November 30, 2019
13 mins read

ጋሰለ አረሩ፤ አዴፓ ብአዴን፤ ብልጽግናም ይህ አድግ ነው! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

መልከ-ጥፉን በስም ቢደግፉት መልከ-ጥፉነቱ በላፒስ ተፍቆ አይጠፋም፡፡ በንጹሀን ደም እጅና እግሩ የተጨማለቀው፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጠመውና አገር እስከማስገንጠል ብሄራዊ ክህደት የፈጠመው ይህ አድግ “የብልጥግና ፓርቲ ነኝ!” እያለ ጭራቅ መልኩን በስም ሊደግፍ እየጣረ ነው፡፡ መንዘላለዘልና መጃጃል የማይሰለቸው ስንቱ ዜጋም የይህ አድግን ብልጽግና ሊውጥ አፉን እንደ ሰማይ ከፍቶ እየተጠባበቀ ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት በመርዝ በተለወሰ ከረሚላ ከአንዴም ሁለቴ፤ ተሁለቴም ሶስቴ የሚንዘላዘል ዜጋ ዓይምሮው በላቦራቶሪ መፈተሽ ያለበት ከንቱ ፍጡር ነው፡፡ በራሱ ተስፋ ቆርጦ በሱሰኛ ይህ አድጎች እምነት ጥሎ የሚንዘላዘል አማራ የጅል ጅን ስለሚኖርበት ዲ ኤን ኤ (DNA)ው መጠናት ያለበት አሳዛኝ ፍጡር ነው፡፡

የብአዴን “አዴፓ ነኝ” ማለት የአረሩን “ጋሰለ ነኝ!” ማለት የሆነውን ያህል የይህ አድግ “ብልጥግና ነኝ!’ ማለትም የአረሩንና የጋሰለን ታሪክ እንደገና የሚያስተርክ ነው፡፡ ባደኩበት ሰፈር አቶ አረሩና አያ አዳነ የሚባሉ ሰዎች ይኖሩ ነበር፡፡ አቶ አረሩን ኮስማናዋ እናቱ እማማ ሐብትሽ ምን እያበሉ እንዳሳደጉት አላውቅም ቁመናው የገደል ግማሽ ያኻክል ነበር፡፡ ጥምቡልዝ መልኩም የተወቀጠ ኑግ ይመስል ነበር፡፡ አቶ አረሩ የገደል ግማሽ እንደሚያህል ለመግለጥ የሰፈሩ ሕዝብ ” አረሩ ብቻውን የቤት ጣራ ተሸክሞ መሄድ ይችላል” ይለው ነበር፡፡ አያ አዳነ በተቃራኒው ቁመናዋ እንደ ስንበሌጥ የሰነነች መልኳም በቀይና በቀይዳማ መካከል ያለች ቆፍጣና ጎበዝ ነበረች፡፡ አቶ አዳነ በሰንጢ ንግግሯ እንደ አለቃ ገብረ ሃና የምትታወቅ ጠቢብ ነበረች፡፡ የአያ አዳነን የንግግር ሥስለትነት ለመግለፅ ማህበረሰቡ “የአዳነ ንግግር ያልጋለ ብረት ከመቅፅበት ይቆርጣል” ይላት ነበር፡፡

በዚሁ ሰፈር ካቶ አረሩ በተጨማሪ አረሩ የሚባል ጠብደል ጥቁር አለሌ ይኖር ነበር፡፡ ስለ አህያው አረሩ ባላውቅም አቶ አረሩ የህዝቅኤል ጋቢሳን ያህል ሥሙን ይጠላው ነበር። አቶ አረሩ ከአለሌው ለመለየትና  አረሩ የተባለውም የተቀቀጠ ኑግ በመሰለው ቆዳው ምክንያት ስለመሰለው ባካባቢው ባልተለመደ መንገድ ስሙን ጋሰለ ወደ እሚባል ስም ቀየረና አረፈው፡፡ ይኸንን በአካባቢው ያልተለመደ የሥም ለውጥ  የተረዳ አብዛኛው የአቶ አረሩን ሥም በየቤቱ እያነሳ እየጣለ ሌላውም “ሥሙን መለወጥ መብቱ ነው!” እያለ የአንድ ሰሞን የቡና ቴራቲም ወሬ አደረገው፡፡

ብዙውን ጊዜ ተመንጋው ጋር የማትነዳዋ አያ አዳነ ግን የአቶ አረሩ ድንገተኛ ሥም ቅየራ የአንድ ሰሞን የቡና ወሬ ሆኖ እንዲቀርና እንደዚህ ዓይነት ባህል እንዲለመድም አልፈቀደችም፡፡ አብዛኛው ሰው አቶ አረሩን በአዲሱ ስሙ ጋሰለ እያለ ሲጠራው አያ አዳነ ግን በሥሙ አፍሮና በማንነቱ ተሸማቆ ስም በቀየረው አቶ አረሩ በሽቃ በማያስፈልገው ቦታ ሁሉ “አረሩ” ብላ እየተጣራች አስቸገረችው፡፡ ይኸንን የአያ አዳነን ጥኑ አቋም የተመለከቱ ሽማግሌዎችም አረሩን በፈለገው ስም ጋሰለ ብላ እንድትጠራው  አያ አዳነን ቢለምኗትም “ሥምን የሚያወጣው ወላጅና እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ እናቱ እማማ ሐብትሽ ባወጡለት ሥም እጠራዋለሁ” ስትል በአቋሟ ጠናች፡፡

ባያ አዳነ እምቢተኝነት ያልተደሰተው የድሮው አረሩ ያሁኑ አቶ ጋሰለ በበኩሉ “አዳነ ጋሰለ ብሎ ታልጠራኝ ምላሱን እቆርጠዋለሁ” እያለ በሰፈሩ ማስወራቱን ቀጠለ፡፡ ዳሩ ግን ጋሰለ የሚባል ሥም ከአያ አዳነ አንደበት እንኳን በውኑ በህልሙና በቅዠቱም አልወጣ አለ፡፡ እንዲያውም አያ አዳነ በበነነ በተነነው “አረሩ….” የሚለውን ቃል ከወትሮውም በበለጠ እያነሳች አቶ ጋሰለን ማሳቀቁንና እንደዚህ ዓይነት በራስ ተሸማቆ ሥምን የመቀየር ባህል እዳይለመድ ማስተማሩን ቀጠለች፡፡

አቶ ጋሰለና አያ አዳነ በእንዲህ ዓይነት ውጥረት ውስጥ ሳሉ በአንድ የሰንበት ቀን አያ አዳነ አቶ ጋሰለ ጋቢውን ተከናንቦ ድንኳን መስሎ አህያው አረሩ ሳር ከሚግበት መስክ ተቀምጦ አየችው፡፡ አያ አዳነም በአቶ ጋሰለ አጠገብ ስታልፍ “ደህና አደርክ አረሩ” የሚል ሰላምታ አቀረበች፡፡ አቶ ጋሰለ ሰላምታውን እንዳልሰማ ሁሉ “ምን አልክ?” ሲል በንዴት ጠየቀ፡፡ አያ አዳነም በሽመሉ አለሌውን አረሩን እየጠቆመች “ያኛውን አረሩ ነው!” ስትል መለሰች፡፡

እናቱ እማማ ሐብትሽ ያወጡለትን ስም በማንነቱ አፍሮ እንደቀየረው አቶ አረሩ በቀደም ብአዴንም ሥሙን አዴፓ ብሎ ቀየረው፡፡ አሁን ደሞ ይህ አድግ በማንነቱ አፍሮ ፈጣሪው ህወሀት ያወጣችለትን ሥም ብልጽግና በሚል አብለጭላጭ ሥም ቀየረው፡፡ በአለሌው አረሩ ሥም እንደተሰየመው አቶ አረሩ ሁሉ ይህ አድግም ቀላሹ ህወሀት ባወጣችለት ሥምና በባርነት ግብሩ ተሸማቀቀ፡፡ ይህ የተሸማቀቀ ወንጀለኛ ድርጅትም ሥሙን ወደ ብልጥግና ቀየረና አረፈ፡፡

ዳሩ ግን ጋሰለ የሚለው ስም የአቶ አረሩን መልክና ምንነት እንዳልቀየረው ሁሉ ብልጥግና የሚለው ሥም የይህ አድግን መልክና ምንነት አይቀይረውም፡፡ ብልጥግና የሚለው ስም ይህ አድግ ለሰላሳ አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ የፈጠመውን ወንጀልና ክህደት እንደ እንዶድ አያፀዳውም፡፡ ብልጥግና የሚለው ሥም ይህ አድግ የህወሀት የእጅ ስራ መሆኑን፣ ህወህትም የሻብያ ዲቃላ መሆኑን፤ ሻብያም የታሪካዊ ቅኝ ገዥዎችና አረቦች የማደጎ ልጅ መሆኑን አይቀይረውም፡፡

ብልጽግና የሚለው ስም ብአዴንን ተአሽከርነት አያዋጣውም፡፡ ብልጽና የሚለው ስም ብአዴንን ጌቶቹ ሲያዝዙት የአማራን ወጣቶች ተማሰርና ተመግደል አይገታውም፡፡ ብአዴን አጋሰስ ሆኖ እየተጫነ ያዘረፈውን ሐብት አያስመልሰውም፡፡ ብልጽግና የሚለው ሥም ብአዴን የአማራን ዓይን ጨፍኖ ለህወሀት ያስረከባቸውን ራያን፣ ሁመራና ወልቃይትን አይመልስም፡፡

ብልጽግና የሚለው ማታለያ ብአዴን ከቢሮው ጣራ አልሞ ተኳሽ አንጠልጥሎ ባህርዳር ያሰዋቸውን ወጣቶች ነፍስ አይመልስም፡፡ ብልጽግና የሚለው ማጭበርበሪያ ስም ብአዴን በህወሀት አሽከርነት በድብቅ ስፍራዎች ያስቀበራቸውን፣ ያሰለባቸውን፣ ያስገረፋቸውን፣ ያስጠለፋቸውና አካለ ጎደሎ ያስደረጋቸውን ዜጎች አይታደግም፡፡ ብልጽግና የሚለው ሥም ብአዴን በአምባ ጊዮርጊስ፣ በጎንደር፣ ደብረታቦር፣ ዳንግላ፣ ቡሬ፣ ወልዲያ፣ ማጀቴና ሌሎችም ቦታዎች ያስፈጃቸውን ዜጎች አያስረሳንም፡፡

ብልጽግና የሚለው ማታለያ ብአዴን “አያገባኝም” እያለ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በጉራፈርዳ፣ በጎሬ፣ በወለጋ፣ በመተከል፣ በሀገረ ማርያምና ሌሎችም ሥፍራዎች ያስፈጃቸውንና ያሰደዳቸውን አማሮች ታሪክ አይፍቀውም፡፡

ስለዚህ አቶ ጋሰለ አረሩ ነው፡፡ ግልቡ ብልጽግናም ኢህዴግ ነው፡፡ አዴፓም ብአዴን ነው፡፡ እማማ ሐብትሽ  ለልጃቸው ያወጡለት ሥም አረሩ ነው፡፡ ከአማራ መቃብር ሪፐብሊኳን ለመመስረት ህወሀት ያደለበችው አለሌ ይህ አድግ፤ ለበኩር ልጇ የሰጠችው ሥም ደሞ ብአዴን ነው፡፡

አረሩ፣ ይህ አድግም ሆነ ብአዴን ካለ እናቶቻቸው ፈቃድ ሥማቸውን መቀየር ክህደት ነው፡፡ አረሩ ሺ ጊዜ ሥም ቢቀይር እናቱም ሺ ጊዜ እማማ ሐብትሽ ናት፡፡ ብልጽግና የተባለው ይህ አድግም ሺ ጊዜ አስቀያሚ መልኩን በስም ሊደግፍ ቢሞክር ፈጣሪው ጭራቁ ህወሀት ነው፡፡ ብአዴንም ሺ ጊዜ ሥም ቢቀይር እናቱ ሰይጣኗ ህወሀት ናት፡፡ በአፈጣጠራቸው አፍረው አረሩ፣ ይህ አድግም ሆነ ብአዴን ሥማቸውን ቢቀይሩም እናታቸው፣ መልካቸው፣ ግብራቸውንና ታሪካቸው ዘላለማዊ ናቸው፡፡

ስለዚህ መልካቸውን፣ ግብራቸውንና ታሪካቸውን በሚገልጡትና እናቶቻቸው ባወጡላቸው ሥሞች አረሩ፣ ብአዴንና ይህ አድግ ተብለው ቢጠሩ መልካም ነው፡፡ ጋሰለ አረሩ፣ አዴፓ ብአዴን፣ ብልጽግናም ይህ አድግ ነው፡፡

 

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.

5 Comments

  1. But the problem with you is beadin leaders were non amharas who did all that to amharas like beteket, addisu , and cos but now better with Yohannes , Demele and cos . Even if not as expected at least amharas are in better condition now though not perfect , they are in the middle of the mountain to reach top needs more struggle before it is late and pulled by guys like you and your cos . Complaint and negativity doesnot take nowhere rather support and organize your self .
    The previous mistake is not them only , what did we do you and me just bla bla talk help them encourage in the mean time organize ,at least amharas have their own media , party and movement which will never even think before that is why Professor asrat was killed by meles for saying Amhara at least now peoples are aware and organize freely though there is some problem in the name of Amhara .
    The other thing there are peoples inside who want to pullback the struggle may be like you, negativity is the enemy of freedom struggle , wake up from your sleep and analyze the situation do your best and help .Now by far amharas are about 50-60 percent better than before not still 100 percent which you expect .

  2. Ato Enasib, the supporter perhaps member of “ADP”

    Are you saying what the writer wrote below is untrue or you do not care about the looting of Amara resources, and the lives of the massacred Amaras through out the country? You will never climb a mountain lead by traitors-Badin=ADP. Members of ADP are slaves that OPDO bought cheap from TPLF.

    Think about it. It is this much ADP embarrassed Amaras.

    “ብልጽግና የሚለው ስም ብአዴንን ተአሽከርነት አያዋጣውም፡፡ ብልጽና የሚለው ስም ብአዴንን ጌቶቹ ሲያዝዙት የአማራን ወጣቶች ተማሰርና ተመግደል አይገታውም፡፡ ብአዴን አጋሰስ ሆኖ እየተጫነ ያዘረፈውን ሐብት አያስመልሰውም፡፡ ብልጽግና የሚለው ሥም ብአዴን የአማራን ዓይን ጨፍኖ ለህወሀት ያስረከባቸውን ራያን፣ ሁመራና ወልቃይትን አይመልስም፡፡

    ብልጽግና የሚለው ማታለያ ብአዴን ከቢሮው ጣራ አልሞ ተኳሽ አንጠልጥሎ ባህርዳር ያሰዋቸውን ወጣቶች ነፍስ አይመልስም፡፡ ብልጽግና የሚለው ማጭበርበሪያ ስም ብአዴን በህወሀት አሽከርነት በድብቅ ስፍራዎች ያስቀበራቸውን፣ ያሰለባቸውን፣ ያስገረፋቸውን፣ ያስጠለፋቸውና አካለ ጎደሎ ያስደረጋቸውን ዜጎች አይታደግም፡፡ ብልጽግና የሚለው ሥም ብአዴን በአምባ ጊዮርጊስ፣ በጎንደር፣ ደብረታቦር፣ ዳንግላ፣ ቡሬ፣ ወልዲያ፣ ማጀቴና ሌሎችም ቦታዎች ያስፈጃቸውን ዜጎች አያስረሳንም፡፡

    ብልጽግና የሚለው ማታለያ ብአዴን “አያገባኝም” እያለ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በጉራፈርዳ፣ በጎሬ፣ በወለጋ፣ በመተከል፣ በሀገረ ማርያምና ሌሎችም ሥፍራዎች ያስፈጃቸውንና ያሰደዳቸውን አማሮች ታሪክ አይፍቀውም፡፡”

  3. Naming is your types of person job I used to oppose and suffered by woyane being an amhara and I donot like poletics but like truth , many in the name of free writing and suggestion confused people and pull back struggle ,I donot want to say you Dw May be you are .
    But the truth amharas are the most wisest and cool people which can read what you think even before speak any amhara will tell you what you want and who you are even before you speak .
    The other thing what I am saying is not amhara is safe and excellent condition what am saying is by far better today than yesterday and sure best tomorrow by struggle of peoples , amharas are weather you like it or not in the middle of their struggle not done yet but I have 100 percent belive with amhara struggle with abn, adp, atbegnoch , fano all are aware thank you to woyane he teaches the amhara people the good lesson in the hard way . Unity is power and the core of struggle what ever they are . Cheers .

  4. This the party of Enasib. Woy enasib! Minew ante bitasib tebanda patietef

    “አዴፓ ዝንታለም ቅሌት ልብሱ ?!
    —————————————
    በቀደምለት በህዳር 13 ብአዴን— አዴፓ “39 የትግልና የድል” ታሪኬን እዘክራለሁ ባለበት በአንድ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ በተዘጋጀ መድረክ ተጋብዤ ነበር።
    በዝግጅቱ ላይ “የአማራ ህዝብ ወቅታዊ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች” የሚል መወያያ በእኔ ፣ ሌሎች ሁለት የአዲስ አበባ አዴፓ አመራሮች ደግሞ በጋራ ስለአልማ የወደፊት አቅጣጫዎች አንድ ሰነድ ካቀረቡ በኋላ ለውይይት ሶስት ሆነን መድረክ ላይ ተሰየምን።
    ———————
    ከአንድ ሰአት በላይ በዘለቀው “ውይይት” ከታዳሚው በኩል በአዴፓ ላይ የወረደው የትችትና የወቀሳ ናዳ እጅግ የሚያሳቅቅ ነበር። የተናጋሪዎቹ አንደበት እሳት ይተፋል ማለት ይቀላል።
    አዴፓ የአማራን ህዝብ መምራት የሚጀምረው መቼ ነው? በዚህ ለውጥ ሂደት ውስጥም አማራውን አሳልፋችሁ ልትሰጡ ነው ወይ? ከሰው በፊት ለውህደትና ክስመት መንቀዥቀዣችሁ ለምንድነው? ህዝቡንስ ለወጉ እንኳን መች አማከራችሁት? የመሳሰሉት ጥያቄዎች አልቀሩም።
    ———————
    አብዛኞቹ ተናጋሪዎች እጅግ የተቆጡበት ጉዳይ በኦሮሚያ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአማራ ተማሪዎች ላይ የሚፈፀመውን ወከባ ፣ ጥቃትና ግድያ ዘመቻ አስመልክቶ አዴፓ አንዲት ቃል እንኳን ትንፍሽ ያለማለቱ ነበር።
    አንዱ አስተያየት ሰጭ እንዲያውም በህዝባችን ላይ ይህ ሁሉ የህልውና ስጋት እየናጠጠ ልማት ፣ ውህደት የሚል የቅንጦት ፕሮግራም ማዘጋጀታችሁ የጤና አይመስልም ብለው ነበር።
    በእውነቱ አዴፓ በአማራ ተማሪዎች ላይ ያ ሁሉ ግፍ ሲፈፀም በህግ አምላክ ብሎ ለመጮህ እንኳን ያሳየው ዳተኝነት ዛሬም የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ መሪ የለውም ያሰኛል። ድርጅቱ መቼም ከተጠያቂነት የማያመልጥበት ታላቅ የፖለቲካ ስህተት ነው።
    —————
    በእለቱ ከሁሉም በላይ ታዳሚውን ያስደመመው አንድ የአብን አባል ነኝ ያለ ግለሰብ ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ ደረሰብኝ ያለው ገጠመኝ ነበር። እንደሚከተለው በራሱ አንደበት ላቅርብለት።
    “የምኖረው ለገጣፎ ነው። በሰኔ 15 ሌሊት ሀገር አማን ብዬ ተኝቼ ሳለሁ የቤቴ በር በሃይለኛ እርግጫ ተሰበረ። በወቅቱ ተደናግጬ ስነሳ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች `ና ውጣ አንተ የምኒልክ ድኩላ` በማለት እያላጉ ወስደው በአካባቢው ካለ ፖሊስ ጣቢያ ሽንት ቤት ወረወሩኝ።
    በተከታዮቹም ቀናት ሌሎችንም አማሮችን በተመሳሳይ እየለቀሙ ማምጣት ቀጠሉ። ታሳሪዎች በተፈጠረው ነገር እየተጨነቅን ሳለ ፣ የአዴፓው ም/ከንቲባ ኢንጂነር እንዳወቅ ራሳቸው ተጠርንፈው ሲወረወሩ አይናችንን ማመን ተስኖን ነበር። የት ይደርሳል ያሉት ጥጃ ሉካንዳ ተገኘ የሚባለው ደረሰ።
    ኢንጂነር ከንቲባው እንደሌሎቻችን በእስር ሳይከርሙ ቢፈቱም ፣ በወቅቱ የአማራ ህዝብ ምን ያህል ወደሌላ የውርደት አዙሪት እየገባ መሆኑን አንስተን ተወያይተናል። አንዳንድ አንኳር ጉዳዮችንም ቃል አስገብተናቸው ነበር።
    እኔም ከታፈስኩ ከአንድ ወር ቆይታ በኋላ ለመፈታት በቅቻለሁ። ዛሬ ወደዚህ ስብሰባ የመጣሁትም ም/ከንቲባ እንዳወቅ የገቡልንን ቃል ምን እንዳደረሱት በጀማው ፊት ለመጠየቅ ነበር። በዝግጅቱ ባለመገኘታቸው አዝኛለሁ።
    ይሁን እንጂ አዴፓን በተመለከተ ያለችኝ እንጥፍጣፊ ተስፋ ትላልቅ ባለስልጣኖቹ እንኳን እንደ በግ እየተጎተቱ ከመታሰር ለመታደግ የማይችል ወራዳ መሆኑን በአይኔ በብረቱ በማየቴ አክትሟል። አማራውን የሚያድን ከአብን ውጭ ተስፋ የለም!” ሲል ንግግሩን ደመደመ።
    ————————
    መድረኩን ይመሩ የነበሩት የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ራሳቸው በጠሩት ድግስ ላይ ይህ ሁሉ መዓት ይወርድብኛል ብለው እንዳልጠረጠሩ ሁኔታቸው ያሳብቃል። ንዴታቸውን እንደምንም ውጠው ምላሽ ለመስጠት ሲፍገመገሙ ያሳዝኑ ነበር።
    በበኩሌ ከንፈር ከመምጠጥ ውጭ ማን ነገረ ፈጅ አደረገኝና ልርዳቸው? እንዲያው ከጎናቸው ተቀምጬ የ39 ዓመታት አኩሪ የትግልና የድል ገድል እያሉ በራስ ላይ መሳለቅ ምስጢሩን አሰላስል ነበር። እስከዛሬም ሊገለጥልኝ አልቻለም።
    አይ አዴፓ መቃብር ሃውልቱ ላይ “በቅሌት ኖሮ በቅሌት ሞተ” ተብሎ ቢፃፍለት አይደንቀኝም!”
    © Tewodros Hailemariam

  5. Funny you can name it I swear to lord am not and I never be a member of political party in Africa mainly poletics is business to have luxury life in misery of millions either , beadin , tplf , opdo or what ever . What am saying is in this critical time the only solution is working together in unity to avoid another slavery from tplf to olf if you hear mr. Demeke and Yohannes it is obvious that they are under immense stress and struggle even they said that no more another superiority , despite all faults the only solution is keeping the struggle together in unity even with adp since no strong power like them at this time the other thing mr . Ayalew as you have said abn , at least in this era where Amhara has its own media do you think they will keep quite if there is severe danger and another complete slavery of Amhara I have trust at least by abn, fano , another Amhara parties not 100 percent though with adp but peoples try to put Amhara for divide and slave policy , work hard support organize blaming and naming doesnot take nowhere . Now thanks to lord Amhara know and aware of his enemies and priblems . I donot like poletics but can die for freedom mr. , Amhara is now in better condition again and again than before but still needs more struggle with unity , keep the organizations , struggle the only way for equality, justice and freedom .

Comments are closed.

Previous Story

ለማ መገርሳ በመደመር ፍልስፍና እንደማይስማሙ ገለፁ

Next Story

እነሆ የዓለም ዓይኖች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ አነጣጥረዋል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop