May 10, 2019
6 mins read

ማኅበራዊ ፍትሕን ለማስፈን እንረባረብ!- በተክሉ አባተ

ግንቦት 1 ቀን 2011 ዓ/ም! ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር ከ107 ወደ 100 ወረደ። የቀድሞ ሰባት ፓርቲዎች ራሳቸውን ሰውተው (አክስመው የሚለው ጥሩ ቃል አይመስለኝም) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰኘ ብሔራዊ ፓርቲ መስረተዋል። የኢዜማ አመሰራረትና አቋም ቀልብ ይስባል! አንደኛ ከወረዳ የመነጨ የአባላት መሠረት አለው። ሁለተኛ የአመራር አባላት በምርጫ ተሰይመዋል። ሦስተኛ ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣንን ለመመለስ ይሠራል። አራተኛ ትክክለኛ የፌደራል አወቃቀርንም ይከተላል። አምስተኛ ብሔራዊ የፖለቲካ ቁመና ይኖረዋል። ባጠቃላይ ሲታይ ለብዙ ጊዜ ግንባር፣ መድረክ፣ ኅብረት፣ ቅንጅት፣ ንቅናቄ፣ ወዘተ በሚሉ እንቅስቃሴዎች ሲቃኝ የነበረው ባተሌው ፖለቲካችን ቢያንስ አዲስ ስምና ርዕይ ይዞ መጥቷል። ይህን እውን ለማድረግ ርብርብ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከልብ ሊመሰገኑ ይገባል። እንኳን ደስ አላችሁም ልንላቸው ይገባል!

የኢዜማ መቋቋም ዘርፈ ብዙ አንደምታዎች ይኖሩታል። የብሔር ፖለቲካ ብቸኛ መንገድ እንዳልሆነ ግንዛቤ ይወሰዳል። በሀገር ወዳዱ ዘንድ ሁሉ አዲስ የፖለቲካ መነቃቃት ይፈጥራል። ምናልባትም አስተዋጽዖ ለማድረግ ፍላጎት እያለው ግራ በመጋባትና በመጠራጠር ከመሀል ወይም ከዳር ሆኖ ለሚመለከት ሁሉ ጥሩ እድል ይፈጥራል። ሌሎች 100 ፓርቲዎች ኢሕአዴግን ጨምሮ መስዋእትነት ከፍለው ውህደት እንዲፈጽሙ ይጋብዛቸዋል። አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም ሀሳቡ ያላቸው ደግሞ ቢያንስ በይሉኝታ ሀሳባቸውን እንዲሰርዙ ያስገድዳቸዋል። መንግስትና ገዥው ፓርቲ ፈርጠም ያለ እውነተኛ ተፎካካሪ ፓርቲ እንደተወለደ በመገንዘብ አገልግሎታቸውን ይበልጥ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ እንዲያደርጉ ይጋብዛቸዋል። ኢትዮጵያዊነት ሁሉም ነገዶች የሚጠለሉበት ጃንጥላ ስለሆነ ስጋትና ጥርጣሬን ያስወግዳል። ብሎም በክልሎች መካከል ከወሰን ጋር በተያያዘ ሊኖር የሚችለውን አላስፈላጊ የእርስ በርስ ንትርክን መፈናቀልን መገዳደልን ያስቀራል። ከተለያዩ  ነገዶች የተመሰረቱ ቤተሰቦች በአንድነትና በፍቅር ይጸናሉ።

ይሁንና ኢዜማ ከመክሰም ወይም ከመከፋፈል ድኖ ማኅበራዊ ፍትሕን በኢትዮጵያ ለማስፈን እጅግ ልዩ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ ያስፈልገዋል። አባላቱን እያበዛ የሰፊውንም ሕዝብ ልብና አእምሮ እየማረከ መሄድ ግድ ይላል። እስካሁን ድረስ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሄዱበትን ውጤት አልባ ጉዞ ግምት ውስጥ በማስገባት እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ካሁኑ አትራፊ መንገዶችን መለየትና መከተል ያስፈልጋል። ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ተናብቦ ተቻችሎ መጓዝ ያስፈልገዋል። ከዚህ በፊት እንደተለመደው መሪዎች ብቻቸውን የፓርቲን ፍጻሜ የሚወስኑ መሆን የለባቸውም። ኢዜማ ራሱን አደራጅቶ ለቁም ነገር በቅቶ ኢትዮጵያን እንዲታደግ የፓርቲው አመራርና አባላት ድርጅታቸውን የሚቆጣጠሩበት የሚገመግሙበት የሚመሩበት ሥርዓት መለየትና ሥራ ላይ ማዋል ይገባቸዋል። ሀገሩን የሚወድ ሰፊው ሕዝብም ፓርቲውን ለመደገፍም ሆነ ለመውቀስ የሚጠቀምበት ግልጽ መስፈርት ሊኖረው ይገባል። የፓርቲው አባላትና ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ሁሉ ኢዜማ ዘመን ተሸጋሪ ፓርቲ እንዲሆን የበኩላቸውን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ጉዳዩ ሀገር የማዳን እንጅ የአንድ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። እርስዎም ኢዜማን እየደገፉ እየተቹም የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ። ማኅበራዊ ፍትሕ በፓርቲ አመራሮችና አባላት ብቻ ሊሰፍን አይችልምና!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አስተያየት ካለዎት በ[email protected] ይላኩልኝ!

 

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop