“የመደብ ትግል የማያቋርጥ በመሆኑ ፣ በሰው ለሰው ግንኙነት ና በመደቦች መካከል ግጭት አያቋርጥም፡፡ተጨቋኝና ጨቋኝ መደብ እሰካለ ጊዜ ድረስም ግጭት የማያቋርጥ የዕለት ዕለት ክስተት ነው፡፡”
ካርል ማርክስ
“መደብ ብሎ ነገር የለም ፡፡ጨቋኝና ተጨቋኝ መደብ ብሎ ነገር የሉም።የማርክስ ትወራ ተርት ተረት ነው፡፡” የሚል የተቃውሞ ሃሰብ ያላቸው ልሂቃን እና ዓለም በመደብ የተከፋፈለች ናት።”የገበሬው፣የላብ አደሩ፣ ፣የንዑሥ ከበርቴው ና የከበርቴው መደብ ዛሬም አለ ” የሚሉ በሌላ ወገን፣ ዛሬም ድረስ፣አዛና አዚህ “እሰጥ አግባ “ቢሉም ፤የካርል ማርክስ አስተሳሰቦች ፣በእያንዳንዱ ማህበረሰብ ወስጥ እያንዳንዱ ግለሰብ ና ቡድን የሚታወቅበትን ትወራ ተመርኩዘው ፣በወቅቱ ጥልቀት ባለው ምልከታ የቀረቡና ቅቡል እንደነበሩ ይታወቃል።እነዚህ ሃሰቦች ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ፣ የምናጣጥላቸውና “አይረቡም ፡፡”ብለንም በማንቋሸሽ ፣እውነታቸውን ለመሸፋፈን ከቶምአንችልም። ይልቁንስ ዛሬም በቅጡ መጠናት የሚገባቸው እንደሆኑ መገንዘብ ተገቢ ይመስለኛል።ምንም እንኳን በካርል ማርክስ ሃሳብ ውስጥ ሴጣኑ አለ ብለን ብናሥብም…
በካርል ማርክሥ ትወራ ውሥጥ ፣ “ሴጣኑ” ቢኖር እንኳ ፣”ሴጣኑን ” ከውሥጡ አውጥቶ በማሳየት እውነታውን በተጨባጭ ማሥረዳት እና ቀና ህሊና ያለው ወደጥፋት እንዳይሄድ ማሳወቅ እንጂ ፣ዝም ብሎ በደምሳሳው” ሴጣናዊ ሃሳብ በትወራው ውሥጥ አለ።አትጠጉት! “ብሎ ማሥፈራራት አይገባም።
ዛሬ በሃያንደኛው ክፍለ ዘመን “ሥለመደብ “ባይወራም የማህበረሰብን መታወቂያ በትወራ መልክ የሚተነትኑ፣መደብን በቡድን ቀይረው ፣”የእኔ ማነኝ ጥያቄን” አሉታዊ ና አወንታዊ ጎን በጥናታዊ ጽሑፋቸው የሚያቀርቡ ምሁራን ብዙ ናቸው። “ስለ እኛ እና እነሱ” የወቅቱ ” የዘረኝነት መደብ “የሚያወሱ።
ለምሳሌ ስለ ማህበረሰብ መታወቂያ ትወራ ( social identity theory ) እንዲህ የሚል ሃሰብ በጥናታዊ ፅሑፋቸው ያቀረቡ አሉ።
“social identity theory states that the in-group will discriminate against the out group to enhance their self-image.”
Henri tajfel and John turner (social psychologist)
“የሄ የማህበረሰብ መታወቂያ ትወራ ሃሰብ የሚያነጣጥረው በአንድ ቡድን ውስጥ ባለና በቡድኑ ውስጥ በሌለ ላይ ነው ፡፡በቡድኑ ውስጥ ያለ በቡድን ውስጥ ያላከተተውን የሌላኛውን ጥቅም በማሰጣት የራሱን ቡድን ጥቅም ለማብዛት የሚጣጣርበት ሁኔታ በዚህ ትወራ ይገለፃል፡፡”
በሌላ በኩል ሌለኞቹ የማህበረሰብን ሥነ ልቦና የሚያጠኑ ምሁራን ደግሞ ፣
“…a social identity is a person’s knowledge that he or she belongs to a social category or group.”
“የማህበረሰብ መታወቂያ ማለት ፤እንደ ግለሰቡ ዕውቀት የሚወሰን ሲሆን፣እርሷና እርሱ በመረጡት ማህበረሰብ ውስጥ በንፅፅር በጉልህ ሊታወቁ እና በሌላውም ቡድን እወቅናን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡” ይሉናል፡፡ (ማይክል ኤ ሆግ እና ዶምኒክ አበርሃም)
ለምሳሌ ሰው ፤በቤተሰቡ፤ በኃይማኖቱ፣በፍቅር ግንኙነቱ ወይም ባፈቀራት ሴት፣በግል ፍቅሩ ወይም ሆቢው ፣በሙያው ወይም በቡድን ሙያዊ ሥራው፣ባለው ሥልጣን እና ቦታ፣ በታዋቂነቱ ፣በከፍተኛ ትምህርት ተማሪነቱና ተሳትፎው፤በልዩ ልዩ የስራ ዘርፉ (ገበሬ፣ነጋዴ፣ወቶአደር ወዘተ፡፡)
የመጀመርያው ትወራ ውጉዝና ዘረኝነትን አንፀባራቂ በመሆኑ የሚወገዝ ነው፡፡ሁለተኛው ተፈጥሯዊ በመሆኑ የምንኖርበት ህይወት ነው።
ከዚህ አንፃር በእኛ ሀገር የመጀመርያው የእነሱና የእኛ የሚል ያውም በዘርና በጎሣ ላይ የተመሰረተ አመለካከትና አስተሳሰብ ፣በ28 ዓመት ውስጥ ለፍሬ የበቃ ነው፡፡ጥቂት የማይባሉም ግለሰቦች “በቡድን ስም “የራሳቸውን የዘረኝነት መደብ ፈጥረዋል፡፡በዚህም ይታወቃሉ፡፡ ልዩ መታወቂያቸውም ቋንቋዬ የባላል፡፡ (ማንነት የምትል ማነህ?በሬ በሬ እንጂ የላም ማንነት የለውም፡፡የበሬም ሆነ የላም መታወቂያ ግን “የጋማ ከብት” ነው፡፡የፈንረጅ ይሁን የአበሻ፡፡ከብት ከብት ነው።”ጉርጥ አደፈጠም ዘለለም ያው ጉርጥ ነው።” ገባህ፡፡ በቀቀናዊ አመለካከትን ከሚፀየፉ መካከል አንዱ ለመሆን ብቸኛው መንገድ፣ማንበብ ፣ማዳመጥ ና በራስ መንገድ ማሰብ መሆኑንም ተገንዘብ። )
ለመሆኑ ቋንቋ ምንድነው? የመግባብያ መሳርያ አይደለም እንዴ? ቋንቋ መግባቢያ ነው።ተደማምጦ ለመሥማማትም ሆነ ላለመሥማማት ቋንቋውን ማወቅ ያሥፈልጋል።
።የፈለጉትን ሃሳብ ለመግዛትና ለመሸጥም ጭምር ቋንቋን ማወቅ አሥፈላጊ ነው።…
ሰዎች በየዕለቱ የተለያየ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች ጋር በኑሮ እና በሥራ አስገዳጅነት በየትም ሥፍራ በሚገኙበት ጊዜ፣ “ጉዳያቸውን ለመተኮስ” የሚግባቡበት ቋንቋ ያስፈልጋቸዋል።
አንድ ግለሰብ ፣ ለራሱ ጉዳይም ሆነ ለራሱ ላልሆነ ጉዳይ ቋንቋውን ወደማያውቀው አካባቢ ወይም አገር ቢሄድ የሚሄድበትን አካባቢ እና ሀገር ሰው ቋንቋ ካላወቀ ፣ጉዳዩን በቀላሉ ለመከወን ይቸግረዋል።
ለምሳሌ አንድ የአማርኛ ቋንቋን ህሊናው መተርጎም የማይችል (በአንዳንድ ስብሰባዎች “ይህንን ቋንቋ የማትሰሙ እጃችሁን አውጡ።” ሲባል እሰማለሁ።ሰው ጆሮው እስካልታመመ ወይም ሲወለድ የማይሰማ ሆኖ እስካልተወለደ ድረስ እንዴት “የማይሰሙ” ተብሎ ይጠየቃል?) የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ አማርኛ ተናገሪዎች ብቻ ባሉበት ቢገኝ፣ የሚፈልገውን ነገር በቀላሉ ለማግኘት ይከብደዋል።አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪውም እንዲህ ዓይነቱ ችግር በትግራይ ገጠር ቀበሌዎች ቢሄድ ያገጥመዋል።በተቃራኒው አያት፣ምጅላቶቹ ኦሮሞዎች የሆኑ ህፃን፣ትግሪኛ ተናጋሪዎች ጋር ካደገ በኋላ ፣”ጆሮህን ልንቆርጥህ ነው።”ብለው በኦሮምኛ ቢያሥፈራሩት በአንጎሉ ተርጉሞ ምን እንዳሉ መረዳት አይችልምና በንግግራቸው ሊሥቅ ይችላል።ሌላውም ቋንቋ ተናጋሪ በተመሳሳይ መልኩ ቢያድግ እንዲሁ ነው።
በአጭሩ ፣ቋንቋን በመወለድ አናገኘውም።በደም ፣በጅን(በዘር)አይወረስም።
እንዲሁም ቋንቋ ከመግባቢያነት የዘለለ ትልቅ ፋይዳ የለውም።አንዱ ቋንቋም ከሌላ ቋንቋ አያንስምም አይበልጥምም።ሁሉም ቋንቋ ተወራራሽ ብቻ ሳይሆን፣የሚፈጠር፣የሚያድግ፣የሚጎለምስ፣ ዓለም አቀፍዊ ሊሆን የሚችል ነው።አንዳንዱ ቋንቋ የሚቀጭጭ እና እየሠለሰለ የሚሞት ነው። የሞተ ቋንቋ አንድ ጥቀስ ብባል ጋፋትኛን እጠቅሳለሁ።በመላ ኢትዮጵያ መግባብያ ለመሆን የበቀ ኢትዮጵያዊ ፊደል ያለው ቋንቋ ጥቀስ ብባል ደግሞ አማርኛ እላለሁ።
ዛሬ ፣ የአማርኛ ቋንቋ በብዙ ነገር ያደገ እና ያልታወጀለት ብሔራዊ ቋንቋ ሆኗል። በብቸኝነት ግን ራሱን አላሳደገም።በውስጡ ከሀገር ውሥጥም ሆነ ከውጪ ቋንቋዎች የወረሳቸው ቃላቶች በጣም ብዙ ናቸው።
የትግሪኛ ቋንቋ ፊደላት በአማርኛ ፊደል ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ነው። አማርኛ ቋንቋ ዲቃለ ቋንቋ ነው።በውስጡ ብዝሃነትን ያቀፈ ነው።አንዳንድ” አለሃሳቢያን “ግን ሁሉንም ነገር ወደ ዘር የመውሰድ አባዜ ሥላላቸው ቋንቋውን ለአንድ አማራ ለተባለ ጎሣ ሰጥተውታል።ይሄ ደግሞ አለማወቅ የፈጠረው ነውና ለማወቅ ቢተጉና ስለቋንቋ ሰፊ ምርምር ያደረጉትን በመጠየቅ ቢማሩ መልካም ነው።
የእነሱ ና የእኛ በሚል የዘረኝነት መደብ ላይ የተመሰረተ የቋንቋ ምልከታ፣ከፋፋይና አውዳሚ ነው።ሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሁሉም ዜጎች ሀብት ናቸው።ሊያውቃቸው የሚችልበት መንገድ ቢፈጠርለትም ተጠቃሚ መሆኑን ያውቃል። “በቋንቋ የነገሡ” የሀገሬ ፣ፖለቲከኞች ግን ይህ እውነት ፈፅሞ የማይዋጥላቸው ነው።”ወደሥልጣን መምጫና ኬኩን በብዛት ለመብላት በኢትዮጵያ አሁን ያለው የማደናበርያ ብቸኛው መንገድ ቋንቋ በመሆኑ ፣ቋንቋን ለሆዳዊ ዓላማቸው ማስፈፀሚያ ሲያውሉት ይስተዋላሉ። “የእነሱ እና የእኛ እያሉ።”
እስካወቅኸው ድረስ በዓለም ላይ ያለ ቋንቋ ሁሉ የራሥህ ነው።
ሁሉም ቋንቋ መግባብያ ነውና ገዘብህ ብታደርገው ይጠቅምሃል።ቋንቋ የአንድ ጎሣ ሀብት ብቻ አይደለም። በሥምምነት እገሌ የሚባል መታወቅያ(idntity )ሊሰጠው አይገባም።
ሁሉም ጎሣ ፣የሁሉንም ጎሣ መግባብያ ቋንቋ መናገር ባይችልም፣ ሲወራ ወደ ቋንቋው ቀይሮ መረዳት አያቅተውም።(ጎግል ትርጉምን ይጠቅሷል)
የአማርኛ ቋንቋን ዜጋው ሁላ ካወቀና በቋንቋው እሥተተግባባ ድረሥ አማርኛ የእሱም ቋንቋው ነው።
እንግሊዘኛ በአብዘኛው የዓለም ህዝብ ሥላወቀው ዓለማቀፋዊ ቋንቋ ሆኖል።(በአፍሪካም ጥቂት በማይባሉ አገራት ብሔራዊ ቋንቋቸው ነው። )ፈረንሳይኛናአረብኛም እንዲሁ።ታዲያ የእኛ የኢትዮጵያውያን ብቻ የሆነውን ልንኮራበት የሚገባንን ቋንቋ ለምን እንጠላለን??? አማርኛን በሔራዊ ቋንቋችን ማድረግስ ለምን እንደነውር ይቆጠራል???
ከላይ በጠቀሥኩት” የእነሱ ና የእኛ” በሚል ኩንን ምክንያት እና መልካምና ጠቃሚ ሃሣብን ከሌሎች ወንድሞቻችን መቀበል ሞት መሥሎ ሥለሚታየን እውነትን መቀበል ስለሚያዳግተን አይደለምን???።
እውነትን መቀበል ካዳገተንና ሆዳችን ከሀገር ተረካቢው ትውልድ ከበለጠብን ፣ ለምን አንድ ፊቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ አረብኛ ይሁን አንልም??
አለቃ ለማ (የአብዬ መንግሥቱ ለማ አባት) ያሉትን ነው የደገምኩት።(እሳቸው ናቸው ጥራዝ ነጠቆች አማርኛ አልደረጀም፣እንደእንግሊዘኛና ላቲን አልሆነም እናም መቀየር አለበት ብለው ሲያስቸግሩ እና በሤራ ቋንቋውን ሊያጠፉ ሲሞክሩ፣ “አማርኛን ከጠላችሁ …ለምን አረብኛ አይሆንም ያሉት።” አንብቡ ዝርዝሩን ልጃቸው አብዬ መንግስቱ በመፃሐፋቸው ፅፈውታል።)
እናንተ ሰዎች፣የነገ አፈሮች፣አትሳቱ፤ቋንቋ አያስፈራችሁ። የነሱ ና የእኛ በማለት ልዩነትን አትዘምሩ። ቋንቋ ሰው ከሰው ጋር የሚግባባበት የሰው ዘር በሙሉ ሀብት ነው። “የእኛ ና የእነሱ የሚል “የዘረኝነት መደብ” ወይም መታወቂያ የለውም።