መንግስት በአዲስ አበባ ኤርፖርት ሁለት ተቀጣጣይ ሲሊንደሮች አገኘሁ አለ

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ መንግስት የደህነነት መስሪያ ቤት ባለፈው እሁድ ኦገስት 11 ቀን 2013 በአዲስ አበባ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሁለት ተቀጣጣይ ባዕድ እቃ የያዙ ሁለት ሲሊንደሮች መገኘታቸውን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል በመንግስት ሚዲያዎች ላይ ባሰራጩት ዜና እንደገለጹት ሲሊንደሮቹ በአውሮፕላን ማረፊያው የመንገደኞች መነሻ አከባቢ እንደሚገኙ ጥቆማ ያደረሱት የፅዳት ሰራተኞች ናቸው ብሏል።

የመንግስት ሚድያዎች እንደዘገቡት የፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች ሲሊንደሮቹ ተቀጣጣይና በቀላሉ በእሳት በመያያዝ ጉዳት ማድረስ የሚችሉ መሆናቸውን መረጋገጡን እና ሲሊንደሮቹ የያዙት ተቀጣጣይ ንጥረ ነገር ባህሪም እየተጣራ ነው።

መንግስት ይህን ተቀጣጣይ ሲሊንደር በአዲስ አበባ ኤርፖርት ማን እንዳስቀመጠው ባይገልጽም አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ግን መንግስት ከዚህ ቀደም ካለው ባህሪ አኳያ ራሱ ሲሊንደሩን አስቀመጦ በአንድ ድርጅት ላይ ለማላከክ ነው ይላሉ። አስተያየት ሰጪዎቹ ጨምረውም ከዚህ ቀደም መንግስት ኦነግን ለማስጠላት የትግራይ ሆቴልን ጨምሮ የተለያዩ ቦታዎችን በማፈንዳት ኦነግን በአሸባሪነት መፈረጁን፣ ይህን ሆቴል አፈነዱ ተብለው በቴሌቭዥን የቀረቡት ሰዎች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሌላ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መታየቸውን፤ በቅንጅት ላይ በኋላም በግንቦት 7 ላይም አኬልዳማ ድራማን ለመሥራት የጠቀመውን በማስታወስ አሁን በአዲስ አበባ ኤርፖርት ተቀመጠ የተባለውን ተቀጣጣይ ሲሊንደር ከመንግስት ውጭ ሌላ ሰው ያደርገዋል የሚል እምነት እንደሌላቸው አስታወቀዋል።

ሌሎች አስተያየት ሰጪዎችም ይህን ዜና የመንግስት ድራማ ያደርጉታል። መንግስት በሃገር ቤት ተቃውሞ ሲበዛበት እንዲህ ያሉ ተልካሻ ምክንያቶችን በማቅረብ ሰዎችን በሽብርተኝነት ለመክሰስ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው ሲሉ መንግስት የበተነውን የተቀጣጣይ ሲሊንደር በአዲስ አበባ ቦሌ አየር መረፊያ የመገኘቱን ዜና ያጣጥሉታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: የጎደለው ሊቨርፑል

9 Comments

  1. ወይ ወያኔ እናንተ ታልፋላችሁ ምን አለ ልጆቻችሁ አንገታቸዉን የሚደፉበትን
    የቤት ሥራ ትታችሁላቸዉ ታልፋላችሁ ???????????

  2. I have evedence those cylinders were installed by WEYANE and his servants inorder to blame other innocent peoples. Weyane is always doing such a trash system..

  3. No body doing this kind of cheep scum idiotic and shameless except weyanes to terrorized the innocent civilian people in ETHIOPIA.DEATH to weyanes.it will be soon

Comments are closed.

Share