August 15, 2019
14 mins read

በሰይጣን ግዛትም ሥላሤዎች አሉ – እንተዋወቃቸው፡፡ – ወልደ ማርያም ዘገዬ

በፈረንጅኛው Trinity ባማርኛው ሥላሤ አብን (the Father)፣ ወልድንና (the Son) መንፈስ ቅዱስን (the Holy Spirit) ይይዛል፡፡ በምሥጢረ ሥላሤ ትምህርት ሥላሤዎች አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ በሚል አገባብ ይታወቃሉ፡፡ ይህ እንግዲህ በሥነ መለኮት ወይም ቴዎሎጂ ሃይማኖታዊ የዕውቀት ዘርፍ የሚተነተን ነው፡፡

እስካሁን ባለው የሥነ መለኮት ትምህርት ፀላዔ-ሠናያት የሆነው ሣጥናኤል እምቅድመ ፍጥረተ አዳም ወሔዋን ዘመን  ጀምሮ ከእግዚአብሔር መንግሥት በጠባዩ መማረጥ ሳቢያ ከገነተ ሰማይ ወደ ደይነ ምድር መወርወሩንና መሰል ሰብኣዊና ረቂቅ ፍጡራንን ወደ ግዛቱ ከመጠቅለሉ ውጭ እንደ እግዚአብሔር መንግሥት “ሥላሤ” የሚባል ሥነ ተፈጥሮ የለውም፡፡ ሰይጣን በልማድ እንደምናውቀው የክፋት ምንጭና የብልግናዎች ሁሉ ቁንጮ መሆኑን ነው፡፡ ሣጥናኤል፣ ጋንኤል (ሲበዛ አጋንንት)፣ ዲያብሎስ፣ ሉሲፈር ወዘተ. በሚባሉ የክትና የሠርክ ስሞች የሚታወቀው ሰይጣን የሞት፣ የስደት፣ የጠብ፣ የግጭት፣ የስቃይ፣ የመከራ፣ የርሀብ፣ የበሽታ፣ የዕልቂት፣ የድርቅ… ተምሣሌትና ዋና መንስዔ እንደሆነ የሁላችን ግንዛቤ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሰይጣንን ኃይል ለተለያዬ ዓላማ ይጠቀማሉ፡፡ ገንዘብና ሥልጣን ለማግኘት ሲባል ከትንሽ ገንዘባዊ መስዋዕትነት እስከሰው ነፍስ ጭዳነት ለሰይጣንና አጋፋሪዎቹ በማቅረብ ብዙ የሀብትና የሹመት ደረጃዎችን የሚወጡ እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የሁሉም መጨረሻ ግን አያምርም፡፡ አንድ መዋቲ ሰው ደግሞ በሰይጣን ከሚያልፍለት በእግዚአብሔር ደጅ በድህነት ኖሮ ቢሞት ይሻለዋል፡፡ የሰው ወርቅ አያደምቅም፡፡ …. ሰይጣን ብድርን ሲያስከፍል በነፍስ እንጂ በቁስ አይደለም፡፡ ሰዎች ይህን ቢረዱ ከሚታየው የሰው ለሰው መጨካከን ከዕጥፍ በላይ ይቀንስ ነበር፡፡

ከዚህ ተፈጥሮው በመነሣትም በግብርም በአስተሳሰብም እርሱን የሚመስሉ ፍጡራን ከሰዎችም ሆነ ከሌሎች እንስሳት ሲገጥመን “ሰይጣን” እንላቸዋለን፡፡ ዓለማችን እጅግ ብዙ የሰይጣን ምሣሌዎችንና ቀጥተኛ ወኪሎችን አስተናግዳለች፡፡ እነዚህ ሰይጣናት (devil-incarnates) የንጹሓን ዜጎችን የዕለት ከዕለት ሰላም ከማወክ አልፈው ለበርካታ ጦርነቶችና ግጭቶች መንስኤ በመሆን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የዓለማችን ዜጎች ዕልቂት ዋነኛ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ሰይጣናዊ ሰዎች ሂትለርን ከጀርመን፣ ሙሶሊኒን ከጣሊያን፣ መለስን ከኢትዮጵያ እዚህ ላይ በዋቢነት ብንጠቅስ አይበዛባቸውም፡፡ እነዚህ ከሞታን ሠፈር የምናስታውሳቸው የአጋንንት ወኪሎች ናቸው፡፡ የዓለማችን ቅርጽ እንዲህ ማስጠሎ የሆነው የነዚህ “ሰዎች” አሉታዊ ሚና ጎልቶ በመውጣቱ ነው፡፡ ጊዜያቸውም ስለሆነ፡፡

በአሁኑ ወቅት በሕይወት እየኖሩ ሰይጣንን በሚያስከነዳ ክፋትና ተንኮል ሀገርንና ሕዝብን እንደዶሮ እየገነጣጠሉ የሚገኙ የሰይጣን ልጆች ደግሞ በየሀገሩ አሉ፡፡ እንደኢትዮጵያ ግን በሌሎች አይበዙም፡፡ ኢትዮጵያ መንግሥትም ባለቤትም ስለሌላት በተለይ በአሁኑ ወቅት እነዚህ የአጋንንት ውላጆቸ እንደልባቸው እየፈነጩ ይታያሉ፡፡ የዘመንን ፍልስፍናዊ ቅኝት በሚገባ መጠቀም ማለት እንደነሱ ነው፡፡ ከነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹና ይህን ካምፕ በፊታውራሪነት የሚመሩት የሚከተሉት “ኢትዮጵያውያን” ናቸው፡፡

  1. ሕዝቅኤል ጋቢሣ (ፕሮፌሰር ይሉታል)
  2. በቀለ ገርባ
  3. ጃዋር ሞሀመድ

 

እነዚህ ናቸው በሀገራችን “የሰይጣን ሥላሤዎች ናቸው” ያልኳቸው፡፡ አንድም ሦስትም እየሆኑ ሀገርንና ሕዝብን ለማጨራረስ ቀን ከሌት  ያለ አንዳች መታከት የሚባዝኑት የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶችን ማወቅ ተገቢና ወቅታዊም ነው፡፡ እነሱም ይህን አያጡትም፡፡

ሕዝቅኤል ጋቢሣ ሌላው ሁሉ ቀርቶ የአብራኩ ክፋይ የሆነች ልጁ ከዩኒቨርስቲ በቅርቡ ተመርቃ በኢትዮጵያ ባንዲራ ስትደምቅበት የሰይጣን ሽንት የሆነው እርጉም አባቷ ግን የሚሠራው ሁሉ የልጁን ሀገር ድራሽ ማጥፋት ሆነ፡፡ “እበት ትል ይወልዳል” ይባላል፡፡ የዚህን የሰንበት ጽንስ ዕኩይ ተግባር እኔ ልቅርና አባቱ ሰይጣን ራሱ ዘርዝሮ አይጨርሰውም፡፡ የሚናገረውና የሚጽፈው ሁሉ እንዳንዳች ነገር የሚቆንስና የሚገለማ ነው፡፡ በምን ቀን ይህን መሰሉ የአጋንንት መንፈስ እንደተጣባው አይታወቅም፡፡ ዘመድ አዝማድ ቢኖረው የሰውዬው ደዌ ብዙዎችን ሳይበክልና የጋራ መኖሪያችንን ሳያወድም ክፍል ተቆጥሮለት ወደ ታወቀ ጠበል ወስዶ ማስጠበል ነበር፡፡

በቀለ ገርባ የሚሉት በሽተኛ ደግሞ አለ፡፡ ከሰው ልጅ ተፈጥሮ በማፈንገጥ “ኦሮሞ ወንድ ከኦሮሞ ሴት ውጭ ከተኛ ዘሩን እንዳጠፋ ይቆጠራል…” ብሎ ሲናገር ቅንጣት የማያፍር ጥቁር ሰይጣን ነው፡፡ “በኦሮምኛ ካላናገሯችሁ ምንም ዕቃ አትሽጡላቸው፣ ‹ነጋቲ ቡላ› በሏቸው” የሚልና ግም ነጭ ጭቃ አናቱ ላይ ተሸክሞ የሚዞር በሰው አምሳል የተፈጠረ የለዬለት ጋኔን ነው፡፡ ለስሙ የቋንቋና ሥነ ጽሑፍ መምህር ነው፡፡ ግን የቋንቋና ማኅበረሰብን ዕድገትና ዘፈቀዳዊ ግንኙነት አያውቅም፡፡ ቋንቋ ባሕርያዊ እንዳልሆነም የማይረዳ ገልቱ ነው፡፡

ጃዋር እንኳን ከሰይጣንም በላይ ነው፤ ሰይጣን ቢሞት የሚተካው አልጋ ወራሹ ጃዋር መሆን አለበት – ሰይጣን የሚሞት ከሆነ፡፡ እንደሚታማውና መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ጋንኤል ኢትዮጵያን ለመበታተን እንደ ግብጽ ባሉ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የተመለመለና በብዙ ሚሊዮን ዶላር ተገዝቶ ሥራውን በስኬት እየተወጣ ያለ ጎልማሣ ነው፡፡ ይህ ሰው እስካለ ድረስ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ገና ብዙ ፍዳ ያገኛቸዋል፡፡ (ይህ አባይ የሚሉት ወንዝ ምነው ጋና ወይ ካሜሩን ውስጥ በሆነ! ጠቅሞ ላይጠቅመን አሣራችንን አበላን አይደል?) የተከፈተለት ሚዲያ ከፌዴራል መንግሥት በግልጽም በድብቅም ድጋፍ እንደሚያገኝ ከመነገሩም በተጨማሪ የላኩት ኃይሎች ስለገንዘብ ምንም እንዳያስብና እንዳይጨነቅ ዋስትና የገቡለት ይመስላል፡፡ ለዚህም ሣይሆን አይቀርም እንደኢሳት ያሉ ጣቢያዎች ነጋ ጠባ የገንዘብ ዕርዳታ በመለመን ሥራ ሲጠመዱ የጃዋር ኦኤምኤን (OMN) ግን እንኳንስ ገንዘብ ሊለምን ለሠራተኞቹ የሚከፍለው ደሞዝ ራሱ ከማንም ጋር የማይወዳደርና ሥራ አስኪያጁ ጃዋርም ጥይት በማይበሳው እጅግ ውድ መኪና የሚንፈላሰስ፣ ወፍ ከሰማይ በሚያወርዱ ሥልጡን ኮማንዶዎች ከሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር በበለጠ የሚጠበቅና ተሰሚነቱና ተፅዕኖውም ከማንም በላይ የሆነው፡፡ ይህን ሁሉም ያውቃል፡፡ ክርስቲያን ታደለ የሚባል የአብን ምክትል ሊ/መንበር(?) ወዶና ፈቅዶ ያልተወለደበት አማራነት ወንጀል ሆኖበት በጎሣዊ ማንነቱ ሰበብ ከበርካታ መሰሎቹ ጋር ተይዞ ሲታሰርና ሲሰቃይ ጃዋር ግን ሲዳማን ከደቡብ ለመገንጠል በግልጽ ዐዋጅ ዐውጆ ለብዙ ሕዝብ ዕልቂትና ለንብረት ውድመት ዋነኛ ተጠያቂ መሆን ሲገባው ማንም ዝምቡን እሽ አላለውም – የሚገርም የነገሮች ሂደት፤ በታሪክ የሚያስጠይቅ ልዩ ኦህዲዳዊ የአስተዳደር ዘይቤ፤ በታሪክ ማኅጸን የተረገዘው ህግ ሲወለድ እስከሞት ሊያስቀጣ ለሚችል ከፍተኛ ወንጀል የሚዳርግ በዘረኝነት ላይ የተመሠረተ ሸውራራ ኦነጋዊ መንግሥት የተተከለበት አስደናቂ ዘመን፡፡ ይህ የሚያሳየው የፌዴራል መንግሥት ተብዬው የኦህዲድ ባለሥልጣናትም  ጃዝ ብሎ ጃዋርን በላከው ኃይል ተፅዕኖ ሥር መውደቃቸውን ነው፡፡ እንጂ በአንድ ሀገር ውስጥ የተለያየ ሕገ መንግሥትና አስተዳደር ያለ በሚያስመስል ሁኔታ አማራውን እያጠቁ ኦሮሞው አገር ምድሩን እንዲቆጣጠርና ጽንፈኞች ያሻቸውን እንዲያደርጉ ፈረሱም ሜዳውም ባልተለቀቀላቸው ነበር፡፡ ይህ አሣፋሪ ዘመን ማለፉ አይቀርም፡፡ ሲያልፍ ግን ብዙ ጠባሳ እንዳይጥል አእምሮን ከአሁኑ በቅጡ መጠቀም ይገባል፡፡ በዱባ ጥጋብ የሚፈነጥዝ ዘረኛና ሤረኛ ሁሉ ቆም ብሎ የማሰቢያ ጊዜው አሁን መሆኑን መረዳት አለበት፡፡ “እዩኝ፣ እዩኝ” “ደብቁኝ፣ ደብቁኝ”ን እንደሚያስከትል ከወዲሁ ካልተረዳን ዛሬ ትናንትን እንዳልሆነ ሁሉ ነገም ዛሬን አይሆንምና ቢያንስ ለመጪው ትውልዳችንና ለልጆቻችን በማሰብ ከፈረሰኛ የስሜት ደንገላሣ ወጥተን በጥሞና እናስብ፡፡ እነደቻሣና ኩምሣ እየሰማችሁኝ ነው? ከነሐጎስና ገረ’ግዚሃር ካልተማራችሁ ከማን ልትማሩ ትፈልጋላችሁ? ዕደጉ እንጂ! እኛም “ወፌ ቆመች” እንበላችሁ፡፡ እንደቀጨጫችሁ አትቅሩብን፡፡ የናንተ ማደግና መለወጥ ለጋራ ቤታችን ወሳኝ መሆኑን ተገንዘቡ፡፡

ስለ አጋንንታዊ ሥላሤዎች ይችን ታህል ካወራን ለዛሬ ይብቃኝ፡፡ እምነታችንን አጥብቀን እንራመድ፡፡ ለአጋንንት መድኃኒቱ የእምነት ጽናት ነውና በፈጣሪ ብቻ እንታመን፤ ለርሱም ችግራችንን እንንገረው፡፡ መሥራት ያለብንንም እንሥራ፡፡ ዝም ብለን ግን አንቀመጥ፡፡

 

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop