የሊቅ ዐቢይ አስቸጋሪ ምርጫ።የግል አስተያየት – ከ(ፕ/ር ኀይሌ ላሬቦ)

haile larebo
ፕ/ር ኀይሌ ላሬቦ

የሊቅ ዐቢይና የነለማ ቡድን ተብሎ የሚጠራውን አንጃ ደጋፊዎች፣ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምዱ የአንድነት ጐራ ናቸው ብል ስሕተት አይመስለኝም። የነለማ ቡድን ግን ሁሉም የኢሕአዴግ አባላት ናቸው። የዚህ ቡድን  ደጋፊዎች ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያዊነትና ኢሕአዴግ በመልካም እንተርጉም ካልን ሆድና ጀርባ፣ በመጥፎ እናስመስል ከተባለ ደግሞ እባብና ርግብ መሆናቸውን ነው። ምንም ብንመኝ፣ ሁለቱ በፍጹም አብረው ሊኖሩም ሊደመሩም አይችሉም። “መደመር” የሚለው የሊቅ ዐቢይ ፈሊጥ ለነዚህ ሁለቱ በፍጹም አይሠራም። ባንድ አልጋ እንኳን ቢተኙ፣ ሕልማቸው ተጻራሪ ነው። ኢትዮጵያዊነት ዘመን ተሻጋሪና ለማንም የማይበገር፣ ሌላውን ጐረቤቱንም ሆነ አካባቢውን እያሰፋና እያቀፈ የሚሄድ፣ እንከን የለሽ ስብጥርና ጒንጒን ማንነት ነው። ኢትዮጵያም ሆነ ኢትዮጵያዊነት የሚታወቁት በተፈጥሯቸው ማንንም አስተናጋጅና ዐቃፊ በመሆናቸው ነው። የኢትዮጵያዊነት ዐቃፊነት፣ ኢትዮጵያ ከተባለው ግዙፍ ምድር መጥቆ ወሰኑንና ድንበሩን ዐልፎ፣ ለሌላውም ዓለምና ሕዝብ ተትረፍርፏል። የዓለም፣ በተለይም ጭቁንና ጥቊር፣ ሕዝብ በምዕራባውያን መብቱ ተጨፍልቆ ይኖር በነበረበት ወቅት፣ የነፃነትና የእኩልነት ትግሉን ድምፅ፣ በያለበት ሲያክላላው፣ ሲያስተጋባው፣ ሲያክለውና ሲያንረው ቈይቶ፤ የኋላ ኋላ ግቡን ለመምታት የበቃው በኢትዮጵያዊነት ዙርያ በመሰለፍና በመሰባሰብ ነው።

ኢሕአዴግ በተቃራኒ በባሕርዩ ከፋፋይ፣ በልዩነት ላይ ያተኰረ፣ በጥላቻ መሠረት ላይ የተካበ፣ የጐጠኞችና የአገር ከሓጂዎች ጥርቅማጥርቅም ነው ማለት ይቻላል። ብዙዎች የሚሳሳቱት ኢሕአዴግን እንደፖለቲካ ድርጅት እያዩ ነው። ኢሕአዴግ የተፈጠረው የኢትዮጵያን ጥፋት ከኋላ ሁነው ይሸርቡ በነበሩት በውጭ ኀይሎች ሤራና ምክር ሲሆን፣ በእጁ ጠፍጥፎት ህልውና የሰጠው ግን፣ የታላቂቷ ትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ሕዝባዊ ሓርነት ወያኔ (ሕወአት) ነው። ሕወአት በኢትዮጵያ ጥንታዊነትና ታላቅነት አያምንም። ለሕወአት ከራሱ ዐልፎ ዓለምን ያደነቀው፣ የመላው ዓለም ጥቊርና ጭቁን ሕዝብ የሚኰራበት፣ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው፣ የ’አማራ’ ንጉሥ ብሎ ከሚጠራው ከአፄ ምኒልክ ዳግማዊ ነው። የቀረው የሰካራሞቹ፣ የባለምትሐቶቹና የባለአስማቶቹ ደብተሮች የፈጠራ ሐተታ ነው። ከስድስት ሺ ዓመታት በላይ ያስቈጠረውን፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ የርስበርስ መወላለድ፣ በአምቻና በጋብቻ መተሳሰር፣ በባህልና በሀብት መሰበጣጠር፣ በቋንቋና በሃይማኖት መወራረስ፣ ሕወአት አጥብቆ ይክዳል። በሕወአት ትርክት መሠረት፣ ኢትዮጵያ አንድ አማራ በተባለ ጨቋኝ ብሔረሰብ ወረራ የተቋቋመች፣ መቶ ዓመት የማይሞላ ታሪክ ያላት አገር ናት። በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያ፣ አማራው በሁሉም ዘርፍ የበላይነቱን ይዞ ይገዛት የነበረ፣ አማራ ያልሆነው ብሔረሰብ ግን፣ በግፍና በገፍ የሚማቅባት እስር ቤት ናት።የሕወአት ሕልምና ምኞት ይህችን ኢትዮጵያን  አፍርሶ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ በሌለበት መልኩ፣ በድርጅቱ አምሳል በአዲስ መልክ መገንባት ነው። ይኸንን ግብ ለመምታት የሕወአት ዋና ዓላማ ‘አማራን’ ማጥፋት ነው። በሠለጠነ ቋንቋ በመተርጐም ሕወአቶች ተልእኳቸውን በመሪያቸው ስም “የመለስ ራእይ” ይሉታል። የሕወኣት ከፍተኞች መሪዎቻቸው የድርጅታቸውን ዓላማ ለማሳካት እንዲያመችላቸው ሲሉ፣ የአማርኛ ተናጋሪውን ሰብኣዊነት ለመካድ በየጊዜው ተናገሩት ተብለው በየቦታው የሚጠቀሱትን ንግግሮች ከዚህ በታች አስቀምጫለሁ። ፍርዱንና ኂሱን ለአንባቢው ልተወውና ወደዋናው ጉዳይ ልለፍ።

ኢሕአዴግ፣ ሕወአት በራሱ ኀይል ብቻ ግቡን ለመምታት ስለሚሳነው፣ ድርጊቱን እግብር ለማዋል ታስቦ የተፈጠረ ግንባር ነው። በተሻለ አገላለጥ የሕወአት ሥራ አስፈጻሚ አካል ቢባል ይቀላል። ኢሕአዴግ በሕወአት ተሸንሽኖ በተሰጠው ክልል፣ አማርኛ ተናጋሪውን በቋንቋ መስፈርት ብቻ እየፈረጀ፣ “ነፍጠኛ”፣ “የምኒልክ ሰፋሪ”፣ “ጨቋኝ” ወይንም “የጨቋኝ መደብ” እያለ በማሳበብ፣ ልሕቅና ደቂቅ፣ ወንድና ሴት፣ ሕፃንና ሽማግሌ፣ ነፍሰጡርና አሮጊት ሳይለይ በጅምላ ልዩልዩ ስልትና መሣርያ በመጠቀም ሲገድል፣ ሲጨፈጭፍ፣ ሀብቱንና ንብረቱን ሲነጥቅ፣ ሲያፈናቅል ኑሯል። ልክ በአውሮጳ ከጀርመን ቊጥጥር ሥር የነበሩ ግዛቶች በናዚዎች የተዛባና የሐሰት ስብከት ተመርተው፣ በአይሁዶች ላይ የፈጸሙትን ግፍ፣ ኢሕአዴግም፣ በአማርኛ ተናጋሪው ሕዝብ ላይ ከዚያ የማይተናነስ ኢሰብኣዊ ጭካኔና የዘር ማጽዳት ተግባር እንደፈጸሙ መታወቅ ይገባል። ስለዚህ በሰብእናውም ሆነ በጠባዩ ኢሕአዴግ በአውሮጳ ከታየውና ዓለምን ለአሰቃቂ ከፍተኛ ዕልቂት ከዳረጉት ከመንታው ፋሽስትና ናዚ አይለይም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ...ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ ... !

ሕወኣት ለኢሕአዴግ አባልነት ከፈለፈላቸው ዋናውና ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱት አንዱ ትናንትና የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት [ኦሕዴድ] በመባል፣ ዛሬ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስም የሚጠራው ነው። ኦሕዴድ ኦሮሞኛ ተናጋሪ ብሔረሰብ ከቀረው የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ለዘመናት በመወላለድ፣ ባህልና ቋንቋ በመወራረስ፣ ድር ማጉ ኢትዮጵያዊ መሆኑንና፣ አብዛኛው አሁን ላለበት አካባቢ (አዲስ አበባን ጭምር) መጤና አዲስ ሰፋሪ መሆኑን የረሳ ይመስላል። ከደቡብ ከኬንያ ጠረፍ ተነሥቶ እስከመሃል ኢትዮጵያ ያለውን ሰፋፊ መሬት ይዞ የሚገኘው፣ ከፊቱ ያለውን እያጠፋ፣ እንደሀዲያ፣ ከምባታና ጉራጌ የመሳሰለውን ኀይለኛውን ብሔረሰብ ደግሞ አልፎት እየሄደ፣ ጸጥለጥ ብለው የገበሩለትን ብሔረሰቦች ግን ጉዲፈቻ፣ሞጋሳ [ሞገሳ]፣ ገበር የተባሉ ሥርዐቶቹን በመጠቀም፣ ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ደፍጥጦ፣ ሰብእናቸውን ጨፍልቆ፣ በኦሮሞነት እንዳጠመቃቸውና፣ በሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ይገዛቸው እንደነበረ ዘንግቷል ማለት ይቻላል። ኦሕዴድም (እንደሱም “የኦሮሞ ሕዝብ ወኪልና ነፃ አውጪ” ነኝ ብሎ ራሱን በራሱ የሾመው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ))፣ እወክላለሁ ያለው ሕዝብ ራሱ “የሉባ” ሰፋሪ ሁኖ እያለ፣ አማርኛ ተናጋሪውን፣ ሕግና ሥርዐት አስጠባቂውን (በዱር በገደል ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት የሞተውን ኦሮሞን ጭምር) “መጤ”፣ “ነፍጠኛ”፣ “የምኒልክ ሰፋሪ” እያለ በመብራት እየፈለገ፣ በጥይት እየረሽነ፣ ከነሕይወቱ እየቀበረ፣ ለዘመናት ከኖረበት ቤቱና አካባቢው እያፈናቀለ፣ ከፍተኛ ግፍና በደል እንደፈጸመ ይነገርለታል ብቻ ሳይሆን፣ ሁለቱም አሁንም ቢሆን በዚህ ተግባር እንደተሰማሩ ናቸው። ሊቅ ዐቢይ እንግዴህ የዚህ ግፈኛ ድርጅት ማለትም የኦዴፓ አባል ብቻ ሳይሆን ሊቀመንበሩም ነው። ግን ኢትዮጵያዊነትን፣ አንድነትንና ፍቅርን በመስበኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጫፍ እስከጫፍ በየሄደበት በሆሆታና በእልልታ ተቀብሎታል።

ይሁንና የሊቅ ዐቢይ ሥራ እስካሁን ድረስ ተከታዮቹንና ደጋፊዎቹን በቃላት ከማሞኘት ዘልሎ የሄደ መስሎ አይታየኝም። በቅርቡ በአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስብሰባ ሥነሥርዐት ላይ ባደረገው ንግግሩ፣ የኦዴፓ መሪዎች በለገጣፎና በአዲስአበባ ዙርያ፣ ጽንፈኞቹ ናቸው የተባሉት ደግሞ ወኪልና ደጋፊ አፍ ባጣው በጌዴዎ ሕዝብ ላይ፣ እየፈጸሙ ባሉት ግፍ፣ ጭፍጨፋና ፍንቀላ እስካሁን ድረስ አንዲትም ቃል ትንፍሽ አላለም። አንዱን ጐሣ በክልሌ መኖር  አይገባህም ብሎ ማጽዳት የኢሕአደግ መሠረታዊ እምነቱ ስለሆነ፣ ሊቅ ዐቢይ ለነዚህ ጉዳዮች ደንታም ያለው አይመስልም።

ሊቅ ዐቢይ ብዙ ደጋፊዎች እንዳሉት ይገባኛል። ለእኔ ግን አያያዙ ገና ከመጀመርያው አልጣመኝም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ካንድ መሪ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ለብዙ ጊዜ ስላልሰማና፣ ቃሉ በአንድ መሪ አፍ ተደጋግሞ ሲጠራ ማየቱ በጣም ስለጠማው፣ ሊቅ ዐቢይ በየጊዜው “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” ሲል በሚያስተጋባው ጩኸቱና ማር በተቀባ ንግግሩ የብዙዎቹን ዐይን እያሳወረ የሄደ ይመስለኛል። ይሁንና በኔ አስተያየት እስካሁን ድረስ አንድም መሠረታዊ የሆነ ለውጥ አላመጣም። ኢሕአዴግና ሕገመንግሥቱ እንዳሉ ናቸው። ይልቅስ ሊቅ ዐቢይ፣ ሕወአት ኀይል በመጠቀም እግብር ላይ ለማዋል ያልቻለውን የጐሣ የክልል ሥርዐት፣ ተቃዋሚውን በማፍዘዝና በማደንዘዝ እያጠናከረው ይገኛል ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በጥብቅ ሥር እያስያዘውም ይገኛል። ደጋፊዎቹ የረሱት ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያን ማሞገስ ከማንኛውም የአገር መሪ የሚጠበቅ መሆኑን ነው። እስረኞችንም መፍታት እንደትልቅ ነገር አድርጎ መቊጠሩ እጅግ የተሳሳተ አመለካከት እንደሆነ መታወቅ ይገባል። እስረኞቹ የፈጸሙት ምንም ዐይነት ወንጀል የለም። ይልቅስ ሰዎቹ ከመጀመርያውኑ መታሰር የማይገባቸው፣ የኢሕአዴግ የግፍና የጭካኔ ሰለባና መግለጫ ናቸው። የታሰሩትም ሊቅ ዐቢይ ራሱ አሁን የሚያሞግሳትን የኢትዮጵያን ስም ስለጠሩ፣ እየመራ ያለውን የኢሕአዴግን የጐሣ ፖለቲካ ስለተቹ ብቻ ነው። ሊቅ ዐቢይ ግን ደጋግሞ የኢትዮጵያን ስም ቢጠራም፣ አጠንክሮ እየደገፈና እያራመደ ያለው የጐሣን ፖለቲካ ነው።

ሊቅ ዐቢይ ተጨማሪ ጉዱ በየጊዜው ብልጣብልጥ/ሸዋጅ ለመሆን መሞከሩ ነው። የብዙዎቹን ብሔረሰቦች መፈናቀልና መገደል እስካሁን ድረስ በሕወአት እያሳበበ ቈይቷል። የራሱ ወገን ሲያደርግም በሕወኣት ተተናኩለው ነው እስከማለትም ደርሷል። በቅርቡ የለገጣፎን ሕዝብ ያፈናቀለችው እሱ ራሱ ሊቀ መንበር ሁኖ የሚመራው የራሱ ድርጅትና ወገንና ሹም ናት። ርግጠኛ አይደለሁም እንጂ ራሱ ወይንም አቶ ለማ የሾማት ሳትሆን አትቀርም ብዬ አምናለሁ። ሊቅ ዐቢይ ስለጉዳዩ ሲጠየቅ የሰጠው መልስ፣ ካንድ ዱርዬ/ሸዋጅ እንጂ፣ በፍጹም ከአንድ ጤናማ የአገር መሪ (ያውም ለኖቤል ሽልማት ይታጭ እየተባለ ካለ) አይጠበቅም። ይኸንን በተመለከተ፣ ከሁሉም ይበልጥ የገረመኝና ማመን ያቃተኝ ድርጊቱን አለማውገዙ ብቻ ሳይሆን፣ እንደአንድ አገር መሪ ለተፈናቀሉትም ሆነ ለአፈንቃዮቹ አንድም ነገር አለማለቱና ምንስ ዐይነት እርምጃ እየተወሰደ እንዳለ አለመናገሩ ነው። ሊቅ ዐቢይ ደጋግሞ የሚሰብክልን የመደመር ፖሊቲካ መሠረቱና ዐምዱ ፍትሕ፣ ነፃነትና እኩልነት መሆኑን የተረዳ አይመስልም። ከመንግሥት ፍቅር መጠበቅ ሞኝነት ነው። ፍትሕ፣ ነፃነትና እኩልነት ግን የመንግሥት ግዴታው ነው። እነሱ ከሌሉ መንግሥት የለምና።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “አይቴ ብሔሩ ለአማራ . . . የአማራ አገሩ ወዴት ነው?” ኢትዮጵያ አይደለምን?

የሊቅ ዐቢይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጨዋው በዚህ ብቻ አላበቃም። በየጊዜው የአገሩን ችግር እንዲቀርፉ ሲል የሚያቋቁማቸው ኮሚቴዎች፣ በሥራው እንዲያግዙት ሲል የመረጣቸው አጋሮቹ ሚኒስትሮች ግልጥ አድርገው ደጋግመው የሚያመለክቱት ሊቅ ዐቢይ ያከበረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ምን ያህል የሚያላግጥበት መሆኑን ነው ብዬ አምናለሁ። ሚኒስትሮቹን ብንመለከት፣ አጋሮቹ ሳይሆኑ ከእሺ ጌታዬ ከማለት ውጭ ሌላ ፋይዳ ያላቸው ሰዎች አይመስሉም። በየመስኩና በየአስተዳደሩ ዘርፍ ለሚታዩት ለአገሩ ችግሮች መፍትሔ እንዲያመጡ የሚመርጣቸውና የሚሾማቸው ሰዎች፣ ነፃና ገለልተኛ የሆኑ አይደሉም፤ በጉዳዩም ዕውቅና ያላቸውም ናቸው ማልት ያዳግታል። ይልቅስ ከመነሻው የችግሮቹ ጠንሳሾች፣ ፈጣሪዎችና አራማጆች ናቸው ማለቱ ይቀላል። ለይስሙላ፣ አለበለዚያም ለሽወዳና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ካልሆነ በስተቀር፣ ማንም ጤናማና ቅንነት ያለበት ሰው፣ አገሯ ያላት የከባድ ችግሮች መፍትሔ በምንም መልክ ከነዚህ ዐይነት ሰዎች ይመጣል ብሎ እንደማያስብና እንደማይጠባበቅ ርግጠኛ ነኝ። ይኸ ዐይነቱ ፍርዴና አስተያየቴ የሊቅ ዐቢይ አማካሪዎቹን ጭምር ይመለከታል። በቅርቡ ስለአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይ ላይ ለውይይት መነሻ ሲል ስሙን ሳይገልጽ ራሱን የጠቅላይ ሚኒስቴር የሕግ አማካሪ በማለት ለሊቅ ዐቢይ የሰጠው የኢትዮጵያ ታሪክ ግንዛቤው የሹሙን ዕውቀት የሚገልጥ ከሆነ፣ ሊቅ ዐቢይ ራሱን ያጀበው በጅሎችና በጥራዘነጠቆች መሆኑን ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በነእንደዚህ ዐይነቶቹ ሰዎችና አማካሪዎች የተከበበና የሚመከር ከሆነ፣ እሱም ጠፍቶ ኢትዮጵያንም ሊያጠፋ ይችላል የሚል ጥብቅ እምነት አሳድሮብኛል[1]

በሌላው በኩል ደግሞ ሊቅ ዐቢይን ብቻ መውቀሱ ሚዛናዊነት ያጣ ፍርደገምደልነት መስሎም ይታየኛል። የአንድነት ኀይል ነን ባዮች፣ ወይንም የጐሣ ሥርዐት ይደምሰስ የሚሉ ኀይሎች ርስበርስ ከመነታረክና ቁሞ ከመመልከት በዘለለ፣ የመደራጀት ፍላጐትም ጥረትም እስካሁን ለማሳየት አልቻሉም። “ኢትዮጵያ አትጠፋም፣ ለዘላለም ትኖራለች፣ ወይንም ትኑር” ከማለት አልፎ ያሳዩት ትብብርና ተጨባጭ ተግባር የለም። የሚጠብቁት ሊቅ ዐቢይ የጐሣንና የጐጥን ሥርዐት በተአምርም በዐዋጅም ቢሆን ገርስሶ፣ የአንድነትን መና ከሰማይ አውርዶ እንዲመግባቸው ነው፣። የትግል መንገዱንም ተአምራዊ በሆነ ኀይሉ ጠራርጎ እንዲያቀናላቸው እንጂ እንደጽንፈኞቹ አጠንክረው መታገልና በየቦታው የተበታተኑትን እንደአሸን የፈላ ደጋፊያቸውን ባንድጋ ማሰለፍ ግዴታቸው እንደሆነ የተገነዘቡ አይመስሉም። እነሱ ራሳቸው ባንድ አፍ ለመናገርም ሆነ፣ የጽንፈኞቹን ድርጊት አጠንክረው ለማውገዝ ሲሞክሩ አልታዩም። ለምሳሌ ሌላው ቀርቶ በአዲስ አበባ ያለው ሕዝብ እንኳን፣ ጥቅሙና ህልውናው በጽንፈኞቹ እየተነካና እየተጐዳ እያለ፣ ከተማዋ ብዙ የተማረና የነቃ ኀይል ቢኖራትም፣ በሷ ላይ የሚደረገውን ደባና የተሸረበውን የጥፋት ምዝበራ የሚቋቋምና የሚመክት ኀይል ለማደራጀት አልቻለም። ታዲያ ጽንፈኞቹ ቢያይሉበትና ፍላጎታቸውን ለማርካት ለስለስ ቢል፣ ሊቅ ዐቢይን ብቻ መውቀሱ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። ይበልጥ መወቀስ ያለበት ጡንቻው እያለው ሊቅ ዐቢይ ሲደበደብ፣ ጥቅሙና ህልውናው ሲደፈር ዝም ብሎ ተመልካቹ የከተማው ነዋሪ ነው ባይ ነኝ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምሕረት ሲሉ : ፍትሕ ስንል ለየቅል!!! - ከቴዎድሮስ ሃይሌ

ይኸ ማለት ግን፣ ሊቅ ዐቢይ አላፊነቱን ሊወጣ ካልቻለበት ምክንያቶች እንዳንዱ ሁኖ ሊታይም ሊቀርብም አይገባውም። በአገር ውስጥም ሆነ፣ ከአገር ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንም ሳይገፋው፣ በገዛ ፈቃዱ፣ በነቂስ ወጥቶ ‘የኢትዮጵያ ኔልሶን ማንዴላ” እስከማለት የዘመረለት፣ ድጋፉን አለአንዳች ማመንታት የለገሠለት፣ ቢያንስ ለግማሽ ዘመን በአገሪቷ ታይቶ ያልታወቀ መሪ አሰኝቶታል። በኢትዮጵያውያን ዘንድ ብቻ አይደለም ሊቅ ዐቢይ አድናቆቱን ያተረፈው። በአፍሪቃና በአብዛኛውም ዓለም እንጂ። በሱ መነሣት፣ ከግማሽ ዘመን በላይ ተዋርዶና ተሽቈልቁሎ የነበረው ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ ወደጥንታቸው ክብርና ማዕርግ ተመልሰዋል። ዓለም በሙሉ ተገርሟል። ኢትዮጵያዊ መሆን ቡራኬና ምርቃት መሆኑን ብዙዎች ተሰምቷቸዋል። ብዙዎቹም ሊቅ ዐቢይ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃም ትንሣኤ መሪ ነው እስከማለት ደርሰዋል።

ሊቅ ዐቢይ ግን ይኸንን አለአንዳች ልፋት ያገኘውን ሕዝባዊ አመኔታና ክብር፣ ሞገስና ልዕልና ጠቃሚ ነገር ለመሥራት እንደመጠቀም ፈንታ አንድ ዓመት እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በከንቱ አባከነው ማለት ይቻላል። ሁናቴውን ሳይጠብቅ በድንገት የአንድ ቢሊዮን ብር ሎተሪ ካሸነፈ፤ ኋላ ግን ምንም ሳይሠራበት በጥቂት ጊዜ ውስጥ እንዳባከነው ሰው ማምሰል ይቻላል። ዐቢይም ያደረገው ይኸንኑ ብል ስሕተት አይመስለኝም። ከተቀበለው ሕዝባዊ ደጋፍና አንጻር ስንመለከት፣ ሊቅ ዐቢይ እንኳን አገሩን ኢትዮጵያን ቀርቶ፣ በዙርያዋ ያሉትን ኤርትራንም፣ ጂቡትንም፣ ሱዳንና ሱማሌን ጭምር አጣምሮ አንድ አገር ለማድረግ ዕድል ነበረው ማለት ይቻላል። ግን እንደድንገተኛ ሎተሪ አሸናፊው፣ እሱም ዕድሉን ሳይጠቀመው እያባከነው ይገኛል ብቻ ሳይሆን በከንቱ አባክኖታልም። የዚህም ምልክት፣ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወቀሳና ስድብ ከየአቅጣጫው አድናቂው ከነበረው ሕዝብ ሲዘንብበትና ሲጐርፍበት ማየቱ ነው።

ለታላቅ ታሪክ የታጨ ሰው ሁኖ እያለ፣ ሊቅ ዐቢይ ተኰትኩቶ ካደገበት ከኢሕአዴግ የአስተሳሰብ ቁም ሣጥን ሊወጣ አልፈለግም። የኢሕአዴግን የጐሣና የተዛባ ርእዮተ ዓለም የሙጥኝ ብሎ የያዘና ከሱም ሊወጣ ያዳገተው ይመስላል። ከዚህም የተነሣ፣ ከወዲያ ማዶ ያለውን ሰፊውንና የደስ ደስ ያለበትን፣ ለምለሙንና ታላቁን አድማስ ለማየት አልታደለም። እንደገባኝ፣ የጐጥና የጐሣ ዓለም ራእዩን አሳውሮታል። ወይንም ተኰትኩቶ ያደገውም ሆነ፣ ተከቦና ተወጥሮ ያለው ይኸንን ርእዮተ ዓለም በሚያቀነቅኑ ኀይሎችና ሰዎች በመሆኑ፣ ዐልፏቸውም ሆነ ጥሏቸው ለመጓዝም ሆነ፣ አንድነት፣ ነፃነትና እኩልነት ከጠማው ከሚወደው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሁኖ ለመገሥገሥ ፍላጎትም፣ ጥረትም አላሳየም። “መንግሥተ ሰማይን ላላየ፣ ገሃነም ድንቁ ነው” ወይንም “ዐባይን ያላየ ምንጭ ያደንቃል” የሚለው አባባል በሊቅ ዐቢይ የተፈጸመ ይመስላል። ይኸም ሁኖ ግን ሊቅ ዐቢይ አዝማሚያውን ለመቀልበስ አሁንም ዕድሉ ሰፊ ነው ብል ስሕተት አይመስለኝም። ከፊቱ ያለው ምርጫ ግን ሁለት ብቻ ነው። ሁሉንም ዐቃፊ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ወይንም ርስበርስ ከፋፋይ ኢሕአዴግና ጐጥነት። መካከለኛ መንገድ ያለ አይመስለኝም። በመኻል ቁሞ ቢቀር በሁለቱም ሳይተፋ እንደማይቀር አያጠራጥርም።

[1] የሕግ አማካሪው የአዲስ አበባን ባለቤትነት በተመለከተ ለምን ታሪክ ላይ መመሥረት እንደማያስፈልግ ምክንያቱን ሲገልጥ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ብለን እስከዛሬ ስንጠቀምባቸው የነበረው የአንዳንድ ብሔሮችን ገድል ብቻ የሚዘክር እንጂ፣ አብዛኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ታሪክ፣ በተለይም የኦሮሞችን ታሪክ የማይወሳ በመሆኑ ይህንን አግላይታሪካዊ መረጃለክርክር መርቻ ዋቢ” አድርጎ ለማቅረብ እንደማያምንበት ይናገራል። አንባቢው እንዲረዳ ያህል ላሳስብ የምወደው፣ ከማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ይበልጥ በሰፊ የተጻፈለት ብሔረሰብ ቢኖር የኦሮሞ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የሁሉም አገር (የምዕራባውያን ጭምር) ታሪክ የተጻፈው ለገዢው ክፍል በገዢው ክፍል ስለገዢው ክፍል እንጂ የተራው ሕዝብ አይደለም። የኢትዮጵያም ታሪክ ከዚህ የተለየ አይደለም።

 

3 Comments

  1. ዶ/ር ላሬቦ፣ እንደሚገባኝ ከደቡብ ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የወጡ ምሁር እንደሆኑ ነው። ነገር ግን እንደአንድ ምሁር እና የታሪክ ተመራማሪ ለማንም ለምንም የማያዳላ፣ በማስረጃ የተደገፈ የታሪክ መዘክር ከማቅረብ ይልቅ፣ በሚያቀርቡት የጽሁፍም ሆነ የቃለመጠይቅ ሃትተታዎ ሽንጥዎን ገትረው ለአምሃራ እና ለአምሃራ ትርክት ጥብቅና መቆምን፣ በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ኦሮሞን በአዉሬነት አምሳል ለመሳል ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ። ይህ አካሄድ ከአንድ ምሁር ነኝ ከሚል ሰው በፍጹም እንደማይጠበቅ የሚስቱት አይመስለኝም። ሌላው ቢቀር እዚሁ ጽሁፍዎ ላይ ያቀረቡት ሃተታ፣ ከአንድ ተራ ካድሬ እንጂ ከአንድ ምሁር፣ ያዉም ከአንድ የታሪክ ተመራማሪ የሚጠበቅ አይደለም!!

    ለምሳሌ፣
    “በሕወአት ትርክት መሠረት፣ ኢትዮጵያ “አንድ አማራ በተባለ ጨቋኝ ብሔረሰብ ወረራ የተቋቋመች፣ መቶ ዓመት የማይሞላ ታሪክ ያላት አገር ናት።” ብለው ይከሳሉ። ነገር ግን ፖለትከኛ ካድሬነት ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት መልክ እንደአዲስ የተዋቀረችዉ በሚኒልክ ዘመን መሆኑን እንኳን እርስዎ፣ የአንደኛ ደረጃ ተማሪም አይስተዉም። ችግርዎ “አማራ” የሚለው ቃል ለምን ተጨመረበት ከሆነ ደግሞ የሚኒልክ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ከየትኛው ብሄረሰብ እና ባህል እንደነበረ እንደ ምሁር ብተነትኑልን መልካም ነበር።

    ሌላው፣
    “ኦሮሞኛ ተናጋሪ ብሔረሰብ … አብዛኛው አሁን ላለበት አካባቢ (አዲስ አበባን ጭምር) መጤና አዲስ ሰፋሪ መሆኑን”፣ “ከደቡብ ከኬንያ ጠረፍ ተነሥቶ … ከፊቱ ያለውን እያጠፋ፣ እንደሀዲያ፣ ከምባታና ጉራጌ የመሳሰለውን ኀይለኛውን ብሔረሰብ ደግሞ አልፎት እየሄደ፣ ጸጥለጥ ብለው የገበሩለትን ብሔረሰቦች ግን … ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ደፍጥጦ፣ ሰብእናቸውን ጨፍልቆ፣ …በሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ይገዛቸው እንደነበረ” ያትታሉ። እዚህ ላይ አንድ ሁለት ጥያቄዎች አሉኝ።

    አንደኛ፣ የኩሽ ዘሮች ዋነኛው ግንድ የሆነው የኦሮሞ ህዝብ አሁን ባለበት አካባቢ ነባር ህዝብ ላለመሆኑ ምን አስተማማኝ መረጃ አለዎት?

    ሁለተኛ፣ በፖቱጋሎች መድፍ የተደገፈውን የሃበሻ ነገስታትን የተደራጀ ጦር እና በቱርኮች ነፍጥ የታገዘውን የአዳል ሱልጣንን ጦር በአንድ ጊዜ የመከተው ኦሮሞ፣ እንደሀዲያ፣ ከምባታና ጉራጌ የመሳሰሉትን “ኀይለኛውን ብሔረሰብ” እንዴት ሊፈራ ቻለ? እነዚህ “ኀይለኛው ብሔረሰብ” ኦሮሞን የመከቱበት ዜዴ እና መሳሪያ ምን ነበር? ካልሆነስ፣ እንደሚባለው “የኦሮሞ ወረራ” ለከብቶቹ ግጦሽ ፍለጋ ብቻ ከሆነ፣ ለምለም የሆነውን የሀዲያ፣ የከምባታና የጉራጌ የመሳሰለውን ሃገር ትቶ ደረቁን የትግራይ ተራሮችን ለመቧጠጥ ምን አስከደው? የታሪክ ተመራማሪ ስለሆኑ እነዚህ ጥያቄዎችን አገላብጠዋል ብዬ ስለማስብ ነው።

    ሶስተኛ፣ ኦሮሞ “በሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ይገዛቸው” የነበሩ ህብረተሰቦች እነማን ናቸው? ጉዲፈቻ እና ሞጋሳ የሚባሉ “በኦሮሞነት ማጥመቂያ” አሰራሮች እንዴት እንደሚተገበሩ በጥልቀት ሊያብራሩኝ ይችላሉ?

    “የሕወአት ሕልምና ምኞት ይህችን ኢትዮጵያን አፍርሶ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ በሌለበት መልኩ፣ በአዲስ መልክ መገንባት ነው።” ብለውን ነበር። ታድያ እርስዎ ጨቋኝና ተጨቋኝ ያሉባትን ኢትዮጵያን ነው የሚመኙት፣ ወይስ ግንባታው በ”ሕወአት” ቢሆን ኖሮ ነው ሊዋጥልዎት ያልቻለው? ለርስዎ የታየዎትን “ሰፊውንና የደስ ደስ ያለበትን፣ ለምለሙንና ታላቁን አድማስ” የምናይበትን እና የምንደርስበትን መንገድ ለአቢይ ቢጠቁሙልን!

    ጥያቄ ስላበዛሁ እንደሌሎቹ የርስዎን ሊቀ ሊቃዉንትነት እንደተጠራጠሩት “ምሁር ተብዬዎች” በቁጣና ስድብ ሳይገርፉኝ ለጥያቄዬ አጥጋቢ እና ምሁራዊ ጥልቅ ትንታኔ እንደሚሰጡኝ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ!

    እኔ ምርምር ባልችልም፣ ከሌሎች መቅዳቱ ስለማያቅተኝ ይህችን የአይንስታይን ጥቅስ ጀባ ልበልዎት፣
    @መማር ማለት ያለዉን እዉነታ መሸምደድ ሳይሆን፣ ማሰብ እንዲችል ጭንቅላትን ማሰልጠን ነው@ ትርጉም ከኔ!
    “Education is not the learning of facts, but the training of the mind to think.” Albert Einstein

  2. This guy is kambata.
    He says Kambta survived Oromo expansion because kambata is strong…kkk!
    He conflates unworthiness with entitlement and peace with weakness!

    Is it true that this guy moved to the United States after he had been rejected by an Amhara in London?

    Anyways, the constant theme in his mouth (?) is animus towards his betters. He shares this with many of his brothers.

    What he fails to understand is that Oromo means brave! Oromo means love! Oromo means peace!

    Only the brave can love! Love brings peace! Peace begets brave people – the Oromo!
    Bravery, Love, and Peace are alien concepts to him. He feels at home spewing vulgarity. His speech fits his …
    One thing is for sure: he will fail in spreading prejudices and ignorance. His ranting is like a small budget comedy movie that turned out to be a tragic, costly failure. This is what Amhara and Oromo expect from the likes of this guy. Nothing more, nothing less. Kambata!
    The Amhara will never accept him as their peer. Why should they? To be fair, many Amharas get disgusted by excessive and incessant and irrational outbursts. They don’t want to be seen with this guy on Sunday mornings, i.e., during church service. The only time he is allowed to appear for a few minutes before them is late Sunday afternoon for a short radio program.
    I believe this guy is good for nothing but belittling Giants! He is also getting too old and ugly even for that project. Only a little guy says darn, nay, damn, nay vulgar things about Abiy. Abiy is in a different league than this guy. Hope Abiy doesn’t get to see this article because the country he envisions doesn’t not have a place for little minds who feel uncomfortable with clear ideas!
    I don’t want the Prime Minister to know that there a few individuals like this guy in Ethiopia as well. It is a pity but a hard reality.

Comments are closed.

Share