March 7, 2019
26 mins read

ጉልበት ዓልባ መሆን ብዙ ርቀት አያሥጉዝም ” – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

መንግሥት ጉልበት አልባ የመሆን ዕጣ ፈንታ የለውም።መንግሥት የሀገርን ሠላምና ፀጥታ ለማስፈንና ለማስከበር ሲል ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ መጠቀም ይንሮበታል።ይህንን መንግስታዊ  ግዴታውን ሲወጣ እግረ መንገዱን ወንጀል በመስራት ተጠቃሚ ለመሆን ያኮበኮቡትን በሙሉ ወንጀል መስራት የሚያስከፍላቸውን ዋጋ በተጨባጭ በማሳየት የወንጀል ድርጊት እንዳይስፋፋ ያደርጋል ።
 የአንድ ሀገር ህዝብም ፣ፍትህ ለሁሉም እኩል መሆኗን፣ህጉ አድርግና አታድርግ ብሎ ያስቀመጠው፣የደነገገውና ያወጀው፣በእያንዳንዱ ዜጋ የሚተገበር፣የተፃፈና ያልተፃፈ ህግ ና  እስከ ህልፈተ ህይወት የሚዘልቅ የዘወትር በህብረተሰቡ የታወቀ የሞራል መመሪያ social norm እንዳለ ፣ማወቅ የሚችለውም፣ መንግስት ህዝብ የሰጠውን  ህልፍና በአግባቡ ተወጥቶት ሲመለከት ነው።
 (ህዝብ የሚባሉው በተወሰኑ ግለሰቦች ቅስቀሳ ለሆዱ ተገዝቶ የማይጮኸውን ኩሩውን፣ በሚሊዮን የሚቆጠረውን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሙሉ እንደሆነ ይሰመርልኝ።)
      መንግሥት አንድ ዜጋ ወይም ሰው፣አብረውት፣የተፈጠሩና ከባህሪው የማይነጠሉ፣ወይም ሊነጠሉ የማይችሉ፣መብቶች እንዳሉት አሳምሮ ያውቃል።ከነዚህም መካከል ደስታን እና የደስታን ምንጭ እሥከህልፈተ ህይወቱ መሻት ነው።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ከዚህ መብቱ በተጎዳኝ የሌላን ዜጋ መብት ፣በቡድን ተደራጅቶም ሆነ በግለሰብ ደረጃ የማደፍረስ ይቅርና “ጫፉን የመንካት”መብት እንደሌለበትምለዜጎች ማሳወቅ የሚችሉው በህግ አግባብ ነው።
      ሰው፣በህይወት ሲኖር ፣ህይወቱን በደስታ የማኖር ተፈጥሯዊ መብት አለው ሥንል በመላው ኢትዮጵያ በጨረቃ ቤት እና በጎዳና ላይ የሚኖሩትንም ጭምር ሣንዘነጋ መሆኑን አሰምርበታለሁ።
      አለመታደል ሆኖ  በእኛ ሀገር ህይወትን በደስታ ለማኖር ያልቻልንበት ቀናቶች፣ወሮችና፣ዓመታት ይበዛሉ።የሰቋቃ ኑሯችንን ያባሰብን ዓመት ደግሞ የ27 ዓመቱ የኢሕአዴግ አገዛዝ ነው።
    ሰውን የምናይበት ፍልሥፍና ቋንቋዊ ከሆነበት ከግንቦት 20/1983 ዓ/ም ጀምሮ
(ግንቦት 20 ታስቦ መዋል አለበት እንጂ ተከብሮ ሥራ የማይሰራበት ቀን መሆን የለበትም።ባለማወቅ ሰበብ በአዋቂዎቹ ምዕራባዊያንኑ ና በአሜሪካኖች  ሥውር እገዛ እንዲሁም፣ በተለያዩ ግላዊ ምክንያቶች የወቅቱን የኢትዮጵያ መንግሥት ከሥልጣን መወገድ የሚፈልጉ የወቅቱ የጎረቤትና አንዳንድ የአረብ መንግሥታት መሪዎች ድጋፍ፣ወንድም ወንድሙን ገድሎ ሥልጣን ሥለያዘ ወይም ቀኝ እጅ ግራ እጅን በመቁረጡ እንዴት ልናከብረው እንችላለን?)
       አንድ ለአምስት በመጠርነፍ ፣ግለሰባዊ ነፃነታችን ተደምስሶ በቡድን ነፃነት ተተክቶ፣ እንደእንሥሣ በጠመጃቸው እያስፈራሩ ሲነዱን ኖረዋል።
    ጥቂቶቻችንንም፣ ሰው ለሆነው፣ለራሳችን የተለየ ምናልባትም የመልአክት መልክ ና ትርጉም እየሰጠን፣ቆዳችንን በማዋደድ ወደር በሌለው ግብዝነት እየተመፃደቅን ፣ እንድንኖር በፍርፋሪ ገዝተውናል።
    ብዙዎቻችንን ግን ፣እንደትናትናዎቹ ባለማወቅ አረንቋ ውስጥ እንደነበሩ ፊውዳሎች፣ጠጅ የመጠጣት መብት የእኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ጠጅ እቤትህ ተገኘ ?በማለት ነፍሳችንን እናስጨንቀዋታል።
   በእርግጥ ዛሬ ያ፣አስጨናቂው ኢሕአዴግ በመንግሥት ከፍተኛው ሥልጣን ላይ የለም። በየክልሎቹ ግን አለ።እኔ በበኩሌ ዶ/ር አብይ የከፈትቱት ቤት 27 ዓመት ሙሉ ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም፣ዛሬም ያ ቤት የሚከረፋው በሐጢያት የተጨማለቁ፣ሰዎችና ሰው፣ሰው የማይሸት አስተሳሰባቸው በተከፈተው ቤት ፣ማለትም በዛሬዋ ኢትዮጵያ በየክልሉ ሁሉ ሥላሉ ይመሥለኛል።
   ዛሬም፣ በሥውር የኢትዮጵያን እድገት ብልጽግናዋን የማይፈልጉ ፣ አንድ ወንድም በሌላው ወንድሙ ላይ ድንጋይ አንስቶ   “ቼበለው!”  እንዲል እያደረጉት ነው። …
    …………… እንሆ፣ጥላቻ፣በጥላቻ፣ጎሠኝነት፣በጎሠኝነት፣ትምክተኝነት፣በትምክተኝነት፣ጠባብነት በጠባብነት፣ዘረኝነት በዘረኝነት…ሆዳምነት በባሰ ሆዳምነት፣የጎሣ ነጋዴነት፣በባሰ ጎሣ ነጋዴነት፣ሥሥታምነት በባሠ ሥሥታምነት፣በሥልጣን መባለግ፣በባሠ የሥልጣን መባለግ …አውሬነት፣በባሠ አውሬነት፣ሰው መሆንን መርሳት፣ በባሠ ሰው መሆንን መርሳት…ቀስ፣በቀስ እየተተካ ነው።
     እውነት፣እውነት እላችኋለሁ፣የጠ/ሚር አብይ ፣በፍቅር፣ሥለፍቅር፣ሰው መሆንን ብቻ በማመን፣ የመደመር እና በአንድ ልብ የማሳብ  ፍልስፍና በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ በቅጡ አልሰረፀም።ምክንያቱም ጠፍሮ ከያዘን የወያኔ ዘራዊ እና ቋንቋዊ አስተሳሰብ ገና አልተላቀቅንምና ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ፣ የሚሊዮን ዓመታት የሰውን ጥንታዊ አፈጣጠር ማሳወቂያ አፅሞን በየክልሉ በማዞር፣  ሉሲ በአፀደ ነፍስ፣ ከነ ልጅ ልጆ በአካል ብትከሰት እንኳ ያ የዘረኝነት፣ያ ቆዳችን አንድ ሆኖ ሣለ ቆዳችንን የማዋደድ አስተሳሰብና የተንሸዋረረ አመለካከት በቀላሉ የሚለቀን አይመስለኝም።
     በዚህ ሥር የሰደደ ቆዳን የማዋደድ ፍልሥፍና፣ጦስ እና ጥንቡሳስ ሰውየው፣እንደሙሴ  ክፉኛ እየተቸገሩ ነው።ለአፍታ ዞር ሲሉ፣ከምታዩት የበለጠ ተአምር አሳያችኋለሁ  ባዩ(ልክ እንደምን ልታዘዝ ድራማ) ሺ ሆኖ ይጠብቃቸዋል።
     እውነት፣እውነት እላችኋለሁ፣ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) እንደ  መንግሥት ጠንካራ  በትረ ሥልጣን ” ሊኖራቸው ይገባል። በተዘጋ ቤት ውስጥ ያሉትን የበሰበሱ እና በሙስና በሽታ የተያዙትን ፣ጠራርገው፣የማሶገድ ብቃት እንዳላቸው ለጠላትም ለወዳጅም ማሳየት መንግሥታዊ ህልፍናቸው ነው።በዘላቂነት የህዙብን ሰላም ሉማስከበር ና  የሀገር ደህንነትን ለማረጋገጥ የህግ የበላይነት በተጨባጭ እንዲኖር የሚያሥችል አዲስ የአደረጃጀት ለውጥ በክልል ፖሊሶች ላይ ሊፈጥሩ ካልቻሉ፣እስካልፈጠሩ ጊዜ፣ ድረስ፣እንቅልፍን እንደገደሏት ይወቁ።
     ከ65 አመት በላይ ፣የሆናቸውና ዛሬም ከመቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በነበሩ መጥፎ ትዝታዎች ወጣቶን ሙሾ አውራጅ ሆነው የሚያስለቅሱትን ና ትውልዱ ባልሰራው ሐጥያት ተጠያቂ እንዲሆን በብሉይ ህግ ለመዳኘት እየቃጡ ያሉትን ከድርጊታቸው ማስቆም ታሪክ የጣለብዋ ኃላፊነት ነው። ዜጋ ሁሉ፣ በጎውን የኢትዮጵያ ታሪክ ፣በየደረጃው እንዲማር   ማደረግ ፣ለነገ የማያሳድሩት የቤት ሥራዎት ይመስለኛል። …..
   ከቆዳ ማዋደድ ያልዘለለ አስተሳሰብ ያላቸውን ተማሪዎች የሰው ልጅ፣ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ አመጣጡን ፣ከእምነት፣ከሣይንሥ እና ከፍልስፍና አንፃር ማሳወቅ ተገቢ ነው።ለምን ቢባል ፣ ስልቻ እና ቀንቀሎ ልዩነት እንደሌለው ካላወቀ ፣ሥለዜግነት በውል ሥለማይገነዘብ ፣አሁን በእኛ ሀገር ከሚታየው ኋላቀር እና የሆዳሞች ፖለቲካ ከቶም አይላቀቅምና።
         ሙሴ  ህዝቡን ከዚህ የፈጣሪ ሃይል እና ከሰው ሰራሹ ጣኦት አንዱን ምረጡ ብሎ፣ህዝቡን ከለየ  በኋላ የወረወረው የእግዛብሔርን ቃል የያዘው ፅላት፣ በጣኦቱእና በተከታዮቹ ላይ ያደረሰውን ታላቅ መቅሰፍት ህዝቡ አይቶ፣ ባለማወቅ የተነሰ ለጣኦቱ ይሰግድ የነበረው ሥህተቱን ከመቅሥፈት ተገነዘበ። በክስተቱ ወደ ልቦናው ተመለሰ።ጥፋቱንም በውል ተረዳ።…የኢትዮጵያ መንግሥትም ፣እውነትን በዚህ ዓይነት መንገድ ለማሳወቅ መቻል ይኖርበታል። በዚህ ዓይነት የመንግሥትን የህዝብና የሀገር አሌንታነት ማረጋገጥ ካልቻለ፣በኢትዮጵያ ላይ ያንዣንበበውን በሆዳዊነት፣በድሎታዊነት እና በስስታማዊነት እጅግ የተደራጀ አሥፈሪውን ሞት ያረገዘ  የዕልቂት ደመና ማስቆም ከቱም እንደማይችል ከወዲሁ  መገመት ነብይ አያሰኝም።
        ደግሞም ማኬቬሊ እንዳለው፣” ጉልበተኝነትን እና ሕጋዊነትን በውል ዳር ድንበራቸውን መገንዘብ እንጂ፣ጉልበት አልባ መሆን አያዋጣም።”
በምንድነው፣አሜሪካ ኃያል የተባለችው? መልሱ ከባድ አይደለም።በአሜሪካ በህግ ቀልድ የለም።ህግን ለማስከበር የሚችሉ፣ፖሊሶች፣አቃቢ ህጎች፣ፍርድ ቤቶች እንዲሁም፣በብር አፋቸውን መዝጋት የማይፈልጉ ጋዜጠኞች ሥላሉ ነው።
    በዚህ በቴክኖሎጂ እጅግ በዘመነ ዓለም ውስጥ ፣ህግን ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ ይልቅ የዘመነ ፣የመከላከያ እና የፖሊሥ ኃይል ያስፈልገናል።ጉልበት አልባ መሆን ብዙ ርቀት አያዝጉዘንም።
የለውም።መንግሥት የሀገርን ሠላምና ፀጥታ ለማስፈንና ለማስከበር ሲል ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ መጠቀም፣እግረ መንገዱንም ወንጀል በመስራት ተጠቃሚ ለመሆን ያኮበኮቡትን በሙሉ ወንጀል መስራት የሚያስከፍላቸውን ዋጋ በተጨባጭ ማሳየት የመንግሥት ግዴታ ነው።
የአንድ ሀገር ህዝብም ፣ፍትህ ለሁሉም እኩል መሆኖን፣ህግ አድርግና አታድርግ ብሎ ያስቀመጠው፣በያንዳንዱ ዜጋ የሚተገበር፣የተፃፈና ያልተፃፈ እስከ ህልፈተ ህይወት የሚዘልቅ መመሪያ እንዳለ ማወቅ ይኖርበታል።
      አንድ ዜጋ ወይም ሰው፣አብረውት፣የተፈጠሩና ከባህሪው የማይነጠሉ፣ወይም ሊነጠሉ የማይችሉ፣መብቶች አሉት።ከነዚህም መካከል ደስታን እና የደስታን ምንጭ እሥከህልፈተ ህይወቱ መሻት ነው።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ከዚህ መብቱ በተጎዳኝ የሌላን ዜጋ መብት ፣በቡድን ተደራጅቶም ሆነ በግለሰብ ደረጃ የማደፍረስ ይቅርና “ጫፉን የመንካት”መብት የለውም።
      ሰው፣በህይወት ሲኖር ፣ህይወቱን በደስታ የማኖር ተፈጥሯዊ መብት አለው ሥንል በመላው ኢትዮጵያ በጨረቃ ቤት እና በጎዳና ላይ የሚኖሩትንም ጭምር ሣንዘነጋ መሆኑን አሰምርበታለው።
      አለመታደል ሆኖ  በእኛ ሀገር ህይወትን በደስታ ለማኖር ያልቻልንበት ቀናቶች፣ወሮችና፣ዓመታት ይበዛሉ።የሰቋቃ ኑሯችንን ያባሰብን ዓመት ደግሞ የ27 ዓመቱ የኢሕአዴግ አገዛዝ ነው።
    ሰውን የምናይበት ፍልሥፍና ቋንቋዊ ከሆነበት ከግንቦት 20/1983 ዓ/ም ጀምሮ
(ግንቦት 20 ታስቦ መዋል አለበት እንጂ ተከብሮ ሥራ የማይሰራበት ቀን መሆን የለበትም።ባለማወቅ ሰበብ በአዋቂዎቹ ምዕራባዊያንኑ ና በአሜሪካኖች  ሥውር እገዛ እንዲሁም፣ በተለያዩ ግላዊ ምክንያቶች የወቅቱን የኢትዮጵያ መንግሥት ከሥልጣን መወገድ የሚፈልጉ የወቅቱ የጎረቤትና አንዳንድ የአረብ መንግሥታት መሪዎች ድጋፍ፣ወንድም ወንድሙን ገድሎ ሥልጣን ሥለያዘ ወይም ቀኝ እጅ ግራ እጅን በመቁረጡ እንዴት ልናከብረው እንችላለን?)
       አንድ ለአምስት በመጠፈር፣ግለሰባዊ ነፃነታችን ተደምስሶ በቡድን ነፃነት ተተክቶ እንደእንሣ በጠመጃቸው እያስፈራሩ ሲነዱን ኖረዋል። ሁላችንም ሰው ለሆነው፣ለራሳችን የተለያየ ትርጉም እየሰጠን፣ቆዳችንን በማዋደድ ወደር በሌለው ግብዝነት እየተመፃደቅን እንድንኖርም እንደእስሳ በሆድ ገዝተውናል።
    (እንደትናትናዎቹ ባለማወቅ አረንቋ ውስጥ እንደነበሩ ፊውዳሎች፣ጠጅ የመጠጣት መብት የእኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ጠጅ እቤትህ ተገኘ ?በማለት ነፍሳችንን እናስጨንቀዋታል።)
   በእርግጥ ዛሬ ያ፣አስጨናቂው ኢሕአዴግበመንግሥት ከፍተኛው ሥልጣን ላይ የለም። በየክልሎቹ ግን አለ።እኔ በበኩሌ ዶ/ር አብይ የከፈትቱት ቤት 27 ዓመት ሙሉ ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም፣ዛሬም ያ ቤት የሚከረፋው በሐጢያት የተጨማለቁ፣ሰዎችና ሰው፣ሰው የማይሸት አስተሳሰባቸው በተከፈተው ቤትማለትም በዛሬዋ ኢትዮጵያ በየክልሉ በመኖራቸው ነው።
   ዛሬም፣ በሥውር የኢትዮጵያን እድገት  የማይፈልጉ አንድ ወንድም በሌላው ወንድሙ ላይ ድንጋይ አንስቶ   “ቼበለው!”  እንዲል እያደረጉት ነው።        እንሆ፣ጥላቻ፣በጥላቻ፣ጎሠኝነት፣በጎሠኝነት፣ትምክተኝነት፣በትምክተኝነት፣ጠባብነት በጠባብነት፣ዘረኝነት በዘረኝነት…ሆዳምነት በባሰ ሆዳምነት፣የጎሣ ነጋዴነት፣በጎሣ ነጋዴነት፣ሥሥታምነት በባሠ ሥሥታምነት፣በሥልጣን መባለግ፣በባሠ የሥልጣን መባለግ …አውሬነት፣በባሠ አውሬነት፣ሰው መሆንን መርሳት፣ በባሠ ሰው መሆንን መርሳት…ቀስ፣በቀስ እየተተካ ነው።
     እውነት፣እውነት እላችኋለሁ፣የጠ/ሚር አብይ ፣በፍቅር፣ሥለፍቅር፣ሰው መሆንን ብቻ በማመን፣ የመደመር እና በአንድ ልብ የማሰብ  ፍልስፍና በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ በቅጡ አልሰረፀም።ምክንያቱም ጠፍሮ ከያዘን የወያኔ ዘራዊ እና ቋንቋዊ አስተሳሰብ ገና አልተላቀቅንምና ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ፣ የሚሊዮን ዓመታት የሰውን ጥንታዊ አፈጣጠር ማሳወቂያ አፅሞን በየክልሉ በማዞር፣  ሉሲ በአፀደ ነፍስ፣ ከነ ልጅ ልጆ በአካል ብትከሰት እንኳ ያ የዘረኝነት፣ያ ቆዳችን አንድ ሆኖ ሣለ ቆዳችንን የማዋደድ አስተሳሰብና የተንሸዋረረ አመለካከት በቀላሉ የሚለቀን አይመስለኝም።
     በዚህ ሥር የሰደደ ቆዳን የማዋደድ ፍልሥፍና፣ጦስ እና ጥንቡሳስ ሰውየው፣እንደሙሴ  ክፉኛ እየተቸገሩ ነው።ለአፍታ ዞር ሲሉ፣ከምታዩት የበለጠ ተአምር አሳያችኋለሁ  ባዩ(ልክ እንደምን ልታዘዝ ድራማ) ሺ ሆኖ ይጠብቃቸዋል።
     እውነት፣እውነት እላችኋለሁ፣ጠ/ሚ አብይ አህመድ (ዶ/ር) እንደ  መንግሥት ጠንካራ  በትር ሥልጣን ” ሊኖራቸው እና በተዘጋ ቤት ውስጥ ያሉትን የበሰበሱ እና በሙስና በሽታ የተያዙትን ፣ጠራርገው፣የማሶገድ ብቃት እንዳላቸው ሊያሳዩን እና የህግ የበላይነት በተጨባጭ እንዲኖር የሚያሥችል አዲስ የአደረጃጀት ለውጥ በክልል ፖሊሶች ላይ እስካልፈጠሩ ጊዜ፣ ድረስ፣ለደቂቃ ልተኛ ካሉ የማይቀለበስ አደጋ ያገጥማቸዋል ብዬ እሰጋለሁ።
    (ይህ ወጣት ትውልድ ከ65 አመት በላይ ፣የሆናቸውና ዛሬም ከመቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በነበሩ መጥፎ ትዝታዎች መነዳቱን እንዲያቆም በጎውን የኢትዮጵያ ታሪክ ፣በየደረጃው እንዲማር   ማደረግ ፣ለነገ የማያሳድሩት የቤት ሥራዎት ነው።ከቆዳ ማዋደድ የዘለለ አስተሳሰብ ያላቸውን ተማሪዎች የሰው ልጅ፣ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ አመጣጡን ፣ከእምነት፣ከሣይንሥ እና ከፍልስፍና አንፃር ማሳወቅ ተገቢነው።ለምን ቢባል ስልቻ እና ቀንቀሎ ልዩነት እንደሌለው ካላወቀ ፣ሥለዜግነት በውል ሥለማይገነዘብ ፣አሁን በእኛ ሀገር ከሚታየው ኋላቀር እና የሆዳሞች ፖለቲካ ከቶም አይላቀቅምና።)
         ሙሴ  ህዝቡን ከዚህ የፈጣሪ ሃይል እና ከሰው ሰራሹ ጣኦት አንዱን ምረጡ ብሎ፣ከለያቸው በኋላ የወረወረው የእግዛብሔርን ቃል የያዘው ፅላት፣ በጣኦቱእና በተከታዮቹ ላይ ያደረሰውን ታላቅ መቅሰፍት ህዝቡ አየ። ባለማወቅ የተነሰ ለጣኦቱ ይሰግድ የነበረው ሥህተቱን ተገነዘበ። በክስተቱ ወደ ልቦናው ተመለሰ።ጥፋቱንም በውል ተረዳ።…የኢትዮጵያ መንግሥትም ፣እውነትን በዚህ ዓይነት መንገድ ለማሳወቅ መቻል ይኖርበታል። በዚህ ዓይነት የመንግሥትን የህዝብና የሀገር አሌንታነት ማረጋገጥ ካልቻለ፣በኢትዮጵያ ላይ ያንዣንበበውን በሆዳዊነት፣በድሎታዊነት እና በስስታማዊነት የተጠናከረ የዕልቂት ደመና ማስቆም ከቱም እንደማይችል ከወዲሁ  መገመት ነብይ አያሰኝም።
        ደግሞም ማኬቬሊ እንዳለው፣” ጉልበተኝነትን እና ሕጋዊነትን በውል ዳር ድንበራቸውን መገንዘብ እንጂ፣ጉልበት አልባ መሆን አያዋጣም።”
በምንድነው፣አሜሪካ ኃያል የተባለችው? መልሱ ከባድ አይደለም።በአሜሪካ በህግ ቀልድ የለም።ህግን ለማስከበር የሚችሉ፣ፖሊሶች፣አቃቢ ህጎች፣ፍርድ ቤቶች እንዲሁም፣በብር አፋቸውን መዝጋት የማይፈልጉ ጋዜጠኞች ሥላሉ ነው።
    በዚህ በቴክኖሎጂ እጅግ በዘመነ ዓለም ውስጥ ፣ህግን ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ ይልቅ የዘመነ ፣የመከላከያ እና የፖሊሥ ኃይል ያስፈልገናል።ጉልበት አልባ መሆን ብዙ ርቀት አያዝጉዘንም።

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop