October 15, 2024
56 mins read

የእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ ልምድ ለፋኖ የህልዉና ትግል መቅሰፍት ነዉ!!

Eskinderአንተነህ ሽፈራዉ (ኢ/ር) October 15, 2024

መርህ አልባዉ እክንድር ነጋ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ ብቅ ባለ ቁጥር በአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል (ፋኖ) አመራሮች ላይ እጅግ በጣም መርዛማ የሆኑ ስም የማጥፋት ዘመቻዉን አጠናክሮ የቀጠለበት ከመሆኑ ባሻገር የአማራ ሕዝብ ዉርስ እና ቅርስ የሆነዉን የፋኖን የህልዉና ትግል ጥላሸት ለመቀባት ምን ያክል እየተሯሯጠ እንደሆነ በተለያዩ ወቅቶች ከሰጣቸዉ ቃለመጠይቆች መገንዘብ ችለናል።

የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማም እስክንድር በተለያዩ ጊዜያት ከሰጣቸዉ ቃለመጠይቆች ውስጥ ጥቂቶችን ብቻ በዋቢነት በማቅረብ ከመሞገት ባለፈ ከተመሳሳይ አሳፋሪ ድርጊቱ እንዲታቀብ ለመጠቆም ጭምር ነዉ። በመጨረሻም “መነሻችን አማራ መደራሻችን ኢትዮጵያ” የሚባለዉ የእስክንድርን እና ተከታዮቹ መፈክር በፋኖ አመራሮች መካከል ልዩነት ከመፍጠሩ ባሻገር ሌሎች ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰቦች በፋኖ የህልዉና ትግል ላይ ሆን ብሎ ጥርጣሬ እና ስጋት እንዲኖራቸዉ ለማድረግ የሄደበት ርቀት ምን ያክል አደገኛ እንደሆነ በድጋሜ ለማሳየት ጭምር ነዉ።

እዚህ ላይ አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ከላይ ከርዕሱ ላይ የእስክንድርን የባልደራስ የፖለቲክ ልምድ ሳወግዝ አንዳንድ ወንድሞች/እህቶች ባልደራስን እንደ ድርጅት ያወገዝኩ መስሏችሁ ቅር ልትሰኙ እንደምትችሉ በሚገባ እገነዘባለሁ። ነገር ግን እኔ እያወገዝኩ ያለሁት እስክንድር ወደ “ፋኖ የህልዉና ትግል ይዞት የመጣዉን የባልደራስ የፖለቲካ ልምድ እንጂ” በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ዉስጥ ሆናችሁ እዚያዉ በባልደራስ የፖለቲካ አደረጃጀት ዉስጥ የምትችሉትን አስተዋፆ ለምታምኑበት አቋማችሁ እያደረጋችሁ ያላችሁትን ወገኖቼን ክብር የመንካት ፖለቲካዊ እና ሞራላዊ መብት የሌለኝ መሆኑን ከወዲሁ እንድትገነዘቡልኝ እፈልጋለሁ!! የእኔ የፖለቲካ ልዩነት በፋኖ አመራሮች መካከል ልዩነት እየፈጠረ የህልዉና ትግሉ እያመሰዉ ካለዉ መርህ አላባዉ እስክንድር ጋር እንጂ የፋኖን የህልዉና ትግሉን መርህ ተከትለዉ የሚችሉትን መሰዋዕትነት እየከፈሉ ያሉትን የአማራ ልጆች አለመሆኑን በድጋሜ ማሳወቅ እፈልጋለሁ!!

ከዚህ በፊት ግን ለጽሑፉ መነሻ ይሆን ዘንድ የአማራ ፋኖ በጎጃም የሰሜን ሜጫ አቸፈር አመራሮች “በሰላም ኮሚሽን” ስም በእጃቸዉ የገቡ የብአዴን-ብልፅግና ካድሬዎች እና ሰላዮች የአብይ ፋሽስታዊ ወራሪ (Ethno-Fascist) ኃይል በአማራ ሕዝብ ላይ እያካሄደ ላለዉ የዘር ማጥፋት (Genocide) ተባባሪ ሆነዉ ማኅበረሰቡን ሲያወናብዱ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸዉ ምክንያት ለእርምት ይረዳ ዘንድ ከምክር እና ተግሳጽ ያልዘለለ መጠነኛ ቅጣት በመፈጸሙ ምክንያት “በብአዴን-ብልፅግና ካድሬዎች እና ሰላዮች ላይ ፋኖ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳካሄደ አድርገዉ” እስክንድር እና ተከፋይ ጋዜጠኞቹ በአማራ የህልዉና ትግል ላይ የከፈተዉ/ቱት ስም የማጥፋት ዘመቻ እና ክስ ሌላዉ የእክንድር ፀረ-ፋኖ ድርጊት በቀላል የማይታይ መሆኑን ማሳወቅ ተገቢ ሆኗል።

እናም እስክንደር ራሱን ግንባር ቀደም የሰብአዊ መብት ተሟጋች አድርጎ በማቅረብ ለትምህር ሰጭነት ሲባል በአደባባይ የተወሰደን የምክር እና መጠነኛ ተግሳጽ ልክ ከፍተኛ የሰብአዊ ጥሰት ወንጀል እንደተፈጸመ አድርጎ በማራገብ ለተለያዩ ዓለምአቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ኤምባሲዎች አቤቱታ በማቅረብ በፋኖ የህልዉና ትግል ወሳኝ አመራሮች ላይ ስም ማጥፋት የከፈተ መሆኑን እስክንድር ራሱ በአንደበቱ በራሱ ሚዲያ በኩል በግልጽ ያሳወቀን መሆኑ ማስታወስ ተገቢ ነዉ። ይህም በዓለማችን እጅግ በጣም ታላቅ ክብር እየተሰጠዉ ያለዉን የፋኖን የህልዉና ትግል ለማጠልሸት እስክንድር ምን ያክል ላይ ታች እያለ እንደሆን መገንዘብ ይቻላል።

የእስክንድር ስም አስጥፊነት ባለብዙ ፈርጅ መሆኑን ከላይ እንደ መነሻ በቀረበዉ ክስ ከተገነዘብን በቀጣይ በሌሎች የእስክንድር ቃለመጠይቆች ላይ የቀረቡ መርዛማ ንግግሮችን የበለጠ ቀረብ ብለን ለማየት እሞክራለሁ።

፩ኛ/ እስክንድር ከ Jeff Pearce ጋር ያደረገዉ ቃለመጠየቅ፡ –

ምን እንኳ እስክንድር ከ Jeff Pearce ጋር በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላደረገዉ ቃለመጠየቅ ወዲያዉ ግብረ መልስ የተሰጠዉ ቢሆንም [My Response to Eskinder’s Interview with Jeff] በዚህ የእስክንድር ቃለመጠየቅ እጅግ በጣም ብዙ ስም ማጥፋቶችን አካቶ የያዘ ቢሆንም ከምንም በላይ ግን የፋኖ የህልዉና ትግል አመራሮች የእስክንድርን የተለመደ የለበጣ ምርጫ ባለመቀበላቸዉ ምክንያት ድርጊቱን “ከአፍሪካ አምባገነኖች” ጋራ ለማዛመድ የሄደበት ስም የማጥፋት ሴራ እጅግ በጣም አጥንት የሚሰብር እና የፋኖን የህልዉና ትግል በዚህ ደረጃ ጥላሽት መቀባት በአማራ የህልዉና ትግል ላይ ትልቅ ስም የማጥፋት ዘመቻ ብቻ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ የለየለት ክህደት መሆኑ በሚገባ መታወቅ አለበት።

በተለይም እስክንድር ለቃለ መጠይቁ የተጠቀመበት ቋንቋ በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚደመጥ እንግሊዘኛ ቋንቋ መሆኑን በሚገባ እያወቀ የፋኖን የህልዉና ትግል አመራሮች ከአፍሪካ አምባገነኖች ባሓሪ ጋር አዛምዶ ማቅረቡ ትልቅ ቅጽፈት እና ራስ ወዳድነት ከመሆኑ በላይ ትልቅ ክህደት እና ኃላፊነት የጎደለዉ ስም ማጥፋት (Defamation) ድርጊት ነዉ። እስክንድር ብዙ ወንድሞቻችን/እህቶቻችን እንዲሁም ትርፍ አምራቹ ገበሬ ቀንበሩን ሰቅሎ ከእነ ልጆቹ ከአብይ ፋሽስታዊ ወራሪ ኃይል ጋር ፊት ለፊት እየተዋደቀ እና ሕይወቱን ለትግሉ ቤዛ እያደረገ ያለዉን ፋኖን በዚህ ደረጃ መወንጀል እስክንድር አሁንም ቢሆን የፋኖ መሪዎችን ከማስገደል እና በህልዉና ትግሉ ላይ ሌላ ክህደት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን በሚገባ ያሳያል።

፪ኛ/ የደም ነጋዴዎች የሚለዉ ሥም ማጥፋት፦

ያለ ይሉኝታ መናገር እና ስም ማጥፋት የለመደዉ እስክንድር መተኪያ የሌላትን ሕይወታቸዉን ለአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል ቤዛ እያደረጉ ያሉ የህልዉና ትግሉ መሪዎችን በተደጋጋሚ ጊዜ “የደም ነጋዶች” እያለ ስም ማጥፋቱ ሌላዉ የእስክንድር መርዛማ ንግግር ነዉ። “ሚሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” እንዲሉ እዉነት እንነጋገር ከተባለ እስክንደር አንድም ያሰለጠነዉ እና ያስታጠቀዉ የፋኖ ኃይል ሳይኖር በአማራ ሕዝባዊ ግንባር (Amhara Popular Front) ስም በተለያዩ ጊዜያት ከዲያስፖራዉ ከፍተኛ ገንዘብ የተሰበሰበ እሱዉ ራሱ ሆኖ እያለ ሕዝባቸዉን ይዘው ታግለዉ እያታገሉ ያሉትን እዉነተኛ የህልዉና ትግል አመራሮች “የደም ነጋዶች” ብሎ ስም ማጥፋት ሌላዉ የእስክንድር ይሉይታ ቢስነት መገለጫ ነዉ።

እስክንድር ራሱ ያቋቋመዉ እናት የፋኖ ኃይል ሳይኖረዉ እና የተባለዉ ግንባር ጭራሽ ሳይመሰረት ከእዉነተኛ መረጃ የራቀዉን ዲያስፖራዎች የተሰሳተ መረጃ በመስጠት በተሰበሰበ ከፍተኛ ገንዘብ ጥቃቀን ክፍተቶችን እየፈለገ የፋኖ ታጋዮችን ልክ እንደ ሸቀጥ በገንዘብ ለመግዛት መሯሯጡ እጅግ በጣም ከፍተኛ ስህተት ከመሆኑ ባሻገር ራሳቸዉን በገንዘብ የሸጡ የፋኖ አመራሮች ነገ እጅግ በጣም የሚያፍሩበት ርካሽ የትግል ታሪካቸው መሆኑን ሊረዱ በተገባ ነበር። በተለይም የፋኖ የህልዉና ትግል ትርጉሙ እና የፖለቲካ መትከሉ በሚፈለገዉ መጠን የማይረዱትን እና ዛሬም በዚያዉ በብአዴን ፖለቲካ ሥነልቦና ዉስጥ የሚዳክሩትን ከበቂ በላይ ታዝበናቸዋል። ለዚህም ነዉ እነዚህ ሰዎች ዛሬ በጥቂቱ የኃላፊንት ቦታ ያልታመኑ ነገ ለትልቁ የኃላፊነት ቦታ ጭራሽ የማይታመኑ መሆናቸዉን ራሳቸዉ ያጋለጡ!!

፫ኛ/ የእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ ልምድ ለአማራ ፋኖ የህልዉና ትግል መቅሰፍት መሆኑ!!

መርህ አልባዉ እና በአማራ ፋኖ የህልዉና ትግል አመራሮች መካከል የመከፋፈል እና የልዩነት ምልክት የሆነዉ እስክንድር ነጋ ከሰሞኑ እሱ ራሱ በሚቆጣጠረዉ ሚዲያ “የህልዉና ትግሉን መቀላቀሉ የፋኖን የሽፍትነት ታሪክ እና ባሓሪ ፖላቲካዊ ሰዉነት እንዲኖረዉ እንዳስቻለ” አድርጎ በማቅረብ ፋኖን የሽፍታ ስብሰብ እንደነበረ አድርጎ መርዙን ረጭቷል። ይህም የአማራ ሕዝብ ዉርስ እና ቅርስ በሆነዉ ፋኖ ላይ እጅግ በጣም አሳፋሪ የሆነ ስም የማጥፋት ዘመቻ መሆኑ መታወቅ አለበት።

እዉነት ለመናገር እስክንድር የአማራ ሕዝብ ዉርስ እና ቅርስ የሆነዉን የፋኖን ታሪካዊ እና መልካም ስም በዚህ ደረጃ ማዉገዝ እና ጥላሸት ለመቀባት እርቆ መሄዱ እጅግ በጣም አስደንጋጭ ብቻ ሳይሆን ለአማራ ሕዝብ ያለዉን ስር የሰደደ ጥላቻ ፍንትዉ አድርጎ የሚያሳይ መሆኑ ነዉ። ለመሆኑ እስክንድር በየትኛዉ አማራዊ ፖለቲካዊ ሰዉነቱ እና ልምዱ ነዉ “የፋኖ የፖለቲካ ምልክት/ሰዉነት ሆኜ እያገለገልኩ ነኝ” ለማለት የደፈረ? ይህን የእስክንድርን የትግል ነጠቃ በስሱም ቢሆን እንደሚከተለዉ ማሳየት ተገቢ ሆኖ ቀርቧል!!

እናም እዉነት እንነጋገር ከተባለ እስክንድር በባልደራስ የፖለቲካ ሕይወቱ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሕዝብ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ መብቱን እና ጥቅሙን በትግሉ እንዳያስከበር እስክንደር ከፍተኛ መሰናክል ሆኖ መቆየቱ ነዉ የሚታወቅ። በተለይም የአዲስ አበባ 65% በላይ ነዋሪ የሆነዉ የአማራ ሕዝብ በቀን አስር ጊዜ በቁሙ እየሞተ፣ እየታሰረ እና ከሚችለዉ በላይ ለፋሽስቱ አብይ አገዛዝ ግብር እንዲከፍል እና ከገብያ እንዲወጣ መደረጉ እየታወቀ፣ ከሥራ ቦታዉ በማንነቱ እየተባበረ እና እየታሰረ፣ ለዘመናት ከኖረበት ባድማዉ እና ቤቱ በቤተሰቦቹ አናት ላይ እየፈረሰ እስክንድር በባልደራስ ፖለቲካ ልምዱ ሰንደቅዓላማ ይዞ ከመዞር ባለፈ ሕዝብን ታግሎ ሲያታግል አይታወቅም።

እንዲያዉም “ባልደራስ ለእዉነት ዴሞክራሲ” በአብይ የቅጽፈት ምርጫ ተወዳዳሪ ሆኖ በመቅረብ ለአብይ ሕጋዊ ሽፋን ሰጭ ከመሆን ባለፈ እስክንድር ምንስ “አማራዊ የፖለቲካ ልምድ እና እዉቀት ኖሮት ነዉ” የፋኖ የህልዉና ትግል የፖለቲካ ምልክት አድርጎ ራሱን ያቀረበ? ይህ ከላይ ለማመላከት እንደተሞከረዉ የአማራ ሕዝብ ዉርስ እና ቅርስ የሆነዉን ፋኖን ጭቃ መቀባት ብቻ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል ዙሪያ የተሰባሰቡ እጅግ በጣም ብዙ የአማራ ምሁራኖችን ጭምር መናቅ ነዉ።

እስክንድር ራሱን የፋኖ የህልዉና ትግል የፖለቲካ ሰዉነት መሆን ችያለሁ ሲለን ግልጽ የሆነዉ ጉዳይ እስክንድር የአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል መርሆዎች ምን እንደሆኑ ዛሬም ድረስ አለማወቁን ነዉ እየነገረን ያለ። ምክንያቱም እስክንድር ምንም እንኳን የአማራዉን ወጣት በፖለቲካ አንቅቶ፣ አደራጅቶ፣ አሰልጥኖ፣ አስታጥቆ እና ታግሎ ማታገል ባይችልም እንኳ ቢያንስ ቢያንስ የፋኖ የህልዉና ትግል መርሆዎች ምን እንደሆኑ ማወቅ ነበረበት። የፋኖ የህልዉና ትግል መርሆዎች ሲባልም የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችን አበጥሮ ለይቶ መያዝ ብቻ ሳይሆን እነዚህን ወሳኝ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ ምን ዓይነት የትግል ስልት (Strategy) መከተል እንደሚሻል የፋኖ አመራሮች አስቀድመዉ ለይተዉ የያዟቸዉ መሆኑን እስክንድር ዛሬም ድርስ አያዉቅም። ለዚህ ደግሞ እነ ፋኖ ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ አስቀድመዉ በጠሩት ምድር አንቀጥቅጥ የተቃዉሞ ሰልፍ “የአማራ ሕዝብ አሳሳቢ የሆነዉ የህልዉና ጉዳይ፣ የአማአራ ሕዝብ አጽመርስት እና የማንነት ጉዳዮች፣ የፖለቲካ እና ኤኮኒሚያዊ መብቶቹ፣ የአማራን አጽመርስት በመዉረር ላይ የተዋቀረዉ ሕገወጡ የፌዴራል አደረጃጀት እንዲሁም ሌሎች ጥያቄዎች “በሰልፍ የማይመለሱ ከሆነ ሰይፍ እናነሳለን” ብለዉ ፋና-ወጊ የፋኖ አመራሮች ትጥቅ እንዳነሱ እስክንድር መገንዘብ ነበረበት!!

እርግጥ ነዉ እስክንድር የፋኖ ፖለቲካ መርሆዎች ምን እንደሆኑ ዛሬም ድረስ ስለማያዉቅ እንጂ ለህልዉና ትግል “ወታደራዊ ክንድ ያስፈለገበት” ዋናዉ ገፊ ምክንያት የአማራ ሕዝብ ለረጅም ዓመታት በሰላማዊ መንገድ ያነሳቸዉን ጥያቄዎች በትጥቅ ትግል ለማስመለስ እንጂ ከአብይ ፋሽስታዊ ወራሪ ሠራዊት መሳሪያ ማርኮ መታጠቅ ለብቻዉ የፋኖ የህልዉና ትግል ስኬት ተደርጎ ሊወሰድ እንደማይችል እስክንድር ገና አላወቀም። ምክንየቱም ወሳኙ የህልዉና ትግሉ ስኬት የሚለካዉ የፋኖ አመራሮች የማታጋያ ጥያቄዎቻችን ብለዉ የያዟቸዉ አንድም ሳይሸራረፉ ሲመለሱ ብቻ ነዉና። That means, the “Military Muscle of FANO” is used as a means/tool to achieve the Amhara Political end, Questions, but itself not as the end goal of the Survival struggle!! ለዚህም ነዉ የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሊቀመንበር እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ምስረታ ጀምሮ “ፋኖ ማለት ትጥቅ ያነሳ ፖለቲከኛ ነዉ” በሚል ደጋግሞ ለማስገንዘብ የሞከረ።

እናም እዚህ ላይ አንድ መገንዘብ ያለብን ወሳኝ ጉዳይ የእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ ልምድ ከፋኖ የህልዉና ትግል ጋር ፍፁም ተፃራሪ በመሆኑ ወደ ፋኖ የህልዉና ትግል ተስቦ ሊመጣ አይገባም ነበር። ምክንያቱም የእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ ልምድ ከፋኖ የህልዉና ትግል መትከሎች ጋር ፍጹም ተፃራሪ በመሆኑ በፋኖ አመራሮች መካከል የልዩነት እና የቅራኔ ምክንያት ሊሆን ችሏል። በተለይም አንዳንድ የፖለቲካ ልምድ ክፍተት ያለባቸዉን የፋኖ አመራሮች የፋኖ የህልዉና ትግል መርሆዎችን ዛሬም ድረስ በአግባቡ ሊገነዘቡ ባለመቻላቸዉ እስክንድር ደካማ ጎናቸዉን እየፈለገ የባልደራስን የኢትዮጵያዊነት የፖለቲካ ተዉሳክ/ቫይረስ ሊጭንባቸዉ በመቻሉ በፋኖዎች መካከል (እስክንድር) የልዩነት ምልክት እንጂ የፋኖ የፖለቲካ ሰዉነት ወይም ምልክት ሆኖ እያገለገለ አይደለም። ለዚህም ነዉ እስክንድር “መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ” የሚል ፀረ የፋኖ የህልዉና ትግል የማደናገሪያ መፈክር ይዞ እየከፋፈላቸው ያለ!!

የፋኖ የህልዉና ትግል መነሻዉ መሰረቱ አማራነት ሲሆን መዳረሻዉም ሕገ ወጡን የአራት ኪሎ የአብይ ፋሽስታዊ (Ethno-Fascist) አገዛዝ በትጥቅ ትግል አሽቀንጥሮ መጣል ሲሆን ፋኖ አራት ኪሎን በክንዱ ከተቆጣጠረ በኋላ በአማራ ሕዝብ ላይ የታወጀዉ ሕገ መንግሥታዊ፣ መዋቅራዊ እና መንግሥታዊ የዘር ፍጅት በሕጋዊ አግባብ ሊቀለበስ የሚችልበት አስቻይ ሁኔታ ይፈጠራል። ይህንም ተከትሎ ፋኖ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ባለድርሻ አካላት (ከዘር ፍጅት ወንጀል ነፃ ከሆኑት) ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ በኢትዮጵያ “መጻዊ ዕድል ፋንታ” ላይ በጋራ ይመክራል፤ ዘላቂ መፍትሔ በጋራ ያስቀምጣል። ይህም የፋኖ የህልዉና ትግሉ መዳረሻ ይሆናል።

እናም የአማራ ሕዝብ ዘላቂ እና ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ፋኖ ለአማራ ሕዝብ ዋስ እና ጠበቃ ሆኖ ይሰራል፣  የአማራ ሕዝብ ጠበቃ የሆነዉ ፋኖ በወርዱ፣ በቁመቱ፣ በሃቅሙ እና በክብደቱ መጠን የፖለቲካ ሥልጣን ይይዛል፤ በፌዴሬሽን ስም በሕገወጥ መንገድ የተዘረፉ የአማራ ሕዝብ ታሪካዊ አጽመርስቱን ያስከብራል፤ እንዲሁም ሌሎች ጥያቄዎቹም በአግባቡ እንዲመለሱ ይከራከራል፣ በአጠቃላይ ለአማራ ሕዝብ ጠንካራ ድምፅ ሆኖ ይቀርባል። ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረዉ ፋኖ የድርሻዉን የፖለቲካ ሥልጣን መያዝ መቻል የአማራ ሕዝብ ህልዉና ለዘለቄታዉ አስተማማኝ ሆኖ እንዲጠበቅ ያስችላል።

ይህ የፋኖ የህልዉና ትግል መርሁ ሲሆን ከእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ ልምድ ጋር ሙሉ በሙሉ ተፃራሪ ነዉ። ለዚህ ነዉ የእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ ልምድ ለፋኖ የህልዉና ትግል “መቅሰፍት” ነዉ የምንለዉ!! በሌላ አገላለጽ የእስክንድር በፋኖ የህልዉና ትግል ዙሪያ መቆየት ለፋኖ የህልዉና ትግል የጎን ዉጋት ሲሆን ይህ ዓይነቱ ችግር በፖለቲካ ትንታኔ ሲታይ ከዳንኤል ክብረት የሚለየዉ የእስክንድር ጥቃት በተቋም ዉስጥ ያለ የዉስጥ ጠላት “An enemy, a wrong element, infiltrating a friendly entity” በሚል የሚፈረጅ ሲሆን የዳንኤል ክብረት በፋኖ ላይ እያካሄደዉ ያለዉ ጥቃት ዉጫዊ መሆኑ ነዉ ልዩነቱ!!

በመሆኑም ሁሉም የፋኖ አመራሮች ወደ አንድ ወሳኝ የትግል ማዕከል እንዲሰባሰቡ እና የፋኖ የህልዉና ትግል በፍጥነት እና በጥንካሬ ወደ ፊት እንዲገሰግስ እንዲሁም የአብይን ፋሽስታዊ አገዛዝ በተሎ ለመገርሰስ እንዲቻል የሚከተሉት ወሳኝ ጉዳዮች የግድ መከናወን ይኖርባቸዋል። እነሱም፦

፩ኛ/ ከፋኖ የህልዉና ትግል መርሆዎች የተለየ የፖለቲካ አካሄድ እና አቋም ያለዉ እስክንድር ነጋ ለአማራ ሕዝብ ህልዉና ሲል ራሱን ከፋኖ የህልዉና ትግል ቢያንስ ለጊዜዉ እንኳ ገለል ማለት እና “ከፋኖ ድል በኋላ” እንደተለመደዉ ድል ለዴሞክራሲ የሚለዉን መፈክር ይዞ በሰላማዊ መንግድ በባልደራስ ወይም ሌላ ራሱ ለሚያቋቁመዉ ድርጅት መሪ ሆኖ በአዲስ ሞራል ለመምጣት ራሱን በተሎ ማሳመን፣

፪ኛ/ ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሰዉ ተግባራዊ ካልሆነ እስክንድር በፋኖ አመራሮች መካከል ዋና የልዩነት ምክንያት ሆኖ ስለሚቀጥል የዉስጥ መከፋፈሉ ተባብሶ ሊቀጥል ይችላል። ይህም የአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል አሁን ከምንጠብቀዉ በላይ ወደ ከፋ ችግር ሊያድግ እንደሚችል አለመገመት ጅልነት ነዉ። በተለይም አሁን ባለዉ ተጨባጭ ሁኔታ እስክንድር ሸዋን እና ወሎን ሁለት ሁለት ቦታ ከፋፍሎ ቅራኔዉን እያባባሰዉ ሲሆን ጎንደርን ከሁለት ወደ ሦስት ጎራ መከፋፈል ችሏል። ይህም በተራዉ እስክንድር ለራሱ ያለዉ ግንዛቤ የተዛባ እና እጅግ በጣም ሲበዛ ራስ ወዳድ ከመሆኑ አኳያ አራቱን የአማራ ሕዝብ ማዕከሎች እርስ በእርስ እንዲጋጩ ከማድረግ አይመለስም። ይህም የህልዉና ትግሉን ማጓተት ብቻ ሳሆን የአማራ የህልዉና ትግል እጅግ አደገኛ ሁኔታ ዉስጥ ስለሚገባ እስክንድርን የሚቀርቡት የቅርብ አማካሪዎቹ ለህልዉና ትግሉ እየተከፈለ ያለዉን ከባድ የሕይወት መሰዋዕትነት እና የንብረት ዉድመት ግምት ዉስጥ በማስገባት እስክንድር ከህልዉና ትግሉ ራሱን በአስቸኳይ እንዲስብ በማድረግ በሸዋ፣ በወሎ እና በጎንደር ሁለት እና ሦስት ጎራ የተከፈሉ የፋኖ አመራሮች ለሚመሩት አካባቢ ሕዝብ እና ለአጠቃላዩ የአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል አንድነት እና ስኬት ሲባል ልክ እንደ ጎጃም ወደ አንድ፣ አንድ፣ አንድ የፋኖ አመራር በአስቸኳ መመጣት ይኖርባቸዋል፣

፫ኛ/ ከላይ በተጠቀሱ ቁጥር ፩ እና ፪ መሰረት በማድረግ የወሎ፣ የጎጃም፣ የጎንደር እና የሸዋ ፋኖ መሪዎች የየአካባቢያቸዉን የአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል ሊወክሉ ይችላሉ የሚባሉ እኩል የሰዉ ኃይል ሊመሰረት ለታሰበዉ የአማራ ፋኖ አንድነት ተቋም ይዞ በመቅረብ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት (For Example 9 X 4 = 36 Amhara Fano Leadership Council) ማቋቋም እንዲሁም የአማራ ፋኖ የዕለት ከዕለት ሥራዎችን የሚያስተባባር በተመሳሳይ ሁኔታ ከአራቱም እኩል አመራሮች በማዋጣት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በማለት (3 X 4 = 12 Executive Body) ማዋቀር እና በመጨረሻም አራት አባላት ያሉት (1 X 4 = 4 Leaders Committee ከመካከላቸዉ አንዱ ስብሰባ መሪ ማድረግ ይቻላል፣ ሌሎችም ምክትሎች ሆነዉ የዘርፍ ኃላፊ መሆን ይችላል)።

በዚህ መልክ የጋራ አመራር እና አሰራር መፍጠር ይቻላል – ይህ ግን ለአብነት ያክል እንጂ በሌላ ሊተረጎም አይገባም። የዚህ ዓይነቱን የጋራ አመራር እና አሰራር ስልትን መከተል የሚያስችል አደረጃጀት መዘርጋት ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀዉን የአማራ ፋኖ አንድነት ጠንካራ ተቋም መፍጠር ይቻላል። ይህ እንዲሆን ግን የተራ ቁጥር አንድ ተግባራዊ መሆን እጅግ በጣም ወሳኝ ነዉ።

በየትኛዉም መመዘኛ ለህልዉና ትግሉ ሕይወታቸዉን ሳይሳሱ ቤዛ ሊያደርጉ ወደ ትግሉ ሜዳ የወጡ የፋኖ ወንድሞቻችን/እህቶቻችን እንደ ሸቀጥ በገንዘብ ለመግዛት እያደረገ ያለዉ ሕገ ወጥ (unethical) ድርጊት እጅግ በጣም ይቅር የማያስብል ወንጀል ነዉ። በእስክንድር እኩይ ስራ የህልዉና ትግሉን ቢያንስ ቢያንስ ላለፉት ፲፭ ወራቶች በተፈለግዉ ፍጥነት እንዳይራመድ ጠፍንጎ የያዘዉ መሆኑ መታወቅ አለበት። ሸዋን ሁለት ቦታ፣ ወሎን ሁለት ቦታ፣ ጎንደርን ሦስት ቦታ ከፋፍሎ የራሱን አንጃ ለመፍጠር እያደረገ ባለዉ የጎንዮሽ ትግል የአማራን ሕዝብ የህልዉና ትግል ወደፊት ሊያራመድ አልቻለም – ትግሉ እጅግ በጣም ዉጣ ዉረድ የበዛበት እና የጎንዮሽ እንዲሆን ማድረጉ ብቻ ሳይሆን መሰዋዕትነቱ የበዛት እና ጊዜዉም የተራዘመ እንዲሆን እያደረገዉ ነዉ።

ሌላዉ አንድ እዚህ ላይ አብሮ ሊነሳ የሚገባ ጉዳይ ምንም እንኳን የፋኖ አመራሮች “ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በጋራ ተናበን እያካሄድነ ነዉ” ቢሉም ይህ ለብቻዉ በቂ ባለመሆኑ ከላይ በግልጽ ለማስቀመጥ እንደተሞከረዉ የህልዉና ትግሉ በአስቸኳይ ወደ አንድ ጠንካራ የትግል ማዕከል መምጣት አለብት!! ይህ እዉን እንዲሆን ከተፈለገ ደግሞ እስከንድር እና በስፋት ያሰማራቸዉ ተከፋይ ጋዜጠኞች (አማካሪዎቹ) ከአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል በአስቸኳይ ገለል ማለት ይኖርባቸዋል!!

እርግጥ ነዉ እስክንድር ከተለያዩ አቅጣጫዎች ዶላር በገፍ የሚያቀርብለት አካል እስከቀጠለ ድርስ የአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግሉ ጊዜ መርዘምም ይሁን ሕዝባችን በፋሽስታዊዉ አብይ አገዛዝ ቢጨፈጨፍ (እስክንድርን) የሚያሳስበዉ አይደለም። ለዚህ ደግም በእሱ እና ተከፋይ ጋዜጠኞቹ ባደረጉት ባዶ ጩኽት ምክንያት በደብረ ኤልያስ ታሪካዊ ገዳም አባቶች እና ሕፃናት ላይ ለደረሰዉ ጭፍጨፋ ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌለዉ አይተናል። ዝርዝሩን ከላይ ከመጀመሪያዉ የተቀመጠዉን ማስፈንጠሪያ በመንካት ማወቅ ይቻላል!!

በመጨረሻም ለዚህ ጽሑፍ እንደ መዉጭ ይሆነን ዘንድ “መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለዉ የእስክንድር እና ተከታዮቹ አደገኛ መፈክር በፋኖ አመራሮች መካከል ልዩነት የፈጠረ ብቻ ሳሆን ሌሎች ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰቦች በፋኖ የህልዉና ትግል ላይ ብዥታ እና ጥርጣሬ ለመፍጠር ጭምር የሚቀነቀን ቢሆንም የትኛዉም የፋኖ የህልዉና ትግል አመራር የአማራ ሕዝብ የህልዉና ጥያቄን “ቀደሚ የትግል ግብ” አደረገ እንጂ ከድል በኋላ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በኢትዮጵያ መፃዊ ዕድል ፋንታ ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ ተመካክረዉ (with common consent) የሚወስኑ መሆናቸዉን በአጽንኦት ገለጹ እንጂ ፋኖ ባለድርሻ አካላትን የማግለል ወይም በተናጠል ከወዲሁ ለብቻዉ የሚወሰነዉ ጉዳይ አለመኖሩን ደጋግመዉ ነግረዉናል።

እዉነቱ ይሄዉ ሆኖ እያለ “የመነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ” የሚለዉ መፈክር ባለቤቶች ከባልደራስ እና ግንቦት 7 ፖለቲካ አመለካከት ዉጭ ያለዉን የፋኖ አደረጃጀት/አመራር አግላይ፣ ጠባብ እና ፅንፈኛ እያሉ ከመወንጀል ባለፈ ግድያ እንደሚያካሂዱባቸዉ በማኅበራዊ ሚዲያ ጭምር አቋማቸዉን ግልጽ አድርገዋል።

ከዚሁ “መነሻችን አማራ መደራሻችን ኢትዮጵያ” ከሚለዉ የእክንድር እና ተከታዮቹ መፈክር ጋር በተያያዘ ፕ/ር መሳይ ከበደ ከልደቱ አያሌዉ ጋር በምንጊዜም ሚዲያ ባደረጉት ዉይይት [Prof Messay and Ato Lidetu] “የዚህ የእስክንድር ዓይነቱ መፈከር ኢትዮጵያዊነትን በሌሎች ማኅበረሰቦች ላይ አስቀድሞ በኃይል የመጫን መርህ አልባ አካሄድ መሆኑን” በሚገባ ካብራሩ በኋላ “አዲሱ የፖለቲካ አካሄድ በኢትዮጵያ መጻዊ ዕድል ፋንታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅድሚያ በመወያየት የሚወሰን እንጂ አስቀድሞ በተናጠል በመወሰን የሌሎችን ይሁንታ ማግኘት አስቸጋሪ ነዉ” ብለዋል,,, እንዲያዉም “አስቀድሞ በተናጠል የመበየን አካሄድ የሚፈለገዉን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማምጣትም በጣም ያስቸግራል” የሚል በሳል ትንታኔ ለማቅረብ ሞክረዋል። በመሆኑም ይህ የእስክንድር የባልደራስ ፖለቲካ አካሄድ የፋኖን የህልዉና ትግል ምን ያክል ብዥታ ዉስጥ እንደጣለዉ መገንዘብ ይቻላል።

“According to an extremist Oromo activist, “Ethiopianism is the predominant form of Amhara nationalism in Ethiopia. … The primary goal of Fano has been and still is, like fascist Amhara feudal rulers of the past, to create one country, one flag, one Amharic language, one Amhara culture, one psychological makeup Amhara view, and one Christian orthodox religion-Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.” “For another Tigrayan extremist, Fano’s “plan A has been to materialize their ambition to reinstate a unitary government system and put Ethiopia under their centralized power control.” ,,, According to him, Shaleka’s slogan, “‘መነሻችን አማራ መድረሻችን ኢትዮጵያ” [Our starting point is Amhara, and our destination is Ethiopia],” is unacceptable because “we cannot fight for Amhara edition of Ethiopia while fighting Oromummaa edition of Ethiopia.” [Prof. Messay Kebede] ለዚህም ነዉ የአማራ ሕዝብ የህልዉና ትግል ከእስክንድር የባልደራስ የፖለቲካ አካሄድ በመርህም ይሁን በባሃሪ የተለየ ነዉ የምንለዉ።

አሁንም ከዚሁ መፈክር ሳንወጣ ከእስክንድር “መነሻችን አማራ መዳረሻች ኢትዮጵያ” ከሚለዉ የፖለቲካ መርህ የተለየ አማራዊ የፖለቲካ አቋም አላቸዉ የሚሏቸዉን የፋኖ አመራሮች “አማራ” ሲሉ “የአማራ ክልል ተብሎ በሚጠራዉ ክልል ዉስጥ ብቻ ያለዉን አማራ ማለታቸዉ ነዉ” ብለዉ አዲስ ዓይነት የማወናበጃ ዘመቻ ይዘዉ ብቅ ብለዋል። በዚህ ረገድ የእስክንድር ተከታይ የሆነዉ ረ/ፕ ጌታ አስራደ ከሰሞኑ ከመሳይ ጋር ባደረገዉ ቃለመጠየቅ ላይ ሆን ብሎ እዉነቱን አዛንፎ ያቀረባቸዉን ትንታኔዎች ቀረብ ብለን ለማየት እንሞክራለን። እርግጥ ነዉ ጌታ አስራደ ከአማራ የህልዉና ትግል አኳያ ያነሳቸዉን ታሪካዊ አረዳዱ መልካም ቢሆንም በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሄደባቸዉን አደገኛ አካሄዶች ግን ለህልዉና ትግሉ ጎጅዎች እና መርህ አልባዎች በመሆናቸዉ ችግሩን በስሱ ለማሳየት እሞክራለሁ!!

ሀ/ የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ መሰናክልን በተመለከተ!! “የህልዉና ትግሉ ከግለሰቦች ፍላጎት በላይ ነዉ” የሚለዉ የጌታ አስራደ አገላለጽ እጅግ በጣም ትክክል ቢሆንም መሬት ላይ ካለዉ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ የግድ መታየት አለበትና አገላለጹ “ተጨፈኑ እና ላሞኛችሁ” ዓይነት በመሆኑ ተቀባይነት የለዉምና ይህ ዓይነቱ አካሄድ መቆም አለበት። የዚህ ሃሳብ መሰረታዊ ችግሩ እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ የአማራ ፋኖ ኃይል እየመራ ያለን መሪን ከአንድ ተራ ግለስብ ጋር በማወዳደር ግለስቡን “እንደ መምቻ ብትር” አድርጎ ለመጠቀም መሞከር ተግቢ አይደለም። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸዉን በግልጽ “እኔም ስኳድ ነኝ” የሚሉ ግለሰቦች በተለያዩ ማኅበራዊ ሚድያዎች ብቅ እያሉ ቃል በቃል “እንቶኔን እና እንቶኔን ከአመራር ቦታዉ ዘወር በማድረግ እነ ጌታ አስራደን ማምጣት አለብን” የምትል የሞኝ ዘፈን ይዘዉ (ዐይናቸዉን በጨዉ አጥበዉ) ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋልና ይህ ዓይነቱ አካሄድ በባሃሪዉም ይሁን በይዘቱ ሁለት ሊወዳደሩ የማይችሉ አፕሉን ከብርቱካኑ ጋር “An Apples with Oranges, False Equivalence” የማወዳደር ዓይነት ነዉና ተቀባይነት የለዉም!!

“የአማራ ፋኖ አንድነት ሊሳካ ያልቻለ በግለሰቦች የሥልጣን ጥማት ነዉ” ብሎ ጌታ አስራደ በጅምላ ለመወንጀል የሄደበት አካሄድ እጅግ በጣም አደገኛ እና መርህ አልባነት መሆኑ መታወቅ አለበት። ምክንይቱም የአማራ ፋኖ አንድነት ምስረታ ሊሳካ ያልቻለ በእስክንድር እና ተከታዮቹ መርህ አልባ አካሄድ እንጂ ከእሱ ዉጭ ባሉ የአማራ ፋኖ አመራሮች የሥልጣን ጥማት ምክንት አለመሆኑ መሬት ላይ ያለዉ ተጨባጭ ሁኔታ አፍ አዉጥቶ እየተናገረ ነዉ። ለዚህም እስክንድር ራሱ ያደረጀዉ አንድም የፋኖ ሰዉ/አካል ሳይኖረዉ ከዲያስፖራ በሚያገኘዉ ገንዘብ የተለያዩ የፋኖ አንጃዎችን በመፍጠር ራሱን የፋኖ መሪ አድርጎ ማቅረብ የፋኖን የአደረጃጀት መርህ ሙሉ በሙሉ መፃረር ነዉ። በሌላ አገላለጽ እስክንድር እንደ ሌሎች የፋኖ መሪዎች የራሱ የሆነ የፋኖ አካል/አደረጃጀት ሳይኖረዉ ራሱን ልክ ከዉጭ በደሞዝ ተቀጥሮ እንደ ሚመጣ የንግድ ተቋማ ሥራ አስኪያጅ በማድረግ የፋኖ የህልዉና ትግል ልምራ ማለት በእርግጥም ከፍተኛ የሆነ የሥልጣን ጥማት እና አንጀኛነትን ማስቀደም ነዉ። እናም ግለሰቦች የሚባሉት መመዘን ያለባቸዉ በፋኖ የህልዉና ትግል ባነቁት፣ ባደራጁት፣ ባሰለጠኑት፣ ባስታጠቁት እና ታግለዉ እያታገሉ እና በሚመሩት የፋኖ ኃይል/አደረጃጀት እንጂ በፋኖ አመራሮች መካከል በሚፈጥሩት አንጃ መሆን የለበትም!!

እናም የአማራ ፋኖ አንድነት እዉን ሊሆን የሚችለዉ በመርህ እና መርህን በመከተል እንጂ በጥላቻ ንግግር እና የመሪዎችን ስም በማጥፋት ሊሆን አይችልም። እነ ጌታ አስረደ “ግለሰቦች” እያሉ የሚወነጅሏቸዉ ግዙፍ የአማራ ፋኖ ኃይል መሪዎችን ሊሆን እንደሚችሉም መታወቅ አለብት – ያዉም የአብይ ፋሽስታዊ ወራሪ ኃይልን 70% ክንዱን እየሰበሩ ያሉትን!! እንደዚህ ያለዉ አካሄድ እነዚህን በሳል እና ልምድ ያላቸዉን አርበኞች ሊመሰረት ከታሰበዉ የአማራ ፋኖ አንድነት አመራርነት የመወዳደር ዴሞክራሲያዊ መብታቸዉን አስቀድሞ ለመንፈግ “የግለሰቦች የሥልጣን አባዜ” እያሉ መወንጀል በየትኛዉም አካሄድ ተገቢ አይደለም። የትኛዉም የፋኖ አመራር ብቁነቱ የሚመዘነዉ መሬት ላይ በሚመራዉ የአማራ ፋኖ ኃይል/ተቋም እንጂ በፋኖ አመራሮች መካከል በሚፈጥረዉ አንጃ ሊሆን አይችልም። ይህ ከሆነ የህልዉና ትግሉን መርህ አልባ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የህልዉና ትግሉን ከመጥለፍ ተለይቶ አይታይም።

ለ/ አማራ ማለትን በተመለከተ!! ከእስክንድር “መነሻችን አማራ መዳረሻች ኢትዮጵያ” ከሚለዉ መፈክር የተለየ አማራዊ የፖለቲካ አቋም አላቸዉ የሚሏቸዉን የፋኖ አመራሮች “አማራ” ሲሉ “የአማራ ክልል ተብሎ በሚጠራዉ ክልል ዉስጥ ያለዉን አማራ ብቻ ማለታቸው ነዉ” ብሎ አዲስ ዓይነት ትርክት ጌታ አስራደ ይዞ መቅረቡ እጅግ በጣም አሳፋሪ ነዉ። ጌታ አስራደ ዛሬም ድረስ አላወቀም እንጂ እሱ “የአማራ ክልል” ብሎ የሚጠራዉን የትኛዉም የአማራ ፋኖ አመራር ትህነግ እና የትህነግ መንገድ መሪዎች እና ዱቄት ተሸካውሚዎች “የአማራ ክልል” ብለዉ የፈጠሩትን የበሬ ግንባር የምታክል ክልል “የአማራ ክልል” ብለዉ ለመጥራት የሚጸየፉት መሆኑን ማወቅ ነበረበት። እናም ይህ ዓይነቱ አካሄድ ከላይ በዋቢነት የቀረበዉ ሥም ማጥፋት ዘመቻ ቅጽያ ካልሆነ በቀር አማራ ማለት (ቢያንስ ቢያንስ) በየትኛዉም የኢትዮጵያ ግዛት ዉስጥ ያለዉን አማራ ማለታቸዉ እንደሆነ ጌታ አሰራደ ጠፍቶት አይደለም። ሌላዉ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጌታ አስራደ ከእስክንድር የተለየ የፖለቲካ መርህ የሚከተሉትን የፋኖ አመራሮች አማራ፣ አማራ፣ አማራ እያሉ አማራዉን ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰቦች ለመለየት ጥረት እንደሚያደርጉ አድርጎ የሰጠዉ ትንታኔ እጅግ በጣም ኃላፊነት የጎደለዉ እና በራሱ ላይ እንደመተኮስ የሚቆጠር መሆኑን ማወቅ አለበት። የቄስ ሚስት ሰለጠንሽ ሲሏት መጽሐፍ ቅዱስ አጠበች እንዲሉ!!

ሐ/ የትግል ስልትን በተመለከተ!! በዚሁ ቃለመጠየቅ ጌታ አስራደ “የፋኖ የህልዉና ትግል እስከ አሁን ድረስ ያለዉ ወታደራዊ ብቻ” እንደሆነ አድርጎ ለማቅረብ ሞክሯል። ነገር ግን ይህ የጌታ አስራደ ግንዛቤ እጅግ በጣም ትልቅ ችግር አለበት። ምክንያቱም ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረዉ ፋኖ ትጥቅ ለማንሳት የተገደደበት ዋናዉ ምክንያት የአብይ ፋሽስታዊ አገዛዝን በሰላማዊ ሰልፍ ወይም በቤት ዉስጥ አድማ መለወጥ ስለማይቻል እንጂ ፋኖ ታግሎ ሕዝብን የሚያታግልባቸዉ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች በሚገባ አሉት (ያዉም ጥርት ያለ የፖለቲካ የማታጋያ ሰነድ)!! እርግጥ ነዉ ረ/ፕ ጌታ አስራደ የፋኖን የህልዉና ትግል የተቀላቀለዉ በቅርቡ በመሆኑ የፋኖን የፖለቲካ መትከሎች ገና ባለማወቁ እንጂ ፋኖ ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ (በአጠቃላይ የአማራ ፋኖ ከፍተኛ አመራሮች) ደጋግሞ ለማስገንዘብ እንደሞከሩት “ፋኖ ትጥቅ ያነሳ ፖለቲከኛ” መሆኑን ግልጽ ለማድረግ ሞክረዋል። እናም በግልጽ መታወቅ ያለበት የፋኖ የፖለቲካ አጀንዳ የትጥቅ ትግሉን እየመራዉ እንደሆነ መታወቅ አለበት!! Meaning the political agenda of Fano dictates its military wing!!

መ/ የአማራ ፋኖ አንድነት እዉን እንዲሆን ምን ይደረግ? እነ ረ/ፕ ጌታ አስራደ የአማራ ፋኖ አንድነት እዉን እንዲሆን ከፈልጉ በጎንደር ዉስጥ በሦስት/በአራት ተከፋፍሎ ያለዉ የፋኖ ኃይል ለአካባቢዉ ሕዝብ እና ለአጠቃላዩ የአማራ ሕዝብ ድል ሲባል የግድ ወደ አንድ አመራር መምጣት አለባቸዉ። በተመሳሳይ መልኩ በወሎ እና ሸዋ ያለዉ ተመሳሳይ ችግርም በተሎ እልባት ማግኘት አለበት!! ይህ ሲሆን የዉሕደቱን ሂደት እጅግ በጣም ቀላል እና አስተማማኝ ያደርገዋል። እነ ጌታ አስራደ እና ሌሎች ጓደኞቹ የአማራ ፋኖ አንድነት ሕዉን እንዳይሆን መሰናክል የሆነዉ የዉስጣቸዉን ችግሮች ሳይፈቱ ሆን ብለዉ ወደ ጥላቻ እና መርህ አልባዉን አካሄድ መምረጣቸዉ ተገቢ አይደለም።

እናም አሁን ባለዉ ተጨባጭ ሁኔታ በወሎ፣ በሸዋ እና በጎንደር ያሉ የተለያዩ የፋኖ አመራሮች ለአማራ ሕዝብ ትግል ስኬት ሲባል የዉስጥ ችግሮቻቸዉን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በዉይይት እየፈቱ ልክ እንደ አማራ ፋኖ በጎጃም ወደ አንድ አደረጃጀት መምጣት አለባቸዉ። በራሳቸዉ ዉስጥ ያለዉን የዉስጥ ችግር ቅድሚያ ሳይፈቱ እና አንድነቱን ሳይፈጥሩ በየትኛዉ ልምዳቸው እና የአሰራር ባሃሪያቸዉ ነዉ ሌሎችን አንድ አድርገዉ ሊመሩ የሚችሉ? መርህ ማለት ይሄዉ ሲሆን የፋኖ አመራሮችን ደካማ ጎን እየፈለጉ በገንዘብ መከፋፈል ግን መርህ አልባነት እና የህልዉና ትግሉን መጥለፍ መሆኑን መገንዘብ የግድ ነዉ።

ለዚህም ነዉ እስክንድር መርህ አልባ በመሆኑ ከፋኖ የህልዉና ትግሉ ለጊዜዉም ቢሆን በተሎ ዘወር ማለት ያለበት። እስክንድር ከህልዉና ትግል ዘወር ካለ መሬት ላይ በተግባር የተፈተኑ እና ታግለዉ ሕዝባቸዉን እያታገሉ ያሉ የፋኖ አመራሮች ወደ አንድ የአማራ ፋኖ ጠንካራ አደረጃጀት እንደሚመጡ የታወቀ ነዉ። እስክንድርን በተመለከተ በፋኖ የህልዉና ትግሉ ዙሪያ በአብይ ፋሽስታዊ ወራሪ ኃይል በጥይት፣ በመድፍ፣ በድሮን ወዘተ የተፈናቀሉ፣ ቤት ንብረታቸዉ የተቃጠለባቸዉን፣ በአጠቃላይ የተቸገሩትን እና መጠጊያ ያጡትን ወገኖቻችንን ሊረዳ በሚችል ሥራ ላይ አትኩሮ ከግብረሰናይ እና ሰብአዊ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በምግብ፣ በሕክምና፣ በዉኃ ጉድጓድ፣ በአልባሳት ወዘተ አቅርቦቶች ላይ ቢሰራ ለፋኖ የህልዉና ትግል እጅግ በጣም ትልቅ ድጋፍ ነዉ። ከፋኖ ድል በኋላም እስክንድር የተለመደዉን “ድል ለዲሞክራሲን” ይዞ የፖለቲካ መሪ ከመሆኑ የሚያግደዉ ኃይል አይኖርም – ያኔ መብቱ ነዉና። የረ/ፕ ጌታ አስራደ ከሰሞኑ ከመሳይ መኮንን ጋር ያደረገዉን ቃለመጠየቅ [A/P Geta Asirade] ለዋቢነት ማዳመጥ ይችላሉ!!

ማሳሰቢያ፦ ይህ ጽሑፍ የጸሐፊዉ ሃሳብ እንጂ የትኛዉንም የፋኖ አካል ወክሎ የቀረበ አይደለም!!

ድለ ለፋኖ – ድለ ለአማራ ሕዝብ!!

Diaspora fight
Previous Story

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

Latest from Blog

blank

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ
blank

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ
blank

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
Go toTop

Don't Miss

amhara

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ
7

ናዝሬት ሞጆ መንገድ በፋኖ ተያዘ 7 ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ተሸኙ አሁን የደረሱን የድል መረጃዎች

ናዝሬት ሞጆ መንገድ በፋኖ ተያዘ 7 ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ተሸኙ