ለሞተ ሰው ሣይሆን ይልቁንስ ጣር ላይ ለምትገኘዋ ኢትዮጵያ አልቅሱ! – አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

(ትናንት በተቀመጡበት ድፍት ብለው በደቂቃዎች ውስጥ (እንደሀኪሞቹ አባባል) በስትሮክ ሞቱ የተባሉትን የመሥሪያ ቤቴ ባልደረባ ነፍስ ይማር በዚህ አጋጣሚ፡፡) የሞተ ተገላገለ፡፡ የሞቱ በለጡን፡፡ “በዚያን ዘመን ሞትን ይመኟታል፤ ነገር ግን አያገኟትም” የሚለው ነባር መጽሐፍ ቅዱሣዊ(?) ቃል እውን ሆነ፡፡ ወግ ሆነና ሰው ሞተ ሲባል ይለቀሳል፡፡ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የምገኝበት የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይም ይህንኑ ማየቴ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ባህልና ወግ ነውና፡፡ ግን ደፋር ቀባሪ ጠፋ እንጂ ሁላችንም በቁም ሞተናል፡፡ “አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” የሚል የዱሮ መጽሐፍ ነበር ልበል? አዎ፣ ትክክል ነው – እንደትንቢት ወሰድኩት፡፡

ዛሬ ጧት ከቤቴ ወጥቼ በአንድ ሚኒባስ ታክሲ ሦስት ኪሎ ሜትሮችን ያህል ወደ መሀል አዲስ አበባ አካባቢ መጣሁ – ወደ መሥሪያ ቤቴ ለመሄድ፡፡ ሚኒባሱ በህግ የተፈቀደለት የተሣፋሪ ብዛት ሹፌርና ረዳትን ሣይጨምር 11 ሰው ነው፡፡ እኛን የጫነን ሚኒባስ ግን ማንን ፈርቶ ከነሹፌሩና ረዳቱ 21 ነን – ልክ እንደዛሬዋ የእመብርሃን ዕለት – መስከረም 21 (ያደለው ግሸን ደብረ ከርቤ ሄዶ ይቺን ቀን ያከብራል እኔ እዚህ በንዴት እንጨረጨራለሁ)፡፡ ልብ በሉ – የመኪናው የመጫን አቅምና የተጫነው ሰው ብዛት በፍጹም አይመጣጠንም፡፡ ይህ ደግሞ አደጋን ከሚያበዙ አጋጣሚዎች ቀዳሚው ነው፡፡ ሀገራችን በመኪና አደጋ ምናልባት ከአንደኞች ተርታ ብትሠለፍ አንዱና ዋናው ምክንያት ይህ ከተሸከርካሪዎች አቅም በላይ የሚደረግ ጭነት ነው፡፡ ሌላው እንዲሁ እንደጠበል ጠዲቅ የሚረጭ መንጃ ፈቃድ ነው – በገንዘብ ወይም በሙስና፡፡ ሌላው ሀሽሽና ጫት እንዲሁም መጠጥ ነው፡፡ ሌላም ይኖራል፡፡ …

ወደ መ/ቤቴ ለመጓዝ ታክሲና ሃይገር ለማግኘት ዐይኖቼን ሳማትር የሠልፉ ነገር ወሽመጥ ይበጥሳል – ሰዓቱ ገና ከጧቱ 1፡15 ላይ መሆኑን ያዙልኝ፡፡ ወዲህ ብል ወዲያ ብል ምንም አማራጭ የለም፡፡ ስድስት ኪሎ ሜትሩን የመሥሪያ ቤቴን መንገድ በእግሬ አስነካው ገባ፡፡ ሄደት እያልኩ በመኪኖች በመጥለቅለቁ ሳቢያ እንደኤሊ የሚጎተተውን የመንገድ ላይ ተሸከርካሪ ቆም ብዬ ቃኘት አደርጋለሁ – ምናልባት አንዱ የሚያውቀኝ ቢያቆምልኝና ቢጠድቅብኝ፡፡ ተስፋ ያደረግሁት አልቀረም – አንዱ ወዳጄ ካለፈኝ በኋላ የኋሊት መጥቶ “አምቢቹ፣ ና ግባ!” አለኝና ገላገለኝ፡፡ የሀገራችንን አስጨናቁ ጉዳይ እያወራን ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ስታወራው ይቀንስልሃል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኛ ነገር፡ የተሸነፈ ርእዮተአገርና ገፊ ፖለቲካ፤ (ተክለሚካሄል አበበ )

ግን ግን ወዴት እየሄድን ነው? በሀገራችን ሁኔታ እንደዛሬ ደንግጬ አላውቅም፡፡ የማየው ነገር ሁሉ በፍርሀት እያራደኝ ነው፡፡ መሄጃ ቢኖረኝ እንደወፍ በርሬ ከዚህች አገር በጠፋሁ – እስኪ የምትችሉ ጥደቁብኝ! ከላይ ታገኙታላችሁ፡፡ እውነቴን ነው፡፡

ለዳቦ ሠልፍ፣ ለህክምና ሠልፍ፣ ለትራንስፖርት ሠልፍ፣ ለግብርና ቀረጥ ክፍያ ሠልፍ፣ ለቅጣት ክፍያ ሠልፍ፣ ለቀበሌ ሉካንዳ ቤት ሠልፍ፣ መኪና ስታሽከረከር ሠልፍ፤ ልትጠበል ሠልፍ፣ ለጥንቆላ ቤት ወረፋ፣ ለሙስና ክፍያ ወረፋ፣ ለምግብ ወረፋ፣ ለፓስፖርት ወረፋ፣ ለቦሎ ሠልፍ፣ ለመጠጥ ሠልፍ፣… ሠልፍ… ሠልፍ…. ሠልፍ…፡፡ ሠልፉ ደግሞ ዙሪያ ጥምጥም ነው፡፡ የመስቀል ለት ሥጋ ልገዛ ወደ ቀበሌ ብሄድ ሠልፉ የመስቀል አደባባዩን የዚያን ሰሞን የእሬቻ ሩጫ ሊያክል ምንም አልቀረውም፡፡ (እናንተዬ ምሥጢሩን ሰማሁ – ለካንስ 50 ሽህ ሯጭ እንደተሣተፈ የተነገረው ውሸት ነው፤ 5 ሺም አይሞላም አሉ፤ በዚህ ዓይነት ምርጫውን እንዴት ልናምን ነው?(ይላሉ ሰዎች)) ይህ የሚያመለክተው አንድም የሸቀጥና የአገልግሎት ሰጪው ወይም አቅራቢውና የተጠቃሚው ብዛት አለመመጣጠኑን ነው፡፡ አንድም የሕዝቡ ብዛት ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱን ነው፡፡ አሳሳቢና አስጨናቂ ዘመን፡፡

ከምር ወዴት እየሄድን ነው?

አዲስ አበባ ውስጥ አሥርና ሃያ ደቂቃ የማይፈጅ መንገድ ሰዓታትን ይወስድብሃል፡፡ ይህ ብቻውን የጎንዮሽ ጉዳቱ ቢተነተን በጣም ብዙ ነው፡፡ የነዳጅ ፍጆታን ይጨምራል – በዚያም ምክንያት ገንዘብን አላግባብ ማባከንን ያስከትላል፡፡ ጊዜን ይጨረግዳል- በዚያም ሰበብ ቀጠሮን ማጓተትና የሥራ ሰዓትን ማቃጠልን፣ ከሥራ ኃላፊዎች ጋርም መጋጨትንና ሥራን ሁሉ ማጣትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የሀገር ሀብትን ያሟጥጣል – ነዳጅ ለማስመጣት ብዙ ዶላር እንደማስፈለጉ ለሌላ ጉዳይ ይውል የነበረን የውጭ ምንዛሬ ለነዳጅ በማዋል ያባክናል፡፡ የመለዋወጫ ፍጆታን ስለሚጨምር ይህም ጉዳቱ ትልቅ ነው፤ በዚያ ላይ ለፍጥነት መቀነሻ ተብሎ በየመንገዱ አለዕውቀት የተጎበረው ግንዲላ ግንዲላ እሚያካክል የአስፋልትና የስሚንቶ ንጣፍ መኪኖችን ከጥቅም ውጭ እያደረጋቸው ነው፡፡ ሀገርን በጥበብ ማስተዳደር ዕርምና እንደወንጀልም የሚቆጠር ሳይሆን አይቀርም፡፡ የመንገድ መጨናነቁ በዚህ ብቻ አያቆምም፡፡ ወደ ጭንቅላት ይወጣና ትግስትንም ይፈታተናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼስ እነዚህ የ “Q” ዘሮች መላም የላቸው፡፡ ከዚህ አንጻር AQ, BQ, IQ, SQ, CQ,… ፍዳቸውን እየበሉ ከዜሮ ጋር ወደ መደመር ተቃርበዋል፡፡  EQ (Emotional Quotient)ም በመንገድ መዘጋጋት ምክንያት አሣሩን እየበላ ነው፡፡ አዳሜ ከፊቱ የተገተረው መኪና ምን ገጥሞት እንደተገተረ ባለማስተዋል የመኪናውን ጥሩምባ  ዕረፍት እየነሣ አካባቢን ከማደንቆሩም በተጨማሪ በቡጢ የመኪናውን መሪ እየደለቀ ንብረቱ ላይ ያልተጠበቀ ጉዳት ያደርሳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምን ይደረጋል? እናት አገር ትኑር!

ምን አለፋህ – አዲስ አበባ ትርምስምሷ ወጥቷል፡፡ በረንዳ አዳሪውን፣ ለማኙን፣ ሥራ አጡን፣ ሥራ ፈቱን፣ ጠጪና ሰካራሙን፣ ዘሟቹን፣ ሴተኛ አዳሪዋን፣ ወንደኛ አዳሪውን፣ ቀማኛውን፣ ቦዘኔውን፣ ደላላውን፣ የማርካቶና ፒያሣ እንዲሁም አራት ኪሎና መገናኛ አካባቢ ወከባን፣ የሃይማኖት መላላትና ከናካቴው መጥፋትን፣ የሰዎችን አስመሳይ ባሕርይ፣ የሞራልና የባህል ክሮችን መበጣጠስ፣ በሀገራችን ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቀውን ራስ ወዳድነት፣ በንግዱና ኢኮኖሚው የሚፈጸመውን ማጭበርበር፣ የብሔራዊ ስሜት መጥፋትን፣ በጥቅሉ የዜጎችን ስሜት አልባነትና ብዙዎች የሚመሩትን ሜካኒካዊ የሮቦት-መሰል ሕይወት ስትመለከት ጭንቅላትህ ሊፈነዳ ይደርሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖር አንጎልህን ከሥራ ውጪ ማድረግ ይኖርብሃል፡፡ ከቻልክ ማበድ፡፡

ባይገርምህ በሀገራችን ውስጥ – በአሁኑ ዘመን – ሥራ ያለው የጎዳና ተዳዳሪ ቤተሰብ እኮ በብዛት ታገኛለህ፡፡ በየትኛው ደመወዙ ቤት ይከራይ? የአንድ ሽህና ከዚያም በታች ደሞዝተኛ እንዳለ ታውቃለህ? የቤት ኪራይ ከ2000 ብር በታችስ እንደማይገኝ ታውቅ ይሆን?(በተለይ በመሀል ከተማ?)፡፡ አንቺም አስቢው – ከአንድ ሽህና ሁለት ሽህ ብር ደሞዝ ምኑ ከምን ሆኖ ለቤት ኪራይ ይከፈል?   ለምግብም እኮ አይበቃውም፤ ለትራንስፖርትም እኮ አይበቃውም፤ ለህክምናም እኮ ያስፈልገው ነበር፤ ለልብስና ለልጅ ምግብ፣ የትምህርት ቤት ክፍያና የደምብ ልብስም እኮ ይጠበቅበታል፤ ለመንቀሳቀሻ እኮ ያስፈልገዋል፤ ለተቀማጭማ አይታሰብም፤ እንዴት ይኑር ይህ ሰው? ራሱን ያጥፋ? መተሳሰብንና መተዛዘንን ከሀገራችን ምድር ሙልጭ አድርጎ ያስወጣቸው ማን ይሆን?

ይህች ሀገር ታዲያ በኪነ ጥበቡ አይደለም እየኖረች ያለችው? መንግሥት የት ነው ያለው? ፈጣሪንስ ማን አገተው? በርግጥም ወዴት እየሄድን ነው? እኛን ከተመቸን – በቃ – ሀገር እንደፍጥርጥሯ ትሁን? ቅንጡዎቹና ስለሀገር ችግር አይሞቄ-አይበርዴዎቹ እነበቀለና እነጃዋር ታዲያ ይህንን ችግር ለማስወገድ ነው መሯሯጥ የሚገባቸው ወይንስ ለማባባስ ነው መራወጥ ያለባቸው? የዚህችን አገር ሕዝብ እንኳንስ በጎሣና በሃይማኖት አለያይተን በሁሉም ነገር አንድ አድርገንም ወደ ትክክለኛው የሰውነትና የዕድገት ፈር ማስገባት በቻልን፡፡ እንኳንስ ተጣልተንና ተመነቃቅረን ተፈቃቅረንም በሆነልን፡፡ እዚያና እዚህ ፎቅና የሚያማምሩ ሴቶችን ማነው ቤቶችንና የአስፋልት መንገዶችን ስላየህ ብቻ ኢትዮጵያ አለች አትበል፡፡ ከሌለን ቆየን ወንድማለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኦኖሌ፡-ሀርከ-ሙራ

ለዚህ ሁሉ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ያደረሰን ሕወሓት ግን እግዜር ይይለት፡፡

 

ለማንኛውም አስተያየት martyrof2011@gmail.com

4 Comments

 1. ውሾቹ ይጮሀሉ ሕወሓት እያሉ ፣
  እኛም ብለን ነበር፣
  ከበሮ በሰው እጅ ያምር፣
  ሲይዙት ያደናግር ።

 2. Ethiopia need to sell Ethiopian airlines , Ethio Telecom and Ethiopian Shipping lines , even the hydroelectric dam too will be sold, so the most vulnerable citizens who are often the first to suffer do not suffer if these sells do not happen.For instance, people who show up to their local [public] health clinic that is already only open once a week may now find that it also doesn’t have medicines, Or that school that was going to open this year to meet the needs of a particular neighborhood, it gets postponed.
  The entire economy can be thrown into paralysis. When a government can’t meet its existing debt obligations that makes it very hard to access new money. Lenders that provide this type of financing aren’t going to want to throw good money after bad. And to keep up daily operations, governments need continual access to credit. Ahmed adds that these operations often include not just the provision of services to citizens but business activities that generate much of a government’s income — extracting and exporting natural resources like copper or oil, for instance. These kinds of operations can become impossible without day-to-day credit. Just like for a small business, you need to be able to borrow on a day-to-day basis for your cash flow.
  So this is very much an on-the-ground crisis. It’s easy for us to think of these as abstract financial numbers. But it’s very important to recognize that behind these numbers are the lives of people who are already living in very difficult circumstances with no bailout only choice left is to sell any organization.

 3. GOD bless You!

  You told us the failed Ethiopia with the evils of the previous and current regimes
  This is the present Ethiopia with paradox of every thing. However, we have to struggle with those gamblers so as to bring the previous faith of the community

  Let the real Ethiopian come together and struggle for the survival of the historic Ethiopia otherwise we are going to disappear with this blessed christian land.

  Thank you

 4. Endyte astewaye sew newe yetsafew… Leke belhale….sent tezeko yemyalke chger laye yalche hager laye yezer poltics.. “be enkert laye joro degefe” new…. Oromo.
  . Amara.. Guragya.. Etc yemenlew yehane teshekmen new engdi.. Ke somalia,Syria Iraq ,Libya,South Sudan.. Etc enkwane memare alechalnme….dhenetunse yechalale
  … “KEDETU WEDE MATU” eyegebanse endhone terdetenale….Derome be merabaweyane chana yemta nger devil neger masketlu ayekerm.. Egna kalenkane ena rse be rse be zer mebalate kalakomen.. Nesanet tarike yehonale hager kelalane…

Comments are closed.

Previous Story

የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊሲ አባላት የታደሰውን ቤተመንግስት ለመጎብኘት ቅድሚያ እንደተሰጣቸው ጠ/ሚሩ ተናገሩ

Next Story

ኸረ በህግ አምላክ!!! – ከተማ ዋቅጅራ

Latest from ነፃ አስተያየቶች

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት

የፋኖ አደረጃጀቶች አንጻራዊ ወሳኝነትና የእስክንድር ነጋ ወሳኝ ሚና

ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተነሳው  በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በመዛት ስለነበር፣ ያ ማራ ሕዝብ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን  ጨርቅ በማድረግ ቅኔያዊ ፍትሕ  (poetic justice) ሊሰጠው የሚገባው  በእስክንድር ነጋ መሪነት ነው።    ________________________________________ ያማራ ፋኖ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የቤታማራና የሸዋ

Share