ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ለማሽመድመድ ጠላት የሸረበዉ ሴራ እንደ ድንገት እና ደራሽ ዉሃ ለምናስብ ሠዎች መኖራችንን ስናዉቅ ከመከራ እና ያለፈ ዘመን የማይማር ለምንም ነገር እንደማይሆን መገንዘብ የሚቻል ነዉ ፡፡
በ18ኛዉ ክ/ዘመን መገባዳጃ እና በ19ኛዉ ክ/ዘመን የተደረገዉ የቅኝ ገዥዎች ግዛት ማስፋፋት እና መሬት ቅርምት ሙከራ እና ቅዠት ዕዉን ለማድረግ በአገራችን ኢጣሊያ እና እንግሊዝ የተከሉት ሰንኮፍ እና አሜኬላ ቅርንጫፉ እና ግንዱን ማስወገድ ቢቻልም ስር እና እንክርዳዱ ዛሬም ዕሾኩ እንዲበዛ እና የዕንክርዳድ አመለካከቱም መብዛት የተደረገዉን በጎ ጥረት ሁሉ ያልጠራ እና የሰነፍ እርሻ አድርጎታል ፡፡
የቀኝ ገዥዎች እና አገልጋዮቻቸዉ በሴራ የበተኑትን እሾክ ህዝብን ቁልቋል እና አጋም ህይዎት እንዲዋጅ ተፈርዶበት እንደነበር ሳንረሳ ይህ ሁሉ ድንገቴ የሆነ አለመሆኑን ከነበር ታሪካችን መረዳት ይቻላል ፡፡
እናም የዚህችን አገር ወድቆ መነሳት ለማይሹ ታሪካዊ ጠላቶች የጥፋት ምኞት ዕዉን መሆን ድንገት ሳይሆን የነበር እና ያለ ጥልፍልፍ ደባ የአሜኬላ ፍሬ ነዉ ፡፡
ለዚህም በጥቅል የሚከተሉትን የአገራችን ሁነት ለአብነት ማሳየት ለዚህች አገር ህዝብ እና አንድነት ስጋት ምንጭ የሆኑ ሴራዎች እና ድርጊቶች ማሳያ ይሆኑ ዘንድ እንደሚከተለዉ መመልከት ያቻላል ፡-
- የኢጣሊያን ወረራ በ1896 መጀመሪያ ኢትዮጵያን ለመዉረር የዘመናት የቅዥ ግዛት ህልም ለመተግበር የነበረዉ ዝገጅት ድንገተኛ አልነበረም ይህንም በአደዋ ጦርነት ተግበራዊ አድርጎታል፣
- በ1928 ዓ.ም/1936 ዳግም ለወረራ በተደራጀ እና በዘመናዊ ትጥቅ በአዲስ ስልት የ40 ዓመት የጥፋት ዝግጅት አድርጋ ስትመለስ ድንገት አልነበረም ፣
- ጃኑሆይ እ.ኤ.አ. ግንቦት 05 ቀን 1941 ከ፭ ዓመት ስደት በኋላ ወደ እናት አገር ለመመለስ ያስቻለቸዉ ድል ድንገተኛ አልነበረም ፣
- አመጣጣቸዉም ድንገት ሳይሆን መንታ ዕቅድ የበረበት ነበር ( መንግስትን በማፅናት ስም በኢጣሊያ ቦታ እንግሊዝን የመተካት) ፣
- እንግሊዝ ንጉስ ኃ/ስላሴ ለ፭ ዓመት እንግሊዝ አገር ይገኝ ከነበረ ደሴት ከቆዩበት በሱዳን በጎጃም ኦሜድላ (መተከል) በእንግሊዝ ወታደር ጠባቂ አዲስ አበባ ስትልክ ለክብራቸዉ ወይም ለኢትዮጵያ ነጻነት አለመሆኑ ድንገተኛ ነገር አልነበረም ፣
- ይህ ብቻ አይደለም እንደዛሬዉ ትናንትም ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የተስፋፊዎች የዕግር ዕሳት በመሆኑ በኢጣሊያ የአምስት ዓመት የነጻነት ተጋድሎ በጨካኙ የኢጣሊያ መንግስት እና ወታደር ህይወታቸዉን ከገበሩት 12 ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን በተጨማሪ በነጻነት ትግሉ ግንባር ቀደም የነጻነት መሪ እና አስተባባሪ የነበሩትን በእንግሊዝ ዳኝነት የኢትዮጵያ መንግስት ላደሩት የብሄራዊ ነጻነት ተጋድሎ ዋጋቸዉ የሞት ፍርድ ነበር( ለአብነት ፡ ደጃአዝማች በላይዘለቀ በግናባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ነበሩ ፣
- ወደ 19666 ዓ.ም. የመንግስት ለዉጥ ወቅት የዘመኑ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እንደዛሬዉ በስጋትም በመልካም አጋጣሚ አይተዉት እንደነበር በዘመኑ የነበሩ ሁነቶች ዕዉነተኛ ማሳያወች ነበሩ የሆነዉም ድንገተኛ አልነበረም ፣
- ይህን የ1960ዎች ለዉጥ በጥሩ አጋጣሚ ያዩት ዛሬም በዚያ ዘመን በነበር አስተሳሰብ ኢትዮጵያን ከከተማ አስከ ገጠር ለማመሰቃቀል የሰሩት እና እየሰሩ ያለዉ ደባ የዘመናት ዕቅድ እንጅ ድንገት አልነበረም ፣
- የዚህ ተዉልድ ሰሞነኝነት እና አድር ባይነት ባህሪ ከምንቸገረኝነት ጋር ተዳምሮ የዚያ ትዉልድ ቅሪቶች ዛሬም ኢትዮጵያን እና ህዝቧን በማፈራረስ በከርሰ መቃብራቸዉ የነርሱን እና የጌቶቻቸዉን ጥቅም ከማስከበር ወደ ኋላ አይሉም ለዚህ ነዉ አዲስም ሆነ ድንገተኛ የለም የምንለዉ ፣
- ኢትዮጵያን ከ 18ኛዉ ክ/ዘመን አስከ 19ኛ ክ/ዘመን አጋማሽ(1967 ዓ.ም) ለማፈረስ ያልተሳካለቸዉ የዘመናት ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች በህዝብ መስዋዕትነት የተገኘዉን የ 1983 ዓ.ም. የመንግስት ለዉጥ እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመዉ የሽ ዘመናት የዕድሜ ባለፀጋ አገር እና ህዝብ የአንድ ክ/ዘመን መስጠት ለዛሬ ሁነት መሰረት ለመጣል እንጅ አገር የማፍረሱ የእኛ ዘመን የጠላት ትንቅንቅ ድንገተኛ አለመሆኑን ምልክት ነዉ ፣
- የኢትዮጵያን አንድነት እና የዜጎችን በአገራቸዉ ምድር የመኖር ተፈጥሯዊ እና ሠባዊ መብት የገፈፈዉ ህገ መንግስት እና ያልተማከለ የአገር አስተዳደር በዜጎች እና በአገር ሉዓላዊነት ላይ ያስከተለዉ እና እያስከተለ ያለዉ የዘመናት ሰቆቃ ድንገት ሳይሆን ቀድሞ የተዘራ ዕንክርዳድ ፍሬ ዉጤት ነዉ፣
- ከዘመነ ፍዳ (1983.ዓ.ም አስከ አሁን) ጀምሮ አስከ ዚህች ዕለት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የሆነዉ ሁሉ ምንጩ የሴራ ስምምነት እንጅ ድንገተኛ አልነበረም ፣
- በህዝብ ከፍተኛ መስዋዕትነት መጋቤት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የተገኘ ህዝባዊ ድል ዋጋ እንዲያጣ ሲሆን ከክፋት እና ከጥፋት መንፈስ የሚመነጭ እንጅ ድንገት አይሆንም /አይደለም፣
- በተለያየ ጊዜ ፣ቦታ እና ሁኔታ ዕንቁ እና ንቁ የቁርጥ ቀን ልጆች ለህዝብ እና አገር የከፈሉት የህይወት መስዋዕትነት በእጅጉ በጥዋት በተገመደ የሤራ ገመድ ጠለፋ እንጅ ድንገተኛ አልነበረም ፤የለም ፣
- ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ አስካሁን በዕየለቱ በመላ አገሪቷ በተለይም በቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልል የሆነ እና እየሆነ ያለ ለዚህ ክ/ዘመን የማይመጥን የዜጎች ሞት እና ስደት ( የዉስጥ መፈናቀል) ድንገት ማለት ሠዉ አለመሆን ነዉ ፣
- የት.ህ.ነ.ግ. ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ መነዳት ድንገት ሳይሆን የዘመናት የጥላቻ እና የንቀት ቋጠሮ የሸከፈዉ ድብቅ የጠላት ሤራ እና ይህን ከዳር ለማድረስ አማራጭ መንገድ እንጅ በድንገት አልነበረም ፣
- በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በትግራይ እና ማዕከላዊ መንግስት የተከሰተዉ ግጭት ለዓመታት የተገመደ ወጥመድ እንጅ ድንገተኛ አልነበረም ፣
- ይህን ተከትሎ የደረሰዉ ሠባዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ሆነ ሁለንተናዊ ብሄራዊ ድቀት ድንገት ብሎ መዘናጋት ድክመት ነዉ ፣
- ይህን ከፍተኛ እና የረጅም ዘመናት ብሄራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት አደጋ በጊዜዉ ህግ የማስከበር ማለት መጣኝ ስያሜ ባይባልም በድንገት የተሰጠ ስያሜ አልነበረም ፣
- ለድርጊቱ ተዋንያን እና ፊዉታራሪም “ጁንታ”ማለት ዕዉነተኛ እና መጣኝ ስያሜ ባይሆንም የድንገት ሳይሆን እንዳያማህ ጥራዉ እንዳይበላ ግፋዉ ነዉ ፣
- የአገር ደህንነት ፣ ኢኮኖሚ እና ታላቅ ሠባዊ ችግር ያረገዘን ሴራ ጁንታ ማለት ንፍገት ወይም ሰሞነኝነት ሊያሰኝ ይችላል ምክነያቱም የቆየ ምግበሩ እና ተግባሩ ሲታወቅ መለባበስ የዚህችን አገር ችግር እና መከራ ከማራዘም ዉጭ ያልተገለጠ ችግር በቀላሉ አይፈታም ፣
- በ 100% የሕግ ማስከበርም ሆነ የጠላት ዓመድ መሆን ሲነገረን ድንገተኛ ሳይሆን መባል ስለመበረበት እንጅ ድንገት አለመሆን ይኸዉ ዛሬም በነበር መነባበር ሆኗል ፣
- የት.ህ. ነ.ግ.አመራር እና ተከታዩ መቀሌ እንዲገቡ ሆኖ መለቀቅ የሚጠበቅ እና ቀጣይ መሰል ጉዳዮች ስለመሆናቸዉ አመላካች ስለነበር ተጠባቂ እንጅ ድንገተኛ አልነበረም ፣
- የጠላት የዘመናት ኢትዮጵያ ጥንካሬ ምንጭ የሚለዉን ህዘበ ኢትዮጵያ ማዳከም ፤መበቀል ዕቅድ ወደ ጎረቤት ( ጎንደር፣ ወሎ….) ማስቀጠል ስለነበር ድንገተኛ አይደለም፣
- በሁለቱ አዋሳኝ ክ/ ሀገራት የተደረገዉ የልቀቁልን ድንፋታ የቅዥ ግዛት አባዜ ቁራኞች (ምዕራባዉያን) ጉዳይ ኢትዮጵያን የራሷን ተፈጥሯዊ ባለቤትነት ከቀይ ባህር ቀጥሎ የዓባይን እና የየብስ ወሰን በር እና የመልማት አቅም በማሳጣት የዘላለም ጥገኛ ማድረግ ነዉ ፡፡
እናም ኢትዮጵያዊ የሆንክ ሁሉ ከረጅም ዘመን አስከ አሁን ፣ ከትንሽ የጥፋት ተልዕኮ አስከ ከፍተኛ ፣ ከቅርብ የጠላት ወዳጅ አስከ ሩቅ ታሪካዊ ጠላቶች የሚናገሩትን ትተህ ከዚህ በፊት የሠሩትን መሰሪ አፍራሽ ተግባር ከነቅድመ ታሪክ በመረዳት ንቃት ፣ ህብረት፣ መረዳዳት እና አብሮነት ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዘላለማዊ ነጻነት መቆም ያስፈልጋል፡፡
ምንም ዓይነት በአገር እና ህዝብ ላይ የሚደርስ ችግር እና መከራ በጠላት በዕቅድ እና በሴራ የሚከናወን መሆኑን በመገንዘብ የአንድነት እና ህብረት መቆም በጦርነት ጊዜ ሳይሆን በሠላም ጊዜ የሚደረግ የክፉ ቀን ዝግጅት እና አንድነት በማይነቃነቅ መሰረት ላይ መገንባት ይጠበቅብናል ፡፡
ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቅንጠሳ በአገር እና ህዝብ ህልዉና እንደመቀለድ ስለሚቆጠር ማንኛዉም የሚመለከተዉ ሁሉ በኢትዮጵያ የግዛት አስተዳደር እና የዉኃ የተፈጥሮ ሀብት ላይ የተጠመደዉን የጥፋት ወጥመድ ለመበጣጠስ በጋራ የምንቆምበት ዛሬ ነዉ ፡፡
“አጥፍቶ ጠፊ ጠላቶቻችን እኛን እና አገራችንን በራሳችን አገር እና ተፈትሯዊ ፀጋ በጠላትነት ፈርጀዉ ሊያጠፉን ሌት ተቀን ዕንቅልፍ ባጡበት የዕኛ መዘናጋት እና ማንቀላፋት መቆም አለበት ፡፡ ” መከራ እና ችግርን በማሳነስ ሆነ በማድበስበስ ከጥፋት እና ሞት ስለማያድን ከምግባር አስከ ግብር ዕዉነተኛዉ ነገር በጊዜዉ ሊነገር እና ህዝብም ሆነ የሚመለከተዉ ሊያዉቅ ይገባል ፡፡
“ዕራሱን ያዳነ ዓለሙን ያድናል” እንዲሉ ለራሳችን ከእኛ በላይ ለእኛ የሚሆን አይኖርም እና ከሰሞነኛ እና ድንገተኛ አስተሳሰብ እና ድርጊት በመዉጣት ዞትር ዝግጁ እና ለሚመጣ ሁሉ በቂ ምላሽ ይዘን መገኘት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ነዉ ፡፡
“እናስተዉል አንሁን ልል !!”
ማላጂ
“አንድነት ኃይል ነዉ” !