በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም በጠላቶቿ ተቀስፍ በተያዘችበት ሰዓት ”ምርጫ” ለማካሄድ መሞክር ኃላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን ለተጨማሪ ችግር አገርንና ህዝብን ማጋለጥ ነው። መቼም ቢሆን አሁን ባለው የጎሳ ህግ–መንግስት እየተመራን ዲሞክራሲን አመጣለሁ ማለት ”ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” እንደመሄድ ይቆጠራል። ግን ገዥዎቻችን ”ምረጡን ” ካሉ ምን አማራጭ አለን፤ ከአገርም ከህዝብም የነሱ ስልጣን ይበልጣልና።
ወደ ተነሳውበት ጉዳይ ሳመራ፤
የምርጫ ቦርድ ለምን የአዲስ አበባ እና የድሬደዋን የምክር ቤት ምርጫ ፣ ከአገር አቀፋ በአንድ ሳምንት እንዳራዘመው የሰጠው ምክንያት ወይም ማብራሪያ የለም። እኛ ግን በእናንተው ቋንቋ ቁማሩን እንገራችሁ፤ በ’ርግጥ ምክንያቱ ከቁማርም ያያነስ፤ ዘርኝነት፣ ተረኝነት፣ ዓይን ዓውጣነት፣ ማን አለብኝነት፣ ድንቁርና፣ ህዝብ መናቅና አገርን የማፍረስ ሴራ ነው። ማን ነበር ፤
“በአገር–ኢትዮጵያ ቱጃርና ገዥ ለመሆን ከፈለክ ደደብና ደፋር ሁን:: “ያለው?
የኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግ የድንቁርና ቁማር የሚጀምረው ‘ልዩ ጥቅም‘ የምትለዋ ከህገ-አራዊት ተነጥላ ወጥታ ”የአዲስ አባባ ባለቤት እኛ ብቻ ነን” ወደ እሚል የግብዝነት የተረኝነት ፊሽካ ተነፋ። ህገ-አራዊቱ ”የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናዝሪት ናት።” የሚለውን እና እስከ 1997 ድረስ ሲተገብሩት የነበረውን ዘነጉት። በዚህም ቁማሩን በላን አሉ።
ቀጣዩ ህገ-አራዊቱ እንኳን የማይፈቅደውን በህግ-ወጥ መንገድ በአዲስ አበባ ላይ ህገ-ወጥ ከንቲባ ተጫነባት። ተግባሩም
1/ የከተማዋን ዲሞግራፊ መቀየር::
2/ በተቻለ መጠን ከአዲስ አበባ ውጭ የኦሮሞ ጎሳ ለሆኑት መታወቂያ
ማደል::( እዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት ወያኔ የትግራይን ህዝብ እንደማይወክል ሁሉ ኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግናም የኦሮሞን ህዝብ አይወክልም። በስሙ ግን ይቆምሩበታል፤ ይህ እምነታችን የሁሉንም ጎሳ ድርጅቶችና ፓርቲዎችን የጨምራል።)
3/ የኮንድሚኒየም ቤት ለኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ማደል::
4/ ክፍት ቦታ ወይም ለመዘናኛ የተከለለን ቦታ ለኦነግ/ኦዴፓ ብልጽግና ማደል፣ መዝርፍና የከተማዋን ቅርሶች እያፈረሱ ለራሳቸው ደጋፊዋች በስማቼው ማዞር:;
5/ በመዲነዋ የሚገኙትን የመንግስት መስራ ቤቶችን በኦነግ/ ኦዴፓ ብልጽግና
ደጋፊዎችና አባሎች ማስያዝ::
6/ በየመስራቤቱ ኦሮሞኛ የማይናገሩትን የተለያየ ምክንያት በመፍጠር
ማባብረርና በራሳቸው ሰዎች መተካት::
7/ የመንግስት ግዥውችን ያለ ጨረታ ለኦነግ/ኦዴፓ ሰዎች መስጠት::
8/ የአዲስ አበባን ማንነትና ህብረ-ኢትዮጵያዊነት ለማጥፋት ለኦሮማማ
የጀግኖች ሃውልት፣ ፍርድቤት፣ የመሳሰሉትን በህዝብ ገንዘብ በቢሊዮን የሚቆጠር አውጥቶ መገንባት፣ የስራ ኮንትራቱኑ ኦነግ/ ኦዴፓዊያን ብቻ እንዲሰሩና እንዲቀጠሩ ማደረግ:;
በአጥቃላይ በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ያልተነገር እንጅ ያልተፈጸመ ወንጀል የለም። ታዲያ ይህ ሁሉ ግፍ ተፈጽሞ ወደ ምርጫ ቢሄዱ ምንም ድምጽ እንደማያገኙ ሲረዱ ፤ ተስፋ በተጣለበት በምርጫ ቦርድ በኩል መጡ፤ የቁማሩ ትዕይንት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳንም በላ ::
“…..ሰርቄ በልቼ ሳልታጠብ እጀን
አሁን ከምንግዜው ጩኽት ሞላው ደጀን::” አለ ዘፋኝ::
” የአዲስ አበባና የድሬደዋ ምርጫ ከዋና ምርጫ በአንድ ሳምንት ተራዝሟል’ ተባልን። ይህን የሚለን ብዙ የተነገረለት ገለልተኛ የተባለው የምርጫ ቦርድ ነው። እንግዲህ ”ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት” ማለት እዚህ ላይ ነው።
ለምርጫ ቦርድ በተለይም ለወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ማስተላለፍ የምንፈልገው ምርጫ በአንድ ሳምንት የተራዘመበት ”ቁማር’’፤
-1-
ኦነግ/ኦዴፓ ብልጽግና ከአዲስ እበባ ከተማ ውጭ ኗሪ ለሆኑ እስከ ናዝሪት ድረስ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኦሮሞ ጎሳዎች የአዲስ አበባን መታዎቂያ በገፍና በህገ–ወጥ መንገድ አድሏላ። መቼም ይኽን ለማሰትባበል ከመሞከር ” ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ማሳለፍ ይቀላል።” እንዚህ የአዲስ አበባ መታወቂያ የታደላቼው በአገርዊ ምርጫ ከመረጡ ከአንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ለኦነግ / ኦዴፓ ብልጽግና በመዲነዋ የመመርጫ ወረዳዎች ተገኝተው ግዳጃቼውን ይወጣሉ።
ታዲያ በዚህ ዓይነቱ ተራ ሸፍጥ ዜጋን ወይም አዲስ አበባን ህዝብ ለማታለል መሞከሩ ተረኛ ገዥዎቻችን ምን ያህል ከወያኔ ያነሱና የወረዱ መንደርተኞች መሆናቸውን ይመሰከራል። እንደ ጡት አባታቼው ኮረጆ ቢገለብጡ ይመረጥ ነበር። ይኽም ሆኖ የአዲስ አበባ ህዝብ ለታላቋን ኢትዮጵያ ቅድሚያ በመስጠት ትግሉን ያካሄዳል እንጅ እናነት እንደምትመኙት ብጥብጥ ውስጥ ገብቶ አገር አያፈርስም። የህዝቡን ማንነትና የቆመበትና ማማ ደግሞ የአደዋ 125ኛ የድል በዓል ሲከበር አሳይቷችኋል።
በ’ርግጥ አሁንም ቢሆን አዲስ አበባን ለአዲስ አበቤ ተውለት፤ ተረኝንተ የትም አያደርሳችሁም፤ ከትላንቱ ወያኔ ተማሩ እንላለን። አዲስ አበባ የሁላችንም መዲና ብቻ ሳትሆን የኢትዮጵያዊነት ማሰሪያ ውል ናት።
————————–//————–ፊልጶስ
E-mail: [email protected]