ኃይሌ ሩትስ በሚኒያፖሊስ ቀለበት አሠረ

/

(ዘ-ሐበሻ) በሬጌ የሙዚቃ ስልት የሚታወቀው ድምጻዊ ኃይሌ ሩትስ በሚኒሶታ ትናንት ሴፕቴምበር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ቀለበት አሰረ። ድምፃዊ ኃይለሚካኤል ጌትነት (ኃይሌ ሩትስ) ቀለበት ያሠረው ነዋሪነቷ ሚኒሶታ ውስጥ ከሆነችው ከወይዘሪት ነዋል ስምዖን ጋር መሆኑን ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለከታል።
በዳውንታውን ሚኒያፖሊስ በተለምዶ “SEVEN Steakhouse” እየተባለ በሚጠራው ቦታ ቀለበቱን ያሠረው ድምፃዊ ሃይሌ ሩትስ ሠርጉን ኢትዮጵያ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በዚህ የቀለበት ሥነ- ሥርዓት ላይ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ለመገኘት ሄደው የነበረ ቢሆንም ከበሩ ጀምሮ ፎቶ ግራፍ ማንሳት ክልክል ነው የሚሉ ፖስተሮች በመለጠፋቸው አንዳችም ፎቶ ግራፍ ለማንሳስት አልቻልንም። በተጨማሪም በቀለበቱ ላይ የታደሙት ወገኖችም በስልካቸው ጭምር ፎቶ ግራፍ ማንሳት እንዳልቻሉም ለማወቅ ተችሏል። “ቺጌ” በሚል አልበሙ ታዋቂነትን ያተረፈው ኃይሌ ሩትስ በአንድ ወቅት በዘ-ሐበሻ ላይ በታተመው ቃለ ምልልሱ ላይ “እኔ ብዙ ግርግር አልፈልግም፤ ብዙ መታየትም አልወድም” ሲል መናገሩን ያስታወሱት ወገኖች ምናልባትም የቀለበቱ ፎቶ ግራፍ እንዳይነሳ የከለከለው በሚዲያዎች በኩል ስሙ እንዳይነሳ ይሆናል የሚሉ አስተየት ይሰጣሉ።

ሃይሌ ሩትስ በዘ-ሐበሻ ላይ በታተመው ቃለ ምልልሱ ላይ፡ “ጥያቄ፡- የቤተሰቦችህ ሁኔታ ምን ይመስላል? የት ተወለድክ? የት አደግክ? የት ተማርክ? ከቤተሰብ ያንተን ፈለግ የተከተለ አለ?” የሚል ጥያቄ ቀርቦለት “ዘጠኝ ወንድማማቾች ነን፡፡ ሁለት እህቶች አሉኝ፡፡ ከመጨረሻ ሁለተኛ ልጅ ነኝ፡፡ እናቴ በህይወት የለችም፡፡ አባቴ አለ፡፡ አባታችን ነው ያሳደገን፡፡ ያደግሁት እንግሊዝ ኤምባሲ አካባቢ ነው፡፡ አንደኛ ደረጃን ስላሴ ካቴድራል፤ ሁለተኛ ደረጃን ደግሞ ዳግማዊ ምኒልክ ነው የተማርኩት፡፡ ከዚያ በኋላ ትምህርት አልሆነኝም (ሳቅ)፡፡ እግርኳስ ተጨዋች ነበርኩ፤ እግርኳስ በጣም ነበር የምጫወተው፤ ከዚያ እርሱን ተውኩና ወደ ሙዚቃው ገባሁ፡፡
ሙዚቀኛ በዘሬም የለም፤ እኔ ብቻ ነኝ በድፍረት የወጣሁት፡፡ ለዚያ ነው በወቅቱ ሙዚቃ ስጀምር ተቸግሬ የነበረው፡፡ መግባባት አልነበረም፤ ቤተሰብ የሚፈልገው የሃይማኖት እና ሌላ ሌላውን ሙያ ስለነበር ይህን አይደግፉትም ነበር፡፡ እና በወቅቱ ችግር ነበር፡፡” ሲል መመለሱ ይታወሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዞን 9 ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ በድጋሚ ተቀጠሩ

ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ላይ የታተመውን ቃለ ምልልስ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
http://youtu.be/3AP2cWFtnz8

6 Comments

  1. i heard that this guy was /is pro woyane . They said he had profound love for the renown big time thieve and assassin ,melese Zenawi. If it is not true i stand for correction and apologize in advance .

  2. Debrhsj,

    Even if what you say is true, do you not respect his right as an individual to support and love who-ever he wants? This is a dangereous and unhealthy road-that is so fashionable among the diasopora. To just dismiss people becase they love what we happen to hate. Pls think postive.

    Congragulations Haile Root. All the best.

Comments are closed.

Share