December 16, 2019
16 mins read

ሱሰኛ አማራ ሆይ! ተሱስህ ተላቀህ ወደ ጎበዝ አለቃህ! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ከሰባ አምስት ዓመታት በፊት አይሁዳንና ሌሎችን በመጨፍጨፍ ከሂትለር ጋር የተሳተፉ የናዚ ፓርቲ አባሎች እስከ አሁን እየታደኑ ለፍርድ እየቀረቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ [1-2] ለምሳሌ በአለፈው አመት የ95 ዓመት እድሜ ሽማግሌ ስሙን ለውጦ ከተደበቀበት ተይዞ በ21 ዓመቱ በፈጠመው ወንጅል ችሎት ቀርቧል፡፡ [3] የእኛውን አገር ሂትለር ያገለገሉት ወንጀለኞች ግን በዓለም ሲሸለሙ በአገር ውስጥም የአበባ ጉንጉን ሲጠለቅላቸው ይውላል፡፡ በዚህ መንገድ ነፍሰ-ገዳዮች እየተሸለሙና ሰማእታት ዳግም እየተሰው እግዚአብሄር በየትኛው ንስሃችን ምህረት ሊልክልን ይችላል? በሱስ ነፍዘን ፍትህን እየረገጥንስ እንዴት ሰላም ይሰፍናል?

በለማና አብዮት ሱስ ተመተው እንደ ደነዘዙት መንጋዎች በሲጃራና በአደንዛዥ ዕጥ ደንዝዞ አንዴ ሲዘፍን ሌጋ ጊዜ ሲያለቅስ የማየው አንድ ሱሰኛ ነበር፡፡ ይኸንን ሱሰኛ አንድ ቀን “የያዘህ ሱስ የሚያመጣውን ጠንቅ ትረዳለህን?” ስል ጠየኩት፡፡ ሱሰኛውም “አዎ!” አለና ሱሱ የሚያደርሰውን ጠንቅ ተራ በተራ ዘረዘረልኝ፡፡ እኔም ያንን ሁሉ ማወቁ ገረመኝና “በዚህ ሱስ የሞቱ ሰዎች ታውቃለህን?” ብዬ ስጠይቀው “አባቴ፣ ታላቅ ወንድሜ፣ የአክስቴ ልጅ” እያለ የሞቱትን ሰዎች ደረደረልኝ፡፡ “ያሳዝናል!” በዬ ሀዘኔን ገልጬ “ይኸንን እያወክ ታዲያ ለምን ተዚህ ሱስ መውጣት አልፈለክም?” ብዬ ስጠይቀው የሱሰኛ ነገር የሚመልሰው ግራ ገባውና “በሱስ የተያዝኩት እኮ እነሱ ተሞቱ በኋላ ነው!” አለኝና አረፈው፡፡

ተዚህ ሱሰኛ ጋር በነበረኝ የውይይት ልምድ በለማ በገበያና በአብዮት አመዴ ሱስ አገጫቸው ወደ ጀርባቸው እስቲዞር የተመቱ “የተማርን ነን” ባዮችን ለመፈተሽ ሞከርኩ፡፡ ከንፈራቸው ተአገጫቸው እስቲወድቅ በጀሮ ጠቢዎች ሱስ ሙዝዝ ማለታቸው ገረመኝና “የይህ አድግ የጀሮ ጠቢ መረብ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ህዝብ ሲጨፈጪፍ፣ ሲገርፍ፣ ሲሰልብ፣ ሲያመክንና እግር ሲቆርጥ እንደኖረ ታውቃላችሁ ወይ” ብዬ ጠየኩ፡፡ ሱሰኞችም ሳያቅማሙ “አዎ እናውቃለን አሉ”። በልቤ ይኸንን ታወቃችሁም ዴግ ነው አልኩና “አብዮትና ለማ የጀሮ ጠቢው ድርጅት መሪዎች ሆነው እንደሰሩም ታውቃላችሁ አይደል?” ስል ሌላ ጥያቄ አስከተልኩ፡፡ አንዴ ወለሉን ሌላ ጊዜ ጣራውን እያዩ ሲያቅማሙ ለሰከንዶች ቆዩና “አዎ አገልግለዋል” ሲሉ መለሱ፡፡ ቀጥየም “ታዲያ ተእንደዚህ ዓይነት የሳጥናኤል ጀሮ ጠቢ መሪዎች ጋር ምነው በሱስ ተጠመዳችሁ?” ብየ ሳፋጥጥ ፊታቸው በዱቄት የተሸፈነውን የአቶ ማሞ እጅጉን ወፍጮ መሰለና “እርሱን እርሳው! ተለውጡ በፊት የሆነ ነው! ያለፈን በይቅርታ ማለፍ ነው! እኛ እምናስበው ለወደፊቱ ነው!” አሉኝና ተነስተው ሄዱ፡፡

ህሊናው እንደ ሎተሪ ካርድ ያልተፋቀና በጨጓራው ብቻ የማያስብ እንደሚረዳው እንደ ጫካ የተጨፈጨፉትን ሰዎች አስመልክቶ “እርሱን እርሳው!” የሚለው ዘግናኝ መልስ ተአሳማ እንኳን መውጣት የሌለበት የአራዊት ቃል ይመስለኛል፡፡ “እርሱን እርሳው!” የሚለው መልሳቸው እስከ ዛሬ አካላቴን እንደ ተሞረደ ጦር ይወጋኛል፡፡ “እርሱን እርሳው!” የሚለው መልሳቸው ይህ አድግ ለአርባ ሁለት ዓመታት በወልቃይት፣ በሁመራ፣ በጠለምት፣ በራያ፣ በአርባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ በጋንቤላ፣ በኦጋዴንና ወለጋ የፈጃቸውን ዳግም የመረሸን ያህል ያመኛል፡፡

“እርሱን እርሳው!” የሚለው መልሳቸው አሁን አብዮት አመዴ የሚመራው ይህ አድግ በጎንደር፣ በደብረታቦር፣ በወልድያ፣ በባህርዳር፣ በመተከል፣ በቡሬ፣ በዳንግላ፣ በአጣዬ፣ በባሌ፣ በሲዳሞ፣ በከፋ፣ በኢሊባቦር፣ በቡራዮ፣ በለገጣፎና አዲስ አባባ የፈጃቸውን ህጻናት፣ እናቶች፣ አሮጊቶች፣ ወጣቶችና ጎልማሶች ዳግም የጨረገዳቸውን ያህል ይዘገንነኛል፡፡

“እርሱን እርሳው!” የሚለው ጨካኝ መልሳቸው ህዝብ ለማዳን ህይወታቸውን የገበሩትን እንደ አሰፋ ማሩ፣ አስራት ወልደየስ፣ ሳሙኤል አወቀ፣ ጎቤ መልኬንና ሌሎችንም ሰማዕታት በአደራ በላነት መንፈስ እንዳስባቸው ያደርገኛል፡፡ “እርሱን እርሳው!” የሚለው መልሳቸው ላለፉት አራት ሺህ ዘመናት አገራችንን ለመጠበቅ ከቀይ ባህር እስከ ኦጋዴን ከኦጋዴን እስከ ሞያሌ ከሞያሌ እስክ ጋምቤላ በሌጣ እግራቸውና በባዶ አንጀታቸው እየኳተኑ የተሰውቱን ጀግኖች ሁሉ “እርሳ!” ያሉኝ እየመሰለኝ እንደ መጥፎ ቅዠት ይዘገንነኛል፡፡

እነዚህ የ“እርሱን እርሳው!” ሰባኪዎች ሶስት ወር ሳይሞላ በሱስ ፍቅር ተአገጫቸው የተንከረፈፈው ከንፈራቸው እንደ ቁርባብች ተሸብሽቦና በትካዜ አሞድሙዶ አየኋቸው፡፡ የ“እሱን እርሳው!” ሰባኪዎች የሱስ ጪፈራቸው እንደዚያ የዕጽ ሱሰኛ ወደ ሀዘን ተቀይሮ አየኋቸው፡፡ የሀዘናቸው መንስዔም አብዮትና ለማ የሚጨፍረውን ባስጨፈሩና የሚሰግደውንም ባሰገዱ ማግስት ስልጣኑን ጠራርገው መውሰዳቸው፣ ባንክ ማዘረፋቸው፣ አዲስ አበባን በራሳቸው ሰው መሙላታቸው፤ አገሪቱን ከሞያሌ እስከ ራያና ወልቃት በደም አበላ ማጥለቅለቃቸው፣ ሶስት ሚሊዮን ህዝብ መንገድ ዳር መጣላቸው እንደሆነ ተረዳሁ፡፡

አብዮትና ለማ በወታደር የሚያስጠብቋቸው ወንጀለኞች አከታትለው ቤተክርስቲያኖች ሲያቃጠሉ፣ ምዕመናን ሲያርዱ፣ ተማሪዎችን ተፎቅ ሲወረውሩና ትምህርታቸው ሲያስተጓጉሉ ሱሰኞች “አብይና ለማ ከዱን!” እያሉ መንዘላዘላቸውን ሲያምኑ ሰማሁ፡፡ ዳሩ ግን በዕጸ-በለስ የደነዘዘ ሱሰኛ ተመልሶ ተዚያው እንደሚዘፈቀው እነዚህ ሱሰኞችም የሂትለር ጆሮ ጠቢ ኦስሎ ሌላ የሱስ ንግግር ሲያደርግ ተመልሰው ተሱሷቸው እንደ ጨርቅ ተዘፍዝፈው አየሁ፡፡

የአባቶቻችን አገርና ታሪክ ሲክድና እንደ ሽንኩርት ሲተክትፍ የኖረውን የሂትለር አገልጋይ “የአያቶቻችንን ገድል ተናገረ” ብለው ተፈላ ውሃ እንደ ገባ ጨው ባንዴ ፍርክስክስ ብለው ሲደልቁ ተመለከትኩ፡፡ የሂትለሩ ጀሮ ጠቢ በተሸለመበት ወቅት በመላ አገሪቱ የፈሰሰው የአማራ ደም፣ ወህኒ እሚማቅቁት የአማራ ወጣቶች፣ የታረዱት ክርስቲያች፣ ተቀጥቅጣ ያለፍችዋ የጨቅላ እናት፣ ተሜዳ የፈሰሱት ሴቶችና ህጻናትም በሱስ አብደው ተመጨፈር እንዳላዳኗቸው ተረዳሁ፡፡

የሚገርመው ደሞ ተደላቂዎቹ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊው ሂትለር በሃያ ሰባት ዓመታት የጨረገዳቸው አማሮች ወገኖች መሆናቸው ነው፡፡ የአማራ ሱሰኞች አዳርና ውሎ እንደዚያ የዕጸ-በለስ ሱሰኛ አንዴ ዘፈን ሌላ ጊዜ ለቅሶ መሆኑ የሚያሸማቅቅ ነው፡፡ እነዚህ አሳፋሪ ሱሰኞች በመጀመርያው የሱስ ወረርሽን “አብይ ሙሴ ነውን” ደለቁ፡፡ ሶስት ወር ሳይሞላ አለቀሱ! በሁለተኛው ዙር ወረርሽኝ ደግሞ እስቲያልባቸው “አብይ ኖቤልን” ጨፈሩ፡፡ ይህ አስጨፍሮ የሚያስለቅስ ሱስ ተሱሶች ሁሉ የከፋው ነው፡፡ ተእንደዚህ ዓይነቱ ሱስ መፋታት በእርግጥም ከባድ ነው፡፡ ቢሆንም መዳኛው መፍትሄ ተሱስ መላቀቅ ብቻ ነው፡፡

የአማራ ሱሰኛ ሆይ! ይኸ እንደ ጅል ፍቅረኛ የሚያንዘላዝልህ ሱስ ሊያጠፋህ የሚችል መሆኑ የማይገለጥልህ ለምንድ ነው? በሌሎች እምነት ጥለህና በሱስ ሰክረህ የምትተኛው ስንት ሌሊት ነው? ተድንጋይ ማምረቻው ሳይወቀሩ የወጡ ጀሮ ጠቢዎች የሚያጃጅሉህ እስከ መቼ ድረስ ነው? የአማራን መቃብር የተመኘውን የሂትለር ሎሌዎች እንደ ናዚ ተሳታፊዎች ለፍርድ ማቅረብ ሲገባህ የምታጨበጭብላቸውና የምትሸልማቸው ለሥጋህ ወይስ ለነፍስህ እንዲበጅ ነው?

የአማራ ሱሰኛ ሆይ! እባክህ የሽሮ ፍትፍትህን ጎስጉስና ስካርና ሱስህን ፈውስ! ተክብርህ ለመኖር የሂትለር አገልጋዮችን መመርኮዙን ተውና በራስህ አንገት ጥና! ላንተም ሆነ ለኢትዮጵያ መዳኛ የጎበዝ አለቅነት ሥርዓት ነውና ወደ ጎበዝ አለቃህ አቅና! ተእየሩሳሌም እስከ ማደጋስካር የደረሰውን ግዛትህን የዘረጋው የጎበዝ አለቃ እንጅ መጤው የጥበቃ ጓድ ወይም አውደልዳይ ፖሊስ ሥርዓት እንዳልሆነ ታሪክን መርምር፡፡

አገርህ የተመሰረተችው በጎበዝ አለቆች እንጅ ኮሎኔልና ጀኔራል በሚሉ የተውሶ ማእረጎች እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ የቱርክ፣ የግብጥንና የጣሊያንን ወራሪዎች ደንደስ የተሰበረው በሰላም ጊዜ ገበሬ በጦር ወቅት ሰራዊት በሆኑት የጎበዝ አለቃዎች መሆኑን አጢን፡፡ በኢትዮጵያ ሰላምን፣ ሥርዓትን፣ እምነትንና የመንፈስ ልእልናን ሲያስጠብቁ የኖሩት ጎበዝ አለቃዎች መሆኑን እወቅ፡፡

የአማራ ሱሰኛ ሆይ! አገርህ ቁልቁል መንሸራተት የጀመረችው የጎብዝ አለቅነት ሥርዓት መፍረስ ተጀመረበት ጊዜ መሆኑን ተገንዘብ፡፡ ጎበዝ አለቃ እንደ ፖሊስና ካድሬ በነፍሰ-ገዳይዎች እንደ ቀንበር የሚጫንብህ ሳይሆን ከአብራክህ እንደ ምጥ የሚወጣ የሥጋና የመንፈስ ልጅ መሆኑን እመን፡፡ የጎበዝ አለቃ በጀግነቱ፣ በምግባሩና በመንፈስ ልዕልናው ራስህ የምትመርጠው የአገር ደጀን መሆኑን ተረዳ፡፡ የጎበዝ አለቃ ወንበዴ ገዥዎችን ልክ የሚያስገባ የማህበረሰብ ዋስትና መሆኑን አስተውል፡፡

የጎበዝ አለቃ የአካባቢውን ሰላምና ደህነንት የሚያስከበር የተዋጣለት መሪ መሆኑ እወቅ፡፡ የጎበዝ አለቃ ዳር ድንበርህ ሲደፈር ፎክሮ የጠላትን ጉርንቦ የሚያንቅ አንበሳና ነበር መሆኑን ተገንዘብ፡፡  ጎበዝ አለቃ ባንዳን እንደ ጎባጣ ሞፈር አርቆ ልክ የሚያስገባ የእርሻና የጦር ገበሬ መሆኑን እመን፡፡ ጎበዝ አለቃ ባንዳን እንዴት አርቆ እንደሚያስተካክል ለመረዳት ገድለ-በላይ ዘለቀና ገድለ-አበበ አረጋይን ለማንበብ ፈቃደኛ ሁን፡፡

ጎበዝ አለቃ በሱስ ተጠምዶ ለሂትለር ሰላዮች እስክስታ የማይመታ በአካልና በመንፈስ የጠና የህብረተሰብ አለኝታ መሆኑን አጢን፡፡ ጎበዝ አለቃ ለነጻነቱና ለፍትህ ሲል ለልጆቹም የማይሳሳ ባለማተብ ጀግና መሆኑን ተበላይ ዘለቀ ተማር፡፡ ጎበዝ አለቃ ፍትህን ተጀግንነት፤ እምነትን ተሥራ የሚያዋህድ የተባረከ የአማራ እሴት መሆኑን ተረዳ፡፡

ስለዚህ ሱሰኛ አማራ ሆይ! ተሱስህ ተላቀህ ወደ ጎበዝ አለቃህ አቅና፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

ዋቢ

  1. 10 Most Wanted Nazi War Criminals, History channel https://www.history.com/news/10-most-wanted-nazis
  2. The last Nazi hunters, https://www.theguardian.com/news/2017/aug/31/the-last-nazi-hunters
  3. Nazi war crimes suspect, 94, faces German youth court trial https://www.theguardian.com/world/2018/sep/21/nazi-war-crimes-suspect-faces-trial-german-youth-court

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

 

1 Comment

  1. It was said for decades that Amara had a state named Amara state eventhough Wolqait Raya stolen even SUDAN TAKING AMARAS LAND , the “Amara state” always until now is the only state that let’s non Amaras take over their state government with the Bereket Simon and now Abiy Ahmed controlling their state with Amara officials having no power. Amara to administer its own state all ethnicities of Ethiopia should get the chance to have their own statehood which they administer. Amaras question is Intertwined with the close to eighty Ethiopian ethnicities. Amaras conscious doesn’t allow Amara to be selfish.

    Now there are two urgent choices left to choose from
    1. ABOLISH THE HALF-ASS ETHNIC FEDERALISM
    2. FULLY IMPLEMENT ETHNIC FEDERALISM TO ALL ETHNICITIES EQUALLY AT THE SAME TIME WITHOUT FAVORITISM TO FEW ETHNICITIES OVER OTHERS, there is no other way around it besides these two above.

    Fully implementing ethni federalism means Rather than giving statehood to one ethnicity and making others wait to get statehood , the reformed federal institution which got billions to spend should easily let all eighty ethnicities hold a referendum for statehood at the next election and get over the statehood ethnic controversy Ethiopians are facing all at the same time. It was not fair for ethnicities populated close to Tigray and above to get their own statehood while others did not get their own statehood under TPLF, this unfairness led to uncontrollable population growth just because all ethnicities wanted to have their own statehoods. If we give statehood to all ethnicities regardless of their population size then the population growth problem of Ethiopia can start to be manageable.
    In Ethiopian history for the last fifty years Activism for statehood often led to civil wars , violence , displacements , conflicts and animosities that lasted for generations, so the East African peace prize winner PM should turn his eyes to within Ethiopia and help Ethiopian ethnicities skip the violence part of statehood activism and give all ethnicities the chance to hold a referendum for their own statehood at the same time right now or shop sh ethnic c federalism right away. It could easily be included in the next election of May 2020 just by asking ethnicities if they want their own statehood or not if giving this referendum is not an option then abolish this half-ass ethnic federalism.

    Peace among ethnicities had ended up deteriorating to this stage in 2019 because all ethnicities had not been treated equaly by Meles Zenawi Lencho Letta constitution group with few having their own States and many others not having their own states. Wallelign Mekonnen didn’t tintend what he wrote to be implemented so unfairly.
    If all were given the referendum to create their own states by Lencho Letta and Meles Zenawi transitional.government then all these civil wars , displacements , church burnings , exiles and crimes we see today would not have taken place.

Comments are closed.

4
Previous Story

ፍራሽ አዳሽ – 4 – ተስፋሁን ከበደ -ኛ ሰፈር ሰው አዲስ ነገርና ለውጥ ሲያይ ይፈራል ጦቢያ ግጥምን በጃዝ

index 300x204 1
Next Story

የአገሪቱን ሀብት ሲበዘብዙ የነበሩ ኃይሎች ዛሬ ደርሰው ለፌዴራሊዝም ጠበቃ ነን ሲሉ ለእኔ የሚመስለኝ ኢትዮጵያውያን ላይ ማሾፍ ነው” – ዶክተር ዓለሙ ስሜ በጠ/ሚ ጽ/ቤት ሚኒስትር

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop