የገነባውን ስምና ገቢውን ለመቀነስ ትህነግ ዲያስፖራ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አሻጥር በማድርግ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች በፓብሊክ ዲፕሎማሲው መስክ እንዲመክቱ ጥሪ ቀርቦል፣ተባበሩ፡፡
#{3} የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ፡– የትህነግ አሸባሪ ቡድን ከአዲስ አበባ ወደ ጅቢቲ የኤሌትሪክ ባቡር በማስቆም የሃገሪቱን 85 (ሰማንያ አምስት በመቶ) የውጭና ገቢ ንግድ በማስተጎጎል የኢኮኖሚ አሻጥር ትህነግ በአፋር በኩል ጦርነት በመክፈት የአዲስ አበባ-ጅቡቲን የባቡር አገልግሎት መስመር ለመዝጋት ቢሞክርም በአፋር ህዝብና መከላከያ ሠራዊት የትህነግ አሸባሪዎች በተደጋጋሚ ተደምስሰዋል፡፡ ትህነግ በአፋርና በሱማሌ ህዝብ መኃል ጦርነት በመቀስቀስ ወደ ጅቡቲ የሚወስደው መንገድና የባቡር አገልግሎት እንዲቆረጥ ሙከራ በማድረግ ለትንሽ ቀናት ተቆርጦ የነበረው የንግድ ግንኙነት በኢትዮጵያዊያን ህብረት የንግድ ግንኙነቱ ዳግም ተጀምሮል፡፡
#{4} የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት፡- 100 (መቶ ቢሊዮን ብር) ለትግራይ መቆቆሚያ ወጪ አድርጎል፡፡ ለትግራይ ህዝብ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት የመብራት፣ የስልክና ኢንተርኔት ዝርጋታን ትህነግ በተደጋጋሚ በማውደም ፀረ- ህዝብ አቆሙን ለትግራይ ህዝብ አሳይቶል፣ ህጻናትን ለውትድርና ይመለምላል፣ ያለህግ የትግራይ ሰዎችን ይገላል፣ የትግራየረን ህዝብ በስብዓዊነ ጋሻነት ይዞ በጦርነት ይማግዳል፣ ትህነግን አሽቀንጥሮ መጣል ጊዜው አሁን ነው፡፡
#{5} ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፡- ትህነግ በኢትዮጵያ ውስጥ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የውጭ ምንዛሪ ኃብትን ዶላር፣ ዩሮ፣ ፓውንድ ወዘተ ከሃገር ውስጥ በብር ቀይሮ ወደ ውጭ በማስወጣት የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈፀም ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በውጭ ዲያስፖራ የሚገኘውን ሪሚታንስ አምስት ቢሊዮን ዶላር በአስተማማኝ ህጋዊ መላኪያዎች በመጠቀም ትህነግ እጅ እንዳይገባ በማድረግ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ የአገር አሌንታና መከታ መሆን ጊዜው አሁን ነው፡፡ ሃገሪቱ በ2013 ዓ/ም በውጭ ንግድ 3.6 (ሦስት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር) ማግኘት ከዚህ አስከፊ የጦርነት ኢኮኖሚ እንድትወጣ የትግራይ ህዝብ ትህነግን አሽቀንጥሮ በመጣል ከኢትዮጵያ ወንድሞቹ ጎን በመወገን የውክልና ጦርነቱን ማስቆም ይጠበቅባቸዋል፡፡ የውጭ ምንዛሪ አንድ ዶላር ከ65 አስከ 72 ብር በጥቁር ገበያ መድረስ ዋና ምክንያት የትህነግ ባለኃብቶች ንብረታቸውን በብር እየሸጡ በዶላር ቀይረው ወደ ውጭ ሃገራት በመላክ የሚፈፅሙት የኢኮኖሚ አሻጥር በመሆኑ መንግሥት ጦርነቱ እስኪያበቃ የንብረት ሽያጭ በማስቆም የውጭ ምንዛሪውን ማረጋጋት ይችላል፡፡ የዋጋ ግሽበቱንም የፌዴራል መንግሥትና የክልል መንግሥታት አስፈላጊውን ቁጥጥር በማድረግ የደሃውን ህዝብ ጉሮሮ ሊዘጉ የሚታገሉ አሻጥረኛ ነጋዴዎችን ማስጠንቀቂያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡
#{6} የሳይበርክራይም Cybercrime:- Sabotage:- የኢንተርኔት የሳይበር ወንጀል ዋነኛው የመንግሥታዊ ድርጅቶችና መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ እንዲሁም የግሉን ዘርፍ ድርጅቶች የባንክ፣ የኢንሹራንስ፣ የስለላ ድርጅት (የኢንሳ)፣ የመከላከያ ድርጅቶች፣ ወዘተን ተቆማት ድር-ገፆች በመሰለልና በመጥለፍ መረጃዎች ማግኘት የትህነግ አንዱ የኢኮኖሚ አሻጥር ስለሚሆን አስቀድሞ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡ Cybercrime:- Sabotage:-Another type of hacking involves the hijacking of a government or corporation web site.
#{7} አምስተኛ ረድፈኞች፡– የፖለቲካ ሚስጢራዊ ወይም የህቡዕ ድርጅቶች ወይም አንጃ ሲሆን መንግሥታዊ ተቃዋሚ በመሆን የብሄራዊ ሃገረ-መንግሥቱን ህብረትና አንድነት ውስጥ ውስጡን በመሸርሸር የሚሠራ የፖለቲካ ድርጅት ሚስጢራዊ ሥራ ነው፡ የትህነግ አምስተኛ ረድፈኞች ከመኃል አገር ሆነው መረጃ በማቀበል፣ ገንዘብ በማሰባሰብ፣ የሰው ኃይል በመመልመል፣ የኢኮኖሚ አሻጥር በማድረግ የሚጫወቱት ሚስጢራዊ ሥራዎችን በማስረጃ በመያዝ ለህግ ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡ በትህነግ ሥም በትግራይ ተወላጆች ስም የሚፈፀም ሃሰተኛ ውንጀላ እንዳይፈፀም የህግ ከለላ እንዲጠብቃቸው ግድ ይላል፡፡ Fifth column ፡-Fifth column, clandestine group or faction of subversive agents who attempt to undermine a nation’s solidarity by any means at their disposal. The term is conventionally credited to Emilio Mola Vidal, a Nationalist general during the Spanish Civil War (1936–39).
ተጨማሪ አስፈላጊ ህዝባዊ ጥንቃቄዎች
#{1} የቴሌኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት፣ ትህነግ አሸባሪ ብድን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቆረጥ በማድረግ የሃዋላ አገልግሎት እንዳይኖር በማድረግ የሚፈፀም የኢኮኖሚ አሻጥርን የቴሌኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ከወዲሁ አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይጠበቅባቸዋለ፡፡
#{2} የኢትዮጵያ ነዳጅ አገልግሎት ድርጅት፡– የሃገሪቱ የነዳጅ ክምችት ያለባቸውን ቦታዎች በንቃት መጠበቅ የድርጅቱና የህዝብ ኃላፊነት ነው፡፡ የነዳጅ ቁጠባ መርሃግብር በመንደፍ ጎዶሎና ሙሉ ታርጋ ያላቸው መኪኖች በፈረቃ እንዲነዱ በማድረግ የነዳጅ ቁጠባ ከወዲሁ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
#{3} የመሠረተ ልማቶች ጥበቃ፡- በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ መሠረተ ልማቶች የትራንስፖርት መገልገያ የዓየር ማረፍያ፣ የምደር ባቡር አገልግሎት፣ የመኪና መናህሪያዎች፣ ደረቅ ወደቦች፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ታወሮች፣ የመብራት ኃይል መሰራጭ ምሶሶዎች፣ የውኃ ማከፋፈያ ጋኖች፣ ባንክ ቤቶችና ኢንሹራንሶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ፋብሪካዎች፣ የኢንዱስትሪ ዞኖች፣ የመከላከያ የጦር ግምጃ ቤቶች፣ ሆቴሎችና ትልልቅ ፎቆች፣ ድልድዬች፣ የእቃ ማከማቻ መጋዘኞች ወዘተ የትህነግን የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከል በሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ በፖሊስና በወጣቶች ግብረ ኃይል ቀንና ማታ እንዲጠበቁ ከወዲሁ አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይጠበቃል፡፡
እንደ ሰው በምድር፣
እንደ ዓሣ በባህር፣
እንደ አዋፍ በጠፍር፣
ሽህ በክንፉ፣
ሽህ በአክናፉ
ይጠብቁሽ እናት አገር!!!