July 4, 2021
17 mins read

የራያና ወልቃይት ጉዳይ የአማራ ብቸኛ ጉዳይ አይደለም – ከአባዊርቱ

መንደርደርያ!
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከተጨፈጨፈ ማንነቱ፣ ከተደፈጠጠ መሬቱ፣  ከተዘረፈ ማንኛውም ወገናችን ጋር መቆም ይኖርበታል:: በወልቃይት ከጫፍ እስከ ጫፍ
ባለፈው 30 አመታት ያልታየ ንፁህ የኢትዮጵያ ባንዲራ ደምቆ ተውለብልቧል:: ወልቃይት በኢትዮጵያዊነቱ ከዬቱም የኢትዮጵያ  ህዝብ አይለይም::
ማይካድራ ላይ ከ1000 በላይ ሰላማዊ ሰዋች በህውሀት ካድሬዎች ተጨፍጭፈዋል:: ይህ በምንም መንገድ መደገም የሌለበት ክስተት ነው:: አሜሪካም ሆነ ምእራባውያን የሚዘወሩት ለ 25 አመታት ጭንቅላታቸው እስኪፈነዳ እንደ ድንጋይ ወፍጮ በወቀራቸው መለስ ዜናዊ የፅልመት ተጠሪ በነ ሱዛን ራይስ ነው። እነ ሱዚ ደግሞ አማራና ትግሬውን እንኩዋንስ ልትለይ ቀርቶ ምእራብና ምስራቁንም ከተጋተችው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በቀር ምኑንም አታውቀውም።
Ethiopia
በውሸት የተሞላ ፈረንጅ  ከፅልመት እኩል ዘምቶብናል!
ዌስቴርን ትግራይ፣ ሳውዘርን ትግራይ እያለ የሚያደነዝዘን የፈረንጅ ውርንጭላ ሁላ ትግራይ በታሪክ ምስራቅና ምእራብ የሌላት፣  ደቡብ ና ሰሜን ትግራይ ብሎ ያልተፈጠረባት ምድር ናት።  የሰው ቦታ እየቀሙ አዲስ የፈረንጅ ዳቦ ስም ቢሰጡ ሀቅን አይለውጥም:: ከተከዜ ወዲህ ማዶ ወልቃይት ነው:: ከዚያ ማዶ የትግሬ ሀገር ነው:: ይህ የታሪክ ተመራማሪዎችን ስራ አይፈልግም:: አብዛኛው መስካሪ  ህዝብ በህይወት አለን:: ከ1992 በፊት  ወልቃይትና አርማጨሆና መላው ጎንደር የቤገምድርና ሰሜን ክፍለ ሀገር ነበር:: ራያም የ ወሎ ክፍለ ሀገር ነበር:: ለምንድነው የተከበሩ ልኡል ራስ መንገሻ ስዩምን በህዝብ ፊት እንዲመሰክሩ የማይደረጉት ህይወታቸው ሳታልፍ? ወይስ ከ ከአርባ አመታት በሁዋላ ፅልመት የፈለፈላቸው እራሱን አያውቅ የወያኔ ትውልድ አይምሮ ከኒህ ራስ መንገሻ በላይ ትግሬ ሆኖ ሚዛን ሊደፋ ነው?? ዳሩ አባይ ከሚለማ ሲናይ በረሃ ትልማ የሚል ሽል የሆነ ትውልድ ፈጠረችና ትግራይ ግራ አጋባችን እንጅ የጥንቶቹስ ባለ ገድል ነበሩ።
የዛሬዎቹ ምእራባውያንም እንደ አባቶቻቸው አፍሪካውያንን በመከፋፍል የማጨራረስ አስከፊ ታሪካቸው ዛሬም ተክትሏቸዋል:: አሁን ማን ይሙት አሜሪካ ለትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቿ የበለጠ ቀርበዋቸው ነው? ህውሀት ተላላኪ ድርጅት ነበር:: እንደፈለጉት ብር እያሳዩ የሚያዙት ታዛዥ:: ዐቢይ ለዚህ አስነዋሪ ቅልውጥ አልተመቻቸውም:: እንደውም  የአፍሪካን በራስ ጥረት ከፍ  ማደግን በሰፊው ያወራል:: ይህ ደግሞ እያደር ውስጥና ውጫቸውን እያደበነና  እያሳበዳቸው ይገኛል። እንግዲህ ይልመዱት። የቅድመአያቶቹ ልጅ ነውና የተከሰተባቸው።
ሌላው ህውሀት እንደትናንቱ  ወልቃይትን የሚፍልገው የራሱ አካል መሆኑን አምኖበት ሳይሆን ወልቃይትን ከያዘ በሱዳን መተንፈሻ ኦክሲጂን አገኛለሁ ከሚል ስሌት ነው :: ከዚያም እንደተለመደው ባንዳነቱ ስለማይለቀው በዛች መተንፈሻ ቀዳዳ ከኢትዮጵያ ውጪ ጠላቶች ጋር በመመሳጠር  መሳሪያና የማንኛውም ሀገር መበተኛ ጦር ያስገባበታል:: ህውሀት ሲፈጠር እኔ ካልበላሁት ጭሬ ይበተን እንዳለችው ስግብግብ ዶሮ  ኢትዮጵያን ገዝቶ ለመዝረፍ የሚበቃው ወልቃይትን ዳግም በመውረር ብቻ ነው:: ስለሆነም ኢትዮጵያ ያለ የሌለ ሀይሏን ተጠቅማ ህውሀት በወልቃይት ምድር ዳግም እንዳያንሰራራ አጥብቃ መከላከል ይኖርባታል::  ለዚህም ነው ወልቃይትና ራያ የአማራ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ዋናው ጉዳይ ነው የምንለው::
ውድ ኢትዮጵያውያን!
የህወሀት ጉዳይ ጠላትነቱ ለይቶለት አሁን ላለንበት ደረጃ ደርሰናል። አሁን እንዲለይለት የሚጠበቀው እያንዳንዱ ትግሬ ነኝ ባይ ወገን ነው። ምድረ ባይቶኔ ነሽ አረና ማናችሁም የትግራዋይ ፓርቲ አባላት ሚናችሁን ለዩ። ካሁን በሁዋላ በሁለት ቢላ መብላት አይኖርም ። ተስፋ ሰንቃችሁ የነበራችሁ የአረና ማፈርያ ልጆች ጭምብላችሁ ተጋልጧልና እርማችሁን አውጡ። ምኞታችሁ የወልቃይትና  ራያን መሬት እያረስን እንበላለን ከሆነ የምትላተሙት ከ 99% የኢትዮጵያ ህዝብ መሆኑን አትዘንጉት። እንተላለቃታለን እንጅ የህወሀት ሳይሆን የህወሀትን ጠረን ያሸተተ ትውልድ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ መንበረ ስልጣን አይመጣም። የዶር አቢይ ሰራዊታችንን ከትግራይ ማውጣት እጅግ ብልሀተኛነቱን ያሳያል። እኔ እንኳ ባለፈው በወታደራዊ አገዛዝ በተናጥል ተመኝቼላቸው ነበር። የዶር አቢይ ውሳኔ በጣም አስደምሞኛል። ለምንስ ምስጋና ለሌለው ህዝብ ስሙኒስ ይወጣል እንኩዋንስ መቶ ቢሊዮን። እየገፋችሁ ለዚህ አድርሳችሁናልና ደስ ይበላችሁ። እንግዲህ ቻሉት ረሀቡን። እስቲ ሱዳን ትሁን አሜሪካ፣ ወይም ግብፅ ትሁን በራሳችን ገንዘብ የገዛችሁዋቸው ቅጥረኞቻችሁ ቀለብ በየቀኑ ሲሰፍሩላችሁ እናየዋለን። እንደው የገደላችሁት ፣ የፈጃችሁት አነሰና የኢትዮጵያን መከላከያ ፣  እያረሰና እየጎለጎለ ለ ብዙ አስርተ አመታት ያበላችሁን መከላከያ ምርኮኛ ብላችሁ ፣ ቀጣጥላችሁ ማፌዣ አድርጋችሁ ሰልፍ አወጣችሁ?? ሳይቸግራችሁ የባሰ ወጥመድ ትገቡ እናንት የፅልመት ውላጆች?
ምን እናድርግ?
ከዶር አቢይ ልጀምር መቼስ ተዳፈርክ አይበሉኝና
ክቡር ዶር አቢይ ሆይ!
፩) እያንዳንዱ የብልፅግና ጓዳ ይፈትሹልን።  እያንዳንዱዋን የወያኔ እምባ አድራቂ ሆነ የ አክራሪ ምርኮኛ ለቅመው አሰናብቱልንና በአዲስ ጉልበት እንራመድ። በቃን የጅብና ተኩላ መንጋ  መጫወቻነቱ። አሜሪካኖቹ የንቀታቸው ብዛት ክቡር  አምባሳደር ታዬን (በ ተመድ የኢትዮጵያን ተጠሪ) ንግግራቸውን እንኳ ሳያስጨርሱ ጥያቄ አይሉት ንትርክ ሲጀምሩ አይቼ ልቤ ቆስሏል። እነዚህ  ጅቦች አገሬን አስንቀዋል። እንዲህ አይነት ንቀት በድሮው ዘመን አይታሰብም ነበር። እንኩዋንስ የኢትዮጵያዊን ንግግር ሊያቋርጡ ቀርቶ ከመቀመጫ ተነስተው ነበር የሚያስተናገዱት። እውነት ነው። ስለሆነም ክቡር ጠሚር አቢይ ሙሉ ማንዴቱን በይፋ ይቀበላሉ ብዬም ስለምገምት አደራ ምድረ ካድሬ ሹመኛን አሰናብተው በቴክኖክራቶች ይሙሉልን። የሚያስቡት የተሳለጠ የኢትዮጵያ ብልፅግና እውነት የሚሆነውም እንደዛ ሲሆን ነው። እነዚህ የፅልመት ውላጆች መከላከያውን የበሉት አንሶ ማወራረጃ  አድርገዋልና የራያና ወልቃይትን አጥር በብረት ይቆልፉልን። አዲስ የሀገር አድን ምልመላ በይፋ መጀመር አለበት። ከ ትግራይ በቀር ከሁሉም ክፍላተሀገራት ከባድ ምልመላ መጀመር አለበት። ልዩ ሀይላትን ከመከላከያ ማዋቀር በአስቸኳይ መጀመር አለበት።
 ሌላው በአንዳንድ ተቃዋሚዎች  የሚሰማው ጉምጉምታ ፈረንጆቹ ፊት ወግ ያለው ፌዴራሌ ለመምሰልንና ከንስቲትየንሲ ያላቸው ለማስመሰል በመከራም ጊዜ የራሳቸውን ኢጎና ኢንተረሰት ለመጠበቅ የሚያደርጉት ትንቅንቅ መሆኑ አይጠፋዎትም። ከጀርባቸው የተሰለፈ ምንም አለመኖሩን ያውቁታል – መልእክቱ በተለየ ለአሜሪካኖቹ ነው። ኢትዮጵያ እንዲህ በውስጥም በውጭም ጠላቶች እየተፈተነች የነሱ የወረደ አካሄድ ያስተዛዝባል።
በመጨረሻም አየርመንገዳችን ትርፋማነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የአገር ምሶሶነቱን ከግምት በማስገባት ብዙ እንደቻሉ ይረዳኛል። በዚህ ጉዳይ ብቻዎን እንደሆኑ እሰጋለሁ። የጥንት ተገፍተው የወጡ አመራሮች ሻዶው አመራር ቢመሰርቱና ማን ምን እንደሚሰራ በርቀት ቢመካከሩ እንዴት እጅግ ጉዳዩን ያቀልሎታል ብዬ አስባለሁ። ያሉት ሰውዬ እስከ ትክል ጀሌዎቻቸው የመንቀያው ጊዜ የደረሰ ይመስለኛል በተለየ ሁኔታ ወዳጆቻቸው መቀሌ እየጨፈሩ እያየን። ቴድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ጣቢያ መሪ ሆኖ ያውም ውጭ እየኖረ ለነዚህ ወያኔዎች እንዲህ ልቡ የሚደማ ከሆነ እዚሁ ቅርብ ሸገር ሆኖ የነዚህ ከሀድያን አባሪና ተባባሪ መአት መሆኑን ልቤ ይነግረኛል። የሁሉም ጓዳ ሊፈተሽ ግድ ይላል በተለየ ሁኔታ ደግሞ ቁልፍ የኢኮኖሚ፣ ጤናና ትራንስፖርት አውታሮች። ይህው ነው።
ለኢትዮጵያዊ አገር ወዳዶች በሙሉ!
ወያኔ ቀለቡን የተማመነው ከራያና ወልቃይት እንዲሁም ከውጭ ምፅዋት ስለሆነ፣ የሚያገባን የውጭው ሳይሆን የውስጣችን ስለሆነ  ወያኔ  በኢትዮጵያ መርገጫ ምድር እንዳታገኝ ወገን ወጥረህ ያዝ። ስለሆነም  ምን እናድርግ?
፩) እያንዳንዱ አገር ወዳድ መከላከያን ስፖንሰር ያድርግ። የተቻለውን በጥሬ ገንዘብም ይሁን በማቴርያል ሆነ ሞራል መደገፍ።
፪) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ፈንድ ወሬው የለም። የሚመለከተው ያስብበት
፫)  ወጣቱ መከላከያን መቀላቀል የግድ ነው። ለዚህም ከፍ ያለ ቅስቀሳ በየጫት ቤቱ ሁሉ ሳይቀር መለፈፍ አለበት። ከባድ ስራ ነው ግን መጀመር አለበት።
፬) እያንዳንዱ አገር ወዳድ ምድረ የአገር ነቀርሳ የሆኑትን የወያኔ ቅጥረኞችና ምርኮኛ አክቲቪስቶች ይሁኑ የዩቱብ ጡርተኞችን ገብያ በአድማ መዝጋት ወይም እንዲዘጉ መተባበር።
፭) የትዊተር ዘመቻን ሆን ብለን ስራዬ ብለን መያዝ። ምድረ ሜርስነሪ ፈረንጅ የኢትዮጵያን ስም ሲያጠፋ ተረባርቦ እርቃን  ወዲያው ማስቀረት።
፮) የሱዛን ራይስ አንጋች የሆነችውን የአሜሪካ ተጠሪ ጥቁሯን ሴትዮ በትዊተርና ሜል ማጨናነቅ. ይቺ ውታፍ ምን እንደምታወራ እንኩዋ አታውቅም። እነ ሱዛን የከተቡላትን ኖት ነው የምትደጋግመው እንደ በቀቀን።
፯) አገር ወዳድ ዳያስፖራ ፕሮፌሽናሎች በግልፅ ፖነል ዲስከሺን እየከፈታችሁ መልካሙን ጠቁሙ። እባካችሁ እነ ሲሳይ አጌናና መሳይ ታማኝ በየነን ወደ ኢሳት እንዲመለስ ተማፀኑት። ታማኝ ቢቀላቀላችሁ ከባድ ጉልበት ይሆናችሁ ነበርና ስለ ኢትዮጵያ ብላችሁ አስቡበት አደራ።
፰) የኢትዮጵያ ሀቀኛ ተቃዋሚዎች ማ እንዳሸነፈ ከለያችሁ በሁዋላ የማያወላውል የአቋም ድጋፍ መግለጫ ለመሪው መንግስት ማሳየት። ስትናደዱ አላይም። በወያኔ ጉዳይ መከላከያው የሚከፍለው ዋጋ ሊያንገበግባችሁ ግድ ይላልና ተናገሩለት እንጅ ። ምን እስክንሆን ነው የሚጠበቀው? በውስጥም በውጭም እንደ ሀገር ተዋርደን በነዚህ ፅልመቶች ጦስ እንደምንስ እንቅልፍ ይወስዳል? እስከመቼስ እንዋረድ?
፱) በአሜሪካ የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወገን ሳይታሰብ የሚድተርም ጊዜ ስለሚደርስ በያንዳንዷ ስቴት የሚኖር ባይደን ሆነ ከነሱዛን ጋር የወጉንን ዴሞክራት ተብዬ እንዲሸነፉ ዝግጅቱን ማጧጧፍ። ወገን በጭራሽ መርሳት የለበትም። ይህ እንደ ርስት ሁሌ ዴሞክራቶችን መረጣ መቆም አለበት።   ወገን የቮቲንግ ጉልበቱን መጠቀም አለበት።
አመሰግናለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop