ኦነግ  (OLF) በአስቸኳይ ትጥቅ ይፍታ!! – ከሙሉቀን ገበየሁ

ከ 27  አመታት  መራራ ሰላማዊ የኢትዮጲያ ህዝብ ትግል ቦኋላ የትግሉ መንፈስ በ ኢሕአዲግ (EPRDF)  ተብሎ በሚጠራው ግንባር ውስጥ ሰንጥቆ ገብቶ   በተለይም በቀድሞ ስሙ  ኦህዴድ (OPDO) እና      ብአዴን (ANDM)   አመራር አባላቶች ትግሉን ተቀላቅለው ለውጡን እውን በማድርጋቸው ባለፉት 6 ወራት በአገራችን የሚታየውን የዲሞክራሳዊ መንገድ ጅምር ለማየት ደርሰናል።

 

በዶ/ር አብይ አሕምድና በተለምዶ “Team Lemma”  የሚባሉት አመራሮች ባሳዩት ቆራጥ ኢትዮጲያዊንትን ባጎላ   አመራር  አገራችን ተስፋ ያለባት አገር እንድትሆን አድርጓታል።  ባልፉት ወራት የተደርጉት ዲሞክራሲያዊ እርምጃዎች ፍጥንትና የተገኙት ውጤቶች ብዞዎቻችንን ያስግርመ ነው።  ይህ የሚያበርታታ  እርምጃ በፅኑ የሚደግፍ ነው።

 

ከተደርጉት መልካም እርምጃዎች አንዱ ነፍጥ/መሳርያ  አንስተው የትጥቅ ትግል የሚያድርጉትና በመንግስት በሽብርትኛንት ተሰይመው  የነበሩ የፖልቲካ ሃይሎችን በሰላማዊ መንገድ ሃገራቸው ገብተው እንዲታገሉ መድርጉ ነው።  በይበልጥ የሚታወቁት ኦነግ (OLF)፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት (AG7) ፣  ኦነሌፍ (ONLF)   እንዲሁም ሌሎችንም ይጨምራል። አብዛኛዎቹ  በይፋ ጥሪውን ተቀብለናል ብለው፤  ይፋ ባልሆነ ስምምነት ከመንግስት ጋ አድርገው ወደ ሃገር ውስጥ በሰልፍና በደስታ ገብተዋል። የኢትዮጲያ ህዝብም የድርጅቶቹ ደጋፊዎች እንኳን ድህና መጣችሁ ብሎ በአደባባይ ተቀብሎቸዋል።

 

ዋና መሰርታዊ ጉዳይ በሰላሚዊ መንገድ ትግል እናደርጋልን ማለታቸው  ሲሆን ወደ አገር ውስጥ የገቡት የታጠቁትን መሳርያ አስርክበው ወይም ከጥቅም ውጪ አደርገው ፣ ሰራዊታቸውንም ወደ ሲቭልነት ለመቀየር ወታደራዊ ካንፕ አስግብተው እንደሚሆን ይጠበቃል።  ይህ ካልሆነ ግን ትልቅ ስህተት፣ጥፋት እንዲሁም ይህንን የፈቀዱ ወይም የተስማሙ  የመንግስት ባለስልጣኖች የክህደት ተግባር ፈጽመዋል ማለት ነው። እውቅና ካለው የሃገሪቱ መንግስት ውጪ ማንም የፖለቲካ ፓርቲ ትጥቅ ከያዘ  ሰላማዊ ትግሉን በመተው በመሳርያ ሃይል አላማውን ከማሳካት ውጪ ሌላ የሚያደርገው ተግባር አይኖርም።

ተጨማሪ ያንብቡ:   ህይወት እደዋዛ - ቤተልሄም ጌታቸው

 

የኢትዮጲያ ህዝብ ለ 27  አምታት ያደርገው ሰላምዊ ትግልና መሰአውትነት በሌሎች መሳርያ በታጠቁ ሃይሎች ሊነጠቅ በፍፁም አይገባም።  በተለይም የተወሰነ ህዝብና   ወገን ታሪካዊ ጠላቴ ነው ብሎ የተነሳ  የፖለቲካ ሃይል ትጥቅ ይዞ ከተጠያቂንት ውጪ ያሰማረችውን ነፍጥ ያነግቡ ሰራዊቱ በህዝቡ ውስጥ መግባታቸው በጣም አሳሳቢ ነገር ነው። ታጣቂዎቹ መሳርያ አስረክበው በወታደራዊ ካንፕ  መቀምጥ ሲኖርባችው ይህ ሳይደርግ ከሆነ እጅግ አስጊና ባስቸኩይ ሊስተካከል የሚገባው ነው። ይህንንም የፈቀዱ ሰውች እንዲሁም ይህ እንዳይደርግ ስምምንት ተድርጎ ከሆነም ስምምንቱን ያፈርሰው አካል በአስቸኳይ ሀገር በመክዳት ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል።

 

ሪፖርት ጋዜጣ በ 3rd October   በዘገባው ዜና  መሰረት  የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አሁንም አስታጥቆ እያንቀሳቀሰ ያለውን ጦሩን ትጥቅ እንዲያስፈታ፣ ወታደሮቹንም በአስቸኳይ መንግሥት ወዳዘጋጀው ካምፕ እንዲያስገባ ተጠየቀ፡፡የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥት የገጠርና ፖለቲካ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፣ በግል የማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ እንዳሠፈሩት  የኦሮሞ ነጽነት ግንባር ከዚህ ቀደም የተደረሰውን ስምምነት አክብሮ መንቀሳቀስ አለበት ብሎል። የኦነግ አመራር የሆኑት አቶ ቶሌራ አደባ በበኩላቸው፣ አሁንም ትጥቃቸውን ያልፈቱ የኦነግ ወታደሮች እንዳሉ አምነዋል፡ https://www.ethiopianreporter.com/article/13211

 

 

ከመንግስት ውጪ  መሳርያ የታጠቀ ሃይል ተጠያቂነት ስለሌለበት የፈለገውን ሊያድርግ ይችላል። ሊመስርት የተደከመበትን ዲሞክራሲያዊ ስርአት ገና ከጅምሩ ያደርቀዋል፣ ያጠፋዋል። ሰዎች በሰላማዊ መንግድ በሃስብ የሚደርጉትን ትግል  በመሳርያ ሃይል በማስፍራራት የራሱን አላማ ለማስፈጸመያ ያደርገውል። ጠላቴ ነው የሚለውን ሃይል ከመግደልና ከማጥፋት አይመልስም። ወደፊት የሚደርገውን ምርጫ መሳርያ ያነግበው ሃይል በፈለገው መስረት ህዝቡን ከማስገደደ አይታቀብም።   በአገር ውስጥ የርስ በርስ ጦረነት ውስጥ ሊከትንም ይችላል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግንጥል ጌጥ በማንም አያምርም - ይነጋል በላቸው

 

የኦሮሞ ነፃንት ግንባር  (OLF) ትጥቅ ሳይፍታ ከነሰራዊቱ ህዝብ ውስጥ መግባቱ እጅግ አሳሳቢ ነው። ኦነግ (OLF)   ያለው አማራጭ አንድ ነው። በሰላማዊ መንግድ ትግሉን ለመቀጠል፡ ትጥቁን ባስችኩይ መፍታት፣ ሰራዊቱንም  ወደ ወታድሪዊ ካንፕ ገብተው  የሰላማዊ ኑሮ ተሃድሶ ትምህርት ስልጥና ቀሰመው ወደ ህዝቡ  እንዲቀላቀሉ ማድርግ።   ከለበልዚያ ከሽብርትኛንት ከሚለው ስያሜና ድርጊት ውጪ አይሆንም።

 

ኦነግን (OLF) ወደ አገር ቤት እንዲገባ ለማግባባት ወደ አስመራ የሄዱ የመንግስት አካላት፣ አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ  በዛ ወቅት የተስማሙበትን ና የተፈራርሙትን ስምምንቶች በይፋ ለህዝብ ባስቸኳይ መገለጽ አለበት። የለውጡ ዋና ሞተር ተብለው የሚቆጠሩት አቶ ለማ መገርሳ  ኦነግ (OLF)  ጥትቁን ሳይፈታና ሰራዊቱን ካንፕ ሳይግባ አገር ቤት ህዝቡ ጋ እንዲገባ  ታላቅ ስህተት ይፍጽማሉ ተብሎ አይጥበቅም። ሆኖም ግን ባስቸኳይ ስምምንቱና ከነፊርማው  በይፋ ለህዝብ መገልጽ አለበት ።

 

ዋናው ጉዳይ ግን ኦነግም (OLF)  ሆነ ሌሎችም  ነፍጥ አንስተው የነበሩ  ውይም ያሉ ማንኛውም  የፖለቲካ ሃይሎች ሁሉ ባስቸኳይ ትጥቅ  ፈተው ሰራዊታቸውን ወደ ካንፕ ማስግባት አለባቸው። በአገራችን የተለያዩ ክፍል ለሚታየው ግድያና ብጥብጥ መሳርያ ያነግቡ ሃይሎች አስተዋጾ ትልቅ ነው።

 

የመንግስት መሰረታዊ ዋና ተግባሩ ህግ ና ስርአት ማስከብሩ ስልሆነ፡ የኢትዮጲያ መንግስት ይህ ጉዳይን ባስቸኳይ ስር ሳይሰድ መፍቴ መስጠት አለበት። የኢትዮጲያ ህዝብም በተለይም ወጣቱ ይህን  አገራችን ላይ ያገኘነውን ዲሞክራሲያዊ ስርአት መገንቢያ  ጅምር እድል በፍፁም እንድዳያመልጠን ፅኑ ትግል ያስፈልጋል።

 

የኢትዮጲያ ልጆች ሁሉ በሰላምና በፍቅር መሰርታዊ የግልና የወል መብታቸው የተከበርበት፣ በህግ ፊት ሁሉም እኩል የሆኑበትን፤ ሁሉም ዜጋ ለ ትምህርት፣ ስራ፣ ሃብት ለማፍርት እክሉ እድል ያልበት፤ ደሃ የማይበደልበት፤ ስልጣን በህዝብ ድምፅ ብቻ የሚያዝበት አገር ና ስርአትን  ለመመሥርት እጅጉን እንድስራ አግዚሃቤርም ይርዳን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጥንብ ባለበት  ጂብ አይጠፋም  

 

 

 

 

 

 

 

10 Comments

  1. ለምን ቲፒልፍ ትጥቅ ይፍታ አላልክም ፈሶ ፣ ሃምሳ ፌዴራል ፖሊስ አስሮ ያለው ቲፒልፍ ሆኖ ሳለ

  2. Who are you, or for whom are you speaking? Are you spokesperson of the government?
    Otherwise, have you asked TPLF’s murder squad called Agazi or Abdi Iley’s Liyu police to disarm in a similar tone? Who were on a murder rampage for the last 27 years?

    You stated “(OLF) ትጥቅ ሳይፍታ ከነሰራዊቱ ህዝብ ውስጥ መግባቱ እጅግ አሳሳቢ ነው”. You forgot that OLF is not alien to the people. Its combatants are the Oromo people themselves. If the Oromo people have to disarm, so should the Amhara, the Somali, the Tigreans, etc. Why only the Oromos?? The Oromia regional government should arm the people instead, the same way Ato Gedu said the Amhara should be armed.

    Stop your hysteria about OLF and hands off the Oromo people!

  3. ዳውድ ኢብሳ አገር ውስት ሲገባ ኤርፓርት ያደረገው ንግግር በጣም ተስፋ የሚሰጥ ነበር፡፡ ህዝባችንን እናሰነጥላለን፣ እናስተምራለን፣ ተባብረን ለለውጥ እንሰራለን ሲል ሲፎግረን ነበር ለካ፡፡
    እውነት እንነጋገር ከተባለ በየቦታው ጎልቶ የሚታየው ብጥብጥ ፣ ረብሻ የኦሮሞ ፓለቲካ ድርጅቶች ከገቡ ጀምሮ ነው፡፡ ፕ/ሚሩና ግብረአበሮቹ የወሰዱት እርምጃ ስለሌለ ውስጥ ውስጡን የሚደግፉ መሆን አለባቸው፡፡ በተደጋጋሚ የምናየው ፀቦች በቀጥታ ከኦሮሞ ፓለቲካ ፓርቲ ድርጅት ጋር የተያያዘ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር እየሆነ ለምን ቁርጥ ውሳኔ ከተፈለገም ወደመጡበት እንዲወጡ እንዳልተጠየቀ አይገባኝም፡፡

    የአቢይ አስተዳደር ደካማነት ነው ብዬ አስብና በሌላ በኩል ደግሞ አስተዳደሩ እንደፈለጉ እንዲፈነጩና እንደሁለት መንግሥት እንዲሆኑ የፈቀደላቸው ምክንያት አቢይ እራሱ ቀንደኛ ደጋፊ ሊሆን ይችላል የሚል ሃይለኛ ጥርጣሬ ውስጥ ይከተኛል፡፡ ካርታ ሲያሰመርቁ፣ መጤ እያሉ ወገን ሲያርዱ እያየ በመሪነቱ ከማውራት በስተቀር የወሰደው እርምJጃ አንዳች የለም ፡፡ ለዚህም ነው ደጋፊ አለመሆኑን ያሳየን ማስረጃም እስከ አሁን የለም፡፡
    የበለጠ ችግር ሳያመጡብን ወደዛ ማባረር ነው፡፡ እዛው እንደለመደባቸው በሩቁ አገራችንን ቢጠሉ ይሻላል፡፡

    • Why all neftenyas are so alarmed the moment they hear the name OLF? Is it because they are blinded by 27 years of TPLF’s incessant propaganda or their parents “gala yibelahal!” scare tactic? Or have these groups the fear that their hitherto priveleged position in Ethiopia will come to an end as the subjugated nations and nationalities in Ethiopia follow the Oromo path led by OLF into true liberty and self rule? Time may cure the first, but as for the second one, no army can stop it let alone a concerted media hate campaign.
      Bilisumma is an idea whose time has come.
      “There is one thing stronger than the armies of the world, and that is an idea whose time has come.” Victor Hugo

      • Neftegna?lol get out of here.
        I think it is time to look inward, my man Abba Caala. Your OLF is on steroid now.lol
        Trust me, “true liberty” comes when we’re free from OLF violence, when OLF given up hatred, when OLF tolerate differences, when OLF stop killing non-oromo Ethiopians as settlers/outsiders.

        I kinda like the idea of “self rule”, but i don’t know how practical would be in the current Ethiopian political climate. First, OLF must stop target eviction of non- oromo Ethiopian citizens around the country, and also OLF must show the non-oromo citizens mutual RESPECT, common purpose! including to my fellow neftegnas.
        FYI- I’m not afraid of Oromo, but i’m afraid of OLF type of politics that involve violence, killing, inflammatory rhetoric…

      • የኢትዮጵያውያኖች አገራችንና ኦሮሞ ሃገር Oromo Nation መስራቾች ማለቴ ነው፡፡ ይቅርታ አድርግልኝና አክራሪ ኦሮሞ ስለኢትዮጵያ አገሬ አምልጧቸው ሲወያዩ ሰምቼ፣ አይቼም አላውቅም፡፡ ጉዳያቸው ኢትዮጵያ ሳይሆን ኦሮሞ ሃገር Oromo Nation መመስረት ነው አላማቸው፡፡
        እውነት እንነጋገር ከተባለ አገራችን ኢትዮጵያ የሰላም አገር እንድትሆን ፍላጎት ሁላችንም ካለን መጀመሪያ አገርን በማፍቀር፣ ሰንደቅ ዓላማን በማክበር ብንጀምርና የጎደለንን ፍላጎት ለመሙላት ተከባብረን መስራት ይሻላል እንጂ አሁን እያየን ያለው ሁኔታ ወደጥፋት፣ እልቂት ነው የሚወስደን፡፡

        ፕ/ሚሩ ለዜና አቅራቢ ሲያወራ ሰምተሃል? የመንግሥት ወታደሮች ለሥራ ሲላኩ የዕለት እንጀራ ለመብላት የአገር ነዋሪ ላይ ነው ተስፋቸው፡፡ እግዜር ያሳይህ ከዚህ የበለጠ ድህነት ምን አለ? ምን አይነት መንግሥት ነው ያለን? ወታደርን የሚያህል የአገር ዘበኛ መመገብ የማይችል፡፡ የሚያም፣ የሚያሳዝን አገር ነው ያለን፡፡ የፕ/ሚሩ ፑሽ አፕ ሌላው በጣም የሚያምና የሚያሳፍር ቲያትር ነው፡፡ ለጊዜው እዚህ ላይ ማንሳቱ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሰውየው ይቀልዳል በማይቀለድበት ሰአት፡፡ አገር መምራት ሳይሆን ፎቶ ለመነሳት ነው የሚሽቀዳደመው፡፡

        በጥያቄህ መልስ ምክንያት በአጋጣሚው ልልህ የፈለኩት አገራችን ብዙ ነገር ማስተካከል ያስፈልገናል፡፡ ወታደሮቻችንን መመገብ መቻል አለብን አገር ለመቆራረስ ወይም የግላችንን ፓለቲካ ጥማት ለመወጣት ከመራወጣችን በፊት ማለቴ ነው፡፡

  4. ሁሉም ነፍጥ ታጥቀው “ይታገሉ” የነበሩ ሃይሎች በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው መሳሪያ በመፍታት በሰላማዊ ትግል አምነው ወደ አገር ውስጥ ገብተዋል ተብሎ ቢታሰብም በልኩ አላገኘናቸውም፡፡ ስሜት በተቀላቀለበት ሁኔታ ህዝቡ ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ባደረገላቸው አቀባበል የሰከሩት የኦነግ አመራሮች ትጥቅ ያልፈቱ አባሎች በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡ ይህ በአንድ ሉአላዊ መንግስት አስተዳደር ውስጥ መሳሪያ የታጠቀ ሃይል በነጻ እንዲንቀሳቀስ መብት አለኝ ብሎ ሲያወራ በአለም ላይ የመጀመሪያው አሳፋሪ ድርጅት ነው፡፡ የኦነግ እብሪት ይህ የመጀመሪያው ባይሆንም በ2004 ዓ.ም 20000 ጦሩን ኢህአዴግ እንዴት ጥጥቅ እንዳስፈታወ አንረሳውም፡፡ ጥጥቅ መፍታት ማለት ምንድነው፣ ማነውስ እኛን ትጥቅ የሚያስፈታን እያሉ በታወቁ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ ሃላፊዎቻቸው ጭምር ሲታበዩ የመንግስት ዜጋውን ቅር አሰኝቶታል፡፡ ይህ የመንግስት ( ፌዴራሉና የኦሮሚያ ክ/መ) ዝንታ ምንጩ ፍርሃት፣ ትግስት ወይንስ በስምምነታቸው መሰረት የተፈጸመ፡፡ ለዚህ መልስ በአፋጣኝ ካልተሰጠ ይዞት የሚመጣውን አደጋ መተንበይ ያዳግታል፡፡ አንድም የጦር አውድማ ላይ ተዋጉ ሲባሉ ያልሰማናቸው ታጣቂ ተብዬዎች አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ማቅራራት ህዝብና መንግስትን ከመናቅ በላይ ምን ልንላቸው እንችላለን፡፡ ይህ ተግባራአቸው ማሸበር ወይስ በሰላማዊ ትግል ማመን፡፡ እረ የመንግስት ያለ

  5. የኦነግ ጥያቄ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚገባውን ሚና መጫወት አለበት ነው። ይህም ትክክል ነው። መደነቅ ያለበትን እናድንቅ።ኦነግን ማመስገን ዘረኛ-ነት ከሆነ ኦነግን መተቸት ቅዱስነት ሊሆን ነው? የራሴን ለራሴ ያለ ስህተት ከሆነ የራሴም ለራሴ የናንተም ለኔ የሚልስ ምን ሊባል ነው? ኦነግ ራስ በራስ የመተዳደር (Self Determination and Self Rule) ጥያቄ እንጂ የመገንጠል (Secessionist) ዓላማ አለው ብዬ አላምንም። የመገንጠል ዓላማ እንኳ ቢኖረው ለመገንጠል የፈለገበትን ምክንያት ጠይቆ መፍትሔ መፈለግ እንጂ ማጥላላት ምናመጣው!? እገነጠላለሁ ከሚል በላይ ተገንጣይን የሚያጥላላ ወገን የባሰ ገንጣይ የለም።

    አሁንም ኦነግ የመገንጠል ዓላማ አለው ብዬ አላምንም። ቢኖረውም ለኦነግ ያለኝ ክብር አይቀንሰውም። ኦነግ ባሁኑ ሰዓት ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር ላይኖረው ይችላል። ኦነጋዊ አስተሳሰብ ግን በኦሮሞ ህዝብ ልብ ውስጥ አለ።

    ኦነግ የስልጣን ጥማቱ ለማርካት ሲል ከህወሓት ኢህአዴግ ጋር አልተሞዳመደም። ብአዴንና ኦህዴድ ለስልጣን ሲሉ የህዝባቸውን ጥቅም አሳልፈው በመስጠት የህወሓት ቅጥረኛ አሻንጉሊቶች ሆነው ከህዝብ ይልቅ ግዝያዊ ስልጣን መርጠው ጌቶቻቸውን ለማገልገል ህዝባቸውን ሲበድሉ ነበር።

    ኦነግ ግን ህዝቡን መርጦ ከህወሓት ጋር ተጣልቶ ጫካ ገባ፤ ለህዝብ ቆመ እንጂ ለስልጣን አልተሸጠም። ክብር ይገባዋል። ከስልጣን በላይ ህዝብን የሚያስቀድም ድርጅት ያልተመሰገነ ማን ሊመሰገን!? አሻንጉሊት? አሻንጉሊት ክብር የለውም! ልብ በሉ የኦነግ አባላት ለ27 ዓመት ያህል በህወሓት ኢህአዴግ ሲሰቃዩ የኦህዴድ ባለስልጣናት የጨቋኑ ስርዓት ቁልፍ መሳርያ ነበሩ።

    የኦነግ ጥያቄ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚገባውን ሚና መጫወት አለበት ነው። ይህም ትክክል ነው። መደነቅ ያለበትን እናድንቅ።

  6. አጭበርባሪው የገዳይ ኩባንያው ፋሺሽት-ወያኔ ሕውሃት ትጥቁን በአስቸኳይ ካልፈታ፤ኦነግ ትክክለኛ እርምጃ ነው የወሰደው፤ሕውሃት ትጥቁን በአስቸኳይ በራሱም ሆነ በአባላቱ ይሁን በካድሬዎች እጅ ላይ ያለውን መሣሪያ ወይም ትጥቅ በአስቸኳይ መፍታት እለበት።ያለበለዚያ ኦነግን ብቻ ትጥቅ ፍታ ማለት ትርጉሙ ሌላ ነው፤ለምን ጉጅሌ ትጥቁን አይፈታም????????????????????????????????????????ማነው ምክንያቱን የሚያውቅ እና የሚያስረዳኝ?????????????????????????????????????????????????????????????ዋናው ዕብድ ጉጅሌ ተደብቆ፤ለምንድነው ኦነግ ላይ ሰዎች የሚረባረቡት ????????????????????????????????????????አጋንንቱ የገዳይ ኩባንያው ፋሺሽት-ወያኔ ታጥቆ ለምንድነው ለሰላም ወደ አገር ቤት የገባውን ኦነግ ለይተው የሚረባረቡበት?????????????????????????????????????????

    አጭበርባሪው ይውጣ።

    ኣሁንም በኦነግ ስም ፋኅሺሽቷ ወያኔ፤
    ያልተነቃ መስሏት ጀመረች እእንደያኔ።
    ግንሳ ያላወቀችው አንዴ አምኖ የተካደ፤
    ጅል ሆኖ አይደግምም አውቆ ካላበደ።
    እናም ጉጅሌ አብዷል ሰዎች ተጠበቁ፤
    እጁ የጨበጠውን አይቀርም ማነቁ።
    እንደው ለጫወታ የኦነግን ላንሳ፤
    ጉጅሌ እየጮኸች ፣ነገር ልታስረሳ፤
    ሲመሽ አይዞህ ብላው፤
    ቀን ቀን ስትጠላው።
    ማታ እንደልማዷ፤
    ቀን ቀን ከነኣመዷ።
    ራሷን ስትቀይር በእሽትነቷ፤
    ከኣጋንንት ታድራለች እንዲቀር መሞቷ።
    አትመኑኝ እዪዋት ትንፈራገጣለች፤
    እንዳበደ ውሻ ሁሉን ትነክሳለች።
    እናም በኦነግ ሥም ተንኮል ሥትሰራ፤
    ወገኔ አትቀበል መርምረህ አጣራ።
    ይህ መራራው ቃሌ ሐቅ ሆኖ የመጣ፤
    ዕውነቱን ለማግኘት
    አጭበርባሪው ይውጣ።

Comments are closed.

Share