March 28, 2019
24 mins read

የሱሪ በአንገት አውልቅ አስገዳጅና ጠማማ ሃሳብ  በጎሠኝነት ላይ ያጠነጠነ የአድማ ፓለቲካ

  + ሰውነትን የረሳ  የ107 ፖርቲ  የትርፍ ዳቦ ፍለጋ ትንቅንቅ =አውቶሚክ ቦንብ
በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
     አሁን ኢትዮጵያን እያስተዳደራት ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት መሆኑንን እና የሚመሩትም በኢሕአዴግ የተሾሙ ናቸው።
   ጠ/ሚር ከሆኑም ገና አንድ ዓመታቸው ነው። “ሱሪዎትን በአንገትዎት አውልቁ ” የምትሉ አብዳችኋል። ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ።በግል ሚዲያም ሆነ በመንግሥት ሚዲያዎች፣ሚዛናዊ እና ገንቢ ሃሳብን አራምዱ። ነፃ ሁኑ።ዘር፣ጎሣ፣ይሄ ፍቺው እንኳን የተምታታ ብሔር ብሔረሰብ  እናንተንም አያምታታችሁ። የሚያዳምጣችሁን ና የሚመለከታችሁን ህዝብ አክብሩ። ዘሬ ተነካ ብሎ ፣ጎሣዬ ፣ቋንቋዬ እያለ ባሻ አሸብርና ፊት አውራሪ መሸሻን ለመሆን የሚቃጣውን ወደ ምልታዘዝ ድራማ ውሰዱት አሪፍ ኮመዲ ትራጀዲ ይወጣዋልና ሃሳቡ።
   ውድ  ጠ/ሚርአችንም ለራሶትም አሥቡ።ተረጋጉ።ጤንነትዎትን ጠብቁ።ለአንድ ዓመት በጀሠን ቦልት ፍጥነት ሮጠዋል ።ሩጫዎትም አላባራም።ለድካምዎት እና ለነፍሰ ገዳዮች እንኳ ባሣዩት ርህራሄ እናደንቅዎታለን። እንደሙሴ ትዕግሥትዎት ይብዛ።ለእስካሁኑ በእጅጉ እናመሰግናለን።
      “እኔ  መንገዱን የምጠርግ ሆኖም ግን የመጥመቁ ዮሐንስን ሚና የማልጫወት አሸጋጋሪ መንግሥት ነኝ።” በማለት እንደተናገሩ በማሥታወሥ ከጎንዎ እንቆማለን።
    ከ107 ሉሥልጣን   ከሚፎካከሩ ፓርቲዎች ውስጥ  እንደ ዲዮጋን በፀሐይ ብርሃን ተጨማሪ ባውዛ ተጠቅመን ብንፈልግ እንኳ የእርሶን ዓይነት መሪ አናገኝም።         (መሪያችን በፓርቲያችን ውስጥ አለ የምትሉ እንዳላችሁ አልዘነጋሁም። ) ምክንያቱም  ብዙዎች ፓርቲዎች  አግላይ ከመሆናቸውም በላይ ፣በዘመድ አዘመድ፣በቋንቋ እና በጥቅም አጋርነት የተሳሰሩ ናቸውና ፣ገለልተኛውና አርቆ አሳቢው የኢትዮጵያ ህዝብ ድራማቸውን ዳር ሆኖ እያየ ከመገረም ባሻገር እንደማይደግፋቸው የታወቀ ነው። (በበኩሌ ምንም አጓጊ ተስፋ ይኑረው ፣በዘር፣በቋንቋ፣በጎሣ  ላይ የተመሠረተ ፓርቲ ፣ በተፈጥሮው ሁሉንም ዜጋ ሊያካትት እና የሁሉም ዜጎች ፓርቲ ሊሆን አይችልም።በቋንቋ  ሥም አጥሮታል እና አሳታፊ ባለመሆኑ፣በአናት በአናቱ ቅራኔን የሚፈለፍል እና ሰው ፣ከሰው ጋር ተስማምቶ እንዳይኖር የሚያደርግና ሲብስ ደግሞ እንደ አውቶሚክ ቦንብ  የሚያወድም ነው።
    ይህንን ጠ/ሚርአችን ልብ ሊሉ ይገባል። አዲስና ሁሉንም ቋንቋ ተናጋሪ በአባልነት የሚይዝ  “የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የመደመር ፓርቲ” (ኢአመፓ) ካልተመሰረተ በሥተቀር ሌላው ዓለም ላይ በሌለ “በደሴት የቋንቋ ፓለታካ” ሀገር ተረጋግታ አትቀጥልም።
   የላቀ አእምሮ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንንም የሚያገል አክሳሪ የፓለቲካ አካሄድ ነው ብዬም አምናለሁ።  በትልልቅ ከተሞችም(በለብዙ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆናቸው) እንዳልሠራ በተግባር ታይቷል ።
     በኢትዮጵያ እጅግ የሚያሥገርም የላቀ አእምሮ ያላቸው እምቦቀቅላዎች  እንዳሉ ይታወቃል።በነሱ ልክም  ከግብዝነት የፀዱ ፖለቲካን በቅጡ የሚያውቁ ምሁራን እንዳሉም አንዘንጋ!!  …እነዚህን እጅግ ጠቃሚ ዜጎች  በቋንቋና በብሔር ላይ የተመሠረተው ፣የተለመደው አደረጃጀት ወላፈኑ ሊያሥጠጋቸው ከቶም አልቻለም።…
    መጥኔ ለጠቅላይ  ሚኒስትሩ ።ትዕግሥቱን እና ዝቅ፣ዝቅ ማለቱን ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብዝቶ ይስጣቸው።  “አንደበት” አመፀኛ ና የማይገራ ሚጢጢ አካል መሆኑን፣ሰዎች በዚህ ሚጢጢዬ  “አንደበት” ፈጣሪን እንኳን ሲረግሙ እንደሚስተዋሉም ላሥታውሳቸው  እፈልጋለሁ።
    እናንተ ተቺዎችጠ/ሚር አብይ አህመድ ሰው እንጂ ፈጣሪ አይደለም። እናም ፍፁም  ሊሆን አይችልም። እናንተም ወጣቶች ከ1967 ጀምሮ በቀይ ና ነጭ ሽብር  በከንቱ የረገፈውን ወጣት አሥታውሱ !!!..
“የመጀመሪያው መጨረሻ”
“እኔ ሰው አይደለሁም!”ዕወቅ ” ትግራዊ” ነኝ!
እኔም” አማራ ነኝ።” ሰው ነህ አትበለኝ !
ለምን ሰው ትለኛለህ?”ኦሮሞ!” ብለህ ጥራኝ።
አቤት አልልህም፣”አንተ ሰው! “ስትለኝ።
እኔ ብሔረሰብ፣ጎሣና ክልልነኝ።
ወላይታ ጋሞ፣እኔ ሲዳማ ነኝ!
አገው፣ኩናማ ዕወቅ መዠንገር ነኝ።
የወል መጠሪያዬን ጎሣዬ ወስዶታል
በጎሣና በቋንቋ መጠራት ግዴታዬ ሆኗል።
ኦባማ፣ ኬኒያዊ ዘር  ኖሮት አሜሪካንን ሲመራ
ትራፕ ከጀርመን ፈልሶ፣ ሲሆን እሱም አውራ
አንተ ኢትዮጵያዊው፣ወደኋላ ተመልሰህ
ዘመነ መሳፋት ውስጥ መክሊትህን ቀብረህ
“ሰው ከቶም አይደለሁም _ቋንቋ ነኝ “ትላለህ።
ለሆድህ ተገዝተህ
ቋንቋ፣ጎሣ እያልክ …
በዘውግ ፖለቲካ…
ህዝብን ታባላለህ…
” መልኬን ቁመናዬን፣እርሳው ሰውነቴን
ከአለም ህዝብ ጋር፣ያለው አንድነቴን።
ወግድ! አጨቅጭቀኝ፣በቃ! እኔ አገውነኝ!
ጉራጌ ወላይታ፣አፋር ቅማት ነኝ!
ራያ፣አርማጮህ፣ቤንችና ማጂነኝ!
ቦዲ፣ሀመር፣ሸካ፣በርታ፣ሲዳማነኝ!”
እንዲል ፣
ቀዬው ድረስ ወርደህ ትቀሰቅሳለህ
በማህበራዊ ሚዲያ እሳት ትጭራለህ።
ይህ ብቻም አይደለም፣ያንተ ተንኮልህ
ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር ግንባር ፈጥረህ
በአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ውስጥ ልዩነትን አጉልተህ
ታስብላለህ፣
“እኔ ሰው፣አይደለሁም !”የጠራው መንዜ ነኝ
የተጉለት የቡልጋ…እኔ የሸንኮራ ነኝ!
ከጎጃምም የደጀን… የደብረማርቆስ ነኝ።
ከጎንደርም ጎደር !ደብረታቦሬ ነኝ።
እውቅ ፈሪ  ሁላ!እኔ አርማጮህ ነኝ።
እኔ ያባ ጃሌው…ዕወቅ የቋራ ነኝ !!
ዕወቅ” ሰው ነኝ! ” ባይ ሁላ!!
ከኦሮሞም ኦሮሞ እኔ ወለጋ ነኝ!
የነቀምቴ !የነጆ…የደምቢ ዶሎ ነኝ !!
“እኔ ሰው አይደለሁም! “በቃ አሩሲ ነኝ !!
ባሌ!ጮሬ …ሸዋ ! ጅማ፣ኢሉአባቦራ
ከረዩ፣ቦረና፣ቆቱ…ሐረርጌ ነኝ !
“ሰው ነኝ !!” ባይ ሁላ ፣ በቃ አፍህን ዝጋ !!
በቋንቋ ፖለቲካዬ  ላይ፣ አታምጣ አደጋ።
ከ27 ዓመት በፊት ለሥልጣን ስበቃ
ተገን አድርጌ ነው የቋንቋን ጠበቃ !!
እንደሥልጥኑ ዓለም ፣ በሀገር ሰው ብመካ
ይኑር ብል አንድ ቋንቋ ሀገሬን የሚያስመካ
ልራመድ ብሞክር፣በምዕራቡ ፖለቲካ
107 ፖርቲ፣አይኖርም ነበር ፣ወሬውን እየከካ!
ቋንቋ ሥልጣን መሥሎት፣በግብዝነት እያስካካ!
መች ይኖር ነበር፣ተቧድኖ ፣ እየተላላሰ ሲያወካ!
አልገብቶህ እንደሆን፣የሴራ ነው የእኛ ቦጠሊቃ!!
በማለት የሚጀምር “ብርሌ ከነቃ፣አይሆንም ዕቃ!”
ተራምደህ እለፈው፣አትቁም አጋርህን ጥበቃ!
“ብዝበዛህን አጣድፍ፣ህዝብ ከእንቅልፉ ሳይነቃ!!!…”
መሻወጊ ጥቅምት 14/2011 ዓ/ም
107 ፖርቲ እና የትርፍ ዳቦ ፍለጋ ትንቅንቅ በኢትዮጵያ
      በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
     በኢትዮጵያችን የዳቦ ጥየቄ ለዘመናት መልስ አላገኘም፡፡መልስ ያላገኘውም፣በየዘመናቱ የመጡ እና ወደ  አፈርነት የተለወጡ ጥቂት መንግሥታት ፣ዳቦ ሰራቂዎች እንጂ ዳቦ አምርተው ለህዝብ በአግባቡ የማያከፋፍሉ በመሆናቸው ነው፡፡
      የፈውዳሉ ሥርዓት፣መለኮታዊ ሥልጣን፣አለኝ ብሎ፣ ከእግዜር በታች ከኢትዮጵያ ህዝብ በላይ መሆኑን ሃይማኖትን ጠቅሶ፣በብሉይ እምነት መሰረት  ̋ ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ ̋ በማለት፣ ̋ የሀገር ዳቦ የእኔና የቤተሰቤ ብቻና ብቻ ነው፡፡በፍቃዴ፣ለወደድኩት ያሻኝን አደርግለት ዘንድ ሥልጣን አለኝ፡፡ ከፀሐይ በታች የስልጣን ባለቤትም እኔ ነኝ፡፡ “ ባይ በመሆኑ፣በግልፅ የተትረፈረፈ ዳቦ በግሉ ቢያከማች  ከቶም አያስገርምም፡፡
   የሚስገርመው ደርግ “ይህ ደም መጣጭነት ነው እንጂ መለኮታዊ ስልጣን አይደለም።”  በማለት ፣ቀኃሥን ከዙፋን አውርዶ  ሲያበቃ ፣አባላቱ በሂደት ራስ ወዳድ ፣ግብዝ፣ትምክህተኛ እና አምባገነኖች እየሆኑ  መጡ።… ፣በመጨረሻም ቁንጮው መሪ ሳይቀሩ፣ በህዝቡ የጋለ የሀገር ፍቅር ስሜት ላይ፣ ቀዝቃዛ ውኃ ቸልሰው መኮብለላቸው አይረሳም።
    ከዚህ እኩል  የሚያስገርመው ና የሚያሳዝነው፣በደርግ የአገዛዝ ዘመን ፣ለወያኔም ሆነ ለሻቢያ ከኢትየጵያ ጦር እኩል ስንቅና ትጥቅ፤በማከፋፈል፣ በዜጎች ህይወት የነገዱ፣ በእህቶቻችን እና በወንድሞቻችን  ደም የጨቀየ ዳቦ የግበሰበሱ መኖራቸው ነው፡፡ ዛሬም ከታሪክ አልተማርንም።
“ዋ! ከታሪክ ያለመማር፣ታሪክን ለመድገም ያስገድዳል።”
     እዚህ ላይ ፣ አንባቢ ልብ ሊለው የሚገባ እውነት አለ፡፡ይኸውም በየዘመናቱ በሥልጣን ኮርቻ ላይ የወጡ፣የኢትዮጵያ መንግስታት የየራሳቸው በጎና ጥሩ ጎን እንዳላቸው የሚክድ የታሪክ ፀሐፊ ያለመኖሩን ነው፡፡ይሁን እንጂ ለህዝብ ዳቦ ከማከፋፈል አንፃር፣አንዳቸውም ሚዛናዊ አልነበሩም፡፡ይልቁንም፣በሚስጥርና በግለፅ፣ለግላቸውና ለጥቅም ሸሪኮቻቸው፣የተትረፈረፈ ዳቦ በማደል፣ህዝብን የሚያስርቡ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ገበናቸውን በማስጣት ሥንፈትሸው፡፡
     ሁሉም፣የኢትዮጵያ ገዢዎች፣  ይነስም ይብዛ፣የሀገርን ሀብት ወይም ዳቦ፣ለራሰቸው ና በተዋረድ ላሉ የሥርዓቱ አውራዎች ሲየከፋፍሉና ኑሯቸውን ሲያደረጁ እንጂ፣ህዝብ ና ሀገርን በተገቢው መንገድ በማሳደግ ቢያነስ በቀን ሦስት ጊዜ ዜጎች  እንዲበሉ ሲያደርጉ አልተሰተዋሉም፡፡
   (እናስ በዳቦ ጥያቄ ሥልጣንን ያገኛት፣የአፍሪካ ፖለቲከኛ፣ዳቦ ያለጠባቂ ሜዳ ላይ ተበትኖ ሲያገኘው ላያግበሰብስልህ ነው?…)
      በየሰርዓቱ የነበሩ ቱባ ባለስልጣነት ሁሉ፣በህዝብ ሥም፣እየማሉና እየተገዘቱ የህዝቡን ዳቦ የሚሰርቁ፣ሌቦች ነበሩ፡፡ሰርቀውም ሲያበቁ፣በሀገርና በውጪ፣የሚምነሸነሹ ብቻ ሳይሆኑ፣የበዛ ዳቦ በስማቸው በባንክ በማከማቸት ህዝብን የሚያስርቡ እነደነበሩ ታሪክ መስክሮባቸዋል፡፡( የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ባለሥልጣናት  ዘረፋ ግን በዛ! )
     ዛሬም ልዩ የቁጥጥር ሥርአት ባለመዘርጋቱ  የተነሳ በፌደራልና፣በየክልልሉ ያሉ አንዳንድ አገልግሎት ሰጪዎች (፣በቀበሌ የተመደቡ የፖለቲካ ሹማምነት ፣የማዘጋጃ ሹማምነት፣ህግ አስፈፃሚ አካላት፣ገቢዎች ወዘተ)በጨረታ ሥም፣በህገወጥ ግንባታ ሥም፣የመንግስት ገቢ በማስገባት ሥም፣የቀበሌ ቤትን በመቆጣጠር ስም፣ህግን እና ህገመንግስትን በመጠበቅ ሥም፣የሚደረገው ብዝበዛ አላባራም።
    ዛሬም፣በተዋረድ ያሉ፣አንዳንድ ባለሥልጣናት፣(አገልጋይነታቸውን የዘነጉ)ተገልጋዩን፣ያለጉቦ አንገለግልም በማለት እያንገላቱት ነው።በቀበሌ ነዋሪነት፣መታወቂያ ሥም ሳይቀር እየዘረፉት እነደሆነ ታዛቢ ያወራል፡፡
     ታዛቢ ሲያወራ የመንግስት ጆሮ በመስማት እውነትን በረሱ መንገድ በማግኘት ፣ሳይዘገይ መፍትሄ መስጠት አለበት የምንልበት የመንግስት አወቃቀር ሥርዓት ላይ ገና አለደረስንም፡፡ዛሬ እና አሁን፣ የመንግስትን ሥልጣን የያዘው የለውጥ ኃይል ፣አንዚህን የህዝቡን ዳቦ፣እጁን እየጠመዘዙ የሚቀሙ፣ (ትንሾን ጣት ሳይቀር የሚቆሩጡ)ዘራፊዎችና ሌቦች ላይ ጨከን ያለ የህግ ቅጣት እንዲያገኙ የሚያደርግ ህግና የቁጥጥር ሥርአት ለመዘርጋት ፣ቀና ደፋ ማለቱን የሚሳዩ፣ተጨባጭ መንግስታዊ ሥራዎች መኖራቸውን ባንክድም ፣የቀደመው ታሪካችን ትርክት እንደ በጋ ጉም፣በአብይና በቲም ለማ ሃሳብ እንደ በጋ ጉም ታይቶ እብስ የሚል ባለመሆኑ፣ሁሉም ፖለቲከኛ ሰው ሆኖ መቆሙን በውል ሊገነዘብና፣ሰው ለሆነው ወገኑ በሞላ ከልቡ ለማገልገል ቅን፣በጎና፣በፍቅር የተሞላ ህሊና ሊኖረው ይገባል፡፡ይህ ካልሆነና 107 ፖርቲ ትርፍ ዳቦ ለማግበስብስ በሴራ የሚራኮት ከሆነ ነገራችን ሁሉ “የእምቦይ ካብ ” ሆኖ ይቀራል።
    ያለፈውን የጭቆና እና የብዝበዛ ሥርዓት ፣ሙሉ ለሙሉ በአዲስና በትወራ ብቻ ፣ሆዳችንን በማይነፋ፣በቅን ዜጎች የሚመራ እና ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው ሥርዓት ለመቀየርም፣ከአዲሱ የለውጥ ኃይል ጎን ከመሰለፍ ውጪ አማራጭ የለንም፡፡
       ያለፈው ሥርዓት፣ ሙሉ ለሙሉ እስታለተቀየረ ድረስና ‘የፓርቲና የመንግስት አሰራር መቀላቀሉ እስካለከተመ ድረስ” ፤ቀበሌ “በመዘጋጃ አገልግሎት “እሰካልተተካና ለሠላማዊ የሰልጣን ሽግግሩ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብ በጠቅላላ ተጠቃሚ ለሚያደርግ የዴሞክራሲ፣የሰላም እና የመቻቻል መድረክ፣ በራችን ክፍት እስካልሆነ ድረስ፣አሁን ከምናየው የከፋ ትርምስ በዚች ሀገር እንደሚከሰት መገመትም ከለውጥ ኃይሎች ጋር እንድንሰለፍ ያስገድደናል፡፡
      እንደምታውቁት፣ “ሴጣኑ ያለው በዝርዝሩ ውስጥ ነው፡፡ “ ከህዝብ ጋር ሁሌም የሚገናኝ የስልጣን መቀመጫ ወይም ወንበር ያለው እታች ነው፡፡ቀበሌ ነው፡፡የለውጥ ኃይሉ መቀመጫውን ከምስጦች ሳያፀዳ ፣ተደላድሎ መቀመጥ አይችልምና የኢትየጵያ መንግስት ልክ እንደአውሮፓና አሜሪካ የተደላደለ እንዲሆን እታች ያለው ህዝብ ከዳቦ ዘራፊዎች ነፃ መውጣት ይኖርበታል፡፡ለዚህም ላይ ያለው መንግስት  አዳዲስ የቁጥጥር ሢሥተም ለመፍጠርና ለመተግበር  ቁርጠኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
    ሁሉም ዜጋ ወዛደሩ፣ወታደሩ፣ገበሬው፣የመንግስት ሰራተኛው ፣ነጋዴው፣ተማሪው ፣አስተማሪው፣በተለያየ ሥራ የተሰማራ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ፣ከመሞቱ በፊት ፣ለትውልዱ የሚያስተላልፈው ሀብት ከሀገሩ  ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ማግኘት እንዲችል ፣የህግ ልእልና መታወቅ እና ህግ መከበር ይኖርበታል፡፡ይህንን ዕውቀት ማሥረፅ  እና መተግበር የሚቻለው ደግሞ፣ሰው ሁሉ በህሊናው እንዲገኝ የሚያደርግ ተከታታይ የሆነ በጥበብ የተሞላ እውቀት፣ሁሉም በሚገባው ቋንቋ እንዲያገኝ በማደረግ እና በድፍን ኢትዮጵያ ተዞዙሮ በመሥራት ሀብት የማፍራት መብቱ ሲረጋገጥለት ነው።
ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ ህሊና እና ሞራል ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ያስፈልጉናል።
   ለህዝብ ጥቅም መከበር እንታገላለን የሚሉ  በ107 የፖለቲካ ፖርቲ ውስጥ የምናስተውላቸው ፖለቲከኞችአሥቀድመው  “ያለምንም ሸፍጥ” እውነተኛ ተሐድሶ እና ንስሐ መግባት ይጠበቅባቸዋል።ይህን ካደረጉ ለማያባራ ዳቦ ሢሉ ተቧድነው የሙሰረቱትን የጎሣና  የዘር ፣ቋንቋን ማዕከል ያደሩገ አደረጃጀትን በመተው ለሀገሪቱ ዜጎች  እኩል  ጥቅም ሲሉ ፣ ተዋህደው ርእዮተ ዓለማዊ ፓርቲ  ማቋቋም ለትውልድ የሚጠቅም ታሪክ በወርቅ ቀለም የሚፅፈው አኩሪ ተግባር ነው። የዘመናዊው ዓለም ወቅታዊ የመንግሥት አደረጃጀትም  ይኸው  ነው።   “ሆድ ወይም ሞት !!!”ብለው ችክ ካሉም የማይበሉትን ሀብት ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንደሚያከማቹ ከወዲሁ ይወቁት።

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop