July 23, 2021
3 mins read

አጭር ግልጽ መልዕክት ለክቡር ጀነራል ተፈራ ማሞ – መስፍን አረጋ  

tefera
ጀነራል ተፈራ ማሞ

ክቡር ጀነራል ተፈራ ማሞ፡፡  የአማራን ሕዝብ በተመለከተ ሰው በጠፋበት ሰው ሁነው በመገኘት ያማራን ልዩ ኃይል ለመምራት ፈቃደኛ በመሆንወ ከፍተኛ አክብሮቴን ልገልጽልወት እወዳለሁ፡፡  እግረ መንገዴን ግን ባዲሱ ሹመትዋ የሚሰማኝን ከፍተኛ ስጋት ልገልጽልወ እፈልጋለሁ፡፡

የአማራን ልዩ ኃይልና ፋኖን በማዳከም አመርቂ ውጤት አስመዝግቦ ለዐብይ አሕመድ ታማኝነቱን በማረጋገጥ ለከፍተኛ ሹመት የበቃው አቶ ተመስገን ጡሩነህ እና መሰሎቹ፣ አሁንም ቢሆን ይህን ልዩ ኃይልና ፋኖን በሙሉ ልብ መደገፍ ቀርቶ በበጎ ዓይን ይመለከቷቸዋል ብየ አላምንም፡፡  እነዚህ ግለሰቦች አማራዊ ሰብዕናቸው በወያኔ ስለተሰለበ፣ ሊታደጓቸው ከተሰለፉት ከአማራ ልዩ ኃይልና ከፋኖ ይልቅ ሒሳብ ሊያወራርዱባቸው የሚገሰግሱትን ወያኔንና ሳምሪን ቢመርጡ አይገርምም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ባማራ ልዩ ኃይል አከርካሪውን ተመትቶ የነበረው ወያኔ፣ በብርሃን ፍጥነት አንሰራርቶ ካማራ ሕዝብ ጋር ሒሳብ ለማወራረድ እስከመዛት የደረሰው፣ በዐብይ አሕመድ ጠቅላይ አዛዥነት የሚመራውን መከላከያን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተቆጣጠሩት ኦነጋውያን በሚያደረጉለት ከፍተኛ ድጋፍና ማመቻቸት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡

ስለዚህም ወያኔና ኦነጋውያን ከነ አቶ ተመስገን ጥላሁን ጋር በመመሳጠር ባማራ ሕዝብ ላይ ትልቅ ሴራ እያሴሩ ሆኖ ይሰማኛል፡፡  ሴራውም እሰወን ጀነራል ተፈራ ማሞን ጦርነት ውስጥ በመግደል፣ በማስገደል፣ ወይም በማስማረክ፣ ወይም ደግሞ በእርስወ የሚመራ ዘመቻ ከፍተኛ ሽንፈት እንዲደርስበት በማድረግ፣ የአማራን ሕዝብ ሞራል መግደል ነው፡፡  የእርስወን አዲስ ሹመት በተመለከተ የሚሰማኝ ከፍተኛ ስጋት ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡  ስጋቴን ከፍ የሚያደርገው ደግሞ አቶ ዐበረ ዐዳሙ ለሚመራው ሕዝብ የመቆርቆር ስሜት ማሳየት ከመጀመሩ ባጭሩ መቀጨቱ ነው፡፡

 

አክባሪወ መስፍን አረጋ

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop