ለመሆኑ የህዝባችንን መብት ያፈነውን ወያኔን በምርጫ የረታው የግንቦቱ 1997 የህዝባዊ ትግል ዋና መሪ ቅንጅትን በእኔነት ሽኩቻ ካፈረሱት በላይ የጎዳ በወያኔ ከኬንያ ተመልምሎ የተላከው ህዝቡ ክህደቱ ወይም ተንሸራታች ያለው ልደቱ አያሌው መሆኑን የ CRDA ምርጫ ታዛቢ ፓስተር ከበደ ደጉ የሰጠውን ተአማኒ ምስክርነት ያልሰማ ከዩቱብ ላይ ፈግሎ ይስማው:: ልደቱ በዚያ የጎደፈ ታሪኩ ሳይወሰን የመለመላቸው ተከታዮች ሃገር ቤት ሳለ ጸሃፊው ያገኛቸው የኮሌጅ ባልደረቦቹ የሚገኙበት በዚያ የትግል ዘመን የወጣቱን ትግል የወያኔ ፓርላማ ሲያጣጣል ታጥቂው ሲያስር በዘግናኝ ሁኔታ ሲገርፍ ሲገድል ከድሃ ህዝብ የተሰበሰበውን ደሞዝ ከመቀበል ውጭ ምን ያህል የህዝቡን ትግል ደግፈው ነበር? ይልቁንስ ከፋፋይ የትግሉ ተሳታፊዎችን በልዩ ልዩ መለያያይ ወያኔ ከከፋፈለበት በተጨማሪ በእድሜ ከ50 በላይና በታች ብለው የአዛውንቶቹን የዳበረ ልምድ ያጣጣሉ ነበሩ:: በመጨረሻም ጡረታ ሲወጡ ስንት የህዝብ ብሶት ማቅረብ የሚገባቸው አንዱ በሚኖርበት በለገጣፎ አካባቢ የጅብ ጩሀት ረበሸን ብሎ በሚዲያ የተናገር ሲሆን የሚረብሸው የሚዘገንነው የእናት በወያኔ ታጣቂ የተገደለ ልጇ አስክሬን ላይ ስታለቅስ በወያኔ ኢሰባአዊ ታጣቂ ስትገፈተር ያሰማቸውን የሰቆቅቃ ጩህት እንዳሰሙ ግን የወያኔ አበልና የውጭ ሃገር ጉብኝት ክባካቤ አደንቁሯቸው ነበር:: በዚህ ሁኔታ የከረሙት ጉዶች ጭራሽ ህወአት ብሎ ራሱ ወያኔ በፈጠረው ስም አልጠራውም ብሎ መቀሌ በመሸጉት የወያኔ ግፈኛ ባለስልጣኖች ፊት ተደፍቶ ሲሞግትላቸው የቆየ ሰው ስለኢትዮጲያ ወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ትንታኔ ያቅርብ የሚል ሚዲያ በጣም የወረደ ሆኖብኛል::
በተመሳሳይ መልኩ የድሮ የወጣቱን ትግል በጀብደኝነት በከተማ የትጥቅ ትግል ብዙዎችን ያስጨርሰው ኢህ አፓ ኣመራሮች የራሳቸውን ትግል ኣጋር መምህር ጌታቸው ማሩን ለስብሰባ ጠርተው ገድለው ክቡር ኣስከሬኑን በአሲድ ያቃጠሉት ኣመራሮች ክፍሉ ታደሰ ድምጹን ሲያጠፋ ያሬድ ጥበቡ ደመቀ መኮንን ላይ የሰጠው ትንታኔ ስ ህተት መሆኑን ሲያስተባብል ዛሬም ሌላ የግዝት መግለጫ ውን የሚያስተናግዱ ጉዶችን ሚዲያ ማለት ይከብደኛል :: የወያኔ የዘር ጥላቻ ዋና አራማጅ ሆኖ በሃረር በአርሲ አማሮች ከገደል ይጣሉ ዘንድ ቀስቃሽ የነበረ ታምራት ላይኔ” የእምነት ሰው” መሆኑ በጎ ሲሆን ዛሬም በእውነተኛ ልብ ያኔ የፈጸመውን ሳይናዘዝ የትግል አጋሩ ቆራጡ አንዳርጋቸው እንደታምራት መስረቅ እችል ነበር ያለውን ለመለስ ዜናዊ ፓርላማ ስኳር በላሁ ያለው ሰውና መሰሎቹ በመደመሩ መቀላቀል በነፍስም በስጋም መብታቸው ሲሆን ዛሬም ፖለቲካውን ሊዘውሩ መድረክ ሊሰጣቸው አይገባም::
የኦሮሞ ወገናችን በክፉ ቃል እየተጠራ ለም መሬቱ በባላባቶች መያዙን የሁሉም ብሄር ዘር በተለይ የአማራ ልጆች የተዋደቁለትን ትግል በመካድ አማራን ጠላት በማደረግ ኢትዮጲያዊነትን የካደው የኦነግ መስራች ሌንጮ ለታ በትግሉ መጀምሪያ ወቅት ከወያኔ ጋር የቀመሩት ህገመንግስት ተብዬ ሃገር አጥፊ መሆኑን ባልደረባው ነጋሲ ጊዳዳ ከማለፋቸው በፊት ሲናዘዙበት ዛሬም ድረስ የሚሟገትለተ ሰው ከትንሿ ኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነት የትልቋ ኢትዮጲያ ሚንስትርነት ይሻለኛል የአሮፓ ብርድ ከሚጠብሰኝ ወደሞቃቷ ኢትዮጲያ መመለስ ይበጀኛል በሚል የህዝቡን ትግል ከግል ጥቅሙ ጋር የሚያነጻጽር ማፈሪያ ሰው እንዴት በዋቢነት በኢትዮጲያን ጉዳይ በበጎ ሊመክር ይጠበቃል?
በሃገራችን በወጣቶቹና በተቀረው ማህበረሰባችን ብርቱ ትግል በፈጣሪ የተገኘውን በጎ ለውጥ የሚመሩት ዶ/ር አብይና ባልደረቦቻቻቸው ከሰሞኑ በጽንፈኞች ጫና ወደእልክ ከገቡበት ይመለሱ ዘንድ በጸሎትም በምክርም መታገል ሲገባ ያኔ የወያኔ የማደንዘኛ ፕሮግራሞችን ማስታወቂያዎችን ይሰሩ የነበሩ ልማታዊ አርቲስት ተብዬዎች ጋዜጠኛ ተብዬዎች እነቴዎድሮስ ጸጋዬ የርእዮቱና መሰሎቹ ዛሬ የለውጡን መሪዎች በተገኘው ቀዳዳ ሲወርፉ ዝም ልበልን?
የራሱን ትዳር ሁለቴ ያፈረሰው የስነመለከት አስተማሪዎቹን ባላ አሻሮ ያለና የወያኔን ህጐወጥ የአስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ በይፋ ይቀጥል ያለ ዶክተር ተብዬው ወዳጄነህ የሃገርና የፖለቲካ ተንታኝ በሆነበት ሃገር እንደ ኣቤ ጉበኛ ኣልወለድም ያሰኛል::
ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ ሆይ ሚዛናዊ እንሁን ሰከን እንበል:: ወዳጄነህ ያለው በአሮጌው የጎሰኝነት አቁማዳ የኢትዮጲያ በጎ አንደነት ወይን ጠጅ አይቀመጥም:: በዚሁም መልክ አሮጌና የተበላሸ ወይን ጠጅ ያላቸው ክፉ ሰዎች በሙሉ ይቅርታ ንስሃ ሳይስተካክለሉ መድረክ ላይ ሊሰብኩን አይገባም:: ቢያንስ አሳዳጅ የነበረው የመጽሃፍ ቅዱሱ ሳውል ጳውሎስ የወሰደውን ያህል ወይም የበለጠ የፖለቲክና የመድረክ እረፍት VACATION ይውሰዱልን በቁስላችን ላይ እንጨት ኣይስደዱብን::