September 2, 2019
14 mins read

የኢሳን (የሶማሌ ጎሳ) ውለታ ፣ አማራ እንዳይረሳ!! –  (ናኦድ አፍራሳ)

ህይወት ያለው ፍጡር  ሁሉ ፣ ቀኑ ሲደርስ እንደሚያልፍ ሁሉ፣ ክፉም ሆነ ደግ ነገር ፣ እድሜ አለው። ለአስራ ሰባት አመታት ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃይ የኖረው ብልሹው  የነመንግስቱ ሃይለማርያም አመራር፣ አገሪቷን ለወራሪዎች ሲያስረክብ፣ ‘አማራን የማጥፋቱን ነገር፣ አደራ’ ያላቸው ይመስላል።

በወያኔና ኦነግ ስር የወደቀቸው ኢትዮጵያ ፣ የመጀመርያው ሰለባ ፣ የሆነው ያው የፈረደበት፣ ያልጠረጠረና ያልተሰናዳው አማራ ነበር። በደርግና በገዛ መሃይምን ልጆቹ፣ በአድሃሪነት ተፈርጆ፣ ትጥቁን ፈትቶ፣ ሃብት  ንብረቱን ተዘርፎ፣ መሬቱን ፣ ተቀምቶ ፣ በጅምላ ብዙ ሺህ አማራ እንደተፈጀ ይታወቃል። የተረፈውም፣ ለድህነት ተዳርጓል ።  በዳር አገር ይኖር  የነበረው አማራ ፣ ከደረሰበት መከራና  ድንጋጤ ሳያገግም ፣ ወያኔና ኦነግ በአዋጅ  ጦርነት አውጀው በርካታ ሺ አማሮች ተፈጁ። እልቂቱ እድሜ ለኦነግ እና ወያኔ፣ ዛሬም አላሰለሰም ። በተለይ በሃረር ፣ በአርሲ፣ በባሌ ፣ በወለጋ፣ በጂማ፣ በኢሉባቦር፣ እልቆመሳፍርት የሌለውን አማራ፣ ኦነግ በቁም እያቃጠለና ቆዳቸውን እየገፈፈ፣ አይን እየጎለጎለ፣ ምላስ እየቆረጠ፣ አንገት እየቀላ፣ ገደል እየከተተ፣ ሴቶች እየደፈረ፣ መፍጀቱ የቅርብ ግዜ ትወስታ ነው። ጉድ እኮ ነው ያሰኛል።  የዛሬቱ ኢትዮጵያ፣ ወራሪ ኦሮሞዎች አሳዳጅ፣  ነባሩ አማራ ደግሞ ተሳዳጅ፣ የሆነባት አገር መሆኗ ።  የአቢይ ኦነግ መንግስት፣ ገና በመውተርተር ላይ ያለውን፣ ያማራ ድርጅት አባላት በሃሰት ወንጅሎ፣ አስሮ የሚያንገላታው፣ የሚገድለው፣ አይቀሬውን የሞት የሽረት ትግል፣ ለመግታት ነው። ይህ ከንቱ ሙከራ ነው። መሬት በሺህ አመቱ ለባለቤቱ ነውና፣ የኦሮሚያቸውን ህልም ፣ እንደ ጉም መትነኑ አያጠራጥርም። ጀግናው ሶማሌ ያለይሉኝታ  ተስፋፊን ኦሮሞ፣ ከኦጋዴን መንግሎ እንዳስወጣ ሁሉ፣ ሌሎችም ነባር ኢትዮጵያውያን፣ አያደርጉትም ማለት አያስደፍርም።

     ኢሳ (ሶማሌ )፣ አማራን ከኦነግ የታደገ፣ ጀግና ነው

‘’ሰው ማለት፣ ሰው የሆነ ነው፣ ሰው የጠፋ እለት ‘’ የሚለው ያበው አባባል ፣ የድንቅ ወገኖቻችንን ፣ የኢሳዎችን ማንነት እንድናነሳ ግድ ይላል። ኦነግ በገጠር ሃረርጌ  የፈጀው አማራ ሳያንስ፣ ድሬዳዋም ከተማ፣ ያልታጠቁን አማሮች ጭፍጨፋ፣  ከመቅጽበት ያቆሙት ጨዋና ጀግኖች የኢሳ (ሶማሌ) ያገር ሽማግሌዎች ነበሩ። የወራሪ ኦሮሞዎች ተጠሪ ነኝ ባዩ ኦነግ፣ አማራውን ከአጽመርስቱ የሚያፈናቅለው መጤ ነህ ብሎ ነው።   የዛሬ 28 አመት ኦነግ ድሬደዋ የፍጸመውን ማንሳት፣ ለዚህ ጸሃፊ ቀላል አደለም። በኢሳ/ ሶማሌዎች ጣልቃ-ገብነት ነበር የኦነጉ ፍጅት ፣ በ68 አማሮች ግድያ ብቻ  ያባራው።  ከሟቾች መሃል ፣ የዚህ ጸሃፊ እናትና አንድ አጎቱ ይገኙበታል። ‘’ዝናብ ሳይመጣ ሁሉ ቤት፣ እንግዳ ሳይመጣ ሁሉ ሴት’’ እንዲሉ፣ የሰው ማንነት የሚታወቀው በክፉ ግዜ ነው።  ቀን የጎደለበት አማራ፣  የጨዋው የኢሳን ፣ ውለታ ሊረሳ አይችልም።

አንባቢ ልብ ሊለው የሚገባው ሌላ ጉዳይ አለ። እነኝህ ሶማሌ ወገኖቻችን ፣ ይህን የመሰለ ለዕልና ያስዩት፣ ታምራት ላይኔ የተባለው፣ የወያኔ አገልጋይ፣ ድሬደዋ መጥቶ ፣  ‘’አማሮች ምንትስ ይሏችሁ ስለነበር ፣ አሁን ግዜያችሁ ነው፣ ፍጇቸው’’ ብሎ ጃስ ባለ፣ በወራት ግዜ ውስጥ ነበር። ታምራት ይህን ሲል ፣ ታዳሚ ሶማሊዎች እንደተጸየፉት ፣ ቪዲዎን የተመለከተ ይገነዘባል።  እግዜር ይባርካቸውና ኢሳዎች የበርካት ሺህ ያልታጠቁን አማሮችን ህይወት ድሬደዋ ታድገዋል። ጀግና ፣ ጀግናን ያከብራል። ኢሳ፣  ያማራን ጀግንነት ጠንቅቆ የሚያውቅ ስለሆነ፣ እነኝህን የክፉ ግዜ ወገኖቻችን፣ ድፍን ኢትዮጵያዊ በተለይ አማራው፣ አይረሳውም።

ሶማሌዎች ነባር ኢትዮጵያውያን እንደመሆናቸው መጠን፣ አትንኩኝ ባይ ስነልቦናቸው ግልጽ ነው ። የድሬዳዋ ኢሳዎች ፣ የኦነግን የፈሪ ድርጊት ፣ የተጸየፉት  ያልታጠቀን፣ ያልጠረጠረን፣ ሴትና ህጻናትን ጭምር አድብቶ መግደል ስለሚረዱ ነው። በሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት፣ ከዲሮ ሰይድ የሚባል ብርቱ የኢሳ ተወላጅ  በትምርቱ፣ አቻ ያልነበረው ትዝ አለኝ።   ለአራት አመታት ፣ ወደ ድሬደዋ ሄዶ መማር ስለነበረበትና የወላጆቹ አቅም አልፈቀደም። ታድያ አንድ ሻለቃ ደጀኔ በሻህ የሚባሉ ሰው፣ ከሶስት  ልጆቻቸው ሳይለዩት፣ ልከው ያስጨርሡታል። ክዲሮ አሜሪካም ለትምርት ሄዶ፣ ከአንደኛ በታች ወጥቶ አያውቅም።  ኢትዮጵያዊ በዋለበት ሁሉ ቁንጮ መሆን አለበት፣ የሚል ጽኑ እምነት የነበረው ወዱ ኢሳ ጓደኛዬ።

             የሶማሌዎች ጥንታዊ ኢትዮጵያዊነትና፣ ወራሪን ኦሮሞ “ጋላ” ያሉበት ምክንያት   

የሶማሌዎች ታሪክ ከረዥሙ የእትዮጵያ ታሪክ ሊነጠል የሚችል አደለም። አማራው ጋር የነበራቸው ዝምድናም ፣ የረዥም ትውልድ ታሪክ ነው። የመን የኢትዮጵያ አካል በነበረችበት ግዜም ሆነ ቀደም ሲል፣ ሶማልያ የኢትዮጵያ አካል ነበረች ። አጼ ዘርዐያእቆብ ፣ በውሃ እጥረት ይቸገሩ የነበሩን ወገኖቹን ለመታደግ፣ ከ 300 በላይ ኤላ ( የውሃ ጉርጓድ ) በኦጋዴን ያስቆፈረው፣ በ 1450 አመተ ምህረት አካባቢ እንደነበር አይዘነጋም።  ዛሬ ድረስ ቀብሪ~ደሃር አካባቢ አገልግሎት የሚሰጡ ጉርጓዶቹ እንዳሉ፣ ምናልባት ብዙ ሰው አያውቅ ይሆናል። ይህ ክስተት ፣ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያን ( ሃረርን ጨምሮ) ከመውረራቸው 120 አመታት በፊት ነበር።  የወያኔዎች አገልጋይ የነበረው አብዲ ኢሌ ፣ አማሮችን  በቅርቡ ያስጨፈጨፈና፣ ቤተክርስቲያናትን ያቃጠለው፣ በጌቶቹ በወያኔዎች ትዛዝና አይዞህ ባይነት ነበር። ስለዚህ ድርጊቱ፣ ሶማሌዎች አይመለከትም። ሶማሌዎች በአማራ ወገናቸው ተመሳሳይ ወንጀል ፈጽመው አይውቁም። በተስፋፊ ቱርኮች ይደገፍ የነበረውን የግራኝን የጥፋት ዘመቻም፣ የሶማሌን ማንነት አይገልጽም። ሶማሌ ጀግና ፣ ለፍትህ ሟች ህዝብ ነው።

ሶማሌ ከ 400 አመታል በፊት ፣ ጋል  የሚላቸውን ኦሮሞዎች ከድንበሩ እንዳበረረ ሁሉ፣ በቅርቡ ደግሞ፣ ከኦጋዴን ነቃቅሎ የጣላችው፣ ወራሪነታቸውን ስለሚያውቅ ነው። ጋላ የሚለው ስያሜ፣ ሶማሌ ለኦሮሞ ያወጣላቸው ነው። ፍቺውም ሃይማኖት የለሽ ነው። ዛሬ በሰው አገር፣ ኦሮምያ የሚል ምድር ከልለዋል። ይኽ ከንቱ ድካም ነው።  በማን አገር? ኦሮምያ ማለትም ወንጀል ነው።

ስለኢሳ ከተነሳ ፣ አንድ የሞቃዲሾ ተወላጅ የሆነ ሶማሌና ፣ ድሬደዋ (አፈተ-ኢሳ እሚባል ሰፈር) ተወልዶ ያደገ አማራን ታሪክ ላንሳ። ሁለቱ በስደት ካናዳ ገብተው ቶሮንቶ መሰናዶ ኮለጅ ይገናኛሉ። አማራው እንደ ወላጆቹ ፣ ሶማልኛን፣ አቀላጥፎ ስለሚናገር፣ ጓደኛሞቹ፣ ዋና ቋንቋቸው ሶማልኛ ነው።  ሁለቱም ብሪቲሽ ኮለምቢያ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በተለያዩ ምህንድስና ዘርፍ ከተመረቁ በኋል፣ የድህረ-ምረቃ ትምርታቸውን አገባደው፣ አንዱ ሞንትሬል፣ ሌላው ሎንዶን ኦንታሪዎ ይኖራሉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ነው ያገቡት ።  ለ 38 አመታት ፣ ያልተለያዩት ጓደኛሞች ፣ ልጆቻቸውም፣ እንደ እህትና ወንድማማች ፣ የሚዋደዱ ናቸው።  ኢትዮጵያዊው የድሬው ተውላጅ ፣ የዚህ ጸሃፊ ታላቅ ወንድም ነው።  ስለዚህ ይህ ጸሃፊም እንደ ታላቅ ወንድም የሚያየውን  ፋራህ መቅተልን ፣ለ32 አመታት ያህል ያውቀዋል።  ከፋራህ የተማራቸው አንዳንድ ቁም ነገር በመትቀስ ጽሁፉን ይቋጫል።

ሶማሌዎች ለኢትዮጵያ የጠላትነት መንፈስ እንዲስርጽባቸው ያደረጉት የግብጽ መህምራኖች መሆናቸው አንዱ ነው። ይህም የሆነው፣ከሶማልያ ነጻነት በኋላ፣ መምህራኖች ይመጡ የነበረው ከግብጽ ስለነበር ፣ እነኚህ መህምራን፣  ኢትዮጵያውያንን እንድ ጭራቅ/ (ኢብሊስ) አድርገው ነበር የሚስሉት አለ ።

ቀጥሎም ፣አንድ ህዝብ መሆናችንን የተረዳሁት ፣ በስደት ቢሆንም፣ ከጥንት ታሪካችን ፣ አንድ ህዝብ እንደነበርን ብዙ መረጃ ተገኝቷል። ይሄም ፣ ሞቃዲሾ ውስጥ ፣ ለህንጻ ስራ መሬት በጥልቀት ሲቆፈር፣ ብዙ የኢትዮጵያ ጽሁፍ መገኘቱ ላንድነታችን አንድ ምስክር ነው የሚል ነብር።

ሌላው የጠቀሰው ነገር፣ ሶማሌዎች፣ ልክ እንደ ኢትዮጵያውያን በአለም ሁሉ በስደት መበተን ነው። ሆኖም ሶማሌዎች ፣ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንዳገራቸው ተደላድለው መኖራቸው ፣ አሌ የማይባል ሃቅ ነው። ይኽም የጠበቀና የጠለቀ የስነልቦና አንድነት  እንዳለን ፣ ሌላ ምስከር ነው የሚል ነበር።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

(ናኦድ አፍራሳ)

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop