Health: ገንዘብ አልበረክትልህ አለኝ፣ ምን ባደርግ ይሻለኛል?

– ገቢዬን እንዴት ልምራ?

– ወጪዬንስ እንዴት መቆጣጠር እችላለሁ?

ቴዎድሮስ እባላለሁ፡፡ መካከለኛ ሊባል የሚችል ወርሃዊ ገቢም አገኛለሁ፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ባለትዳር እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነኝ፡፡ ታዲያ የማገኘው ገንዘብ ሳያንሰኝ ገንዘብ አልበረከትልህ፣ አልበቃህ ብሎኝ ተቸገርኩ፡፡ የያዝኩት ገንዘብ ሁሉ በድንገት ብትንትን ይልብኛል፡፡ ምን እንዳደረኩት ሳላውቅ ብዙ ገንዘብ አጠፋለሁ፡፡ ከእኔ እኩል የሚያገኙ ጓደኞቼ የተረጋጋ እና ሰላማዊ ህይወት ሲኖሩ የእኔ አኗኗር ግን ሁል ጊዜ የተበጠበጠ ነው፡፡ ከባለቤቴ ጋር በዚሁ የገንዘብ ጉዳይ ጠዋት ማታ መጣላት ነው… መበጣበጥ፡፡ መስሪያ ቤት አካባቢም የምታወቀው ገንዘብ በመበደር እና በዚሁ ችግሬ ስለሆነ ሰዎች ይንቁኛል፡፡ እርግጥ ነው ከዚህ ችግሬ ለመላቀቅ እና የማገኘውን ገንዘብ በአግባቡ ለመምራት እና ህይወቴን ለማስተካከል እናንተ መላ አታጡም እና መላ በሉኝ፡፡ እንዴት ነው ህይወቴን በአግባቡ መምራት ያለብኝ? ወጪዬን እና ገቢዬንስ እንዴት ነው ማመጣጠን ያለብኝ?

ቴዲ ነኝ

 የዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፡ ዝቅተኛ የሆነ ገቢህን የመምራት ችሎት መኖር ለበርካታ ችግሮች እንደዳረገህ፣ ትዳርህን ሰላም ከማሳጣት እና ጤናማ ያልሆነ የእርስ በርስ ህይወት እንዲኖርህ ከማድረግ ጀምሮ ብድር ውስጥ እስከመዘፈቅ እንዳደረሰህ ተገንዝበናል፡፡ እንግዲህ በቀጥታ ወደ መፍትሄው ስናመራ በቅድሚያ በተለይ በአሁኑ ሰዓት ዓለምን ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ባጋጠማት ሰዓት ገቢ ያለመብቃት ችግር የበርካቶች ችግር ነው፡፡ የችግሩ ስፋት ደግሞ በርካቶች የተመሳሳይ ችግር ተጠቂ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት ይህ ነገር አንተን ብቻ ሳይሆን የበርካታ ሚሊዮኖች ችግር እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብሃል፡፡

ውድ ጠያቂያችን ቴዲ ወጪና ገቢን ማመጣጠን ወይንም ገቢን በአግባቡ መምራት ማለት ከተቻለ ከገቢ በታች ለማውጣት መሞከር ወይንም ደግሞ ገቢን እና ወጪን እኩል ለማድረግ መጣር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ገቢን ለማሳደግ መጣርም በተለይ በአሁኑ ወቅት ግድ እየሆነ ነው፡፡ ስለሆነም በመጀመሪያ ደረጃ ገቢህን እንዴት መጨመር እንደምትችል አስብ፡፡ ምክንያቱም ገቢህ ባደገ ቁጥር የመምራት ችሎታህም ከፍ ይላል እና፡፡ በአንድ ነገር እርግጠኛ ሁን፤ አሁን እዚህ ያለህ ስራ እና እያገኘኸው ያለኸው ገቢ ከአንተ አቅም ሁለት ሶስት እጥፉ ያነሰ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ በተጨማሪ ስራ ለመስራት አካባቢህ ላይ ምን ሊሰራ ይችላል ብለህ ቅኝት አድርግ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: ጥሩ አድማጭ ለመባል 10 ምርጥ ዘዴዎች (10 Tips to Effective & Active Listening Skills)

በመቀጠል ገቢህን በአግባቡ ለመምራት በትክክል ገቢህን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ሰዎች በአካባቢህ የተረጋጋ ህይወት የሚመሩት በተለያዩ ምክንያት ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንደኛው የተለያየ የገቢ ምንጭ ስለሚኖራቸው ነው ይህ ገቢ ደግሞ በተለያየ መንገድ ሊገኝ ይችላል፡፡ ቀደም ሲል እንደጠቀስነው ተጨማሪ ስራ መስራት አንደኛው መንገድ ሲሆን ገንዘብን በባንክ ውስጥ በማስቀመጥ ተጨማሪ ወለድ በመሰብሰብ ወይንም እቁብ የመሳሰሉ በማህበረሰባችን ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው ትስስሮች ውስጥ በመሳተፍ ነው፡፡

ወደ ጠያቂያችን ቴዲ በመጀመሪያ ገቢን መምራት ማለት ራስን መምራት ማለት መሆኑን ተገንዘብ፡፡ ከዚያ በመቀጠል ራስህን ገምግም፡፡ የምን አይነት ባህሪ ባለቤት ነህ? ለምሳሌ በተለያዩ ሰዎች ውስጥ የተዘፈቅ ከሆነ ይህ አይነቱ ባህሪ ገቢህን ለመቆጣጠር እንቅፋት እንደሆነ አስተውል፡፡ ሌላው በበርካታዎቻችን ዘንድ የሚታየው ችግር ደግሞ ማስመሰል ነው፡፡ ለራስ ሳይሆን ለሌሎች መኖር ማለት ነው፡፡ ሌሎችን ለማስደሰት ጥረት ማድረግ፣ በገቢ ከማትመጣጠናቸው ሰዎች ጋርም ጓደኝነት ከራሳችን ከአቅማችን በላይ እንድንኖር ሊያደርገን ይችላል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የእጥረት አስተሳሰብ (Scarcmentait) ተጠቂ መሆንም አያስፈልግም፡፡ አንድ የአብርሃም ሊንከንን አባባል እዚህ ጋር ማንሳት እንችላለን፡፡ ‹‹ራስህን ድሃ ለማድረግ ደሃዎችን አትረዳቸውም›› ከዚህ አባባል የምንረዳው ነገር ቢኖር ሀብታም ማለት ብዙ ገንዘብ ያለው ሰው ሳይሆን ያለውን ገንዘብ በአግባቡ የመምራት ጥበብን እና ችሎታ ባለቤት የሆነ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ አስተሳሰብህንም ማስተካከል ይኖርብሃል፡፡ ይህ ሲባል በስነ ልቦና ሳይንስ አንድ እውነት አለ፡፡ ይህም እውነት ነው ብለን በአዕምሯችን የተቀበልነው ነገር በእውነቱም ዓለም ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ ስለሆነም አንተም የእጥረት አስተሳሰብን እና ከችግር አስተሳሰብ ራስህን ነፃ አድርግ ከዚያም ገቢህን በጥበብ መምራት ቻል ይህንን ደግሞ ለማድረግ የሚከተሉትን መንገዶች መከተል ይቻላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: ሰዎችን የሚያሳምን ንግግር እንዴት ማድረግ ይቻላል?

1. ቁጠባ፡- እንግዲህ ቁጠባ ሲባል ከምታገኘው ገቢ በተለያየ መንገድ እየቀነስክ ለማስቀመጥ ወይንም ለማጠራቀም መሞከር ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ቁርጠኝነቱን እና ዝግጁነትን ይጠይቃል፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ ራስን በፕሮግራም በመምራት ነው፡፡ የምታገኘውን ገቢህን በአግባቡ እወቅ ንፁህ ገቢህ (Net income) እቅድህ በማድረግ በወር፣ በሳምንት እና በቀን የተከፈለ ገቢን መደልደል ያስፈልጋል፡፡ ከትዳር አጋርህም ጋር በግልፅ መነጋገር ያስፈልጋል፡፡ አነስተኛ ከሚባል ወጪዎች ጀምሮ እስከ ከፍተኞቹ ድረስ በቀን፣ በሳምንት እንዲሁም በወር ተከፋፍሎ ሲቀመጡ አንደኛ ራስህን ለመምራት ዝግጁ እንድትሆን ያደርጋል፡፡

2. የአመለካከት ለውጥ ማምጣት፡- ከላይ እንደተዘረዘረው ገቢን መምራት ማለት ራስን መምራት ማለት ነው፡፡ ራስን ለመምራት ደግሞ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት፣ ይህ ማለት ደግሞ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው አስተሳሰብን ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡

3. ገቢን ማሳደግ፡- አሁንም ከላይ እንደተዘረዘረው ገቢን ለማሳደግ መጣርም የራስህንም ሆነ የቤተሰብህን ህይወትን በአግባቡ ለመምራት ወሳኝ ነው፡፡

4. በጀት ማድረግ፡- በጀት ማድረግ ማለት ህይወትንም ሆነ ገቢን በእቅድ መዘርዘር ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የእቅድ ሰንጠረዥ ማዘጋጀት ያካትታል፡፡

ወርሃዊ ገቢ በብር

ወርሃዊ ወጪ

የቤት ኪራይ

የስልክ

የትራንስፖርት

የቤት ውስጥ ወጪ

የመዝናኛ

የጤና

መጠባበቂያ

እንግዲህ ከላይ ለመዘርዘር በተሞከረው ሰንጠረዥ መሰረት የገቢ መቆጣጠሪያ ቻርት (Personal financial chart) ለማውጣት ትችላለህ፡፡

1. ራስን መሆን፡- ራስን መሆን ማለት ሌላውን ለመምሰል ሳይሆን ራስን ሆኖ በአቅም መኖር ማለት ነው፡፡

2. አማራጭን መፈለግ፡- አማራጭን መፈለግ ማለት በቀላሉ ወጪ ነገሮችን ለመሸፈን መጣር ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በታክሲ ከመሄድ ይልቅ ረጅም መንገድን በቀላል ወጪ ለመሄድ መሞከር አውቶብስን እንደ አማራጭ መጠቀም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እስካሁን ሃብታም ያልሆንክባቸው 10 ምስጢሮች

3. ጥቃቅን ወጪዎችን መቆጣጠር፡- ጥቃቅን ወጪዎችን በአግባቡ መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡ በቀን ማውጣት ስላለብህ ነገር ቀድመህ አስብ፡፡ ለድንገተኛ ወጪዎች ራስህን አዘጋጅ፡፡

4. የባንክ ደብተር ይኑርህ፡- ራስህን ለመቆጣጠር የባንክ ደብተር መኖር ያግዝሃል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ራስህን ከብድር ለማውጣት ጥረት አድርግ፡፡

ውድ ጠያቂያችን ቴዲ እንግዲህ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መንገዶች ወጪን እና ገቢን ለማመጣጠን ይረዳሀል፡፡ ስለሆነም እነዚህን ለመተግበር በዋናነት የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል፡፡

Share