በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው የአማራ ክልል ልዑክ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ሲገባ አቀባበል ተደረገለት::
https://www.youtube.com/watch?v=g7iJChbkX6U
ለአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ ል ዕልና በአንድነት እንሥራ በሚል ይህ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው ልዑክ በዛሬው ዕለት በዚያው በዋሽንግተን ዲሲ ህዝባዊ ስሰብሰባ ያካሂዳል:: አቶ ገዱ ስለጉዞው ዓላማ ሲናገሩ “የጉዞው ዓላማ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአማራ ልማት ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል ነው፡፡ ለውጡን ተከትሎ በክልሉ መንግስት አቋም ላይ በመወያየት በቀጣይ ስራዎች ላይ አብሮ ለመስራት ያለውን መልካም አጋጣሚ ማሳወቅም ሌላው ዓላማ ነው፡፡” ብለዋል::
“ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ያላቸውን አንድነት በማጠናከር ታላቅነትን በጋራ የማስቀጠል ስራም ከውይይቱ ዓላማዎች መካከል ነው” ያሉት አቶ ገዱ ይዘውት የመጡት ልዑክ በሰሜን አሜሪካ በሚኖረው ቆይታ በተለያዩ ግዛቶች የአማራ ልማት ይመለከተናል ከሚሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ይመክራል ብለዋል::
ይህ ልዑክ ዋሽንግተን ዲሲ ደለስ ኤርፖርት ዛሬ ሲደርስ ባልተለመደ ሁኔታ በሕዝቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: ታዋቂ አርቲስቶች እና የተለያዩ ግለሰቦች በአቀባበሉ ላይ ተገኝተዋል:: ከዚህ ቀደም ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ ሲመጡ እንኳን አቀባበል ሊደረግላቸው ይቅርና ተደብቀቅ መጥተው ተደብቀው እንደሚሄዱ ይታወቃ;ል::