“ታማሚ ህሊና  ምንጊዜም ተንኳለኛ ና ጠብ አጫሪ ነው።” – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

September 28, 2019
 የማንም ሰው ህሊና በትዕቢት ና በማን አህሎኝነት ከተወጠረ  ፍርሃ እግዛብሔርን ከውስጡ አምጦ ካወጣ ፣ ታሟል።ህመሙ ለማንም ለምንም ደንታ ቢሥ ያደርገዋል። እራቁቱን አልሄደም እንጂ እብድ ነው።
        ለኃይማኖት ደንታ የለውም።ለአማኞቹ ደንታ የለውም። ።ለእምነት ደንታ የለውም።ለቤተ ክርስትያን ደንታ የለውም።ለመስጊድ ደንታ የለውም።
       ይህ ሰው  ከላይኛው እስከታችኛው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ካለ ደግሞ  የሚያደርሰው ጥፋት ይሄነው አይባልም።
      በእርግጥ ዛሬ በፌደራል ውስጥም ሆነ በየክልሉ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ሥልጣን ኮርቻ ላይ ወጥተው እንዳሻቸው አይጋልቡም ብለን መመሥከር አንችልም?
      ትላንት በዕለተ ደመራ  በደብረዘይት(ቢሸፍቱ) እነዚህን ሰዎች አሥተውለናል። ጉዳዩን ቢቢስ አማረኛ  ዘግቦታል። አንብቡት።ትገረማላችሁ። ለጠቅላይ ሚኒሥቴር  ዶ/ር  አብይ አህመድም ከምር፣ ታዝናላችሁ ።
      እነዚህን ፈፅሞ የማይደመሩ ቀናሽ አሥተሳሰቦችን የሚያሩምዱ የአመራር አባላትን በተዋረድ በፓርቲው ውስጥ  በልዩ፣ልዩ ኃላፊነት ደረጃ፣ ከቀበሌ ጀምሮ በተዋረድ ይዞ ፣  እንዴት ነው፣ በመደመር ና በፍቅር  ፍልሥፍናው፣ ወደ ሠላም ና ብልፅግና የሚያሻግረን??
      ዛሬ የቀሥተ ደመናው ጎላ ያለው ቀለም ልብሴን እንዳሥውበት ከተከለከለ  ነገ እንደ ካንቦድያው መሪ  አረንጓዴ፣ቢጫ እና ቀይ ቀለም ያለውን ማንኛውም ጌጥ ና አልባሳት ያደረገ እንዲገደል ላለመቀሥቀሳቸው ምን ዋሥትና አለን?? ?
      የካንቦድያው መሪ ፖል ፖት፣  መነፅር የሚያደርጉ በመቶሺ የሚቆጠሩ ዜጎችን ፀረ ጭቁን ናቸው ፣ምሁር ና የላባደሩ ጠላት ናቸው በማለት መረሸኑ በታሪክ ተመዝግቧል። እናም ባለሥልጣን ሥለሆንክ እና ፀዳ ያለ ልብስ ሥለለበሥክ ታማሚ ህሊና የለህም ማለት አይደለም።
“ዛሬም ?… ያሳፍራል።”
ልራመድ ስል እግሬን
ልናገር ሥል አፌን
ልፅፍ ሥል እጄን
ከያዝከኝ ወንድሜ
ከያዢሺኝ እህቴ
እኔ ከቶ ማነኝ ?
መናገር ያቃተኝ
መፃፍም ያቃተኝ
መራመድ የማልችል
ያንቺ ፣የሱቅ ዕቃ
የእሱ፣ የሱቅ ዕቃ
ሲያሻህ የምትገዛኝ
ተጠቅመህ የምትጥለኝ
 እኔ የአንተ ቁሥ ነኝ።(…)
ወይንም…
ማንም እንዳሻው
ከህግ በላይ ሆኖ
እንዳልፅፍ…
 እጄን ሸብ አድርጎ
እንዳልናገር…
 አፌን ለጉሞ
በሠላም ልኑር ካልክ
ሸቤ ካላማረህ
አፍህን ዝጋና
በቀቀን ሁን ካልከኝ…
እኔ ብቻ ላውራ
አድምጥ አንተ ብቻ ።
የኔን አሥተጋባ
ሲነጋ ሲጠባ ።
ክልሉ እኮ የኔነው
ቼ ፈረሴ የምለው።
ካልከኝ…
ክልል፣ ፈረሴ ነው
እንዳሻኝ የምጋልበው።
ያንተ ብጤውም …
ያም፣ያም በክልሉ
“ልኡል” ከሆነ ሁሉ …
በነፍጥ ታጅቦ
በጥጋብም ጠግቦ፣
መንግሥት እንደሌለ
ሀገር እንደሌለ
አዛዠ፣ናዛዥ ሆኖ …
በየቋንቋው ገኖ  ።
የወል ሥም ተረሥቶ
ቋንቋ ብቻ ተሰምቶ
ሁሉም በየቋንቋው
ጥላቻን ሢያወራው…
ሌላውን እያሥፈራራ
ካለ እኔ ብቻ ልምራ…
እኔ ብቻ ……….
ድስቱን ላማሥል
እንዳሻኝ  ልጥበሥ
እንዳሻኝ ልቀቅል …
ምን አገባችሁ ?!
ቢያር፣ቢጎረና….
ትቼው፣ረሥቼው
ዘንግቼው ቢገነፍል ?
ከቶስ ምን አገባችው ?
 ብደፋ ና ብጥል?!
ምን ምርጫ አላችሁ
 ሥራዬን ከማድነቅ
ከማቅረብ ምሥጋና
በማለት  እልል !እልል!?
ያለሀፍረት ከተባለ…
ሀገር ምኑን ሀገር ሆነ?
ግና
እንፅናናለን
ይህን የጥላቻ ድግሥ
ፖለቲከኛው ቢደግሥ
“አክ- ቱ ” እሱ ቢያጋፍር(ጥራዝ ነጠቅ አክቲቪሥቱ)
“ልቁ” ቢያሥተናብር ( ሆድ አደር ልሂቁ)
በሐሰት ቀሥቅሳ
ያም፣ያም ፣ ዱላ ቢያነሳ።
ሰው፣ሰውን ገድሎ
ግዳይ አንጠልጥሎ
ቢፎክር ቢያቅራራ…
ይህን የእልቂት ድግሥ
ባለአገሩ አይበላ…
ከተማ  መሽጎ ያ ጎሠኛ
ያ፣ የቋንቋ ፖለቲከኛ…
እዛው ይጎራረሥ
እርስ በእርሱ ይባላ…
ያ፣ ታማሚ ህሊና
ሳያፍር በፖለቲካው
ሣታፍር በፖለቲካዋ
ከቅኝ ገዢዎቹ እንደወረሰው
ከሆዳም ምሁራን እንደተማረው
የኢትዮጵያን ታሪክ አጣሞ
እውነትንም  ክዶ…
የሰው ፣ አዳምነትን
የሰው ሄዋን እነትን…
ሰው ሁላ እህትማማች
ሰው ሁላ ወንድምአማች
አይደለም እያለ
በቋንቋ አምልኮ …
“ይህ ሰው የሚሉት
የበቀለ ከመሬት
መሆኑን እወቁት።
ትግሬ ከትግሬ መሬት
ኦሮሞ ከኦሮሞ መሬት ።
አማራም ፣ሲዳማም
ሱማሌ፣ቤንሻጉል ፣አፋርም
ወዘተ።ወዘተ።ከምድር በቅለዋል
ቋንቋቸውንም ፣አውቀው ተወልደዋል።”
በማለት ፣ ለከተሜው፣  ሐሰትን ያውራ።
ነገር ግን…
ባለአገሩ ይለዋል
“ሥማ አንተ ቱልቱላ …
እኛ አይደለንም ሞኝና ተላላ።
ትላንት በጭቆና ሥም
ከኛ ጋር በድንጋይ ላይ
ተቀምጠህ ሥታወራ
ለእኛ ነፃነት መሥሎን ነበራ!!
ሣይሆን ለአንተ እንጀራ!
ይኸው ዛሬ አንተ  ሰማይ
እኛም  እዚህ  ከድንጋይ
መሆናችንን ታውቃለህ
ለምን በእኛ ሥም
 ዛሬም ትነግዳለህ ??
   መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
     17/1/12 ዓ/ም
Min Litazez 1 1024x528
Previous Story

“Fly out of Ethiopia while you can.” ማለትስ አሁን ነው – አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

97103
Next Story

በኦሮሞ ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉት አቴቴ፣ ጨሌ፣ ዋቀፈና፣እሬቻ የጣኦት አምልኮ ናቸው? ወይንስ አይደሉም?

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም
Go toTop