በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን በጎርፍ አደጋ 28 ሰዎች ሞቱ

የከሚሴ ከተማ በደህናው ጊዜ። (ፎቶ ከዊከፒዲያ)(ዘ-ሐበሻ) ትናንት ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከ7 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት ካለማቋረጠ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ የተነሳ በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን ከሚሴ ከተማ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉ ሲዘገብ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የውስጥ አዋቂዎች ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።

በከሚሴ ከተማ ልዩ ስሙ ቀኖ በተባለ አካባቢ የደረሰው የጎርፍ አደጋ የከሚሴ ከተማን ጨምሮ በዙሪያዋ ያሉ አካባቢዎችን ማጥለቅለቁን የታወቀ ሲሆን የመንግስት ተወካዮች ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በ19 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። ይህን ተከትሎ ሌሎች ታዛቢዎች የሟቾቹን ቁጥር እና የተጎጂዎቹን ቁጥር ከዚህ በላይ ያደርጉታለ።

በዚህ የጎርፍ አደጋ ወደ 300 የሚጠጉ ቤቶች በአደጋው የተጠቁ ሲሆን ከ30 በላይ ቤቶች ደግሞ ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል። በሌላ በኩል በደሴ ከተማም እንዲሁ ሸዋበር በሚባለው አካባቢ በደረሰው ጎርፍ የኤሌክትሪክ መሰሶዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱም በላይ 3 መጋዘኖች በውሃ መጥለቅለቃቸውን የመንግስት ተወካዮች ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአፋር ከ40 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ጫካ ገቡ

2 Comments

  1. Why there no Amhara Zone in “Oromia”, why no Agew Zone in Tigrai. The fake federalism is meant to creat chaos not done to benefit Ethiopians. Say no to the fake constitution and fake federalism. Unite and fight the home grown fascists and build a free and democratic Ethiopia where all live freely and equally without any ethnic or religious dominance and state Terror.

Comments are closed.

Share