November 10, 2019
22 mins read

” ከታሪክ ጠባሣ ለመማር ፍቃደኛ ያልሆነ ህዝብ እና መንግሥት ታሪክን ለመድገም ይገደዳል።” (ሰው ዘ -ናዝሬት)

ከጠ/ሚ መለሥ ዜናዊ በፊት የዚች ሀገር ፕሬዝዳንት የነበሩት የኮ/ሌ መንግሥቱ ዕጣ  ፈንታ እንደ ዓፄ ኃይለሥላሴ ያለመሆን እድለኛ ያሠኛቸዋል።በግል እሳቸውን በቻ።በእርግጥ “የመጀመርያው አውሮፕላን ጠላፊ…” ተብለዋል።ይሁን እንጂ ሲአይ ኤ ኩብለላውን አሥቀድሞ አያውቅም ብለን እሳቸውን እንደ አውሮፕላን ጠላፊ መቁጠር የዋህነት ነው።እንኳን ሲ አይ ኤ የኢትዮጵያ ደህንነት ክፍል ወይም” የነጭ ለባሾች ” ኃላፊ የነበሩት ኮ/ሌ ተሥፋዬ ወልደሥላሴ ፣ሥለ ጓዳቸው የሐራሬ ሥደት   አስቀድመው ያውቁ ነበር።  ለኬጃቢም ሆነ ለሞሳድ ወዘተም። የሳቸው ወደ ሟቹ ሮበርት ሙጋቤ ሀገር ዙምቧቤ ኩብለላ  ድብቅ ሚሥጥር  ሊሆን ከቶም አይችልም።
ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ፣በአለቀ ሰዓት  ነበር ሽንፈታቸውን መቀበላቸውን ና ሥልጣንንን ለመልቀቅ እንደማያመነቱ ፣ረጅሙን የሥንብት ንግግር በማድረግ ” ጉዳዩ የወንበር ጉዳይ ከሆነ፣ ለወያኔው ዓምበል ወንበራቸውን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን በገለፅ ያሳወቁት።
     እርግጥ ነው፣ የእሳቸው መንግሥት ከግነቦት 1981 የእነጀነራል ፋንታ በላይ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እና እሱን ተከትሎ በቆሰለ ነብርነት በሰሜን ግንባር ጦሩ ፊት በመሥመራዊ መኮንኖች እና በጦር አዛዦቻቸው ላይ በወሰዱት ዘግናኝ እርምጃ ወይም በፈፀሙት እና በሥፈፀሙት  ተገቢ ያልሆነ ተግባር፣ መንግሥታቸው የራሱን ጉድጎድ መቆፈሩን አንዘነጋም።
ጠንካራውን እና ልበ ሙሉውን ሀገር ወዳድ እና የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን ጦር ሠራዊት በሥነ ልቡና በመግደል እጁን አሥረው ለሻቢያና ለወያኔ እርድ ሳይታወቃቸው አሳልፈው የሰጡትም ያኔ ነበር። በዚህ ምክንያትም ለመውደቅ አንድ ሃሙሥ የቀረውን  የወደቀ መንግሥት ወይም መሠረቱ የተናጋ መንግሥት ነበር ሰውየው እየመሩ የነበረው። …
ሰውየው ፣  ከ1981 ዓ/ም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ እየመሩ ያሉት  የወደቀ መንግሥት መሆኑ ቢታወቅም  ፣  –መንጌ  ለገዛ አንድ ነፍሳቸውና ለቤተሰባቸው እንጂ፣ለታሪክ እና ለሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ፣የኩብለላቸውን ያህል አልተጨነቁም ነበር።
     ኢትዮጵያን የባህር በር አልባ በማድረግ ሥንት መቶሺ ኢትዮጵያዊያን የተሰውበትን ባህረ ነጋሺን ለባእዳን መጠቀሚያ ላለማድረግ ፣በመዲናዋ መሽጎ ፣በየጫካው ተደራጅቶ የሚዋጋ አርበኛ በማደራጀት ፣ሻቢያን ያማከለ የባህር በርን የማያሳጣ ድርድርን የማድረግ አማራጭንም ከቶም አላዩም ።
ቢያንሥ እንደ ዓፄ ዮሐንሥ እና ዓፄ ቴዎድሮስ ሁሌም በትውልዱ ለሚዘከር መስዋዕትነት ደንታ ሊኖራቸው ይገባ ነበር። ቢያንሥ ለራሳቸው ዘላለማዊ የክብር ሥም  መጨነቅ ነበረባቸው።  ሆኖም አልተጨነቁም። ከኢትዮጵያዊያኑ ከዓፄ ቴውድሮሥ እና ዓፄ ዮሐንሥ መሰዋትነት አንፃር የሳቸውን ኩብለላ ሥናነፃፅረው ተግባራቸው አሣፋሪ ፣አንገት አሥደፊ ሆኖ አግኝተነዋል።– የሚሉ አሉ።
 ሰውየው ከ1981 ዓ/ም ጀምሮ በበላይነት እያሥተዳደሩት ያለው መንግሥት የወደቀ መንግሥት መሆኑን አልተገነዘቡም ነበር። አማካሪዎቻቸውም በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ያሉ ፣ለማደርም በብርቱ የሚጨነቁ ነበርና በጊዜ ባነው ከላይ የጠቀሥኩትን ለመሥዋት የተዘጋጀ እጅ ጠምዛዥ ጦር ለማደራጀት ሳይችሉ በመቅረታቸው  ኢትዮጵያ ዙሪያዋን በከበቦት ሁለመናቸው ሆድ በሆነ ጅቦች እንደትከበብ አደርገዋል።
 ለዛሬው፣እንዲህ ምሥቅልቅሉ ለወጣ የዘርና የቋንቋ ሥንክሳር እና  ፖለቲካዊ ቦልት ይህቺ ሀገር የበቃችው  በእሳቸው የግል  ሥብእና ላይ ይህቺ ሀገር በመንጠልጠሏና የእምነት ሰዎች ሳይቀሩ” መንጌን” ልእለ ኃያል አድርገው በመቁጠራቸው ነው።ነገር ግን መንግሥቱ ኃይለማርያም አጋጣሚዎችን ሳያወላውሉ ፈጥኖ በመጠቀም እና በተፈጥሮ በታደሉት ጆሮ ግብ አንደበት ተጠቅመው ተሥፋን በሚያምነው ህዝብ ልብ ውሥጥ በመጓዝጎዛቸው እንጂ  ከሌሎቹ የደርግ አባላት የተለዩት ከሰው የተለዩ ፍጡር አልነበሩም።ይህንን እውነት ብዙዎቻችን የተገነዘብነው፣ሰውየው ወደሐራሬ ከኮበለሉ በኋላ ነው።
 ኮ/ሌ መንግሥቱ እንደ አንድ ሀገር ወዳድ ወታደር ለዚች ሀገር ለመሞት አልፈለጉም።ይህ የሚያሳብቀው ደግሞ ሰውየው እልም ያሉ ግብዝ እና አምባገነን ብቻ እና ብቻ መሆናቸውን ነው።አምባገነኖች አትድረሱብኝ፣እኔ የምለውን ብቻ ፈጽሙ።ወደ እኔ አትንጠራሩ ግን ለእኔ ሥገዱ ባዮች ናቸው። ሥለሆኑም በዛን ወቅት   የእነ ጀነራል አማን አምዶምንም ሆነ የነ ሻለቃ አጥናፉ  አባተን ቅን እና በጎ ሃሰብ  አለመቀበል ብቻ ሳይሆን በሃሳባቸው ብቻ ገድለዋቸዋል። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን፣ “በሰላማዊ መንገድ፣የሀገሪቱ ሉአላዊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ በፍላጓታቸው ዙሪያ ከአማፅያኑ ጋር  መደራደር የበጃል።  “የሚል አቋም እና የሌበራል አሥተሳሰብ ነበራቸው።መንጌ ግን  እልም ጭልጥ ብለው ወደኮሚኒሥቷ ሩሲያ የገቡት በነ ኃይሌ ፊዳ እና በነሠናይ ልኬ እና መሰሎቻቸው ሥብከት ፣የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ሥም እየለጠፉ ለመግደል እንዲመቻቸው እንደሆነ ዛሬ ግልፅ ሆኗል። ሜሼቪክ፣ቮልሸቪክ፣(አብዮታዊ  ፀረ አብዮት) ሶሻሊሥት፣አድሃሪ ወዘተ።በማለት።
   ፕሬዘዳንት መንግሥቱ (ኮ/ሌ መንግሥቱ ኃ/ማርያም ) የሶሻሊዝም  አብዮት በሀገራችን ሲፈነዳ ፣በፍንዳታው አሥገዳጅነት   ሥልጣን ሳያሥቡት መዳፋቸው ውሥጥ እንድትገባ ፣አጋጣሚ ና ሁኔታዎች የረዷቸው መሪ እንደነበሩ ይታወቃል። በዚህ አጋጣሚ ለመሪነት ሲበቁ ፣በዙሪያቸው የከበቦቸው እና አይዞህ እኛ ከጎንህ ነን።በዚህእና በዚህ መንገድ ሂድ።ይሄንን ያዝ።ያንን ልቀቅ።እነዚያን ተወዳጅ ያንን ጥላ።እነዚህን አጥፋቸው።እነዛን ደግሞ አልማቸው ።ወዘተ።እያሉ የሚያማክሯቸው ነበሩ።
    ኮ/ሌ መንግሥቱ 17 ዓመት የሥልጣን ዘመናቸውን የገፉት በመሣቀቅ ና ህዝቡን በማሠቀቅ ነው። የዛን ጊዜው  መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣(የኤርትራን ህዝብ  ጨምሮ ) ገጣዮች ከተባሉት ጋር ለ17 ዓመት እየተዋጋ መኖሩ አሳቆት ነበር።
    ዛሬ፣ዛሬ እየወጡ ያሉ ያለተነገሩ ታሪኮች የሚያሳብቁት ይህንን እውነት ነው።እንደእውነቱ ከሆነ የኤርትራ ህዝብ እንደ ህዝብ ፣የዘር መሠረቱ ከሆነው  የኢትዮጵያ ህዝብ መለየት አይፈልግም። ይሁን እንጂ የዛሬ 28 አመት በራሥህ ውሳኔ ተገንጠል ሲባል፣ ለህዝቡ” ከነፃነት ከባርነት”  ውጪ ሁለተኛ አማራጭ ምርጫ አልቀረበለትም። ያ እርስ በራሣችን  ያደረግነው ጦርነት ና በታላቅ ሤራ  የተፈፀመው መለያየት፣ የታሪካዊ ጠላቶቻችን እና የገንዘብና የቴክኖሎጂ አቅም ያላቸው ኃያላን ሀገሮች ያልጠግብ ባይነት ሤራ መሆኑን ደግሞ  በኤርትራም ሆነ በኢትዮጵያ የሚኖረው  ህዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል።
    ምንግዜም በዓለም ላይ፣ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ደም አፋሳሽ እኩይ ተግባራት የሚከሰቱት ፣አጭር እና ረጅም ጥቅምን አንገበው በሚንቀሳቀሱ ሥውር  ኃይሎች ነው።እነዚህ  ሥውር ኃይሎች ዛሬም በዚች ሀገር ፣በሥውር እጃቸው የኢትዮጵያን የወደፊት ህልውና ለመወሰን ሌት ተቀን እየጣሩ ነው።ይህንንም ሥውር የጥፋት ተልኮ ለማሳካት በቅንጡ ኑሮ የሚኖሩ ፣ ያለ ራሳቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጥቅም በሥተቀር የማያሥቡ ለሀገር እና ለዜጎች ደንታ የሌላቸውን ሥመ ኢትዮጵያዊያን በግብር ግን ፀረ ኢትዮጵያዊያንን ይጠቀማሉ።
     የቀኃሥ ጠቅላይ ሰለሞናዊ መንግሥትም  ሆነ የመንጌ ሶሻሊሥታዊ  መንግሥት የተንኮታኮተው፣ በአውሮፓና በአሜሪካ መንግሥታት ሥውር እና ግልፅ ጣልቃ ገብነት  ነው።የኃይለማርያም መንግሥት በበቃኝ የተሸነፈው ፣ በኃያላኑ ሥውር እጅ እገዛ አይደለም ለማለት አይቻልም።
     ዛሬሥ ? የህዝቡን የፍትህ፣የነፃነት ፣ የዴሞክራሲ  ፣የመልካም አሥተዳደር እና የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቄ ፣ በህዝባዊው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ፣የህዝቡን ለውጥ የተቀላቀለው ፣ የኢህአዴግ  ግማሽ ጎን ፣ በውጭ ኃይሎች ግላዊ አጀንዳ ላለመጠለፉ  ምን ማረጋገጫ አለን?? ሩሲያም ሆነ አሜሪካ በአባይ ጉዳይ አደራዳሪ ለምን ሆኑ?ዕውን በራሳችን ሀብት የመጠቀምን መብት (ሌላውን ሳንጎዳ )የለንም እንዴ?በእውኑ  እነዚህ ኃያላን መንግሥታት ሥለ እኛ እድገትና ብልፅግና ደንታ አላቸውን ? በዚች ሀገር ጠንካራ የፊደራል ሥርአት እና እንደአሜሪካ አይነት  የፊደራል መንግሥት እንዲኖረን ከምር ይፈልጋሉን?…
   የሚፈልጉ አይመሥለኝም።በራሳችን ጥንካሬ ግን የታፈረች፣የተከበረች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ብንፈጥር አይቃወሙንም።ይህ እንዳይሆን ግን ለብዝበዛ የሚመች ሥርዓተ መንግሥት እንዲኖር የሚፈልጉትን በፓለቲካዊ ሴራ የተቀነበበ   ጫወታ በሥውር ይጫወታሉ። (ውስጡን ለቄሥ ይሉሃል ይኸው ነው)
  ትላንት በድንገት ጠ/ሚ የሆኑት   ይህቺን ታላቅ ሀገር የመምራት ኃላፊነት የወደቀባቸው ዶ/ር አብይ ዛሬ ላይ የወደቀባቸው ፈተና ከ political conspiracy የራቀ አይደለም።  ምንም እንኳን ሀገር ወዳድ እና ለሀገር መሰዋትን  በተግባር የሚያውቁ ወታደር ቢሆኑም የበሰበሰውን የኢህአዴግ ሥርአት ቆርጦ በመጣል አዲሥ ፓርቲ የማቋቋም ጥረታቸው በተለያየ አቅጣጫ ፈተና እያጋጠመው ነው።
    ፈተናው ውስጣዊ እና ውጫዊ ሆኖባቸዋል። ውስጣዊውን ፈተና በህግ የበላይነት፣ፍትህ ለሁሉም ሰው እኩል በሆነችበት መልኩ ይወጡታል።በሚሊዮን ዶላር ኢንቬሥትመንት በተለያየ መልኩ የሚፈፀመውን ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር እንዴት ያከሽፉታል? …እርግጥ ነው፣በተለያዩ ሚዲያዎች ለእንጀራ ብለው ሳያውቁት ሀገርን ለማፈራረሥ ከውጪ ሆነው ቼ በለው የሚሉትን በተግባራቸው ለማሸነፍ ረጅም ጊዜ እንደማይወሥድባቸው ይህ  ፀሐፊ ያምናል።
   (ውስጣዊውን ችግር፣ የኢህአዴግ ግማሽ ጎን ፣ ሥልጣን እንደያዘ  ኢህአዴግን ረግመው ፣  እኛ ነበርን አሸባሪዎች በማለት እንደ  መለሥ መራሹ የህወሓት መንግሥት የ1993 ዓ/ም  ንግግር አይነት ” ኢህአዴግ በሥብሶል ” የሚል አንድምታ ያለው ንግግር በፓርላማ በመናገር ማጋለጣቸውን አንዘነጋም)።
      ኢህአዴግ ሆነው ራሳቸውን የወቀሱት እና  ለተፈፀመው ኢሰባዊ ድርጊት ኃላፊነቱን በመውሰድ፣ኢትዮጵያን ወደ ዴሞክራሲ አሻግራታለሁ በማለት የጠቅላይ ሚንሥትርነትን ሚና  የተወጡት  አብይ አህመድ(ዶ/ር)  ፣ ምንም እንኳ ፣በሰሩት እኩይ ድርጊት እንደሳቸው፣ የማያፍሩትን ሳያራግፉ ፣የመደመር  ፍልስፍናቸውን ተቀበለው ሳይጠምቁ በሥመ ኢህአዴግ ፣ሁሉንም በአንድ  ባቡር አሳፍረው እየተጎዙ መሆኑን ብናውቅም ፣ ቀሥ፣በቀሥ የፍትህ ፣የዴሞክራሲ፣ የእኩልነትና የብልጽግና ፀር የሆኑትን እያራገፉ  ፣ በባቡሩ ውሥጥ ለእውነት የሚሞቱ ለዜጎች ሁሉ ከከንፈር ባለፈ ከምር  በተግባር የሚቆረቆሩትን አሥቀርተው ፣ በአዲስ ፓርቲ እና ሁሉንም ዜጎች አሳታፊ በሆነ አሥተሳሰብ ወራቶች በቀሩት የመንግሥትን ሥልጣን  በህዝብ ይሁንታ ለመያዝ ሁሉም የፓለቲካ ፓርቲዎች በሚወዳደሩበት ብሔራዊ ምርጫ ላይ እናገኛቸዋለን ብዬ ተሥፋ አደርጋለሁ።  …..
   ከምርጫው በኋላ፣ፓርቲያቸው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ተዋህዶም ሆነ ብቻውን፣ በያዘው ህዝባዊ አላማ ካሸነፈና የመንግሥት ሥልጣን ከጠ/ሚሩ እጅ ካልወጣ ፣በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ፓርቲያቸው፣ እተገብረዋለሁ ያለውን ያሥመረጠውን፣ወይም ለድል ያበቃውን የተለያየ ፓሊሲ የመተግበር ግዴታ አለበት።ተግባራዊ ማድረግ ካልቻለ እንደገና ወደግጭት አዙሪት መመለሳችን አይቀሬ ይሆናል።
  ዛሬ እና አሁን ግን  የህዝቡን የዴሞክራሲ ፣የእኩልነት የፍትህ እና የብልፅግና ጥማት ለመመለሥ በሚያሥችል ቁመና ላይ ፓርቲያቸው  እንዳይደለ ይታወቃል።ከአሳታፊነት ይልቅ አግላይ ነው።አግላይነቱ እጅግ የገዘፈ እና በቋንቋ የታጠረ ዘርን ያማከለ ነው።እንደውም ፓርቲው ሳይታወቀው በቆዳ ማዋደድ ፊውዳላዊ አሥተሳሰብ ውስጥ ገብቶ “ከዚህኛው ሰው ያኛው ሰው የበለጠ ሰው ነው ።ምክንያቱም ቋንቋው እና ዘሩ የጠራ ነው።ከእነ እገሌ ጋር ቅርበት አለው።ወዘተ። “በማለት ቆዳውን እጅግ ያዋድዳልና!…
   የፊውዳል ሥርዓት ትምክህትና የአሥተሳሰብ ጥበት ይህ ነበር።በፍቅር እሥከመቃብር የተጠቀሱትን ፊታውራሪ መሸሻን በምሳሌ ማየት በቂ ነው።
   ይህ ፀሐፊ የሚፈራው ዛሬ በተግባር የምናሥተውላቸው ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ፊታውራሪ መሸሻዎች ይህቺን ሀገር እንደፊታውራሪ መሸሻ አሳዛኝ ፍፃሜ ወዳለው ወደማታንሰራራበት ውድቀት እንዳይወስዷት ነው።ይህንን እንስሳዊ እርስ በእርስ የመፋጀት ክንውን ደግሞ ጥቅማቸውን እንጂ ህዝቧን የማይፈልጉት የቅርብና እና የሩቅ ጠላቶቻችን  በብርቱ ይሹታል።
 ይህንን እኩይ ምኞታቸውን ለማክሸፍ፣  ሁሉም ሀገር ወዳድ ማወቅ ያለበት ፣ የእኔ እና የእኔ ሃሳብ ብቻ ይደመጥ ማለት ህመም መሆኑን እና ከዚህ ህመም ለመፈወሥም የሌላውን ሃሳብ ጆሮ ሰጥቶ ማዳመጥ ተገቢ ነው፣እላለሁ።
    በዚህ ጉዳይ  ኢሲኬ ኸርት ቶል  (ECK Hart Toole) A New Earth በተሰኘ  መፅሐፍ የፃፈውን በመጥቀሥ ፅሑፊን እቋጫለሁ።
  Beyond the realm of simple and verifiable facts ,the certainty that’s “I am rights  and you are wrong” is a dangerous thing in personal relationships as well as interaction between ,tribes,religions and so on.
(ጥሬ እውነቶችን ፣ቀላል ና በቀላሉ ሊረጋገጡ የሚችሉ ተጨባጮችን፣በሃሳብ መልክ ከማቅረብ ባሻገር፣”እኔ ልክ ነኝ አንተ ግን ልክ አይደለህም።”የሚል እርግጠኛ የሆነ (የግብዞች) አተካራ፣በግለሰቦች የእርስ በእርስ ዕለታዊ ግንኙነትም ሆነ በጎሣዎች፣ *በኃይማኖቶች -በሀገራት-በእምነት-በባህል-* ወዘተ።መሥተጋብር  ላይ ትልቅ አደጋ ከሳች ነው።)

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop