August 24, 2019
35 mins read

የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ስነልቦናዊ ፍላጎት ፈፅሞ የለውም – ልኡል  ገብረመድህን

Tigray Map

ልኡል  ገብረመድህን (ከአሜሪካ )
8.20.2019

ሕ.ወ.ሓ.ት የትግራይ ህዝብ ልዕልና ሆነ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የሚያሳስብ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም ። የፖለቲካ አመራሩም ቢሆን በዝምድና ጋብቻና የተሳስረ ነው ። የፖለቲካ ስልጣን ሆነ የኢኮኖሚ ስርአቱ የሚመራው በአንድ የቤተሰበ አምድ እና ታማኝ ታዛዦች አማካይነት ሲሆን ሌላው ገና  የአለም የፖለቲካ ፍልስፍና  በአግባቡ ያልተረዳ ጥቅም ፈላጊና ህዝብ ጨቃኝ የፖለቲካ ካድሬ የሰፈረበት አምባገነን ድርጅት ነው ። የሕ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ ፍልስፍና ጠላት ከወዳጅ የሚለይበት መርህ የተሳሳተ ከሆኑም ባሻገር ለትግራይ ህዝብ ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ ፍፁም የሚመጥን አይደለም ። የሕ.ወ.ሓ.ት ድርጅት በትግራይ ህዝብ ላይ ያለመረጋጋት ስነልቦናዊ ችግር እና ጫና ፈፅሟል። The political philosophy of TPLF is pseudophil and conspiratorial in nature and follows dogmatic assumptions to retain its political doctrine . The party has philosophical and political issues when it comes to Democratic values and political strategies . Enemies versus allies in TPLF political doctrine is vegue and has emperical assessment issues . There is no permanent enemy in emperical political doctrine analysis what so ever . TPLF missed golden opportunities to advance political and social advancement in Ethiopia while it was in full capacities. The failure had nothing to do with external political factors as it wished but the political system within the party itself produced suicidal chopping machine to chop itself drastically and unexpectedly .

ሕ.ወ.ሓ.ት አመሰራረቱ ሆነ መሠረቱ ትግራይ ውሰጥ ነው ። ሆኖም ከድል በኋላ በተግባር ከትግራይ ህዝብ ጋር አልነበረም ። የትግራይ ህዝብ የዲሞክራሲ ረሐብተኛ ነው ። የዲሞክራሲ ጉዳይ ሕ.ወ.ሓ.ት አሰተዳደር የቅንጦት ያህል ነው ። ህዝብ (ሰው ) በነፃነት የመሰለው ለመናገር ይሞክራል ግን በካድሬ ማታ ይታፈናል ፣ አልያም  “ ባንዳ ”  የሚል የበሰበሰ ስያሜ ይሰጠዋል ። የሕ.ወ.ሓ.ት ፖለቲካዊ አሰተዳደር ዜጋ አቀፍ ሳይሆን ከፋፋይ እና በቦዶ የሚኮፈሰ ሗላ ቀር የፖለቲካ ድርጅት ነው ። እንዴት በትግራይ ያልታየ ዲሞክራሲ ከትግራይ ውጭ ዲሞክራሲ ሊያኖር ይችላል ? ። እንዴት በትግራይ ያልታየ መልካም አሰተዳደር በሌሎች ተግባራዊ ይሆናል ?። እንዴት በትግራይ ያልታየ የፍትህ አሰራር በሌሎች ፍትህ ይሰፍናል ? ። እንዴት በትግራይ ያልታየ የምጣኔ ሀብት እድገት በሌሎች ሊከሰት ይችላል ?። እንዴት በትግራይ ያልታየ አንድነት በሌሎች እንዲኖር የሚጠበቅ ?። እንዴት በትግራይ ያልታየ የህግ ልዕልና በሌሎች ተግባራዊ ይሆናል ?። በመሆኑም ሕ.ወ.ሓ.ት የሚከተለው የፖለቲካ መርህ የችግር አውድማ ያለው መሆኑ በርካታ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ማንሳት ይቻላል ። የትግራይ ህዝብ ከሕ.ወ.ሓ.ት የተሻለ የፖለቲካ አማራጭ ፍፁም ያስፈልገዋል ። ህዝቡ ለፖለቲካ ስነልቦና ጉዳት ተጋላጭ እየሆነ መቀጠል የለበትም ። የኢትዮጵያ ህልውና በሕወሓት የፖለቲካ መርህ ላይ የቆመ አይደለም ። በመሆኑም የትግራይ ህዝብ እላፊ መሰዋዕትነት የሚከፍልበት አንዳች አሳማኝ ምክንያት ቢያንስ አሁን ላይ የለም ። የሕ.ወ.ሓ.ት አጉል ጀብደኝነት መቃብር ቢያወረደው እንጂ ዳግም የትግራይ ህዝብ እምነት የሚያገኝበት ሁኔታ ጭራሽ ዝግ ባይሆንም የሚሆን ግን አይመስለኝም ። ሕ.ወ.ሓ.ት ካለፈው ስህተቱ በተግባር የማይማር ፣ ከዲሞክራሲ መርህ ጋር ፈፅሞ የማይጣጣም ፣ ለህግ ልዕልና የማይገዛ አምባገነን የፖለቲካ ድርጅት ነው ። በፖለቲካ መርህ ህዝብ እና አገር በማስተዳደር የበሰበሰ የፖለቲካ አሰተዳደር ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችል የፖለቲካ መርህ አለም ላይ የለም ። ሕ.ወ.ሓ.ት የትግራይ ህዝብ ለማስተዳደር የሚያሰችል አንድም የብቃት ፖለቲካዊ መስፈርት የለውም ። ጉዳዩ “  በቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ነው “ ካልሆነ በቀር በፖለቲካ አሰተዳደር የበሰበሰ ፖርቲ በምን የአስተዳደር መስፈርት ሰልጣን ላይ ሊቆይ ይቻለዋል ? ።

ለትግራይ ህዝብ የፖለቲካ ስነልቦናዊ ችግር መነሻ ምክነያት በጦርነት የተሸነፈው የቀድሞ የደርግ ሥርአት ሳይሆን በራሱ ጉያ ያለ የሕ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ ሥርአት የፖለቲካ መርህ ችግር ነው ። ሕ.ወ.ሓ.ት በፖለቲካዊ ልዕልና አመለካከት የተጎዳ ድርጅት ነው ። ድርጅቱ ከህዝብ በላይ አድርጎ የማሰብ አመለካከት ስህተት ነው ። ከህዝብ በላይ ፖለቲካ ያለ አይመስለኝም ። ከህዝብ በላይ ነፃነት የለም ። ከህዝብ በላይ ልማት ሆነ ሰላም የለም ። ለልማት ሆነ ማህበራዊ ስልጣኔ መነሻ የህዝብ አሰተዳደር መመሥረት ነው ። በትግራይ የህዝብ አሰተዳደር የለም ። ያለው የፖለቲካ ፖርቲ አሰተዳደር ነው ። ያለው አፈናና ብልሹ የድርጅት ተግባር ነው ። ያለው የድርጅት ህልውና ማስቀጠል ነው ። ያለው በየ ሆቴሉ ዳንኪራ መውረድ ነው ። ያውም በግብር ከፋይ ገንዘብ ። ያለው ባረጀ ባፈጀ የልማታዊ ዲሞክራሲ አመለካከት መወዛወዝ ብቻ ነው ። ያለው የመለስ ራእይ ሰባካ ጉባኤ ብቻ ነው ። የትግራይ ህዝብ ልማዳዊ ሰልጣኔ ሆነ ልማት በተግባር ወደነበረበት ለመመለሰ የሚተጋ ካድሬ አይኖርም ባይባልም የሚያሰራ የፖለቲካ ነፃነት በሕወሓት መንደር የሚታሰብ አይሆንም ። ለውጥ የሚያስብ ፈጣን ካድሬ መኖሩ ከታወቀ በስነልቦና እንዲሰልም ( በግምገማ እንዲመታ) ይደረጋል ። ይህ አይነቱ አሰራር አላማው ብቃት ማምከን ነው ። ሕ.ወ.ሓ.ት በዲሞክራሲና ነፃነት የታነፀ የፖለቲካ አመራርና አሰተዳደር ችግር በስፋት ያለበት ድርጅት ነው ። አንድ የፖለቲካ ድርጅት በሐሳብ ልዕልናና መርህ ከልተገራ ትርጉም ያለው የፖለቲካ ህልውና አይኖረውም ። የሕ.ወ.ሓ.ት ካድሬዎች በራሳቸው የፖለቲካ ቁመናና ነፃነት መሰራት ካልቻሉ ለህዝብ መልካም ሥራ ይሰራሉ ብሎ ማሰብ ግብታዊ ነው ። There is no either individual political self confidence or substantive action and/ or collective political honesty within the party and such issue makes the party unproductive and hallucinative to become progressive party . Ideally unlibrated political party is the enemy of practicing Human freedom and social democracy. TPLF has lack of or ambiguous political doctrine that looks back not ahead . There is no fixed politics that either looks back or descends erratically and drastically . Tigrai deserves better and verifiable political organization that promotes liberty and emperical democracy . Political dishonesty and injustice severely hinder freedom of living and social economic liberation.

ሕ.ወ.ሓ.ት ትግራይ ከኢትዮጵያ የመነጠል ብቃት ሆነ የስነልቦና ዝግጅት  የለውም ብቻ ሳይሆን ሊኖረውም አይችልም ። የትግራይ ህልውና የሚረጋገጠው የኢትዮጵያ ህልውና ሲረጋገጥ መሆን አለበት የሚለው መሠረተ ሐሳብ ስህተት ነው ። ይህ አይነት አሰተሳሰብ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የግብዝነት ችግር ያላቸው ይመሰላል ። ለፖለቲካ ስልጣን አመቺ ባልሆነበት ወቅት እየመረጡ የመገንጠል አጀንዳ ማንሳት ጊዜያዊ የፖለቲካ ንግድ እንጂ የፍትህና መብት ጥያቄ ፈፅሞ ሊሆን አይችልም ።  ህዝብ የፖለቲካ ሰንቅ እንጂ የፖለቲካ ስልቻ መሆን አይችልም ። ህዝብ የፖለቲካ እዳ ማስያዣ አይደለም ። People are free of political failure consequences. Beyond , politics works for the people upon the people but not just the interest of the political party. The political party shall not grant the people’s will for its survival assumptions and purposes . There shall not be possible argument that brought ordinary people to the center of political discourse as the magnitude of Party politics faces uncertain reality . The political assumption that states who ever controls the politics controls the mind and will of the people is just doesn’t really work. Political honest rewards to gain the heart and mind of most ordinary citizens . ሕ.ወ.ሓ.ት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርአት ተፅዕኖ ፈጣሪ እንዳይሆን ያገደው ራሱ ነው ። ሰው ጤፉ የነበሩ የድርጅቱ የፖለቲካ ካድሬዎች ከአለት የጠነከረ ስልጣን ያላቸው ይመስላቸው ነበር ። ለህዝብ የነበራቸው ንቀት የሚያበሳጭ ነበር ። የፖለቲካ ሰልጣን የህዝብ መሆኑ ጭራሽ የረሱት ይመስሉ ነበር ። ሰው ሲዘልፉ ፈሪሐ ፈጣሪ ፈፅሞ አልነበራቸውም ። በተለያዩ መንገዶች ህዝብ ያሰቃዩ ነበር ። ህዝቡም የፖለቲካ ካድሬዎች በሆዱ ይረግማቸው ነበር ። ሁኔታውም እውን ሆነ። መርገሙም ደረሰ ። በህዝብ የተጠላ የፖለቲካ አሰተዳደር ዲሞክራሲያዊ አሰተዳደር ለመሆን የሚያስችል ተግባራዊ የፖለቲካ መርህ ለውጥ ማካሄድ አለበት ። ለምን በህዝብ ተጠላሁ ብሎ መጠየቅ ተገቢነት ያለው የፖለቲካ ፍልስፍና ጥያቄ ነው ። እንደ እኔ እይታ የሕ.ወ.ሓ.ት አብይ ችግሩ ተራማጅ (progressive ) የፖለቲካ ድርጅት ካለመሆኑ በላይ የፖለቲካ ወቅታዊ ሁኔታ የመተንተን አቅም ዝግጁነት ችግር ይታይበታል ። ከጥላቻ የራቀ ፣ ሐሳብ ላይ ያተኮረ ፣ የህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብት የሚያከብር የፖለቲካ አመራር ለውጥ ያሰፈልጋል ።

የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ጉዳይ አጀንዳው አይደለም ። ለመገንጠል  የሚያስችሉ ምክንያቶች የሉትም ። የትግራይ ህዝብ የደረሰበት የኢኮኖሚ ተፅዕኖ ( Intentional Economic discrimination ) ፣ የእምነት ተፅዕኖ ( Intentional religion discrimination ) ፣ ኢፍትሐዊ የሐብት አጠቃቀም ሻጥር  ( Intentional and systemic Resource discrimination ) ፣ እንዲሁም የቋንቋና ባህል ተፅዕኖ (Intentional lingustc and cultural discrimination ) የለውም ። በመሆኑም ህዝቡ በኢትዮጵያዊነቱ ለአፍታም ያህል አይጠራጠርም ። የመገንጠል አጀንዳ የትግራይ ህዝብ አጀንዳ ይሆናል ብሎ ማሰብ የትግራይ ህዝብ ማንነት በጥልቀት ካለመረዳት ሊሆን ይችላል የሚል አሰተያየት አለኝ ። የመገንጠል አጀንዳ የሚያነሳው የትግራይ ህዝብ ሳይሆን ህዝብ እና የፖለቲካ ድርጅት በተገቢው ሁኔታ መተንተን የተሳናቸው ደካማ  እና ግብዝ ፖለቲከኞች መሆናቸው የሚያነጋግር እንደማይሆን እገምታለሁ ። የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ህዝብ ነው ። የትግራይ ህዝብ የሕ.ወ.ሓ.ት አሰተዳደር ብልሹነት እዳ ከፋይ ሊሆን አይችልም ። የፖለቲካ ድርጅት ለፈፀመው የአስተዳደር በደል ህዝብ ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቱ ሙሉ ሀላፊነት መውሰድ አለበት ። በፖለቲካ ብልሹ አሰተዳደር ምክንያት ህዝብ ላይ ጥቃት መፈፀም አብይ ስህተት ነው ። ከዚህ ቀደም በትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈፀመው ሰብአዊ ጥቃት መደገም የሌለበት ፈፅሞ ስህተት ነው ። የትግራይ ከሕ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ አሰተዳደር በድል ጋር ምን የሚያገናኘው ጉዳይ የለም ። ሕ.ወ.ሓ.ት ለፖለቲካ ፍጆታ የትግራይ ተወላጆች ትግራይ ብቻ እንዲከትሙ ጥሪ ማድረጉ ስህተት ነበር ። የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ የፌዴራል አሰተዳደር ክልሎች ጥሮ ግሮ ለመኖር የሚከለክል የህግ ሆነ የሰላም ችግር የለበትም ። የትግራይ ህዝብ ከወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ምንም አይነት ማህበራዊ ፣ አስተዳደራዊ ፣ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ችግር የለበትም ። የፖለቲካ ድርጅት ችግር የህዝብ ችግር አድርጎ ማቅረብ ስህተት ነው ። Political parasitic is dangerous to enhance Democratic society . Clarity of political ideology is substantially essential to foster sustainable peace, economic development, and political and social integrity at most. Separation of political entity from social assimlation helps to factorize the complixity of social and Democratic claims. Let the real politics works for the people not just  be divisive and  social parasitic.  የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ የሚነጥለው ተፈጥራዊ ሐይል የለም ።  ለመሆኑ ትግራይ ከየት ነው የምትነጠለው? There is no definite natural phenomena that accords secession of Tigrai from its homogeneous soil .

የትግራይ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት የለውም ። የነበረው እና አሁንም ያለዉ የአስተዳደርና የፍትህ ችግር ነው ። የህዝብ መሠረታዊ ፍላጎት የሚፈታ የፖለቲካና የፍትህ ተቋማዊ አሰተዳደር በተግባር ያስፈልገዋል ። ሕ.ወ.ሓ.ት የትግራይ ዘር ፖለቲካ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ህልውና ከማሰብ በፊት የፖለቲካ ውክልና ለሰጠው የትግራይ ህዝብ መልካም አሰተዳደር እንዲሁም ተግባራዊ ማህበራዊ ፍትህ ( Practical social justice ) በተግባር ማሳካት መቻል ይጠበቅበታል ። የትግራይ ተጨማሪ መሰዋዕትነት የሚከፍልበት አንዳች ምክንያት የለውም ። ህዝቡ የሚፈልገው ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፣ ተግባራዊ ፍትህ ፣ ተግባራዊ መልካም አሰተዳደር ፣ ተግባራዊ የዲሞክራሲ ክልላዊ ተቋም ፣ ተግባራዊ ማህበራዊ ልማትና የተረጋጋ ሰላም ነው ። የትግራይ ህዝብ ግጭትና ጦርነት ፈላጊ ህዝብ አይደለም ። ለአብነት ያህል ትግራይ ከጎንደር ጋር የሚያዋስነው ግጨው( ፀለምት)  ለሀያ አመታት ያህል  አካባቢው በፖለቲካ ሴራ ሲታመስ የትግራይ እና ወንድም የአማራ ህዝብ ለደቂቃም ቢሆን ደም አልተቃባም። እንደ የፖለቲካ አሰተዳደር ችግር ቢሆን ኖሮ በግጨው መሬት ላይ የማያቋርጥ ችግር ይከሰት ነበር ። ጉዳዩ የሁለቱም ህዝብ የአካባቢው አዛውንቶች በምክክር እና ተቀራርቦ በመነጋገር ሊፈቱት ችሏል ። ይህ የትግራይ ፖለቲከኞች ሳይሆኑ የትግራይ ህዝብ ብስለት ውጤት ነበር ። የግጨው ጉዳይ ለሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች እንደ ታላቅ የግጭት አፈታት  ተምሳሌት ሊሆናቸው የሚችል ውጤታማ አብነት ነው ። የፖለቲካ ድርጅቶች የህዝብ ስሜትና ፍላጎት መከተል ይኖርባቸዋል ። ህዝብ የፖለቲካ ምህዳር አቅጣጫ አመላካች ሐይል ነው ። የፖለቲካ አሰተዳደር የህዝቡን የፍላጎት አቅጣጫ ማሳኪያ መሣሪያ ነው ። ህዝብ ሰላም እያለ የፖለቲካ መርሑ ሰላም ማዕከል ያደረገ የፖለቲካ ሥራ ማካናወን አለበት ። ህዝብ ልማት እያለ የፖለቲካ ሥርአቱ ልማትን ማሳለጥ አለበት ። ህዝብ ፍትህ እና ዲሞክራሲ እያለ የፖለቲካ አሰተዳደር ህግና ፍትህ እንዲሁም ዲሞክራሲ ማስፈን አለበት ። ሆኖም የፖለቲካ ሥርአት ከህዝብ ፍላጎት በተፃራሪ አቅጣጫ የፖለቲካ ተግባር ሲያከናውን ይስተዋላል ። ይህ አይነቱ አሰራር የአምባገነን ሥርአት ባህሪ ነው ። ህዝብና የዲሞክራሲ ተቋም የሚቆጣጠረው የፖለቲካ ሥርአት በሌለበት ክልል መልካም አሰተዳደር ሆነ ተግባራዊ ፍትህ ይኖረዋል ብሎ ማሰብ ያዳግታል ። ምክንያት የፖለቲካ ሥርአት ልጓም የሚያበጅ ገለልተኛ የዲሞክራሲ እና የፍትህ ተቋም መገንባት ላለውም ሆነ ለመጪው የፖለቲካ ሥርአት መልካም ይሆናል ። በአንድ የፖለቲካ ፖርቲ የበላይነት የሚመራ የዲሞክራሲ ሆነ የፍትህ ተቋም ዲሞክራሲያዊ ተቋም መሆን አይችልም ። በመሆኑም ዳኛ ሆነ ጠበቃ የፖለቲካ ሥርዓቱ መሣሪያ እንጂ የህግን ልዕልና ለማክበር ሆነ ለማስከበር ደንታ አይኖራቸውም ። የዲሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማት የፖለቲካ ሥርአት አገልጋይ ሳይሆን የዲሞክራሲ መርህ እና የፍትህ ልዕልና አስከባሪ ናቸው ።

የትግራይ ህዝብ ራሱን ልኩን የሚያውቅ ጭዋና አስተዋይ ህዝብ ነው ። ለፍትህና ለሰላም ዘብ የቆመ ህዝብ ነው ። የትግራይ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ የፍትህና ዲሞክራሲ እንዲሁም መልካም አሰተዳደር ችግር አለበት ። በትግራይ ለሚፈፀመው የፖለቲካ ሥርአት ግድፈት ሙሉ ሀላፊነት የሚወሰደው የሕ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ አሰተዳደር መሆኑ አጠያያቂ አይሆንም ። ሰፊው የትግራይ ህዝብ አሁንም በድህነትና ድንቁርና ውቅያኖስ ላይ ነው ። የትግራይ ህዝብ ከዲሞክራሲና ፍትህ እጦት ባሻገር ስልሳ ከመቶ የሚጠጋ ህዝብ በእርዳታ የሚኖር ህዝብ ነው ። ወጣቱም ቢሆን ሥራ አጥቶ ለስደት እየተዳረገ ይገኛል ። በትግራይ ያለ የኢኮኖሚ ሆነ የፖለቲካ ሥርአቱ መሠረታዊ እልባት ያስፈልገዋል ። ለፖለቲካ ፖርቲ ሳይሆን ለህዝብ የወገነ አሰተዳደር ያሰፈልጋል ። የትግራይ ሙህራን ከፖለቲካ ውገና ተላቆ ዲሞክራሲና ፍትህ የሰፈነበት ክልል እንዲሆን ታሪካዊ ሀላፊነት አለባቸው ። ማጎብደድ ይብቃ ። ፍርሃት እና ዝምታ ለውጥ አያመጣም ። የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ከኢትዮጵያ መገንጠል አይደለም ። የህዝቡ ጥያቄ የንፁህ ውሃ አቅርቦት ነው ። የህዝቡ ጥያቄ ጦርነት ሳይሆን ሰላምና ፍትህ ነው ። የህዝቡ ጥያቄ ልማትና ዲሞክራሲ ነው ። የሕ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ ሥርአት በባህሪው የለውጥ ፖለቲካ ድርጅት አይደለም ። እንደሚሰመር አንድ ቦታ የተቸነከረ የእንግዴ ልጅ ይመሰላል ። ቢቻለውም እንደ ኢሲያሰ አፈወርቂ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ለመሆን ፍላጎቱ ዜሮ አይደለም ። የሕ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ ሥርአት ለማደስ ሆነ ለመለወጥ አሰቸጋሪ የሚያደርገው ድርጅቱ የሚመሩ የፖለቲካ ሀላፊዎች የፖለቲካ ብስለታቸው ከቃላት ያለፈ ያለመሆኑ ነው ። Political  leadership within the party’s doctrine is dependant and defendant of political theories and assumptions not analytical and empirical and formulated political analysis . The party is good in theoretical and hypothetical analysis that cultivates problematic and gigantic social issues . Political absolutism escorts to visible social and political failures . There is Tigrigna  song recently released to public says, “ ናይ ህዝቢ ድምጺ ይሰማዕ “ which is literally means that let the voice of the people be heard . I definably and determinably agree with that song  or phrase of song .

በትግራይ ያለ የፖለቲካ ሥርአት ይስተካከል ። ዶክተር አረጋዊ በርሄ የትግራይ ህዝብ ለመጉዳት አዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ሴራ ይዶልታል የሚል የፖለቲካ ድርጅት የፖለቲካ መሪ መሰማት ቃር ቃር ያሰኛል ። የትግል ባልደረባው አፈር ለማልበሰ መቀሌ ሲደርስ በህዝብ እንዲጠላ የፖለቲካ ሴራ መሰራት ጊዜው ያለፈበት አሰራር ይመስለኛል ። የትግራይ ህዝብ ማህበራዊ ሆነ ኢኮኖሚያዊ ችግር የሚፈታው በፖለቲካ መጠላለፍ አይመስለኝም ። ይልቁንም ተቀራርቦ በመነጋገርና በመወያየት እንዲሁም በመመካከር ይመስለኛል ። ያለፈው የፖለቲካ ሴራና ጠባሳ ላይ መንጠልጠል ጠቃሚነት የለውም ። የሙታን ታጋይ ልጆች ባንዳ ማለት ተገቢ አይመስለኝም ። የሕ.ወ.ሓ.ት የቂምና ሴራ ፖለቲካ ተወራራሽ ነው ። ይህ ደግሞ የፖለቲካ ታማኝነት ይኖረው ይሆናል እንጂ የህዝብ ፍላጎት እና ማህበራዊ ትስስር አያመጣም ። የፖለቲካ ቂም በቀል የሰነፎች እና አምባገነን የፖለቲካ መሪዎች አይነተኛ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ። የፖለቲካ ሥርአት የመደራደር የሐይል ሚዛን የጠበቀ መሆን አለበት ። የፖለቲካ ሥርአት ስኬት የድርድር ውጤት ነው ። የፖለቲካ ሥርአት የሐይል ሚዛን የዲሞክራሲ መርህ ውጤት ነው ።  ይህ ደግሞ የፖለቲካ ስልጣን  የሚይዝ የፖለቲካ ድርጅት የዲሞክራሲ መርሆዎች እንዲያከብር ያግዘዋል ። The set of Political system shall engage and bind by the core principles of Democratic and philosophical human values.  የሕ.ወ.ሓ.ት የፖለቲካ ሥርአት ይዘትና ቅርጽ መሠረታዊና መዋቅራዊ የፖለቲካ ተግባራዊ ለውጥ አላመጣም ። የትግራይ ህዝብ አሁንም የስነልቦና ሰለባ ነው ። ህዝብ በዲሞክራሲ እና በህግ ልዕልና ማበልጸግ ሲቻል የፖለቲካ ሥርአት ሰለባ አልያም የፖለቲካ ሥርአት አለመረጋጋት ሰለባ እንዲሆን መሆን የፖለቲካ ንፁህ ውድቀት እንጂ ስኬት አይደለም ። በሲቪክ ማህበራት ላይ የፖለቲካ ተፅዕኖ ማሳደር የፖለቲካ ሥርአት ችግር እንጂ የፖለቲካ ሥርአት መረጋጋት አያሳይም ።

የትግራይ ህዝብ ከወንድም ጎረቤት የኤርትራ ህዝብ ጋር መልካም ማህበራዊ ሆነ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲኖረው ሁሌም ምኞቱ ነው ። ሆኖም የሕ.ወ.ሓ.ት ፖለቲካዊ አሰራር ሆነ የመደራደር ብቃት የለውም ብሎ መደምደም አይከብድም ። የፖለቲካ ሥርአት መርዝ ሳይፈወሰ ተፈላጊው ሰላምና መቀራረብ በቀላሉ አይሳካም ። በሁሉም ወንድም ህዝቦች ሰላም እንዳይሰፍን የፖለቲካ ሴራው የተወሳሰበ እና የተበላሸ ነው ። ሰላምና መቀራረብ የሚያሳካ የፖለቲካ ሥርአት በትግራይ ሆነ በኤርትራ የለም ። በመሆኑም የችግሩ ጥልቀት እና ስፋት እንዳለ የሚቀጥል ይሆናል ። የፖለቲካ ሥርአት ችግር እልባት ካላገኘ የሰላምና መቀራረብ መንገድ ፍፁም ዝግ ነው ። በፀሎትና በሙዚቃ ዝግጅት የሚመጣ ሰላም የሚኖር አይመስለኝም ። የኤርትራ የፖለቲካ ሥርአት መሪ እና መርህ አልባ ሲሆን ተግባሩም የሴራ ፖለቲካ ማራመድ ነው ። በትግራይ ያለው የፖለቲካ አየርም ብዙም ከኤርትራ ፖለቲካ የተሻለ አይደለም ። የሁለቱ ጎረቤት አገር የፖለቲካ መዋቅር ሆነ የፖለቲካ ፍልስፍና መርህ አልባ እንዲሁም የፖለቲካ ሴራ ላይ የተተከለ ካሰማ ብረት ነው ። ሁለቱም ህዝብ ማዕከል ያደረገ ሳይሆን ስልጣን ላይ የተንጠለጠለ የፖለቲካ ስሪት አራማጅ ናቸው ። መናናቅ እና መጠላለፉ ከልክ ያለፈ ነው ። ለመነጋገር ሆነ ለመደራደር የሚያስችል ቀዳዳ የለም ። በአምባገነንነት እና ሴራ የተመሠረተ የፖለቲካ ሐይል ለድርድር ሆነ ለሰላሙ እንቅፋት ነው ። የትግራይ ህዝብ ሆነ ወንድም የኤርትራ ህዝብ መካከል ታሪካዊ ግንኙነት እንጂ ማህበራዊ ቅራኔ የላቸውም ። ችግሩ የህዝብ ችግር ሳይሆን የፖለቲካ ሥርአት ችግር ነው ። መፍትሔ በህግ ልዕልና እንዲሁም በዲሞክራሲ መርህ የሚመራ የህዝብ መንግስት መመሥረት ነው ። ህዝብ የፖለቲካ ሰለባ መሆን የለበትም ። A society shall not deserve political impressions and indiscretions for zero sum politics . መርህ አልባ ፖለቲካ በመጪው ትውልድ ላይ የሚያሳድረው የለውጥ ተፅዕኖ ለመገመት አያዳግትም ። ራሱ መርህና ህግ እየጣሰ ሌላውን የሚወነጅል የፖለቲካ ሥርአት የትውልድ ነቀርሳ እንጂ የመልካም አሰተዳደር ተምሳሌት ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ የለም ። ሕ.ወ.ሓ.ት እንዲጠናከር መሪ እና የፖለቲካ መርህ ያሰፈልጋል ። በትግራይ ገለልተኛ የዲሞክራሲ ተቋም መመሥረት ለመጪው ትውልድ የፖለቲካ አሰተሳሰብ አድማስ ይሆናል ። በትግራይ ገለልተኛ የፍትህ ተቋም መመሥረት የትግራይ ህዝብ የነበረ ስልጣኔ እንዲያሰራራ ለማድረግ ያግዛል ። በትግራይ የዲሞክራሲ ተቋም መመሥረት የትግራይ ህዝብ ፍላጎት እና ምኞት ማሳካት ይሆናል ። ፍትህ እና የዲሞክራሲ ሰልጣኔ የትግራይ ህዝብ መለያ ምልክቶች መሆን ይገባቸዋል ። የመጠላለፍ የመንደር ፖለቲካ ይቁም ! . The beginning toward civilization depends on nothing else but Human freedom and the beginning toward poverty relies on political impression and autocracy. Rule of law shall prevail unconditionally for so many good reasons and positive causes for all human living .

በዲሞክራሲ እንዲሁም ኢኮኖሚ የበለፀገች ትግራይ ለማድረግ የትግራይ ሙሁራን እያደረጉት ያለ ሁለገብ የምርምር እና ጥናት ( Academic research)  ተሳትፎ እጅግ አስደሳች ነው ። ውጤታማ እንዲሆኑም የማይመኝ የክልሉ ተወላጅ ያለ አይመስለኝም ። ከፖለቲካ አድርባይነት በመራቅ ሞያዊ አሰተዋጽኦ ላይ ትኩረት ማድረጋቸው ለትግራይ ህዝብ ሁለንተናዊ ለውጥ በር ከፋች ነው ። በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ህዝብ እድገት እና ብልፅግና ለማሳለጥ ሙሁራዊ ተሳትፎ እያደረጉ ላሉ ሁሉ ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ ። የችግር መፍትሔ ተኮር ተግባር ላይ መሆናቸው ደግሞ የበለጠ ያስመሰግናቸዋል ። ህዝብ አገር ያለ ሙሁራን ተሳትፎ ሁሉም አድሮ ቃሪያ ይሆናል ፣ ችግርና ድንቁርና ይስፋፋል ፣ የህግ ልዕልና ይበሰብሳል ፣ የዲሞክራሲ መርህ ይጣሳል ፣ የፖለቲካ አምባገነን ይስፋፋል ፣ ስደትና ድህነት ሥር ይስዳል ፣ በአጠቃላይ ሥርአት አልበኝነት ይከሰታል ። የትግራይ ህዝብ ታላቅ ምኞትና ፍላጎት የሚያሳካ የፖለቲካ መዋቅር እንዲኖር የትግራይ ሙሁራን ሞያዊ አበርክቶ ከሁሉም የላቀ ይሆናል ። ፖለቲከኞች ለመጪው ትውልድ እድገትና ብልጽግና አስባችሁ ሥሩ !  ፈጣሪ የትግራይ ህዝብ ይባርክ ! ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይቀድስ ! አሜን ! ።

 

7 Comments

  1. “የትግራይ ሙህራን ከፖለቲካ ውገና ተላቆ ዲሞክራሲና ፍትህ የሰፈነበት ክልል እንዲሆን ታሪካዊ ሀላፊነት አለባቸው” ይህ ትልቅ አባባል ነው። የትግራይ ምሁራን የህወሓትን የቁልቁለት ጉዛ እንደዚህ በማጋለጥ የድርሻውን ቢወጣ ድርጅቱ ከባህር የወጣ አሳ ስለሚሆን ሽንፈቱን እንዲቀበል በማስገደድ ትግራይን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን መታደግ ይቻላል ።

    እግዚአብሔር ይስጥልን።

    • ፍላጎትህ እና ምኞትህ አየር ላይ ተንሳፎ ለዘላም ይቀራል፡፡ ከህዋህት ውጭ ለትግራይ ህዝብ የሚታገልለት የለም፡፡ከምኞትህ አንጻር የትግራይ እድገት ባንተ አይን በቁልቁለት አሰተሳሰብ አይተኸው ይሆናል፡፡በአፄዎቹ ጊዜ የትግራይ ህዝብ እንዴት እየኖረ እንደነበር አንተም ታውቀዋለህ፡፡

  2. One says “ye’Tigray hizb ye’megentel azmamia alew”; the other says “የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ስነልቦናዊ ፍላጎት ፈፅሞ የለውም”. Mark you, Hizbu min’m sayteyek, mini’m saynager!

    Hizbu.., hizbu…hizbu… I could not get the political meaning of this UNVERIFIABLE magic indicator.

    What can be said in general terms about HIZBU, without counting the numbers, is this: HIZBU aspires for peace, prosperity, harmony regardless of ethnicity, gender, creed, religious affiliation – cos these are universal human values (minus for the malicious politicians/activists).

  3. አሁንም ልዑል የሚል ስም የመሳፍንት ስም ነው ስለዚህ አንተ ራስህ ባንዳ ነህ ወይም የባንዳ ልጅ ነህ ያኔ ፈርጥጠህ የሄድክ ነህ ስለዚ ስለ ትግራይ ህዝብ መስዋእትነት፤ ህልውና የመናገር የመወሰን አቅሙም ሞራሉም የለህም፡፡ ከነፍጠኞች ጋር በመሆን ትግራይ ህዝብን ለመውጋት ለማበርከክ ለማሸማቀቅ ቅድሚያ ህወሀትን ለማደከም ሌት ተቀን የምትሰሩ ሙሁራን ነን ባዮች በብተታቀመሙ ይሻላችዋል፡፡

  4. I don’t agree with the map you post on this page. This is one of the cause of the conflict. Let us start up the people of Ethiopia leave as they were leaving as before without the border & regional state. That brings belonging to me instead of belonging to us.

    • መሬት ሰትፈጠር ተሠምሮ የተሠጠ ይመሥል ወደ ቀድሞ አስተዳደር ይመለስ ማለትህ የጨቋኝ አሰተሳሰብ ከተላበሱት ትምክተኞች አጫፋሪ ወይም የፖለቲካ መሀይም ነህ፡፡!

  5. የትግራይ ህዝብ ሳይሆን፣ የህወሓት መሪዎች የባንዳነት ስነ አእምሮ ነው ያላቸው፤ አሁንም የህዝብ ሰራዊት ተጠቅመው የራሳቸውን ሙሱና መስመራቸው ሊያቆዩ ፈልገው እንጂ ለትግራይ ህዝብ ፍቅር ቢኖራቸው ዲሞክራሲ እና ፍትሕ ማስፋት በቻሉ ነበር።
    አቶ ልአል ስብእናህ አደንቁት ቶም ካልኦት ካባኻ ተዝልቁሁ ህዝብና ምሓለፈሉ።

Comments are closed.

Previous Story

በኢትዮጵያ ከለውጥ ሃይሉ በበለጠ የለውጥ አደናቃፊ እየሆነ ያለው የልሂቃን ያልተገባ መቆራቆስ ነው! – አበጋዝ ወንድሙ

Next Story

ዘረኝነት ትልቁ ዕብደት – (ከሰሞኑ አንኳር አሣዛኝ ክስተቶች ጥቂቶቹ) – ምሕረት ዘገዬ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop