April 5, 2019
18 mins read

ቋንቋ ለብልሆች የመግባቢያ መሣሪያ፤ ለደናቁርት ግን ሕዝብ መከፋፈያ – በገ/ክርስቶስ ዓባይ

በገ/ክርስቶስ ዓባይ

ዓለማችን የአንድ ቁንቋ ብቻ ባለቤት እንደነበረች ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ነገር ግን የባቢሎን ሀገር ሕዝቦች (የዛሬዋ ኢራቅ) በድንገት አንድ አጋጣሚ ተከሰተላቸው። ይኸውም በጭቃ ዳር ያነደዱት እሳት ጭቃውን ወደ ሸክላነት ለወጠውና አጠነከረው። ይህንን የተረዱት የባቢሎን ሕዝቦች ኑ ጡብ እንሥራ እና የአምላክን ሁኔታ እናውቅ ዘንድ ረዥም ግንብ ወደ ሰማይ እንገንባ በማለት ተመካከሩ። ስምምነታቸውንም ተግባራዊ በማድረግ የሽክላ ጡብ እየሠሩ ግንባታውን ተያያዙት። ፈጣሪ አምላክም ሊሆን የማይቻለውን ሞክረዋልና በድርጊታቸው ተቆጣ። ከዚያም ኑ (ሥላሴ) ወደ ምድር እንውረድ የሕዝቦችንም ቋንቋ እንዘባርቅባቸው በማለት የባቢሎናውያንን ቋንቋ ዘባረቁት። ከዚያም ግምበኛው ውሀ ሲፈልግ ጡብ፤ ጡብ ሲፈልግ ደግሞ ውሀ ማቀበል በመጀመራቸው እርስ በርስ ሊግባቡ አልቻሉም። በመጨረሻም ከላይ ያሉት ሠራተኞች ጡቡን እያነሱ ወደታች በመወርወር እርስ በእርሳቸው እንደተጠፋፉ ይነገራል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የቋንቋ ልዩነት እንደተፈጠረ ይታወቃል ኦሪት ዘፍጥረት ም11፡ 1-9።

ከዚያ በኋላ የዓለም ሕዝብ ቁጥር በጨመረ ቁጥር በዘር በነገድና በጎሣ እየበዛ እንደመሄዱ መጠን፤ የቋንቋውም ዓይነት ብዛትና ልዩነት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱ አይካድም። ይሁን እንጂ በጥልቀት ልናስተውለው የሚገባን አንድ በጣም የሚያስገርም ምስጢር አለው። ይኸውም ምንም እንኳ ቋንቋ በተወሰነ አካባቢና በተወሰኑ ብሔር ብሔረሰቦች መጠቀሚያ ቢሆንም ቅሉ፤ ቋንቋ በራሱ ግን ብሔር፤ ዘረ ወይም አገር የለውም። የዚህን ታላቅ ምስጢርነት የማይረዳ ሰው ካለ የአስተሳሰብ ድሁርነት ስላለው እራሱን መመርመር ይገባዋል።

ከአንድ መቶ ዓመት በፊት ተመራጩ የዓለም መግባቢያ ቋንቋ የነበረው ፈረንሣይኛ ነበር። የፈርንሣይኛ ቋንቋ በመላው አውሮፓ በሚባል ደረጃ እንደ መግባቢያ የሚያገለግል የግንኙነት መሣሪያ ሆኖ ቆይቷል። ለምሳሌም የሩሲያ የዛሩ (የአፄው) ቤተመንግሥት የመግባቢያ ቋንቋ ፈረንሣይኛ እንደነበር ይታወቃል። የሩሲያ የዘውድ መንግሥት የፈረሰው ከአንድ መቶ ዓመት በፊት  እ.ኤ.አ በ1917 ዓ/ም በቭላድሚር ኤሊች ሌኒን በተመራው የጥቅምቱ ሶሺያሊስት አብዮት ነበር። ከዚህም የተነሳ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በጀኔቭ ስዊትዘርላንድ የዓለም መንግሥታት ማኅበር እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 10 19201 ዓ/ም ሲቋቋም ለዓለም አቀፍ መግባቢያ እንዲሆን በአንደኝነት የተመረጠው የፈረንሣይኛ ቋንቋ መሆኑ ያልተዋጠላቸው እንግሊዞች ቶሎ ብለው የራሳቸውን ቋንቋ ለማሳደግ የሚችሉበትን ዘዴ ማውጠንጠን ያዙ።

ወዲያውኑም ከፍተኛ በጀት በመመደብ ብሪቲሽ ካውንስል በመባል የሚታወቀውን ታላቅ ተቋም  እ.ኤ.አ በ1934 ዓ/ም በመመሥረት ቀስ በቀስ በየሀገሩ ቅርንጫፍ በመክፈት የማስፋፋቱን ሥራ ተያያዙት። ቀደም ሲል እንደሚታወቀው ፈረንሣይና እንግሊዝ በተለይ በቅኝ ግዛት የማስፋፊያ ዘመቻ ወቅት ከፍተኛ ፉክክር፤ ውድድርና ሽኩቻ ስለነበራቸው ያንኑ ተከትሎ እንግሊዝ በቋንቋውም በኩል እንዳትሸነፍ የተለመችው ዕቅድ ነበር። ለጥሩም ይሁን ለመጥፎ ነገር በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀሰው እንግሊዝ ዕቅዷ ተሳክቶላት እንዳሰበችው እንግሊዝኛ የዓለም ቋንቋ በመሆን ሰምሮላታል። በዚህም የተሳካ ውጤት አማካይነት ማንኛውም እንግሊዝ ዜጋ አቅም እስካለው ድረስ ዓለምን ለመዞር ቢነሳ፤ በሚሄድበት አገር ሁሉ የቋንቋ ችግር ሊገጥመው አይችልም። ምክንያቱም ዓለም በሙሉ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ይነገራልና ነው።

ለዚህ ተጨማሪ ማስረጃ የሚሆነው በማንኛውም ሀገር ትምህርት ቤቶች በተለይ ከሁለተኛ ደረጃ በላይ እንግሊዝኛ እንደመደበኛ ቋንቋ (የመማር ማስተማር ቁልፍ) ሆኖ ስለሚያገለግል ተፈላጊነቱ ከፍተኛ ሆኗል። እንግሊዞች እንዲህ ያለው ከፍታ ላይ ሊደርሱ የቻሉት እንዲሁ በቀላሉ አይደለም። የስዋስው መጻህፍትን በማሳተም፤ የታዋቂ ደራሲዎቻቸውን ሥራዎች በተለያዩ የአረዳድ ደረጃዎች ማለትም በቀላል ቋንቋ እየከሸኑ ለዓለም በማቅረብ፤ የአንባቢያንን ስሜት መማረክ በመቻላቸው ጭምር ነው። የቻርለስ ዲክንስ፤ በርናንድ ሾው፤ የሰር አርተር ኮናን ዶይል ገጸ ባህርይ የሆነው ሸርሎክ ሆምስ፤ የአጋዛ ክሪስቲ፤ የዊሊያም ሸክስፒር፤ ቶማስ ሞር፤ ጆናታን ስዊፍት፤ዳንኤል ደፎ፤ ጄን አውስትን፤ሻርሎት ብሮንቲ ..ወዘተ… ወዘተ..ድርሰቶች የማይጠገቡና የማይሰለቹ ናቸው።

ይህ ብቻም አይደለም፤ ለማስተማሪያ የሚሆን የቋንቋው ባለቤቶች የሚያደርጉትን የአነጋገር ቅላጼ በቴፕና በቪዲዮ በመቅረጽ ሰዎች በቀላል መንገድ ሊማሩ የሚችሉበትን ዘዴ ሳያሰልሱ ተጠቅመዋል። ብሪትሽ ካውንስል ለእንግሊዞች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ የዋለው ውለታ እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። እንግዲህ አንድ ግለሰብ የፈለገውን ያህል የተማረና የተመራመረ ቢሆን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ካላወቀ እራሱን ለዓለም ለመግለጽ ቢፈልግ የሚደርስበት ውስንነትና ማነቆ ካባድ ነው። ምናልባት በአስተርጓሚ መጠቀም ይችላል ቢባል እንኳ፤ እንደሚፈልገው አድርጎ የልቡን መግለጽ አይችልም። ስለሆነም እንዲህ ያለውን እውቅ ምሁር የቋንቋ ችግር ጎደሎ ያደርገዋል ማለት ነው።

ይህንን እንደምሳሌ ከወሰድን አሁን እንግሊዝኛ አገሩ የት ነው? ዜግነቱስ የማን ነው? ዘሩስ ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ የዓለም ይሆናል። የቋንቋ ችሎታ ያለው ሰው እንደልቡ ወጥቶ ወርዶ፤ ነግዶ ሠርቶ ከማንኛውም ማኅበረሰብ ጋር ተግባብቶ መኖር ይችላል። በአብዮቱ ዘመን ማለትም በ1970 ዓ/ም በችኮዝሎቫኪያ በየወሩ የሚታተም Life የሚባል መጽሔት ይደርሰኝ ነበር። በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ጥቅስ ማንበቤን አስታውሳለሁ፡  ‘The more languages you know the most of a man you are!’ብዙ ቋንቋ መናገር በቻልክ ቁጥር ስብዕናህ የላቀ ሰው ትሆናለህ!

ቋንቋ ማወቅ ይጠቅማል እንጂ ጉዳት የለውም። ነገር ግን የቋንቋው የአገልግሎት ስፋትና ጥበት ጥቅሙን ያበዛዋል ወይንም ያሳንሰዋል። ለምሳሌ የቻይንኛ ቋንቋ ማወቅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። ለንግድም ሆነ ለአንዳንድ የቴክኖሎጂ ሽግግር ወይም ኩረጃ ወደር አይገኝለትም። የቋንቋ ዋናው ጥቅም ሕይወትን ለመቀየርና ኑሮን ለማሻሻል የሚረዳ እስከሆነ ድረስ ነው። ምንም ጥቅም የማያመጣ ከሆነ የቋንቋ ዕውቀት የጋን መብራት ከመሆን ያለፈ ፋይዳ አይኖረውምና በግብታዊነት ከመወሰን በፊት እየተስተዋለ ቢሆን መልካም ይሆናል።

ወደ አገራችን ሁኔታ ስንመለስ አማርኛ ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ማለትም ከአፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል። ከታሪክ እንደምንረዳው የአማርኛ ቋንቋ በአክሱም ዘመነ መንግሥት ጊዜ የልዑላዊያን ቤተሰብ መነጋገሪያ ቋንቋ እንደነበር ይታወቃል። የመጨረሻው የክሱም ንጉሥ “አንበሳ ውድም” በ950 ዓ/ም የአይሁድ እምነት ተከታይ በነበረችዋ “ዮዲት ጉዲት” ከመንበረ መንግሥቱ ሲለቅ ወደ  “አማራ ሳይንት” ደቡብ ወሎ በመሄድ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ የማርኛን ቋንቋ ከግዕዝ ቋንቋ  ጋር ማስተማር እንደተጀመረ ይታወቃል። እንግዲህ ቀን የጣላቸው የንጉሣዊ ቤተሰብ ሰዎች ጥቃት እንዳይደርስባቸው በመፍራት እራሳቸውን ደብቀው ይኖሩ ነበር ይባላል። ከዚያም ከሦስት መቶ ዓመታት በኋላ የአክሱም ንጉሠ ነገሥት ዝርያ የነበረው ልዑል ይኩኖ አምላክ፤ እግዚአብሔር ሰሎሞናዊ ሥልጣነ መንግሥቱን በመለሰለት ጊዜ በ1262 ዓ/ም ተቀብቶ ነግሧል። ከዚህም የተነሳ የተማረ ስለነበር የመሥሪያ ቋንቋው አማርኛ እንዲሆን በአዋጅ አጽንቷል።

በዚህም በአለፉት የሰባት መቶ ዓመታት ጊዜ ውስጥ ብዙ በርካታ መጻሕፍት፤ ቀድሞ በብራና ተጽፈዋል፤ በኋላም በማተሚያ ታትመዋል። የአማርኛ ቋንቋ በትምህርት ቤትም ይሰጥ ስለነበረ አገሪቱን ለማገናኘት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳደረገ አይካድም። ነገር ግን ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ የበታችነት ስሜት በሚያሰቃያቸውና የሥልጣን ጥመኝነት በተጠናወታቸው እንደ አቶ መለስ ዜናዊ በመሰሉ መሪዎች ሥር በመውደቋ፤ ከሌሎች ማኅበረሰቦች ወደ ማዕከላዊ ሥልጣን እንዳይመጣ በማሰብ፤ በዲሞክራሲ ስም ሁሉም በየራሱ ቋንቋ እንዲማር በማለት በቋንቋ አጥር ተከቦ ይኸው ሃያ ሰባት ዓመታት ተቆጥረዋል።

አሁን በአለንበት የለውጥ ሂደትም በተለይ የኦሮምኛ ቋንቋ እንደ ሁለተኛ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን የሚል የአክራሪ ኦሮሞ ልሂቃን ጥያቄ እየጎላ መጥቷል። ጥያቄው አግባብ ስለአለው ማንም የሚደግፈው ጉዳይ ነው። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች ውስጥ በቁጥር በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ፤ ቋንቋው ብሔራዊ ይሁንልኝ ካለ የማይሆንበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም። ነገር ግን ሁለት ነገሮችን በጥሞና መመዘን ይኖርብናል።

1ኛ)  አሁን እንመርሃለን የሚሉት የኦሮሞ ልሂቃን፤ እነጀዋር መሐመድ፤ ዳውድ ኢብሳ እና በቀለ ገርባ የመሳሰሉት የሥልጣን ጥመኞች፤ በአገኙት አጋጣሚ አማርኛ ቋንቋ ስለሚችሉ፤ እነርሱና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም የኦሮሞ ሕዝብ ገዥዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንዳይሆን መታሰብ አለበት። ምክንያቱም ኦሮምኛ ብሔራዊ ቋንቋ ከሆነ የኦሮሞ ሕዝብ የአማርኛን ቋንቋ እንዳይማር ሊያደርጉት ስለሚችሉ፤ አገር መምራት የሚችሉ  የኦሮሞ ልጆችን በአካባቢያቸው ብቻ ወስነው እንዳይወጡ ያደርጓቸዋልና ነው።

2ኛ) ሌላው ማኅበረሰብ ይጠቅመኛል እስካላለ ድረስ፤ እና ላሚቱ የበላችው የኦሮሞ መጽሐፍ ተገኝቶ እስካልታተመ ድረስ፤ (ወደፊት በስፋት እጽፍበታለሁ) ምንም ዓይነት የተደራጀ የማስተማሪያ መጻሕፍት በሌለበት ሁኔታ ማስገደድ ሊኖር አይገባምና ነው።

ከላይ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ የኦሮሞ ሕዝብ ቁጥር በሁለተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። “ሞኝ ያስያዙትን አይለቅም “ እንዲሉ ሟቹ መለስ ዜናዊ በአማራው ሕዝብ ላይ የነበረውን ጥላቻ ለመግለጽና በበጀት ምደባም ሆነ በአገልግሎት ተጠቃሚ እንዳይሆን በማሰብ፤ የአማራውን ሕዝብ ቁጥር በግማሽ እንዳሳነሰ አይዘነጋም። ወደ እውነተኛው ቁጥር ከሔድን ግን የአማራ ሕዝብ የኦሮሞን ሕዝብ እጥፍ እንደሆነ ምንም የሚያጠራጥር አይሆንም። ይህም በቅርቡ በሚደረገው የሕዝብ ቆጠራ የሚረጋገጥ ይሆናል።ለማንኛውም ግን ቋንቋ ብሔር ፤ዘርና አገር የለውም፤ ቋንቋ ያወቀውን፤ የተናገረውን፤ የአከበረውንና የተማረውን ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። ለቋንቋ ብሔር፤ ዘርና ክልል ሊሰጡት የሚዳዱትን እንደነአቶ በቀለ ገርባ ያሉ፤እራሳቸው በበታችነት ስሜት ግራ ተጋብተው የኦሮሞን ሕዝብ ጭምር ግራ ከሚያጋቡ፤ የኦሮምኛ ቋንቋን ለማበልጸግ የሚያስችል መጽሐፍ ጀባ ቢሉ አይሻልምን?

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop