ነፍጠኛ ባቀናው አገር፤ አፉን እንደ ሊጥ ዕቃ ቦርግዶ፣
ስምንተኛው ሺ ሲቃረብ፤ አሳማም ነብር ናቀ አሉ፡፡
ነፍጠኛ ባያስከብረው፤ ጠላትን ደፍቆና አናፍጦ፣
ሥሙ ጆቫኒ በሆነ ነበር፤ ይኸ ገንፎ ዘረጦ!
ቀን ዱብ እማያደርገው፤ ግዜ እማይሰቅለው ጉድ የለ፣
ነፍጠኛም በጓጉንችሮች፤ ሲታማ ሲረገም ዋለ፡፡
እንኳን የነፍጠኛን ልጅ፤ እግዜርስ እንዴት ይነደው?
በደም አገር ጠባቂን፤ ድንፈፍ ሲያብጠለጥለው፡፡
ነፍጠኛ አርግ ተምድር፤ ውጣ ሽቅብ ተሰማይ፣
ተምቹ ጉንዳኑ ፎግሉም፤ እንደ ዝንብ ሰፍሯል ገላህ ላይ!
ብአዴን የሚባል አሽከር፤ ተሰዎች ተራ ደርድረው፣
ለሀጫቸውን ተፉታ፤ ነፍጠኛን ሰባበርን ብለው፡፡
ሰማህ ወይ የነፍጠኛ ልጅ፤ ወላጅ የምታሰድብ፣
ተሰብሰብ እንደ ደመራ፤ ክብርህን ጠብቀው ተዝንብ፡፡
የሰውነትህ አስኳሉ፤ ክብር ማእረግህ ወግህ ነው፤
የተሸከምከው ሥጋማ፤ እንደ ሰዳቢህ ከብት ነው፡፡
ሰማህ ወይ የነፍጠኛ ልጅ፤ የምትዋከብ ባገርህ፣
እንደ መከታ ከትመህ፤ አውሬውን ጣለው ዘንድበህ፡፡
አለሌው ቅይዱን ፈቶ፤ የነፍጠኛን ልጅ አስሮታል፣
ቀኑ የባሰ ሳይጨልም፤ ነፍጠኛ ሊያመር ይገባል!
ሰማህ ወይ የነፍጠኛ ልጅ፤ እጅግ የተገፋኻው፣
ያያትህን ክብር በክንድህ፤ ተነበረበት መልሰው!
ሰማህ ወይ የነፍጠኛ ልጅ፤ ቀጣዩ ዘመን ክፉ ነው፣
ክብር ዘላለማዊ፤ ምድር ህይወት ግን አጪር ነው፣
እንደ ነፍጠኛው አያትህ፤ የደፈረህን አናፍጠው!
በላይነህ አባተ ([email protected])
ጥቅምት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም.