May 22, 2021
12 mins read

ፓርቲ፤ መንግስትና ሀገርን መለየት ያስፈልጋል – አብራሃም ለቤዛ

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወጣት ማሀበር ፅ/ቤት  ግቢ በብልፅግና ማስታወቂያ ደምቆለል፡፡ እኔም ዛሬ እንኳን ብዝሃ -ፓርቲ ስርዓት ለመገንባት  በምንተፋተፍበት  ሰዓት ፤ በምርጫ ዋዜማ  የመንግስት ተቋማት ፤የከተማውን ወጣት የሚወክል መስሪያ ቤት በብልፅግና ማስታወቂያ ማሸብረቁ ግርምት ፈጥሮብኛል፡፡ ገዢ ፓርቲ መሆን ማለት ከጠቅላይነት  አባዜ መቼ ነው የምንላቀቀው ስል ለራሴ የማልመልሰው ጥያቄ  መለስሁ፡፡  ኢህአዴግ በገጠር  ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ፤ የእርዳታ እህል ሳይቀር የሚሰተው ለአባላቱና ለደጋፊዋቹ  ነው፤ ማይክሮ ፋይናንስ ጠቋማት በከተማ የሚደራጁት ደጋፊያቸውንና አባላቸውን ነው እያልን ክፉኛ ወቀስነው፡፡   ኢህአዴግ አውራ ፓርቲ ሆኖ አብጦ ያካሄዳቸው አምስት ምርጫዋች በሙሉ  (ከምርጫ 1997 ዓ/ም ውጭ) ምርጫ ሳሆኑ ኢህአዴግ  ለይስሙላ የሚያካሄዳቸው ፤ ዳኛውን የምርጫ ቦርድ  በቁጥጥር ስሩ አውሎ ወደ ምርጫ ውድድር የሚገባበት የይስሙላ ምርጫዋች እንደነበሩ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡

 

ዛሬ ኢህአዴግን  በህዝባዊ አመፅ ሸኝተን ከኢህአዴግ  ታድሰን ወደ ብልፅግና ፓርቲ  አድገናል፡፡ የአጋረችን የኢትዮጵያን ትንሳኤ  ለማብሰር በኢትዮጵያዊያን ህዝብ ድምፅ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ እንተክላለን ብሎ ቆርጦ የተነሳው ብልፅግና ፓርቲ ግን በአደባባይ እየሰራ ያለው  ከኢህአዴጋዊ አውራ ፓርቲ  እንቅስቃሴ ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡   ኢህአዴጋዊ አውራ ፓርቲ  በመሪው ግለሰብ ተክለሰውነት ግንባታ ተጠምደው ፤ ተከታይ አመራር ማፍራት ተስኖቸው ፤ መሪው በሞተ ማግስት ተከታይ  (ተደማጭ አመራር ) ማፍራት ተስኖቸው በመጨረሻ የአቶ ሃይለማርያምን  “ስልጣን በቃኝ  “  ውሳኔ አስከትሎል፡፡  የብልፅግና ፓርቲ  ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህድ  ከኢህዴግ ልምድ ባልተለየ  ፓርቲውና አብይ አህመድ እንዲቆራኙ ፤ አብይ አህመድ ከሌለ ብልፅግና የለም እስከሚመስል ድረስ እየተሰራበት ነው፡፡ የብልፅግናን የምርጫ ቅስቀሳ ቢልቦረርዶች መመልከት በራሱ  ለዚህ ድምዳሜ ማስረጃ ይሆናል፡፡ በኢዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎች የተተከከሉ ቢልቦርዶች  “በዶክተር አብይ ጥላ ስር የተሰበሰብን  ችግኝ እጩዎች ነን ምረጡን” የሚል  መልዕክት ይዘዋል፡፡

አውራ ፓርቲ  እያበጠ እያበጠ  ሄዶ አምባገንን  እየሆነ የመሄድ እድሉ የሰፋ ነው ፡፡ በአገራችን በየጊዜው እየፈነዳ ያለው የሰላም መደፍረስ እና  የአካባቢያችን  ጂኦ-ፖለቲካ  ግጭት  በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉት  የምርጫ ፉክክሩ  ላይ   የራሱን ጥላ አጥልቶበታል፡፡  ምርጫ  ቦርድ ያወጣው የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ተስፋ ሰጭ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን መጭወን ምርጫ የሚያካሄድበት ድባብ በራሱ ነፃ ምርጫ ላይ ተፅኖ አለው፡፡ ዶክተር አብይ አብይ አህመድ  ስለ ህገ-መንግስታዊ  ለውጥ ሲጠየቁ ብልፅግና ህገ-መንግስታዊ  ማሸሻያ ለማድረግ በዴሞክራሴያዊ ምርጫ  ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ቃል -ኪዳን ማሰር አለበት  (መመረጥ) ያሉት  ቃል በብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች እና የመንግስት መዋቅር በያዙት  እኩል የሚደገፍ ሃሳብ ከሆነ  የምርጫ ሂደቱ የመበለጠ አሳታፊ፤ ታማኝና ዴሞክራሲያዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በተጨባጭ  በሀገራችን ፓርቲ (ገዢ ፓርቲ) ፤ መንግስትና ሀገር የሚለው የተቀላቀለ ሃሳብ መሆኑን ተረድተው የምርጫ ቅስቀሳቸውንም ከዚህ አረዳድ መቅረጽ ይኖርባቸዋል፡፡  ገዢው ፓርቲ አባላቱንና ደጋፊዎቹን የሚያሰባስበው የመንግስትን መዋቅር በመጠቀም የሀገርን ሃብት ኢ-ፍታሃዊ በሆነ መንገድ በማከፋፈል ነው፡፡  የአዲስ አበባን የቤት ችግር ለመቅረፍ የተጀመረው ፕሮጄክት በአዲስ አበባ  ለገዢው ፓርቲ  አባላት በማከፋፈል መጠናቀቁን ጥናታዊ ሪፖርቶች አማክተዋል፡፡ በተቃራኒው  ተወዳዳሪ ፓረቲዎች አባላትና ደጋፊዎቻቸው ፓርቲያቸውን ለማደራጀትም ሆነ ለምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን የሀብት ምንጭ የሚሆን ሃብት  ማዋጣት አለባቸው፡፡ ገዢው ፓርቲ  በፓርቲ አይዲዮሎጂ ያሰባሰባቸው አባላትና ደጋፊዎች እንዳሉት ሁሉ ፤ ተወዳዳሪ ፓረቲዎችም   ውስጥ የፖለቲካ ተሳትፎን ለጠባብ የግል ፍላጎት መጠቀሚያ ለማድረግ የሚሳተፉ አይጠፉም፡፡ኢህአዴግን  ገገማ የሆኑ አባላቶቹ አስወግዶ ታክቲካል ለውጥ አድርጎ ብልፅግና በሚል የዳቦ ስም እያጠቃ ያለ ገዢ  ፓርቲ  ነው፡፡  ብልፅግና ከኢህአዴግ በባሰ መንገድ እራሱን  የኢትዮጵያ አዳኝ አድርጎ እየሳላ ያለ ፓርቲ ስለሆነ  አባላቱና ደጋፊዎቹ   ይኸንን   እምነታቸውን ለማስፈፀም የበለጠ  ኢ-ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የመንግስትን መዋቅርና የሀገር ሃብት ለፓርቲያቸው እየጠቀሙ ይገኛሉ፡፡  ይኸነን ሁኔታ ለመለወጥ የብልፅግና ደጋፊዎችን  ማማለል እራሱን የቻለ የትግል ስልት ሆኖ መወሰድ አለበት፡፡

ተወዳዳሪ ፓርቲዎች የሀገር ውስጥ ደህንነት፤ የከተማ ልማት ፤ የትምህርት ልማት ፤የኢንዱስትሪ ልማት፤ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ  አማራጫቸውን ሲያቀርቡ በገዢው ፓርቲ ጥላ ስር ተጠልለው ፤ የፓርቲው መዋቅር ከገዢ ፓርቲነት ከተነጠለ የእነሱም ሕይወት ከአስትንፋሱ እንደሚነጠል ለሚያስቡ  በስም ብልፅግናዋች በተግባር ግን መዥገሮች ለሆኑ አባላትና ደጋፊዎች ማስተማመኛ መስጠት አለባቸው፡፡ ለእነዚህ መዥገሮች የሚሰጣቸው ማስተማመኛ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች አለን የሚሉት ደጋፊም ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡  ጥቅም ፍለጋ የመጣ  ደጋፊ ያሰባሰቡ ፤ በተራችን “መንግስት ከሆን” ፤ ስልጣን ከአገኘን  ብለው የተሰባሰቡ ካሉም ይበተናሉ፡፡

ለመዢገር ብልፅግናዎች የሚሰጣቸው ማስተማመኛ እንደሚከተለው ሊቀርብ ይችላል፡፡

  • የእኛ ፓርቲ  የህዝብ ድምፅ ቢያገኝና መንግስት ቢመሰርት ፤ በፓርቲ አባልነት የተሰበሰበ የፓርቲ ጥማጥቅም  (ቤት፤ መኪና፤ ሌሎች) መንግስት ስንሆን  በምናቋቁመው አጣሪ ኮሜቴ ተለይቶ ቢያንስ ቤት የሌላቸው ብልፅግናዎች የመንግስት ቤትን እስካልበለፀጉ ድረስ አይነጠቁም፡፡
  • የፖሊስ፤ የደህንነትና የመከላከያ ተቋማትን ማፍረስ ማለት አገርን ማፍረስ ማለት ስለሆነ፤ እነዚህ ተቋማት ላይ ምንም እንኳን ያለን እምነታችን የተሞላ ባይሆንም  ፤እነዚህን ተቋማት እኛ ተወዳዳሪዎች እነዚህ ተቋማት የበለጠ ፕሮፌሽናል ኢትዮጵያዊ ተቋማት እንዲሆኑ እንሰራለን እንጂ የብልፅግና ወታደር ብለን የኢህዴግን ስህተት አንደግምም በማለት ማረጋጋት ያፈልጋል፡፡
  • የእኛ ፓርቲ ቢያሸንፍ የምንገነባው ዴሙክራሲያዊ ስርዓት ሀገር በቀል  ሆኖ ፤ ብዙሃን ራሳቸውን የሚሳስተዳድሩበት ፤ ህዳጣን መብት የሚከበርበት ይሆናል እጂ (Majority rule , minority right)  ፤ በሀረሪ ፤ በድሬዳዋ (50/50 እና 40/40/20  )፤ ቤኔሻንጉል፤ ሌሎች ክልሎችም የሚሰራበት የአፓርታይድ ስርዓት አይነት  ይወገዳል፡፡ ይኸን የሚሆነው ግን ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በሰከነ መንገድ ፤ከየአቅጣጫው ተሰብስበበውና፤ መክረው ዘክረው በሚያወጡት ህገመንግስታዊ ሰነድ ይሆል፡፡

እነዚህን ማስተማመኛዋች  ወይንም እውነታዎች ተወዳዳሪዎች ቢያፈነዶቸው አንድም  እንቅፋቶችን ለመቀነስ ብሎም ደጋፊን ለማሰባሰብ ይረዳሉ፤ ሁለትም ሃቀኛ ደጋፊዎችን ለማወቀቅና  የማይደግፉአቸውንምንም ለማወቅ ይረዳል፡፡  ገዢው ፓርቲ መንግስትና ሀገር እየቀላቀለ በሚጠቀምበት ሁኔታ እና  ውስጣዊና ውጫዊ ግጭቶች ብዙሃኑ ላይ “መንግስት አለ ፤መንግስት የለም፤ ተጠቃን” የሚል ጥያቄዋች በሚመላለሱበት ወቅት ለተወዳዳሪዎች ምርጫ ማካሄድ እጅግ ፈታኝ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop