June 29, 2019
14 mins read

የህልውና ዋሥትናችን የአማራ አንድነታችን!  ወደቀ ሲሉት የሚነሳው፣ደከመ ሲሉት የሚበረታው፣ሞተ ሲሉት ህይወት የሚዘራው ጀግናው አማራ አንድ ሁነህ ተነሥ!

ሰኔ 20ቀን 2011ዓም /  አያሌው ፈንቴ    

እሥከዛሬ  ድረስ ትግሬም ሆነ ኦሮሞ የሠሩትና በቀጣይነትም እየሠሩት ያለው ተንኮል መሠረት የጣለው፣ በእነ መለስ ትነግና በእነሌንጮ ኦነግ በ1983ዓም ግንቦት ወር የአማራን ዘር  ለማጥፋትና ርሥቱን ለመቀራመት ቀድመው በተሥማሙት መሠረት፣ በቅድሚያ የኢትዮጵያን አንድነት በማጥፋት፣በዘር በተከፋፈሉ በዘጠኝ(9)መንግሥታትና ባንዲራዎች በመተካት፣አማራው የተገለለበትን የሽግግር መንግሥት አቋቁመው፣ዘርና ቋንቋን መሠረት ያደረገ ህገ መንግሥት ሲፅፉ ነው ።

የተለያዩትንም ነገዶች በክልል የሸነሸኗቸው ለነገዶቹ ጥቅም አስበው ሳይሆን፣

(1) በመንገዳችው ላይ በመቆም እንቅፋት ይሆናል ብለው፣በጠላትነት የፈረጁትን አማራ ኅልውናውንና ቋንቋውን ከጊዜ ጋር አዳክሞ ለማጥፋት ፣

(2) የሚቀራመቱትን መሬት ቋሚና የተረጋገጠ ዋስትና እንዲኖረው ለማድረግ  “ በአገሪቱ ውስጥ ለደረሱት ሁሉ ችግሮች በዳይና ጨቋኝ፣የኢትዮጵያ ሀገራዊና ህዝባዊ አንድነት በሚል የቆሙትና የብሔሮችን እኩልነት የማይቀበሉት ትምክህተኛ አማሮች ናቸው” ብሎ ውሸት በመስበክ፣ ነገዶቹ  ከጎናቸው  እንዲቆሙና በአማራው ላይ  እንዲዘምቱበት ለማሥቻል ከተጠናወታቸው እኩይ ተግባራቸው ተነሥተው ነበር።

ይህም እሥካሁን ከሞላ ጎደል ተሳክቶላቸዋል።ፍፃሜው ግን አይደለም።

ይህ ከዚያን ጊዜ  ጀምሮ የተተከለው መርዝ፣  ከግድያ አንሥቶ፣ቤት ንብረትን አሥነጥቆ እሥከ ማፈናቀል ከማድረስም አልፎ፣መላ አገሪቱን ውሥጡን ውሥጡን እንደምሥጥ  በመብላት   በሚሊዮኖች  የሚቆጠር የአማራ ህይወት ሲቀጥፍ ኖሮ ከትናንትና ወዲያ አምሥት የኦሮሞ የዘር ድርጅቶች  “አዲስ አበባ የኦሮሞ ነው” ብለው ዘረኝነቱን  በገሀድ ነገሩን።ትናንትናም በአጣዬ፣በምድረገኝ(ከሚሴ)፣በመተከል ወዘተ፣ዛሬ ደግሞ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ኦሮሞ በአማራው ላይ ያደረገው  ወረራ ተደግሞ ባህር ዳር ላይ እያየነው ነው።

ትግሬም ሆነ ኦሮሞ ከ28ዓመት በፊት ጀምሮ የተሥማሙበትን  ዛሬም ቀጥለውበታል።አቢይም አሁን በቅርቡ አክሱም ሄዶ ለደብረፅዮን ትልቅ እጅ መንሻ ይዞ ቀርቦ የተነጋገረው “አብንንና የአማራን አክቲቪስቶች፣ፋኖዎችንና እነጄኔራል አሳምነውን ካሠለጠናቸው አዲስ ሚሊሻዎች ጭምር  እንዴት አሥወግደን አማራውን እንደቀደምቱ ልናበረክከው እንችላለን”የሚል ሴራ ለመጠንሰስ እንደነበር ገሀድ ሆኗል።

መልዕክት ለአማራ  ሕዝብ!  አህመድ ኢብራሂም ኤል ቃዚ(ግራኝ አህመድ) ከ1517-1535ሀ) በኦቶማን ቱርክ ተሥፋፊ የውጭ ኃይል መሣሪያና ወታደር እየተረዳ ያካሄደው ወረራ፣ ምንም እንኳን የሌሎች ነገዶች  መስዋዕትነት ባይናቅም በባሊ፣በፈጠጋር(ሐረር)፣በቤተ አማራ(በወሎ)፣በቤጌምድርና በዳሞት በብዛት የረገፈው የአማራ ሕዝብ ነው።የኢትዮጵያ  ሀብትና ንብረት የቱርክንና የየመንን ባለሥልጣናት ከማክበርም አልፎ፣የኮንስታንቲኖፕል ቤተ መንግሥት ዕቃዎች በወርቅ የተሠሩ እሥከመሆን አድረሷቸዋል።

አጼ ገላውዲዎስ በግራኝ ላይ ድል ቢቀናጅም በአካባቢው ግራኝ የሾማቸውን መሪዎች በቁጥጥሩ ማድረግ ተሥኖት፣ ከግራኝ የእህት ልጅ ከኑር ዓሊ ጋር ሲዋጋ ሞተ።በዚህ ወቅት አገሪቱ በጦርነት የደቀቀች በመሆኗና አማራውም ተዳክሞ ሥለነበር “ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል” ሆነና ለጋሎች(ኦሮሞዎች) ወረራ የተጋለጠች ሆነች።

ልክ በግራኝ እንደተደረገው በተመሳሳይ ሁኔታ ወልቃይት ከተወረረበት ከ1972ዓም ጀምሮ የትግሬ ወረራ ከግራኝ ወረራ በባሰ መልኩ እሥከቅርብ ጊዜ አማራውን አዳክሞት ለማገገም በሚጣጣርበት ወቅት ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ባልተናነሰ መልኩ የኦሮሞ ወረራ በአጠቃላይ በአገሪቱ፣በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ አማራውን በማፈናቀል 500ሽህ ኦሮሞ አምጥቶ ማሥፈር ፣በአጣዬ በምድረገኝ በመተከል ወዘተ፣ዛሬ ደግሞ በኦሮሞዎቹ በአቢይና  በብርሀኑ ጁላ የሚመራ “የሁሉም ወታደር ነው” ለማሠኘትና የሚሠሩትን ደባ ተራው ሠው እንዳያውቅ “በመከላከያ እና በፌዴራል ሥም”  የሚጠራ የኦሮሞን ዘረኛና ፀረአማራ ወራሪ ወታደር ባህር ዳር ላይ አስፍሮ መሪዎችን በመግደል ሳይበቃው  ሕዝቡን እያሰቃዬ እየደበደበና እያሠረ   ይገኛል።

ጄኔራል አሣምነው “ከ500ዓመት በፊት ከነበረው የባሰ” ብሎ የጠቀሰው የ16ኛው ክፍለ ዘመንን የኦሮሞ ወረራን ነው።ያንን  የ16ኛው ክፍለ ዘመን ወረራ  በተወሰኑ ዓረፍተ ነገሮች እንቋጨው፣

“በአጠቃላይ ጋሎች(ኦሮሞዎች) ይህንን መጠነ ሠፊ ወረራ ባካሄዱባቸው አካባቢዎች ውስጥ የነበሩትን ነገዶች፣ለጀግንነታቸው መለኪያ  ይሆን ዘንድ የወንዶችን ብልት በመሥለብ  ሳይገቱ ነገዱንም የራሳቸው ለማድረግ “የሞጋሳና የጉዲፍቻ”ሥልቶችን ተጠቅመዋል።ይህ ብቻ አይደለም።

ጋሎች(ኦሮሞዎች)!በግራኝ ወረራ ክፉኛ የተጎዳው የአማራና የክርስቲያን ዕምነት ተከታይ ሕዝብ  ጥንት ይኖርባቸው የነበሩትን ባሊን(ባሌን)፣ፈጠጋርን(አርሲን፣ሲዳሞንና ጎምጎፋን)፣ደዋሮን(ሐረርን)፣ቢዛምን(ቄለም ምዕራብ ወለጋን)፣ዳሞትን(ሌቃ ምሥራቅ ወለጋን)፣እናርያን፣ወዘተ፣በአጠቃላይ ድንግልና ለም መሬቶች  በቀላሉ እንዲለቅ አሥገደዱት።የነባሩን ሕዝብ ሀይማኖት፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነትን አሥለወጡ።”

ሥለዚህ አማራ የሆንክ ሁሉ ወሎ፣ጎጃም፣ጎንደር፣ሸዋ፣ሀረር፣ጂማ ወዘተ ሳትል ከ500ዓመት በፊት አያቶቻችንና አባቶቻችን በአንድነት ተነሥተው የጋላን(የኦሮሞን) ወረራ እንደመከቱት ሁሉ፣ዛሬም አንድነትህን አጠናክረህ ከኦሮሞ ወረራ ራሥህን ነፃ አውጣ። ይህን ማድረግ ከተሳነህ የጋላ(የኦሮሞ) ባሪያ ሆነህ እንደለመዱት በግዴታ በሞጋሳ ባህላቸው የአማራ ማንነትህን አጥፍተው ኦሮሞ ያደርጉሀል።

“አፉ ቅቤ፣ሆዱ ጩቤው”ዶክተር አቢይ አህመድ ደሴ ሄዶ “ደቦራ የምትባል ልጅ አለችኝ።እሷን ለሁለት ከፍዬ ግማሿን ጎንደር ግማሿን ጂማ ላደርጋት ነው ወይ?”በማለት የተናገረው ሥለገረመኝ የኦሮሞዎችን (ኦነጎችን) አንድ ሁለት ነገሮች ልበል፣

-ኦነግ የአማራ ጠላት እንደሆነ ይታወቃል፣ነገር ግን ከኦነግ አመራር ውስጥ የአማራ ሴቶች አግብተው ልጆች ወልደው ሌላውን አማራ ሲጨርሱ የኖሩ እንዳሉ  እናውቃለን።ይህ ገራሚ ነገር ቢሆንም፣

– ከዚህም የባሰ  እንዳለ ልጥቀስ፣ አንድ በስዊድን አገር የሚኖር  አባቱ የጎጃም አማራ፣እናቱ የወለጋ ኦሮሞ የሆነ በአማራ ላይ ጥላቻው ሠማይ የነካ  “አክራሪ ኦነግ”  አለ።ይህ እጅግ በታም ገራሚ ነው።

ሥለዚህ የአቢይ ደቦራ ከጎንደር ሴት ሥለተወለደች “አንድነት “እያለ ለሚያታልልበት መንገድ ምንም ርባና የለውም፣ተሥፋ ይቁረጥ። እርሱ በተግባር ኦሮሞነቱን ብቻ እያጠናከረ፣ብሎም በኦሮሞ እያሥወጋንና በአገሪቱ ላይ እያሥጨፈረብን፣ በአፉ ግን ከልቡ የማያምንበትን አንድነት እየሰበከ፣ለደሴ ሕዝብ ያለውን ንቀት አሳይቷል።ይህም ብቻ አይደለም የደሴን ሕዝብ ልብ የበላ መሥሎት “ ለመጀመሪያ ጊዜ የልጅ እያሱን ፎቷቸውን አሠርተን ቤተ መንግሥት አሥቀምጠናል” ሲል የተወሰኑ አድርባዮች እንዳጨበጨቡለት ታዝበናል።የደቦራንም ሆነ የእያሱን የተናገረው ፣ለርካሽ ፖለቲካው የደሴን ሕዝብ  ያማለለ መሥሎት ነው።እያሱን ደሴ አካባቢ ብቻ ያደረገውስ ማነው? ልጅ እያሱ በአባታቸው ከንጉሥ ሚካኤል ቢወለዱም፣የእናታቸው  አባት እኮ አፄ ምኒልክ  ናቸው። አቢይ!በደሴ ሕዝብ ላይ ያደረገው ርካሽና የወረደ የማታለያ ንግግር ፣ህፃንን ልጅ በከረሜላ ለማታለል እንደመሞከር ነው።የደሴ ህዝብ ግን የአቢይን  ቀላልነትና ዋሾነት ጠንቅቆ ሥለሚያውቅ ታዝቦ ትቶታል።

ቀኝም ነፈሰ ግራ ከእንግዲህ ምርጫችን በቀላል አሉባልታና በጥቃቅን ነገሮች ሳንጠመድ “ለማሸነፍ ጠላትህን አጥብቀህ ጥላ”የሚለውን መፈክር በማንገብ ተደራጅቶ መመከት ብቻ ነው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ የአቢይንም ሆነ የሌላ ሰው ፈቃድ አይጠይቅም።በተግባር ሲታይ ዶክተር አቢይ መንታ ምላስ ይዞ፣አማራውም ሆነ የአንድነት ኃይል ነኝ ባዮቹ፣መንታ መንገድ ላይ ቆመው የየራሳቸውን ትግል አቀዝቅዘው፣የአቢይን የኦሮሞ መንግሥትና የኦሮሞን የዘረኝነት ትግል አጅበው ሥልጣኑን እንዲያጠናክሩለት ሌት ተቀን እየሠራ ያለ አደገኛ ዘረኛ እንደሆነ ነው።

አማራ ሆይ! “ይህች ዓለም የምታጅበው ጉልበት ያለውን “ሥለሆነ አንድነትህን ጠብቀህ አቅም ፍጠር!

ማሳሰቢያ! በአንድ ልብ ቆርጠን ከታገልን፣ከምንፈልገው ግብ ለመድረስ የሚያቆመን ሃይል የለም።  

                                       አማራው አንድ ሁን፣አንድነት ኃይል ነውና!

       አማራ ህልውናውን በትግሉ ያበሥራል!!!!

      አያሌው ፈንቴ        

 

                   

 

 

 

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop