ሰውእየው(አንድ ሁለት) (አጭርልብወለድ) – በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
 ( ይህ ልቦለድ ለአሁኑ ለተመሰቃቀለ ፖለቲካ አሥተማሪ ነው።” ጅብ ከሚበለህ በልተኸው ተቀደሥ።” የሚባለውን ብሂል እደግፈዋለሁ። የአባገነንነት ሽታ እየሸተተኝ ነውና! ያውም በሥማርት ፎኔ።እኔ እስማርት ፎን ይዤና ሥማርት ሆኜ መንግሥቴ እሥማርት ካልሆነ ያሥፈራኛል። ክብር ለኢትዮጵያ ህዝብ።)
ሰው እየው 1,2 …
አጭር ልቦለድ
ከመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
1
“ቶክ ግሮሰሪ ነው፣ ዛሬ የምጋብዝህ…” በማለት ለመጀመርያ ጊዜ የሰው ነጭ ወደሚታይበት”ቶክ ግሮሰሪ” የወሰደኝ የቅርብ ዘመዴ የአራዳ “ከንቲባ” ነው። ከንቲባ የቅጽል ስሙ ነው። ይህንን ቅጽል ሥም ያወጡለት አብሮ አደጎቹ የአራዳ ልጆች ናቸው። “ከንቲባ” ዕውቀት የዘለቀው ከመፀሐፍ ቅዱስ ጀምሮ የተለያዩ መፀሐፍትን ያነበበና ዛሬም የሚያነብ እጅግ ሰው አክባሪና ሁሉም ወዳጁ የሆነ ተጫዎች ሰው ነው። ለዘመድህ አደላህ አትበሉኝና።
     በከንቲባ መሪነት ወደ ቶክ ግሮሰሪ ስንቃረብ የጠጪው ጫጫታ ታላቅ አቀባበል እያደረገልን የጠጪዎችን ወንበሮች እየታከክን ባዶ ጠረጴዛና ወንበር ስንቃኝ በጠጪዎች መካከል ሁለት ባዶ ወንበሮች አገኝተን ተቀመጥን።እንደተቀመጥን በፊት ጥርሱ ገጣጣነት የሚስቅ የሚመስል አንድ እረጅምና ጠውላጋ አስተናጋጅ እየተውረገረገ ሊታዘዘን መጣ።
ሳይወድ በተፈጥሮ አስገዳጅነት የሚስቀውንና በጠጪዎች ሙቅትና ትንፋሽ ፊቱ የወረዛውን አስተናጋጅ “ሁለት በደሌ ስፔሻል!” በማለት ሁለታችንም አዘዝነው። ሁለታችንም ከ1984 ጀምሮ የበደሌ ቢራ ቋሚ ተሰላፊዎች ነን።የምወደውን በደሌ ቢራ እየተጎነጨን የቶክ ግሮሰሪን ጣራና ግድግዳ እንዲሁም በዙሪያችን እንደሻው እየጠጣ ያለውን ሰው መቃኘት ጀመርን፡፡
     ቶክ ግሮሰሪ ፣ አራዳ እንዳሉት እንደመሰሎቹ ዓይነት ግሮሰሪ ነው። እንደመሰሎቹ ግሮሰሪዎች ባንኮኒና የመጠጥ መደርደሪያ ያለው ሲሆን ፣ ከሙዚቃ ድምፅ ፈፅሞ የፀዳ ነው። እንደ አንዳንድ ካፌና ቡና ቤቶች ጆሮ ጠላዥ ሙዚቃ እዚህም ግሮሰሪ ባለመኖር ከንቲባን በልቤ አመሰገንኩት። አንዳንዱ ሆቴልና ቡና ቤት ለረጅም ሰዓት ተዝናንተህ ስትገባ፣ በማግስቱ ጉሮሮህን የሚያምህ እኮ የሙዚቃውን ድምፅ ለማሸነፍ ከጣራ በላይ ሥለምትጮህ ነው። እዚህ ግሮሰሪ ፣ ሌለው ጠጪ በራሱ የልብ ሙዚቃ ቅኝት ነፍሱን እያስጨፈረ ጥሙን፣ድካሙን፣ብስጭቱን ወዘተ፡፡ለግዜው አራግፎ ፣ ሞቅ ብሎት ወይም ሰክሮ ወደየ ጎጆው መሄድ የሚችልበት አመቺ ሁኔታ ተፈጥሮለታል።
ምንም ዓይነት የሚረብሽ ከሰው ቋንቋ ውጪ የሆነ ድምፅ ስለማይሰማም፣ ጠጪው፣ በራሱ ሐሳብ ይወዛወዛል። ይናጣል። ይብሰለሰላል።…. እርስ በእርሱ ሃሳብ ይለዋወጣል። ይነታረካል። ይተራረባል። ይስቃል። ያውካካል። ይደሰታል። ያዝናል። በልቡ ያነባል።ይራገማል።ይዶልታል።… ይለፋደዳል። እንዳንዴም ይተክዛል። ከንፈሩን ይነክሳል። በውስጡ ይዝታል። ይፎክራል። ይራገማል። ከመጠጥ በኋላ ስለሚያደርገው ያብሰለስላል።…
     በዚች ጠባብ ግሮሰሪ የሚገኝ ጠጪ ሁሉ በተለያየ ሃሳብ ቢዋጥ እንኳን፣ የግዱን ከአጠገቡ ካለ ጠጪ ጋር ማውራቱ አይቀሬ ነው። ለምን ቢሉ ተናግሮ የሚያናግር ስለማይታጣበት ነው።ለዚህም ነው “ቶክ ግሮሰሪ “የተባለው።
     “ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል። “ነውና ይትባህሉ ፣ሃሳብን ያለገደብ መናገር በአልኮል መሸጫ ሥፍራዎች ለጠጪው ሁሉ ተፈቅዶለታል። እኛም በዚህ የጠጪዎች የመናገር ተፈጥሯዊ መብት በእጅጉ በተከበረበት መድረክ መሐል ሆነን፣የመጣልንን” በደሌ ስፔሻል “እየጠጣን ከያቅጣጫው የሚመጣው ወሬ ጆሮችንን እየጠለዘን ለአፍታ ቁጭ አልን።
       ጉሮሯችንን አርሰን ሌላ ቢራ አዘን ወደ ግል ጫወታችን ልንገባ ሥንል፣ “እባክህ ተወኝ… ኧ! ደግሞ ለአበሻ! ለዚህ ጦጣ ህዝብ ትጨነቃልህ እንዴ?? ይህ ህዝብ እኮ ክብር አይወድለትም። ወርቅ አንጥፈህለትስታበቃ፣ እኔ አላምንም ያነጠፍክልኝ’ ፋንድያ ነው!’ ይልሃል። ‘ፋንድያ!’ ታቃለህ? የፈረስ፣ የበቅሎ፣ የአህያ እዳሪ ነው’ኮ!! ካካካካካካካካካካካ……!!!” በማለት ከጣርያ በላይ ሲስቁ ቀልባችንን ስለሳበው፣ ሁለታችንም በመገረም ፍጥጥ ብለን ስናያቸው፣ እሳቸውም ትክ ብለው አዩንና ምንም ነውር ነገር እንዳልተነፈሱ ሁሉ በተዝናኖት የጀመሩትን ወግ ቀጠሉ።
    ከሳቸው በተቃራኒ ከጎናችን የተቀመጠው ሰው ሥለ እኚህ ሰው በሹክሹክታ መረጃ ሰጠን።
   እኝህ ለከተ ቢስ ፊታቸው በፀጉር የተሸፈነ፣ አብረቅራቂ ቀይ መላጣ ያላቸው ቀጫጫ ሰውዬ፣ “ኦሾ” በሚባል ቅፅል ሥም ነው፤ የሚታወቁት  ።  ሰውየው እንደነገረን እኚህ አዛውንት   አንድ ቀንም ለንግግራቸው  ሉጋም አስገብተውለት የማያውቁ ለከተቢስ መሆናቸውንም ገለፀልን። በጠብ እንዳንተናኳላቸው በማሰብ።
      “እሾ!” አልኩ በመገረም ።መፀሐፍቶቹን አንብቤለሁ ።የግለሰቡን አስተሳሰብና አመለካከት አደንቃለሁ። ሕይወትን እሱ በተመለከተበት እይታ ማየትም በዚህ እንደሸማኔ ድር ቁልፍልፎ በወጣ ዓለም ፈፅሞ የማይቻልነው። ‘ያአንተ እውነት እኮ ለሌላው ሐሰት ሆኖ በድንጋይ ሊያስወግር ይችላል¡¡’ ያም ሆነ ይህ የሰውየው ድፍረትና ጮክ ብሎ በድፍረት መናገር ‘የሰከረ ብቻ ነው እንዴ ሥለመናገርና ሥለ ንግግር ተፈጥሯዊነት ደመነፍሳዊ መረዳት ያለው??’  የሚል ጥያቄ በውስጤ ጭሮብኛል።
   በጥሞና የሚያዳምጣቸው በግምት በ20ዎቹ ዕድሜ ክልል ያለ ከሳቸው በ50 ዓመት የሚያንስ ሆኖም ግን እንደሳቸው ፂሙን ያሳደገ፣ ሆኖም ፀጉሩ ከሳቸው በተቃራኒ ከመጠን በላይ አድጎ የተንጨበረረ ፣ሥለትም አፍንጫና ሾጤ ፌት ያለው… ግራ መዳፉን ጉንጩ ላይ አስደግፎ በተመስጦ ያዳምጣቸዋል።
     እኔና ጎደኛዬ በንግግራቸው ተደናግጠን ብናፈጥባቸውም እሳቸው ከቁብም ሳይቆጥሩን ይህንን ሥድ ንግግራቸውን ጮክ ብለው ማውራታቸውን ቀጠሉ።
ከከንቲባ ይልቅ ይህ ሥድ ንግግራቸው ያበገነኝ እኔን ነው። ‘እንዴ፤እኝህ ኅምቱ ሽማግሌ የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር አይወድለትም ሲሉ ምን ማለታቸውነው? ከቶ ምንስ ቢሆን ይህን ንግግር ከሽማግሌ አፍ መውጣት ነበረበት? ዜግነታቸውን እረስተው ነው እንዴ እንደባዳ” የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር አይወድለትም። “የሚሉት? እሳቸው ክብር ሊጠላባቸው ይችላል። ሌላውን ዜጋ ግን ወክለው እንዲናገሩ  መብት አልተሰጣቸውም። ይገርማል! የኢትዮጵያን ህዝብ እኮ በቅኝ ግዛት የሚያስተዳድሩት ይመስል ፣ ህዘብ በተሰበሰበበት ህዝብን” ክብር አይወድለትም።”  በማለት በድፍረት ይናገራሉ???፡፡’አንዴት የሚየሰጠላያልተገራ  ልቅ አንደበት ነው ፣የያዙት ?…’በማለት በውስጤ ተብሰከስኩ። እናም በተረበሸው ውስጤ ምክንያት ከአእምሮዬ የገነፈለ ጥያቄ ከከፈሮቼ ድንገት አፈትልኮ ወጣ።
      አባቴ፣ አዳም እባላለሁ። አሁን የተናገሩትን ሳልወድ በግድ አዳምጫለሁ። መቸም ጆሮ በመስማት ቢሞላ ኖሮ ቀን የሰማው ስለሚበቃው የእርሶን አቁሳይ ንግግር የሚሰማበት ክፍተት ባላገኘ ነበር።..ለመሆኑ እረሶ ‘የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር አይወድለትም’ በማለት ጮክ ብለው ሲናገሩ ትንሽ እንኳ አይቀፍዎትም?… እርሷን እና እኔን ጨምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር እንደማይወድለት በተጨባጭ የሚያስረዳ፣ ምን አይነት መረጃና ማስረጃ ይዘው ነው፤ እንዲህ በልበ ሙሉነት በዚህ ህዝብ መካከል ያለአንዳች ይሉንታ ከጣሪያ በላይ እያንባረቁ የሚዘባርቁት??…”በማለት በንዴት እየተንተገተግሁ መልስ እንዲሰጡኝ አፋጠጥኳቸሁ። የጓደኛዬንም የይሉንታ ማሥጠንቀቅያ አሽቀንጥሬ፣ ከእኝህ ጎምቱ ሽማግሌ ጋር ሙግት ለመግጠም ወንበሬን ሥቤ ከፊት ለፌታቸው ቁጭ በማለት በንዴት የሚቀለቀለውን አይኔን ከአይናቸው ሳልነቅል፣ “በልዋ፣የንግግርዋን እውነተኛነት በመረጃ ላይ ተንተርሰው ና በማስረጃ አስደግፈው አስረዱኝ።” በማለት ለሙግቱ እራሴን አዘጋጅቼ ወደ ምክንያታዊ ክርክር እንዲገቡ ወጥሬ ያዝኳቸው።…” መፈናፈኛ መንገድ አግኝተው እንደው እንደዋዛ ማምለጥ ባለመቻላቸው በፊታቸው ላይ የመገረም ፈገግታ ይታያል። በመገረም ውስጥ ሆነው በአትኩሮት እዩኝና፤
     “በቂ፣እጅግ የተሞላ ና አመርቂ መልስ እሰጥሃለሁ። ሆኖም ልናገር አፌን ከከፈትኩበት ግዜ አንስቶ ንግግሬን ቋጭቼ አፌን እስከ ምዘጋ ጊዜ ድረስ፣ የንግግሬን ፍሰት ማቆረጥ፣ ስሜትህን መቆጣጠር አቅቶህ፣ ጠረጴዛ መነረት አይፈቀድልህም። “በማለት አስጠነቀቁኝ። እኔም አንገቴን በመነቅነቅ ተስማማሁ።
    “እውነቴን ነው የምልህ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር አይወድለትም። ክብር ስለማይወድለትም፣ ፊት ልታሳየው አይገባም፡፡ ዴሞክራሲ፣ የሌበራልም ሆነ የአብዮታዊያኑ፣ በፍፁም አያስፈልገውም። የሚያስፈልገው ጨቆኝ’ና አምባገነን መንግሥት ብቻ ነው። እደግመዋለሁ፣እምባገነን መንግሥት። በዱላ እየወገረ፣ በካልቾ እየረገጠ፣ በሣንጃ ቂጡን እየወጋ! አፍንጫውን እየጎረደ፣ ምላሱን እየጎመደ፣የቋንጃውን ጅማት መዞ በመቁረጥ ፣እንዳይራመድ እያደረገ፤ እዛው ቁጭ ብሎ በእፉቅቁ እየሄደ እንዲሰራ ካላደረገው፤ ወይም ደግሞ በሰንሰለት አስሮ፣ በጅራፍ እየገረፈ፤ ወይም ደግሞ ከበስተጀርባው አፈሙዝ ደቅኖ ‘ዋ! ትወሰልትና ውርድ ከራስህ?!’ በማለት እያስፈራራ ፣የሚያሾረው ካላገኘ፣ መች በራሱ ተነሳሽነት ሥራ ይሠራና!…
“የኛ ህዝብ ውዴታን የት ያቅልህና  !ክብርስ መች ይወድለታልና?! እንዴ! ትንሽ ፊት ካሳየኸው እኮ ‘ጭንቅላትህ ላይ ካልወጣሁ ሞቼ እገኛለሁ ። ‘ በማለት ቁም ሥቅልህን ነው የሚያሳይህ። ሥለዚህ አንተ ሁሉን ቻዩን የኢትዮጵያዊውን ወፍራም ቆዳ ሰርስሮ የሚገባ ከጉማሬ ቆዳ የተሰራ አለንጋ ሁሌም ጨብጠህ በእሱና በሱ ብቻ ፀጥ ለጥ ብሎ እየሰራ እንዲኖር ነው ማድሩግ ያለብህ፡፡”
ይህንን ወፍራም ቆዳውን ሰርስሮ የሚገባ በፈረስ ጭራ የተገመደ የቆዳ ጅራፍ ካለህ፣ በእርሱ ሾጥ እያደረግህ፣ ወገቡን እየተለተልክ ካላሰራኽው በስተቀር፣ መቼ በራሱ ጊዜ ሥራዬ አለቃዬ ነው በማለት ይሰራልህና!… አልንጋ ካላየ እኮ ቁጭ ብሎ ወሬውን ሲሰልቅ በመዋል አንተንም ሆነ ሀገሪቱን ኪሳራ ላይ ይጥላል፡፡ይህ ህዝብ እኮ፣ ከሥራ ይልቅ ወሬን እንደነፍሱ የሚወድ ህዝብ ነው።….” አሉና ጉሮሮቸውን ለማርጠብ ቀይ ወይናቸውን ብድግ አደረገው ተጎነጩ።
    ያቺ ጠባብ ግሮሰሪ አንድ ሰው እንደሌለባት ፀጥ፣እረጭ ብላለች።ጠጪው ሁሉ አፉን ዘግቶ የ’ኦሾችንን በሥሜት የታጀበ ንግግር እያዳመጠ ነው። ሽማግሌው ወይናቸውን ተጎነጩ ና ያላአንዳች ይሉንታ የሚያምኑበትንሃ ሃሳብ ማዥጎድጎዳቸውን ቀጠሉ።
“እውነቴን ነው ፤የምልህ፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር አይወድለትም።ነፃ ሆኖ እንዲሰራ  ፈለገህ እንዳሻህ ለማዘዝ የሚያሥችልህን  የቁጥጥር ሉጋም ብታወልቅለት፣ የለየለት ዋልጌና ወሬ ወዳድ የሆነ የሥንፍና ፈረስ ሆኖ ነው፤ የምታገኘው።… ነፃ ባወጣኸው በጥቂት ቀናት ውስጥ ሁሉንም ጠቃሚ ነገር አወዳድሞ በድህነት አረንቋ ተዘፍቆ ነው ፤የምታገኘው።አንተም በሁኔታው ተበሳጭተህ ‘የራሱ ጉዳይ።እስከመቼ በዱላ አሰራዋለሁ?’ በማለት ተስፋ ቆርጠህ ችላ ካልከው፣ እስከወድያኛው ከእንቅልፉ ላለመነሳት ለሪሱ ቃል ገብቶ  ይጋደምልሃል።….
“….ምናልባት ከተነሳ፣ እሱን ሊያስነሳው የሚችለው የሆድ ጥያቄ ነው። ሆዱን ሲሞረሙረው ጠኔውን ለማስታገስ መነሳቱ አይቀርም።ተነስቶ በላብ እና ደም፤በጥለቅ ሐሳብና ልፋት የሚሰራ ስራም ለመስራት አይፈልግም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን አድካሚ ሥራ ሠርቼ   እንጀራ ልበላ አይልም፡፡ አጅግ ቀላሉን ሥራ ይመርጣል፡፡  ቀላል ሥራም ልመና ነው።
     አናም በቀላሉ በተለያየ  ሥልት ታግዞ  የተለማኙን ሆድ በሚያቦጨቡጩ ልመናዎቹ በቀላሉ የለት ጉርሱን ያገኛል። አንዳንዱ ለማኝም በልመና ገንዘብ  ከዕለት ጉርስም የላቀ ተግባር ያከናውንበታል። እቁብ፣እድርና ባልትና ወዘተ።ይኖሩታል።እድሜ  ለለጋሱ ህዝብ እያለም  አንድም ቀን ሳያስተጓጉል ዕቁቡን ይጥላል። እድርና ባልትናም ይከፍላል።
    እንዴ!!ወጣ ብለህ አላየህም ማለት ይቻላል። ልመናን እንደ ትልቅ ገቢ ማግኛና እንዳልተባነነበት የሥራ መስክ የሚቆጥረው ጥቂት አይባልም እኮ!!…
“በየቤተክርስትያኑና በየመስጊዱ ፤በየከተሞቻችን የንግድ መናሐርያዎች  ተዞዙረህ ብትመለከት፣ ብር ካልወለድክ ሣንቲም ካልበተንክ እያለ፣ ‘ኡ!ኡ!አገር ይያዝ፡፡‘ የሚል ለማኝ ታይ ነበር።
     በእንባና በኡኡታ በየቀኑ በሚያገኘው ገንዘብ መሰረታዊ ፍላጎቱን ካረካ በኋላ፤ ሥለመፃኢ ህይወቱ የማይጨነቅ………….. ዕቁብና፣ ዕድር፣ የሌለው፤ በየክልሉ ብትሄድ የማታጣው፣ ለነገ የማይጨነቅ በማሥቲሽ የደነበዘ ፣በገራባ ጫት የጀዘበ  ለማኝም በተቃራኒው እንዳለም አትዘንጋ!።
    ለዛሬ እንጂ ለነገ ከቶም የማይጨንቀው ይህ ዜጋ  አንተን ይጭነቅህ እንጂ! እሱ ዛሬ ባገኘው ጥግብ ብሎ፣ ባገኘው ቦታ ያለሥጋት እንቅልፉን እየለጠጠ ያድራል። ለአንተ የዘወትር ምፅዋት ምስጋና ይግባውና የአንተ እጅ እስካላጠር ግዜ ድረስ ምን ያስጨንቀዋል?…. እውነቴን ነው። በየትኛውም የኑሮ ፈርጅ ብትሄድና ይህንን ህዝብ ብታስተውለው፤ ክብር የሚወድለት ህዝብ እንዳይደለ በቀላሉ ታረጋግጣለህ።…
   ቅንነት፣ ሰብዓዊነት፣ በጎነት ፣ቸርነት፣ ልግስና፣ ፍቅር፣ ወዘተ። አይገባውም። የበጎነት ሥንዘር ካሣየኸው፣ ላደረክለት ምሥጋና ሳያቀርብ፣ ‘ለምን ክንድ አታደርገውም በሥነዝር በቻ ከምትሰጠኝ? ቋንቋና!’ ብሎ ይወቅስኸል።የሰድብሀል ፡፡ እና ምን ትላለህ ይህ ህዝብ’ኮ እንደህፃን የራሱ ባልሆነ ገንዘብ የሚያለቅስ ነው።ደሞም በምቀኝነቱ እጅግ የታወቀና የተጨበጨበለት ህዝብነው። ጎረቤትና የቅርብ ጓደኛው ሲያልፍለት ካየ፣ የጎረቤቱን ህይወት ለመንጠቅ ጉድጎድ ሲመስ ታገኘዋለህ።
“መንግሥት ራሱ ለዚህ ክብር ለማይወድለት ህዝብ፤ ዴሞክራሲ፣ፍትህ፣(የህግ የበላይነት) ሰብዓዊ መብት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ፣ ወዘተ። መብት፣ በመስጠት ይህንን ህዝብ ሞልቃቃ አድርጎታል። በማሞላቀቁም የስንፍና እንጂ የሥራ ወዳጅ በብዛት አላፈራም።”
ይህንን ህዝብ ሥራ ወዳድ ለማረግ ከፈለገህ፣ በአርጩሜ እየገረፍክ፣ በእስረኛ መልክ ይዘህ እንደቀድሞው የቅኝ ገዢዎች  ና ፊውዳሎች በበትርህ ና በጅራፍህ እየነረትክ ና እየገረፍክ በአለንጋህ እየሸነቆጥክ፣ ስታሾረው ነው ‘ሺ ዓመት  ንገሥ!’ በማለት የሚመርቅህ። እና አንተም ያለማሰለስ በየቀኑ፣ ሾጥ! ድው! ድው! ድም! ድም!…በማድረግ አገዛዝህን ተፈሪና ዘላለማዊ ማድረግ የምትችለው።
“ታቃለህ!? ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም ሾጥ! ሽንቁጥ! ድም! ድም! ማድረግን ለጥቂት ዓመታት በመተው ነው ፣ለውድቀት የበቃው። ይህንኑ ዝንጋታውን ተገንዝቦም አይደል ‘የኢትዮጵያ ህዝብ ወርቅ ቢያነጥፉለት ፈንድያ ነው ፣ይላል።’ በማለት አንድ ሃሙስ ሲቀረው ፣አፉን ሳያዳልጠው የተናገረው።…
“መንጌ እውነቱን ነበር፡፡ ከቶም አልተሳሳተም። ይህ ክብር የማይወድለት ህዝብ። ቶርቸር ነበር የሚያሾረው። ያውም እንደ ዓፄ ዘራያዕቆብ በደቂቀ እስጢፋኖስ (በአባ እስጢፋኖስ ተከታዮች ላይ) እና በአባ እስጢፋኖስ ላይ እንዳደረሱት አይነት ዘግናኝ ቶርቸር። ሥቃይና ግድያ። እንዲህ ዓይነቱ ቶርቸር ነው፤ ይህንን ህዝብ የሚያሾረውና ለሥራ የሚያተጋው። በጀርባውና በፊቱ የሚያብረቀርቅ ሥለታም ሰይፍ፣ ወልፈት ሲል አንገቱን ለመቅላት ሲጠባበቅ ሲያይ ብቻ ነው፤ሊሾርልህ የሚችለው።
“ለዚህ ክብር ለማይወድለት ህዝብ ዴሞክራሲ ያለገደብ እሰጠዋለሁ። የሚያሾረውን ሰይፍም አሶግድለታለሁ።የእኔ መንግስት የህዝብ አገልጋይ እና ከራሱ ከህዝቡ የወጣ እና የህዝብ አመኔታ ያለው ነው።ወዘተ።የምትል ከሆነ አለቀልህ።….
“ሺ ዓመት ለመንገስ ከፈለግህ በኃይልና በዱላ ነው ፤መንገስ የምትችለው። ጠመንጃህን እያሳየህ። አፈሙዙን እንዲመለከት እና ዘወትር ‘ተበላው ! ‘እያለ በፍርሃት ቆፍን ውስጥ በመሆን ኩርምት ብሎ የህየወት ድንክ ሆኖ እንዲናር በማድረግነው።…. አገዛዝህ መቀጠል የሚችለው።
“አሻፈረኝ በማለት እንቢኝ ብሎ ወደ አመፅ የሚያመራ ከተፈጠረ ደግሞ ‘እንቢ ላለ ሰው፣ ጥይት አጉርሰው!’..ነውና ይትባሃሉ፣ አመፀኛውን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለምትገዛው ህዝብ ኃያልነትህን ተሳያለህ። ህዝቡን ሁሉ የፍርሃት ሳይቤሪያ ውስጥ ትከተዋለህ።…. የፍርሐት ሳይቤሪያ ውስጥ ያለ ህዝብ ደግሞ መስዋትነትን አጥብቆ የሚፈራ ህዝብ እንደሚሆን የታወቀነው። መስዋትነትን ከፈራ ደግሞ በእያንዳንዱ እርምጃው ዳቢሎስ አብሮት መጓዙን ያረጋገጠ ህዝብ ይሆናል። ፍርሃቱ እጅግ የበዛ በመሆኑም እንደጋሪ ፈረስ ግራና ቀኙን ሳያይ ወደ ፈለክበት ትነዳዋለህ።ተሞጋች ወይም ጠያቂ አይሆንም። ግራና ቀኙን እንዳያይ ሁሌም ጎን፣ ጎኑ እየተራመደ ‘ዋ!!…’ እያለ የሚያስፈራራውን ዳብሎስን እና እርምጃውን አጥብቆ ይፈራል።…” የቀኃሥ መንግስት ሳይታሰብ በፈነዳው አብዮት የተንኳታኮተው እኮ፣ ንጉሡ በመለሳለሳቸውና ጂኒአቸውን ወደጠርሙሱ በመክተታቸው ነው። ያ፣የሚፈራው የማይታየው ጅኒአቸው፤ በገዛ እጃቸው ሢታሰር፣ ህዝብ መጠየቅና መሞገትን፣ ከቤት ወደ አደባባይ ይዞት ወጣ።…. ለምን? እንዴት?ማን ?የትና መች? ማለትም ጀመረ፡፡.ከነዚህ ጥያቄዎችም አልፎ ፤አርሶ ማን ስለሆኑ ነው?.ሺ ዓመት የሚገዙን?..በማለትም በድፈረት ጠየቃቸው፡፡… መኳንንቱንም እናንተ ማን ስለሆነችው ነው የሀገሪቱን ሀብት ጠቅልላቸሁ የያዛችሁት?…..ከቶ ማን ነው ይህቺን ሀገር ለእናንተ ብቻ በሰነድ ያስረከባችሁ ?…..እኛስ ዜጋ አይደለንም ወይ? ከእናንተ በምን እናንሳለን?…ወዘተ፡፡በማለት ጮክ ብሎ ተናገረ።ጠየቀ።አመፀ። በእጅጉ ተቆጣ፡፡ቁጣውንም ያ የእንግሊዝ ጋዜጠኛ ዲቢልቢ፤ የወሎን ህዝብ በርሃብ እነደቅጠል መርገፍ፣በካሜራው ቀርፆ፣ በደርግ አማካኝነት በቴሌቪዢን በማሳየት የህዝብን ቁጣ አባባሰው፡፡ከዛስ በማግስቱ ጠዋት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ህዝብ ግለብጥ ብሎ በመውጣት እንዲያ ያለሰገደላቸውን ንጉስ በአፋጠኝ ከዙፋናቸው ይውረዱ፡፡በማለት ለደርግ ድጋፉን ሰጠ፡፡
ከዘህ ድንገተኛ ተቃውሞ በፊት በነበሩት ወራቶች ፤የህዝብ ቁጣ ገንፍሎ  ህዘብ የሃገርን ንብረት ያወድም ነበር፡፡።በቁሶች ለይ አሳት በመልቀቅና በመሰባበር ኃይሉን ያሳይ ነበር፡፡
“፣በጥቅም ጥያቄ የተጀመረው የወታደሩ፣አመፅም የፖለቲካ ይዘት ይዞ ብቅ ብሎ ነበር። የተማሪውን ሞጋች እና ሥር—ነቀል ለውጥ የሚሻ ጥያቄ፣ ለደሞዝና ጥቅማጥቅም ጥየቃ የመጣው ወቶአደር ፤ጥያቄውን ዞር አድርጎ ፣ የራሱ ፖለቲካዊ ጥያቄ አደረገው።ጥቂት ሰፍሳፋና የነማርክስ ደቀመዛሙርት እና ምሁራን በምክር ደርግ የተሰኛውን ወታደረዊ ኮሜቴ በህቡ  መደገፍ ጀመሩ።ወታደሩ በነሱ ምክር ሥልጣንን ከቀኃሥ እጅ በጠመጃው አስገዳጅነት ‘ደርግ ነኝ ‘ብሎ በማወጅ በኃይል ዙፋን ላይ ወጣ። …
አናም አጅሬ ደርግ ዙፋኑ ላይ ፊጥ አለና የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወደውን ያንን ዱላና ቶርቸር ጀመረ። ያለ አንደች ህጋዊ መሰረት በፍፁማዊ አምባገነንነት ፣ፀጉርህ ደብሮኛል በማለት በቂምበቀልና በቁርሾ አብዮቱን ተገን በማደረግ፣ደርግ፣መአኢሶን
ና የአብዮት ጠባቂዎች ወይም በየቀበሌው የተደራጁ የታጠቁ ኃይሎች ፣ወጣቱን ጨፈጨፉት።በአብዮት ስም- ይህ ክብር የማይወድለት ህዝብ እርስ በእርሱ ተባላ። በቂም በቀል፣ በቆየ ቁርሾ – ንፁሐን እንደቅጠል ረገፉ።…
“አላዋቂዎች የመግደል መብት ሥለተሰጣቸውም፣ ከገደሉ በኋላ’ ቁም!!’ በማለትም አሾፉ። ይህ ድርጊትም ህዝቡን የበለጠ የፍርሐት ሳይቤሪያ ውስጥ ከተተው።…ደርግም ለ13 ዓመታት ህዝብ እየፈራው ኖረ።ከ13 ዓመት በኋላ ግን በእጅጉ ተለሳለሰ። ህዝቡን ፀጥ ለጥ አድርጎ ከመግዛት ተዘናጋ። በስኳር ሱስ ተጠመደ፡፡ ስኳር መላስ አበዛ።በ17 ዓመቱም በሆዱ ሰበብ ተንኮታኮተ፡፡የትም አትደረሰም ያለት ወያኔ በተራዋ ከዙፋኑ ላይ አወረደችው።…
“እውነታው ይኸው ነው። ይህ ህዝብ የሚገዛልህ ቆራጥና ጀግና ሥትሆን እንጂ ሥትልፈሰፈስ እና ይህንን ህዝብ መረን ስትለቀው እንዳይመስልህ?.. ወንድሜ ዴሞክራሲ ለፈጠረው ለግሪክ ህዝብም አልሆነለትም። ።ይሄኔ እኮ አንተ ልትሞግተኝ የፈለከው በህገመንግስትና በዴሞክራሲ ዙሪያ ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም ጨርሻለሁ። መድረኩንም ለአንተ አስረክቤያለሁ። ይህ የሁለታችን ወግ ግን የሃሳብ ፍልሜያ መሆኑን ተገንዘብ። “በማለት ሃሳብ ከአእምሯቸው አፍልቀው እንደተናገሩ እንጂ ሌላ ጠመንጃ እንደሌላቸው ለማሳወቅ፣ ሌባ ጣታቸውን ፊቴ ላይ አነጣጥረው “ብም!!”አሉና ንግግራቸውን አሳረጉ።
2
“ይሰሙኛል አባቴ!….” በማለት ጭክ ብዬ በመናገር የቶክ ግሮሰሪ ጠጪ፣ ቀልቡ ወደኔ እንዲመልስ አደረግሁ።ምናልባት ድፍረት የተሞለውን ንግግር ፀጥ ብሎ የሰማቸውን የቶክ ግሮሰሪ ደንበኛ  ቀልቡን ሳይስበው አልቀረምና ንግግሬ ውሃ እንዳይበላው ስለፈራሁ ነው ፤መጮሄ፡፡አናም ጠነከር ባለ ኃይለ ቃል ንግግሬን ብጀምር አድማጭ እነደማገኝ በማሰብ ጉሮሮዬን ጠራርጌ ንግግሬን ጀመርኩ።
“እንዲህ አይነቱን የተሳሳተና ከእውነታ ጋር እየተደበላለቀ እና በየትም ስፍራ እንደ’ርሶ ዓይነቱ ሰው ያለአንዳች ኃፍረት አፉን የሚከፍተበትን፤ ብስሜት ተሞልቶ፣ በግልፅ የሚናገረውን ቁንፅል ሃሳብ፤ ብዙ ግዜ ሰምቼው ንቄው ትቼው ነበር። የዛሬው ግን የማላልፈው ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ምክንያቱም ከንግግርዎ እንደተረዳሁት ሽማግሌና የተማሩ ሆነው ሳለ ይህንን ኩሩ ኢትዮጵያዊ እንደዋዛ ክብሩን ሰያወርዱና አፅኖት ሰተው ጮክ ብለው በማውራት ተራ ነገር እንዳወሩ ሲቆጥሩት በእጅጉ ተናድጄ ነው፤ ማብራርያዎትን አጥብቄ የጠየቅሁት። ሥለ ሰጡኝም ማብራርያ በእጅጉ እያመሰገንኩ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር እንደሚወድለትና ማክበርንም፣ መከበርንም፣ አሳምሮ እንደሚያውቅ በቅጡ እንዲገነዘቡ፤ የኔንም ሃሳብ ሳያቆርጡ በመስማት ሊያረጋግጡ ይችላሉ።” በማለት በአይኔ የግሮሰሪዋን ድባብ ቃኘው።
“ለህዝብ ክብር ያለመስጠት ዋጋ ያስከፍላል። በመንግስትም ሆነ በግል ደረጃ። ያከበራቸውን ዜጋ በመናቅና ከብር ባለመስጠት፣ ባላቸው ሀብትና ባላቸው ምዳራዊ ኃይል፣ በመመካት(ነገ ማንም ያለኝን አያስጥለኝም በማለት በትቢት በመወጠር፤ ህዝብን በማሸበር፣ወይም ቦካሳና ሂትለርን በመሆን)ባለሀገሩን በፍርሃት ቆፈን ውስጥ በመክተትና በማሸበር ዛሬም ‘ከዶሮ ባልተሻለ ህልም’ እየናሩ ሌላውም የነሱን ፈለግ እንዲከተል የሚወተውቱ መፈጠራቸውን እናስተውላለን።እናም የእርሶ የጭንቀት ንግግር ብዙም አያስገርመንም።
“በእኔ እምነት ዜጎችን በእጅጉ የሚያሳስባቸው ፣ለሀገር እድገት፣ሰላምና ዴሞክራሲ የማይጨነቁ፣ ለህዝቡ ከብር ማጣት ሌት ተቀን የሚሰሩ እና የሚያሴሩ። ሰርክ ለእኔ እና ለጥቅም ሸሪኮቼ ብቻና ብቻ በማለት ህዝብ የሰጣቸውን ሥልጣን የሀብት ማግኛ መሳሪያ ያደረጉት ናቸው፡፡
“እነዚህ ሰዎች ከቀኃሥና ከደርግ ውድቀት ለመማር ያልቻሉና ታሪክ እንዲደገምም ሳያውቁት እየጣሩ ያሉ ናቸውና ‘በቃ!!’ ልንላቸው ይገባናል። በነሱ አልጠግብ ባይነት የሚከሰተው ጦስና ጥንቡሳስ ምንም በማያውቁት ዜጎች ላይ እጅግ የከፋ ጠባሳ ትቶ የሚያልፍ መሆኑን ዛሬ ላይ ቆም ብለን ካሰብን ሳይረፍድ ‘በቃ’! ማለት ግዴታችን ይመስለኛል።
“ዛሬ፣ በዘመነ ግሎባላይዜሽን የዘመነ መሳፍንትን እና ዘመነ አምባገነንነትን የሚሰብኩ፣ቋንቋን የመጨቆኛ መሳርያ እንጂ መግባቢያ አይደለም ብለው የሚያምኑ፡፡ እዛና እዚህ አንደአሸን መፍላታቸው እና ከህዝቡ ይልቅ እኛ እናውቃለን። ማለታቸው ለህዝብ ከብር ያለመስጠታቸውን ያመለክታል።
    ‘ሰውን በዘሩ እና በቋንቋው እንጂ፣ በሌላ አላውቀውም።’ በማለት፣ ለእያንዳንዱ ዘር አቃቂርና የማናቆርያ ታርጋ በመለጠፍ፣ ሰው ሰው መሆኑን ዘንግቶ ቆዳውን በማዋደድ እርስ በእርሱ እንዲተራረድ ውስጥ ለውስጥ መሸረብም፣ ሴጣናዊ ተግባር  ነውና ኃይማኖት አለን የምንል ዞር ብለን የምናመልከውን ፈጣሬ እስቲ እናስብ?? …
     ” ዴሞክራሲ፣ለዴሞከራሲያዊ ሀገር ዜጋ የመናገር ነፃነት ቢያጎናፅፈውም በለየለት ቅጥፈት ተጠቅሞ ህዝብና ሀገርን እንዲያተራመስ መብት አይስጠውም። የዴሞክራሲ፣ መብት በህግ ተደግፎ ሲሰጥ ከግዴታ ጋር እንደሆነም ማወቅ አስፈላጊ ነው።
‘ዴሞክራሲያዊ መብቴ ነው ፡፡ ‘ በማለት በየመሸታ ቤቱ ልክ እንደእርሶ የሌላውን መብት የሚጨፈልቁ ይህንን ግዴታ ከቶም አያወቁትም፡፡
       “የኢትዮጵ ያህዝብ ለዴሞክራሲ እንግዳ አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ለክብሩና ለሀገሩ ሟች የሚሆነው፤ በነፃነትና በእኩልነት በቀየው ከጎረቤቱ ጋር በሁሉም ነገር ህብረትና ፍቅር ፈጥሮ በመኖሩ ነው።ይሄ ነው እኮ ፣ዴሞክራሲ ማለት፡፡
      “የኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት አርንቋ ውስጥ ሰለሚኖር ብቻ፣ ድህነቱን መሳለቅያ በማድረግ፤ ለድህነቱ እያንዳንዳችን አስተዎፆ እንዳላደረግን ሁሉ ‘ክብር አይወድለትም።’ እያልን ራሳችንን እንደባእዳን ቆጥረን ልናቆሽሸው አይገባም።
       “የኢትዮጵያ ህዝብ ክብሩን የማያስደፍር ህዝብ ነው። አትንኩኝ ባይ ነው። ሰውንም ያከብራል። እርሱም ክብርን ይፈልጋል። ክብሩን ከደፈሩ ግን አራስ ነብር መሆኑ እርግጥ ነው። የህንን እውነት በዐድዋ ጦርነት ላይ አስመስክሮል። ወራሪውን የፋሺስት ኢጣሊያንን ጦር በተባበረ ክንዱ ድባቅ በመምታት ለአፍሪካውያን  ኩራት መሆኑ ፈፅሞ አይዘነጋም።…
“እረሶም ሆኑ የአርሶን ሃሰብ የሚጋሩ መገንዘብ ያልባቸው አንድ እውነት አለ፡፡ ይህም እውነት ሀገርን ማበልፀግ የሚቻለው በስራ እንጂ በወሬ አለመሆኑን ነው፡፡
“ግለሰቦች ሀብትን የሚያገኙት በተለያየ መንግድ እንደ ሆን ይተወቃል፡፡ ሰርቶ የሚያገኝ አለ፡፡በሰርቆትም ከበሮ ሐበታም ለመባል የበቃም በዘህ ዓለም ለይ በብዛት መታየቱም አያሰገርምም፡፡ በሎቶሪ ሰበብ በአንዲት ጀንበር ሀብታም የሚሰኝም እነዳለ መዘጋት የለብንም፡፡ ደግሞም ሐብትን ያላነዳች ጥረት በውርስ የሚታደልም አለ፡፡ዘሬ፤ዛሬ ደግሞ ያልተገባ ጥቀምን – ሰጥቶ በመቀበል ሐብት ያፈሩ ኪራይ ሰብሰቢ ወይም ሙስኞች የተባሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡…….
“አርሶ ከየትኛው ጎራ እንደሚሰለፉ ባለውቅም፤ የተመቸዎት እነደሆነ ግን መላ ሰውነትዎ እና ሽቅረቅር አለባበስው ያሰበቅብዎታል፡፡’ የተመቸው ሁሉ ለሰው መች ይሳሳል…፡፡ ‘ በሎ የለ ዘፋኙ?አንዳንድ የተመቻቸው ሰዎች ባልተመቻቸው ሰዎች ለይ የሚየዘንቡባቸው አጸያፊ የቃላት ዶፍ አጅግ የሚከብድና ህሊና ላለው ገለልተኛ ሰው አእምሮ ህመም የሚሆን ነው።
      “እርሶ የብጠለጠሉት በልመና የተሰማራ ሀሉ ልመናን ወዶና ፈቅዶ የገባበት አይደለም፡፡ ወይም በዚህ ዓለም ላይ  ‘ ከሆድ ፣ ከመጠለያ ና ከሴት በስተቀር ሌላው ትረፍ ነገር ነው፡፡ ጥዬው ለምሄደው ምን አለፋኝም?! ‘ ብሎም አይደልም፡፡አንደህ ብሎ ቢያሥብማ  ከትልልቅ ፈላሰፎች ተርታ ይሰለፍ ነበር፡፡ ይህ አባባል የትላልቅ ፈላሰፎች ሃሰብ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው የተመቸ ንሮ አይጠለም፡፡ በሃይማኖቱ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር፡፡
“እንደእርሶ ያሉ በማንኛውም አቋራጭ መንገድ ተጉዘው፣ ወይም በጥረት ወይም በአጋጣሚ ባገኙት ስኬት በመመፃደቅ፣ ራሳቸውን የዚህ ህዝብ አካል እንዳልሆኑ በመቁጠር፣ “ህዝብን በጅምላ ክብር አይወድለትም ሲሉ በእጅጉ ይገርማል።ያናድዳልም…
      “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሰብዓዊ ተፈጥሮው እና በዜግነቱ ከሁሉም ዜጋ ጋር እኩል ነው። ሀብታሙ ከየኔ ቢጤው፣ ድሃው ከሚኒስትሩ፣ አይበልጥም። አያንስም።
“የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ትህምክቱና ኩራቱ የዚች ገናና ሀገር፣ ባለቤት መሆኑ ብቻነው። በአኩሪ ታሪኳ የምትከበር ሀገር ዜጋ በመሆኑ ቢንቀባረር፤ ኮራ፣ጅንን ቢል ምንም አያስገርምም፡፡
      “እርሶም ሆኑ የእርሶ ሃሰብ ተጋሪዎች መግንዝብ ያልባችሁ አንድ እውነት አለ፡፡ይህም እውነት ይህቺን  ሀገር ማበልፀግ”የሚቻለው በስራ እንጂ በወሬ አለመሆኑን ነው፡፡ ሰው ሁሉ ማውራት ይችላል፡ ፡የሚያወራ ሁሉ ግን ሰራተኛና ታታሪ ሆኖ ላይገኝ ይችላል፡፡
    “እንደዚህ ዘመን በወሬ የተሞላ እና ፀዳ ያሉ የማይሰሩ ወሬኞች የበዙበት ዘምን ከዚህ ቀደም  አልነበርም፡፡ በዚህ ዘመን ልጆቻችን ሁላ ሳይቀሩ የወሬ አባዜ ተጠናውቷቸዋል፡፡ የዘመኑ ቴክኖሎጂ አበሳውን ጭመር ነው ፣ይዞ የመጣብን፡፡ ምርጥ እና እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ልጆቻችን ይጠቀማሉ፡፡በእሰማረት ሞባይላቸውም አያሌ ቁምነገሮችን የገበያሉ፡፡  እነሱ እስማርት ባለመሆናቸውም  በሥማርት ፎናቸው(በውድ ና ዘመናይ ሥልካቸው) አያሌ አርኩሰቶችን ሊመለከቱና በዳቢሎስም ሊሰረቁ ይችላሉ፡፡በኢነተርኔት መልካም ነገር እነደሚገበይ ሁሉ መጥፎና አውዳሚ ከፈጣሪ ጋር የሚየጣሉ ቆሻሻዎችም ሊገበዩ ይችላሉ፡፡ እርግጥ ነው፣በመድሃኒት ቤቶችም ውሰጥ እኮ በእወቀት ካልተጠቀምንባቸው ሊገድሉን የሚችሉ መድሃኒቶችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እናም በቴሌቪዢንም ሆነ በኢነተርኔት የሚቀርቡልን ዝግጅቶች፣ባህላችንን የሚቃረኑ ከሆኑ ሊያወድሙን ይችላሉ፡፡ ይህንን እውነት ልብ ማለት ተገቢ ነው፡፡ ይህንን እውነት ልብ የሚሉት አመለካከታቸው ያልጠበበና ከራስ በላይ ንፋስ በማለት፣ አጥር ሰርተው የማይኖሩ ናቸው፡፡
      “በአመለካከት ሚዛን እና በአኗኗር ጥግ፣ የት እነዳሉ ከአነጋገሮ በመነሳት መረዳት አያዳግትም፡፡̋ የተመቸው ሰው ሁሉ ባልተመቻቸው ሰዎች ላይ ሁሉ ያልተገባ ወቀሳ ማቀረቡና የሱ ብለጽግና ልፋቱና ድካሙ ብቻ እነደሆነ በመስበክ ያልተመቻቸው ምንዱባኖችን ሁሉ ሰነፎችና ስራ ጠሎች እነደሆኑ አፉን ሞልቶ ይናገራል፡፡
     “ግን፣ ግን፣በአንክሮ መርምረን የእያንዳንዱን ሰው የህይወት ትንሳኤና ወድቆ መቅረት ሰበብ መገንዘብ ለመፍረድ ያመቸናል፡፡ አያንዳንዱ ሰው ዞር ብሎ የህጻንነቱን ዘመን አና ዛሬ የሚገኝበትን ደረጃ ማሰታወስ ይኖርበታል፡፡ የሃብቱም ምንጭ ልፋት፣ አጋጠሚ፣ ውርስ ወዘተ፡፡መሆኑንም መለየት ይገባል፡፡ ለአንድ ሰው ውደቀትም ሆነ ትነሳኤ አሰተዋፆ የሚያደርጉት በቅረብ ያሉ ቤተሰቦቹ፣ በቅረቡ ያሉ የህበረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ናቸው፡፡ተፈጥሮአዊ አደጋዎች አና ጦርነቶችም አስተዎጾቸው ከፍ ያለ ነው፡፡
      “ከላይ በጥቅል ያነሳሁት ሃሰብ ህዘብ ፤የግለሰቦች ሰብሰብ መሆኑን በለመረዳት ፣የኢትዮጵያ ህዘብ ክብር አይወድለትም ሲሉ የእየንዳንዱ ግለሰብ ውድቀትና ትንሳኤ ማህበረሰቡም ጭምር አነደሆነ እንዲገነዘቡ ለማደረግና እንደግለሰብም እርሶ ኩሩውን እና ሰው አክበሪውን ካልነኩት የማይነካውን አስተዋዩንና አርቆ አሰቢውን ህዘብ ያላነዳች ሐፈረተ በአደባባይ አኮስሶ መመልከት በእውንቱ ሁለት ጸጉር ካበቀሉ አዛውንት  የማይጠበቅ አነደነበር ለማሰገነዘብ ፈልጌ ነው፡፡
     ግን ምን ያደርጋል ?በአደባበይ እርሶንም ጨምሮ ሁላችንንም ክበረ ቢሶች አድርገውን አርፉ፡፡ ያሰዝናል፡፡
“የኢትዮጵያ ሕዝብ ክበረ ቢስ ከቶም አይደልም፡፡ አርሶና መሰሎችዎ በአርግጥም ክበረቢሶች ልትሆኑ አና ለሌለው ሰውም ክበር ላትሰጡ ትቸላላችሁ፡፡ ህዝብ ግን እነደህዘብ ከብር ይወዳል፡፡ በሚገባም አርስ በእረሱ ይከባበራል፡፡ ምን ጊዜም ህዘብ በህዘብ ላይ አውነት ባልሆነ ጉዳይ አነዲነታረክ፣ ጦር እነዲማዘዝ፣የሚደርጉት ግለሰቦች ናቸው፡፡“
     “ህዘብ አበሮ መኖርን፣ መፈቃቀርን ይፈልጋል፡፡ በተለይም ሴቶች የአበሮነትና የፍቀር ተምሳሌቶች ናቸው፡፡
አጥረት ሳይኖር በእጥረት የሚቃጠሉ ለሺዓመት የሚበቃ የግል ሃበት አያለቸው የሌላውን ካልቀማን ብለው ጦር የሚመዙ ወንዶች አንደሆኑ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ሁሌም ሌላውን ሰው በመፈረጅ በጅምላ የመኮንን አና የማጥፋት አባዜ የተጠናወታቸው ወንዶች በዚህ ዓለም ይበዛሉ፡፡
“አሰቲ በየሀገሩ ያሉትን የፓርቲ ውድድሮችን አና አሸናፊዎችን ተመልከቱ ወንዶች አይደሉም እንዴ  አብዛኞቹ የሚቆጣጠሯቸው ??? በጣም ተቀራራቢ ዕወቀትና ሐብት በሌለባቸው ሃገራት ሁሉ ድል አደራጊው ወንድ ነው፡፡
     “አርሶም ዛሬ ያንጸባርቁልን የወንድን ትህምከተኛ እና አምባገነናዊ ኩንን አመልካከት ነው፡፡ ይህ ውረስ አመልካከት ደግሞ በተለያየ ቦታ አና ጊዜ በተለያዩ ወንዶች ሲነጸባረቅ ይስተዋላል፡፡ የመለያየት የመጠላላት የመገዳደልና የመዘራረፍ ተልኮንና ምረጫን ተቀዳሚ ሲያደርጉና ለዚህም እኩይ ድረጊት ስኬት የለማሰለስ የለዕርፍትና ያለ እነቅልፍ ሌትና ቀን የሚሰሩ ወንዶች ናቸው፡፡አርሶም ከነዚህኞቹ አንዱ ነዎት፡፡
“የኢትዮጵያ ህዘብ ኩሩና ጨዋ ህዘብ አነደሆነ የልተገነዘቡትም ከነዚህ ግብዝ ወንዶች ተርታ ስለሚመደቡ ነው፡፡ ባይሆኑ ኖሮ የኢትዮጵያ ህዘብ ለዘመናት በድህነት ውሰጥ ሊኖር የቻለው በንቃተ ህሊነው አንድ የለመሆን በህዝቡ መካከል የገመድ ጉተታ የሚጫወቱ አነደ እርሶ አይነት ሰዎች በመብዛተቸው አነደሆነ ይረዱ ነበር፡፡ በእነዘህ ሰዎችና አነዚህን ሰዎች መጠቀሚያ በደረጎቸው በዕዳን ሰበብም ለዘመናት ሀገራችን በጦርነት እሳት ተልበልባለች፡፡ አነ አሜሪካ ሳይተወቁ በስለጣኔ ቀዳሚ የሆነች ሀገር በራስዎ ልጆች የአረስ በእረስ ጦርነት መዘዝ ወደኋላ ቀርታለች፡፡ በቀኃሥ ዘመን መፅዋች የነበረች ከደርግ ዘመን ጀምሮ ተመፅዎች ሆናለች፡፡
     “ዛሬ ላይ ቆመን ለነገው ትውልድ ማሰብ ከቻልን አነደርሶ አይነቱን ጭፍን አመለካከት ፈጥመን በመቅበር ወደፊት ልንራመድ እነችላለን፡፡ ይህን ማደረግ ከቻልን የሰው ቁሰል በሚገባ ስለሚያመን የኢትዮጵያን ህዝብ ችገርም በቅጡ አነገነዘባለን፡፡ በቁስሉ ላይም አንጨት አንሰድም፡፡
“ከዘህ በላይ ያቀረብኩት የእውነት ሃሰብ ለአርሶና ለመሰሎችዎ በቂ ተምህረት አነደሚሰጥ አምናለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ህዘብ አንደማነኛውም ነፃና ሀገር ወዳድ ህዘብ ሁሉ ሰው አክበሪና በዘው ልክም አነዲከበር የሚፈልግ ህዘብ ነው፡፡አንግደህ ይህንን እውነት ጆሮ ያለው ይሰማ የማይሰማም  አይሰማ !! ” በማለት ንግገሬን ሳበቃ ቤቱ በድጋፍ ሁካታ ተሞላ፡፡ ለካስ ያቺ ግሮሰሪ ጆሮ ሆና ቆይታ ነበር፡፡
የግሮሰሪውን ተስተናጋጅ የአድናቆት ጉርምርምታ ተከትሎ በፅሞና ሲያዳምጡኝ የነበሩት ሸማግሌ “ኦሾ ” ከመቀመጫቸው ብድግ በለው አንገታቸውን አቀርቅረው አንዳች ነገር እየልጎመጎሙ ከግሮሰሪዋ ሲወጡ ሰው ሁሉ ዐይኑን እሳቸው ላይ አፍጥጦ ነበር፡፡ለካስ ህዝቡ አነጣጥሮ የሚተኩስ፤ ኢላመውንም የማይሰት፤ጀግና ይፈል ግነበር???
2007 ዓ/ም
 ለአዘጋጁ
ይህንን አጭር ልቦለድ እንደገና  አሥተካክዬ ልኬዋለሁ። ይቅርታ።
 መሻወጊ
ተጨማሪ ያንብቡ:  መንግሥትም ሆነ እኛ ከልብ ልንጸጸትበት እና ይቅርታ ልንጠይቅበት የሚገባን የ2ቱ ዓመት የእርስ በርስ ጦርነት!! - በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)
Share