አክሎግ ቢራራ (ዶር) “ኢትዮጵያን ማንም አይረዳትም። ብቻዋን ናት። ሞሰለኒን ሃሳቡን እንደገና እንዲያይ የሩሲያ የማስፈራሪያ ቃል እንኳ አላቆመውም። ምን ያድርግ? ፈረንሳዮችና እንግሊዞች አይዞህ፤ ከእግዚአብሄር የተሰጠህ ቅዱስ መብትህ ነው ብለውታል። አሜሪካ እንኳ ሳትቀር በተዘዋዋሪ ደግፋዋለች። አርፈሽ ተቀመጭ፤ ይኼ ነጻነት፤ ነጻነት የምትይው ትግልና መፈራገጥ ለመላላጥ ነው ብላታለች። አይ ኢትዮጵያ!” አዶልፍ ፓርለሳክ፤ ተጫነ ጆብሬ መኮነን (ተርጓሚ) የሃበሻ ጀብዱ ክፍል አንድ “የትግራይ ሕዝብ ዋና ጠላት አማራው ነው። በአማራው ህዝብ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን” ብሎ የፎከረውን ህወሓት/ትህነግን የሚደግፉና የሚያበረታቱ ብዙ የውጭና የውስጥ ኃይሎች መኖራቸው አያከራክርም። ይህንን የህልውና ጥቃት በመጀመሪያ ደረጃ መወጣት ያለበት በአሁኑ ወቅት ኢላማ የሆነው የአፋሩና የአማራው ሕዝብ ነው። ሕዝቡ ግዴታውን እየተወጣ ነው።