June 10, 2019
11 mins read

የሁለቱ ቅንብር የትግል ጉዞአቸዉ – ሙላት በላይ

የዉጭ ወራሪዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ከአሉት የኢትዮጵያ አጥፊዎች ጋር ለመስራት የሚየቆራኛቸዉ በትምህርት፣ በሀይማኖት በእርዳታ፣ በአምባሳደርነት አሳቦ አገር ዉስጥ ገብቶ በመሰለል የኢትዮጵያን ብሎም የአማራዉን የዉጭና የዉስጥ ጠላቶች በህቡ እየተገናኙ ኢትዮጵያ የምትጠፋበትን መንገድ መቀየስ ፤ለዚህ የጥፋት ሥራ የሚሰማሩ ቡድኖች ማደራጀት፤ ማስታጠቅ ብሎም የጦር መሳሪያ የስንቅና ትጥቅ እርዳታ በገፍ በማቅረብ አገርን የመበታተን የመቆራረጥ ሥራ  በጣምራ መስራት ነዉ፡፡ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ተነስተዉ ሳይሳካላቸዉ የተጨናገፉትና ተወልደዉ አሁን ከአለንበት የማጥፋት ደረጃ የደረሱት ሻቢያና ወያኔ የዚህ ዓይነቱ መስሪ ሥራ ዉጤት ናቸዉ፡፡

በኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ለማስፈን፤የተረገጠን ሰባዊ መብት ነጻ ለማዉጣት በሚል ስበብ ገብቶ የሚፈጽመዉ ዓላማዉ የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ነዉ፡፡አንድወቅት አሜሪካ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በሚል ሚስጢራዊ መረቧን ዘርግታ ኢትዮጵያን ለማጥፋት በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማሴር ሥራዋን ሰራች፡፡ምሰጢሩን ያወጣዉም ከኢሳይያስ አፈወርቄ ጋር ያሴር የነበረዉ የአንድ ወረዳ ገዥ የነበረዉ ተስፋሚካኤል ጆርጅ ነበር፡፡ ይህም ሻቢያና ሲአይኤ በቃኘዉ ጦር ሰፈር በሚል እርስ ቅጽ1 ቁጥር 3 ከገጽ 30 አስከ 33 ተብሎ በሚታወቀዉ የአማርኛ መጽሄት ነዉ፡፡

በአሜሪካ እየተረዳ ኢሳይያስ የሚመራዉ ሰልፍ ነጻነት የሚበል  ቡድን የአስመራ ባለስልጣናትን መሪዎችን እያሳደደ ገደለ የሚቃወሙትንም ጭምሮ፡፡ ይህም የሆነዉ ኢ ኤል ኤፍ በኤርትራ በረሀ መመስረቱና ከአረብ አገሮች ጋር በብረቱ የተወዳጀ መሆኑን በመረዳት አክራሪ አረቦች ቀይ ባህርን ለቆጣጠር ነዉ በሚል ስጋት ነበር፡፡ ሪቻርድ ኮፕላንድ የተባለ ተማሪ አገር ይገንጠልም አይገንጠልም የሸንሸንም አይሸንሸንም ብሄራዊ ጥቅማችን እስከ ተጠበቀ ድረስ ከማንም ጋር ቢሆን ማበር አለብን በሚል ከኤርትራ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር የሰላም ጉባኤ በሚል በመንግስት በሰልፍ ነጻነት እና በጀበሀ መካከል ድርድር አካሄደ፡፡ እኢአ ጥቅምት 7 ቀን 1962 ዓ.ም የሰላም ጉባኤ ጥሪ በደጃማች ገብረ ዮሀንስ ተስፋ ማሪያም ፊርማ ጥሪዉ  ለሰልፍ ነጻነት ቡድን ለኢሳይያስ አፈወረቄ ተላከ፡፡ አብርሀም ተወልደና ሰለሞን ወልደ ማሪያም የፈረሙበት የመለስ ደብዳቤ ለመንግስት  ተለእኮ ደጃዝማች ገብረኪዳን ተሰማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ ሌት/ኮነሬል ገብረእግዚአብሄር መሀሪ የኤርትራ ፖሊስ ኮሚሽነር ተስፋሚካኤል ጆርጅ አባል በመሆን የመንግስት ቡድን ከሚቴ ተቋቋመ፡፡ ሂዳር 28 እና ታህሳስ 5 ቀን አንጃ የሆነዉ ሰልፍ ነጻንት የሲአይኤ አባል ሪቻርድ ኮፕላንድየ ማጥመጃ ቡድን አድርጎ ተደራደረበት፡፡ በደቀመሀሪዉ ድርድር ከፕላንድ ለሀብተስላሴ ቡድን በግልጥ ከአሜሪካ እርዳታ እንዲጠይቅ አስገነዘበዉ በኢሳይያስ ተጽፎ ለቃኘዉ እስቴሽን አዛዥ ለኮሌ/ነር ማሙዙር ተላከ ፡፡ የደብደቤዉ ሀሳብ እንደሚከተለዉ ይነበባል

1  በሳላ በርሀ የሚገኘዉ  ታጋይ ክርስቲያን በመሆናቸዉ ከአረብ መንግስታትና ከሶሻሊስት አገሮች በእጅ አዙር በሚገኘዉ መሳሪያ በጀበሀ ቡድን በእየቀኑ የሚታረዱ የሚገደሉ በብዛት መሆናቸዉ፤

2 የጀበሀ ፖሊሲ የአረብ አገሮችን ፖሊሲ የሚያንጸባርቅ በቀዳሚነት የእስራኤልንና የአሜሪካን ጥቅም የሚነካ መሆኑን የሰልፍ ነጻነት ቡድን ዓላማ ከዚህ የተለየ ተራማጅና ዲሞክራቲክ እንቅስቃሴ እንደሆነና አሜሪካ መሳሪያ እንድትሰጠዉ የሚማጸን ደብዳቤ ነበር፡፡የአሜሪካ መንግስት የኢሳይያስን ደብዳቤ በደስታ ተቀብሎ ለችግኝ ፕሮጀክት የተከፈተዉን ቀና መንገድ ይዘዉ ተጓዙ፡፡ለሴራዉ የሚበጅ ስልት ቀየሱ በጀትም መፍሰስ ጀመረ፡፡ኢሳይያስ ከአሜሪካ መንግስት ጥቅም ጋር እንደሚሰራ ቃል ገባ፡፡ የኃይለስላሴ መንግስት ወድቆ ኤርትራ በፌደራላዊ መንግስትነት የሚያዉቅ አዲስ ስርዓት ቢተካ እንኳን እንዳትቀበሉ ሲል ሪቻርድ ከፕላንድ  ለኢሳይያስ አጥብቆ መከረ፡፡ይህን ዓላማ የሚቃወሙ ኃይሎች በሙሉ ቀስ በቀስ እንዲመቱ ሻቢያና ህወሀት ሌሎችን የአሜሪካ አሻንጉሊት ጎረቤት አገሮች በመጠቀም ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ አላማ ማሳካት መረጡ፡፡በዚህ የቅንጅት ስራቸዉ ኤርትራን ገነጠሉ፡፡ ወያኔን በስልጣን ላይ አሰቀምጠዉ አማራን አጠፉ፤ ኢተዮጵያን ከፋፈሉ፡፡ህወሀትን ኮትኩቶ የአሳደጋቸዉ በመሆኑ ወያኔን በመቃወም የፖለቲካ ስደተኝነት ጥያቄ ማቅረብ የአሜሪካን መንግስት  የሸፍጥ ፖለቲካ ያጋልጣል ሰለዚህ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ከሚሽነር በኩል  አገሩ ሲአይኤ አሰፈላጊዉን ሴራ እንዲያጠናክር የሚል የጋራ አቋም ወሰ ፡፡ በዚህም መሰረት

1 በጅቡቲና ኬኒያ የኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱለት ትእዛዝ ይሰጣል፡፡

2 ነሀሴ 17 ቀነ 1996 ዓ.ም የወያኔ ታጣቂዎች በጅቡቲ ከሚገኘዉ የስደተኛ ካምፕ አቶ ግርማ ሞገስ የተባሉትን ስደተኛ አፍነዉ ወሰደዋል፡፡

3 አቶ ሙኸዲን ሙፍታህ ከድር ከጅቡቲ ነሀሴ 12 ቀን 1996 ዓ..ም በ 1992 ጃተኒ/መባትጽዮን ናይሮቢ ዉስጥ የተገደለ የቦረና ተወላጅ ኬኒያወዊ ጠበቃ ሁሴን ሴሪ ናይሮቢ ዉስጥ የተገደለ   በ21/9/93 ዓ.ም አፈወርቅ አለም ሰገድ ቲካ ስደተኛ ካመፕ የተገደለ፡፡ በዚህ የማጥፋት አሰራር ቅንጅት ኢትዮጵያን ብሎም አማራን እያጠፉ  ከዚህ ደረጃ ደርሰዋል፡፡

አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንና አማራዉ ልብ ልትሉ የሚገባዉ እነዚህ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ ዓልመዉ በቋሚነት የተሰለፉ ስለሆነ የአማራዉ ህልዉና ከተጠበቀ  የኢትዮጵያ ህልዉና እንደሚጠበቅ በአንጻሩም የኢትዮጵያ ህልዉና ከተጠበቀ የአማራዉ ህልዉና እንደሚጠበቅ አምኖ በጋራ መሰለፍን ነዉ፡፡አማራ ከኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከአማራ መለየት ከአመጡ ሁሉም በየተራ እንደሚያልቁ ኢተዮጵያን ለማጥፋት የሚዘይዱትን የነሮማን ፐርቻሰካን፣ ፐሮፌሰር ሰብሰኪን፣ ከዲቭ እሰማኤልን፣ ሙዥንገርን፣ ወዘተ ጽሁፎችን አንብቦ መረዳት ነዉ፡፡ ሌሎችን ኢትዮጵያዊያን እና አማራን ነጣጥሎ ለማጥፋት የሚደረግ ጥረት  እድሜልክ እንደሚኖር አዉቀን ተባብረንና ተደራጅተን መጠበቅ ነዉ፡፡ የአማራ ህልዉና ለኢትዮጵያ አንድነት ደርጅት የኢትዮጵያንና የአማራዉን ጥምረት አንድነት ከመነሻ እስከ መድረሻ እተከታተለ ይነግራል፡፡ ያስተማራል፡፡እያአስተማረም ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ህልዉና በአማራው ህልዉና እዉን ይሆናል

ሙላት በላይ

ቁጥር 5 ይቀጥላል

 

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop