July 13, 2020
13 mins read

ፓለቲካው ይደር ለክብርት ሀገር – ምንድነው ዝምታው?  –  ከአባዊርቱ

ወቅቱ ኢትዮጵያን ማፍረስ ወይንም ማዳን ላይ ነው :: ዛሬ በስራ ላይ ያለው መንግስትን አጠናክሮ ሀገርን ማዳን ወይንም ቦርቡሮ  ለውጪ ጠላትና ለውስጥ ባንዳ ማስርከብ ትንቅንቅ ላይ ነው ያለነው። ግልጽና ግልጽ ነው።
የሀጫሉን ተቆርጦ የቀረውን በልብ ስብራት ሰማሁት። የዚህን ድንቅ፣ ቆራጥና ጀግና ልጅ ወኔ ከአወረጫጨቱ ጠያቂውን አጣሞ እስከ ማስቀመጥ ድረስ የዘለቀ ነበር። እንዲህ ነው ጀግና።  ፊትለፊት የሚናገር በጽኑ እምነት። በአንጻሩ ያንን የሳጥናኤል አለቃ ብርሀነ መስቀል ሰኚንም አየሁት – ከ ኮምፒውተር ጀርባ ሆኖ የጥፋት መርዙን ሲረጭ። የሁለቱን ፊት ገጽታዎች ለንጽጽር እያንዳንዱ ወገን ማየት አለበት። የጀግናና በጥራቃን ከሀዲ ትርጉም ዲክሽነሪ መፈለግ አይኖርበትምና።
ለተከበራችሁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች
ከዶር ኦባንግ እስከ ዶር ብርሀኑ፣ ከ ዶር አረጋዊ እስከ ዶር በየነ ጴጥሮስ ፣ የሀጫሉ እልፈትና የህዝቡ እልቂት የሚገዳችሁ ወገን የዖሮሞ ምሁራን በሙሉ እናም  በተለየ መንገድ ታማኝ የኢትዮጵያ ፓርቲ የክብር እንደራሴ ታማኝ በየነ (ባለህበት)
በኢትዮጵያ አምላክ የሆነ አስቸኳይ አገርና ወገን አድን ትብብር ፍጠሩና የሆነ ቢሮ ጠይቃችሁ እዚያው ጠ/ሚር መ/ቤት አካባቢ የምክክር ጊዜያው መ/ቤት አቋቁሙና ዶር አቢይን እርዱት። ታድያ ሁላችሁንም ተቃዋሚ ተብዬዎች  አይደለም  (ህውሀት የለየለት ጠላትን በብዙ ማይልስ ራቋቸው – ባለማፈር እኛሳ እንዳይሏችሁ ነው)። ምንድነው የሚጠበቀው ወገኖች? ፖለቲካውን እርግፍ አድርጋችሁ ተውት እስቲ ለ 6 ወራት ያህል።ለአገር ህልውና ላይ ብቻ ከጠ/ሚሩ እየተቀናጃችሁ ምከሩ። እስቲ አንድ ቀላል ምሳሌ ልስጥ። በጣም የምትወዷት እናታችሁ በጸና ታመዋል ልበል (አያድርስባችሁና)። እኒህ እናትን ለመታደግ በአካባቢያችሁ የመንግስት ክሊኒክ የለም አሉ። ቦታው ገጠር ነው ክሊኒክ የሌለው። ያለው አማራጭ የባህላዊ ሀኪም ነው፣ እሱ ደግሞ በ ሁለት መቶ ኪሜ ርቀት በቅሎና ፈረስ እንጅ መኪና የማይገባው ቦታ ላይ ነው። በርግጠኝነት ፈዋሽ ነው ሰውዬው። ይህንን እያወቃችሁ አይደለም በፈረስና በበቅሎ መሬቱን በእጅም ቢሆን እየቧጠጣችሁ የዳዴ ሄዳችሁ ያንን መድኃኒት አዋቂ ለእናታችሁ አምጥታችሁ ነፍሳቸውን ትታደጋላችሁ ወይስ በህመም ይሙቱ ትላላችሁ? ኢትዮጵያ እኮ ነች የታመመችው።በቃሬዛም ያለችው ወገኖች። እንዴት ዝም ይባላል? እንደምንስ ለመንግስት ብቻ ይተዋል? ምን እንርዳ፣ በሉ እንጅ ። ካደረጋችሁት እሰየው፣ ስላልሰማሁ ነው። ይህን ስል ደግሞ ከዚህ ቀደም የጥምረት መንግስት ብለው የጅቦች መንጋ እንደሚያሾፉት ሳይሆን በመንግስት ጥላ ስር ሆናችሁ የኢትዮጵያን ህልውና ማስጠበቅ ላይ ተባበሩ ማለቴ ነው። እናንተ እያላችሁ፣ በአለም ተበትነን ስንት ምሁራን፣ አዋቂዎች አገራችን አፍርታ እንደ ብርሀነመስቀል ሰኚ አይነት አውሬ በቴሌቪዥን ኡትዮጵያን የምታህል ክቡርና ድንቅ አገር በአደባባይ በግልጽ በቲቪ ሚስማር በትኑ፣ መንገዶችን ዝጉ፣ አገር ትቃጠል አይነት ትእዛዝ ይስጥብን? እንዴት አገራችንን ህዝባችንን ቢንቅ ነው? እኔ ከዚያ ወንዳታ ሀጫሉ  እልፈት ጭራሽ እሣት የለቀቀብኝ ይህ ነው። ሀጫሉስ የወንዶች ቁንጮ ፊትለፊት ናት። አይ ልጅ። እባካችሁ የተቆረጠውንና የወጣውን ቪዲዮ እዩት። ለዚህ ጀግና ለሚሰራለት ሀውልት ማሾፍም ተጀምሯል በዲጂታሎቹ። ሀውልት ቢያንሰውም በቲቪ የማንነቱን ሀውልት ትቶልን አልፏል – በቁም በጥላቻና ዝምታ ሀውልት ሆነን ለቀረነው ይብላኝልን እንጅ
ወገኖች!
ለየልን እኮ። አሁን ኡትዮጵያን ለማዳን ብሎም እያንዳንዳችንን ለማዳን ህብረታችንን የምናሳይበት ወቅት ላይ ነን። ምን መደረግ አለበት? እስቲ ለጊዜው የታየኝን እንዲህ ልበል፣
1) እያንዳንዱ የፓለቲካ መሪ ለተከታዮቹ መሪ ቃል መስጠት። የትብብርና አገር አድን ጥሪ ዘልቆ ይግባ
2) መዋቅሮቻችሁን ለመንግስት አቅጣጫ ማሳለጫ ማዋል
3) ኢንፎርሜሽን መቀባበል
4) ከየክልሉ ሀላፊዎች ትብብርን ማሳለጥ
5) ከዳያስፖራው በመቀናጀት ከሞት ተርፈው አሁንም አየር ላይ ተንሳፈው ላሉት ወገኖቻችን እርዳታ ማሰባሰብ። በአካልም እየሄዱ አይዟችሁ ማለት
6) ከዳያስፖራው የተለያዩ የህግና የሴኩሪቲ ተቋሞች ቅንጅትና ህብረት መፍጠር። እንደ አል ማርያም ያሉ ሳተናዎች እንደ አበበ ሰኚን አይነት ከሀዲዎች በህግ ፊት ገትሮ እርቃኑን ማቆም። ለካንስ ከስራ ስላባረሩት ነው ይህ ከሀዲ?
7) እያንዳንዱ ከውጭ “በሏቸው” ያሉትን ሁሉ በነፍስ እየተለቀሙ ፣ ወረቀት የሌለው ቦዘኔ ተጠርዞ ኢትዮጵያ እንዲላክ፣ የውጭ ዜጋ የሆነውን ደግሞ የብዙ ሺህ አመት አገራችንን ጣልቃ እንደገቡ ሰላቶዎች ተቆጥረው ፍርድቤት እንድትገትሯቸው በአለቁት ደሀ ወገኖቻችን ስም እለምናለሁ። አይደለም ስንት አገር በቀል ምሁራን በውጭ የተወለዱት ልጆቻችን እነዚህን ከሀዲዎች ፍርድቤት መገተር አያቅታቸውም። እንዴት ዝም ይባላል?
8) በቀደም በኢሳት ያየሁዋቸው የቀድሞ ሰራዊት አባላት ጋር  ቅንጅትና ምክክር አድርጉ
9) ግስላዋን አዲሲቱን አቃቤ ጄኔራል አዳነች አቤቤን በተለየ ሁኔታ የሚረዱ የጠበቆችና በኢንተርናሽናል ጀርስፕሩደንስ የተካኑ የህግ ጠበብቶችን ማሰባሰብና ማቀናጀት። ይህ ጉዳይ እነዛን የሰው ጅቦች ሁሉ ዘልቆ ለአለም ሸንጎ ለማቅረብም ጥርግያ መንገድ ይከፍታል። የአቢይን ትእግስት ከመጤፍም አልቆጠሩም። ጭራሽ አይናቸውን በጨው ታጥበው ይህ ሁሉ ሆኖ በእልቂቱም ማግስት ሊያስፈራሩን ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ እናንት የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ዝም ይባላል? የኢዜማ፣ የብልጽግና፣ የምንምን መርህ ሳይሆን የኢትዮጵያን በህብረት እናድን አርማን ከፍ አድርጋችሁ አስደምሙን እንጅ? ይህን ካላረጋችሁ እመኑኝ እንኳን ልትመረጡ በሚቀጥለው ምርጫ ከነ መፈጠራችሁም የሚያስታውሳችሁ ኡይኖርም። ለዚያውም አገር ከተረፈች ነው። እናም ይህ ለማሰብ ጊዜ የሚፈልግ አይደለም። JUST DO IT!!
ማጠቃለያ!
ከፖለቲካ ፖርቲዎች ባለፈ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ወገን ትብብሩን ከመንግስት ያሳልጥ። በየክልሉ ያላችሁም በተለይ ወጣቶች ሰከን በሉ። የመንግስትን መግለጫ ተከታተሉ። ዶር አቢይ ተገቢ የአገር አድን እርምጃ እየወሰደ ነው። ባሁን ጊዜ የሚወስደውን እርምጃ የሚቃወም ጥፋታችንን የሚሻ ነው። እርምጃ ስል ደግሞ ህጋዊና ተመጣጣኝና ተአማኒ ማለቴም ነው። በዶር አቢይ ይሁን በሺመልስ አብዲሣ ስም ሆነው፣ ስልጣንን መከታ አድርገው ውስጣቸው ተሰንገው ግፍ የሚፈጽሙትን ከሀዲዎች ፈልፍሎ የሚያወጣው ህዝቡ ነው። እነዛ ክፉዎች እንዳንተማመን በአደገኛ ሽቦ ተብትበውን ፈርጥጠው እንጅ እንዲህ መጫወቻና የፈረንጅ መዘባበቻ አንሆናትም ነበር። ኢትዮጵያ ስንት ጀግና እንዳላፈራች እንዲህ መሳለቅያ ሆንና አረፍነው። ከአፍሪካ ሀገራት አስቀድመን ህግና ስርአትን እንዳላስተማርን፣ የአፍሪካ ሀገራትን ወክለን ስለነጻነታቸው በአለም ሸንጎ ይሁን ሀያላንን ፊትለፊት በሙሉ ልብና ስብእና እንዳላስተማርን በምሁር ተብዬ የሰው ግሪሣ ስብእናችን ተናግቶ የፈረንጅና ፋና ወጊ ሆነን ለወግና ማእረግ የተዋሱንን አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ሳይቀሩ በትዝብትና አግራሞት ሲያዩን ልብ ያቆስላል፣ መፈጠርንም ያስጠላል።  እናም ወገኖች ይህ ጊዜ የማይሰጥ ስለሆነ ትብብራችን ነገ ተነገወድያ የማይል ነው።
ዶር አቢይ ብዙ ሊያጠፋ ይችላል ። አጥፍቷልም። ዶር አቢይ ኢትዮጵያ ማለትም አይደለም። አገራችሁን የምትወዱ በሙሉ ለአቢይ ብላችሁ ነው እንዴ?  አቢይን ለመውቀስ፣ ይህ ቢሆን ያ ቢሆን ለማለት የቅንጦት ጊዜ ላይ አይደለንም። ለነገሩ በአብዛኛው የሰውዬውን መከራ የሚያበዙት እነዛው ወፈፌዎቹ ወይም ጭምብሎቻቸው ናቸው። ሆኖም እስቲ አገራችንን እናድንና ስነስርአት ባለው መንገድ እንወቃቀሳለን። ይህ ጥቃት በኦሮሞ፣ አማራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የተቃጣ ነው።  ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ ኦሮሞ ሆነው በክርስቲያንነታቸው ብቻ የተጨፈጨፉትን?:: ዛሬ በእኔ እይታ ይህ ኢትዮጵያውያንን ገድሎ ለማገዳደል ረቆ በስራ ላይ የዋለው የዘራፊው ወያኔ እባብ ስራ ነው::
አመሰግናለሁ ይህን እድል በማግኘቴ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop