የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ቃለ ምልልስ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋር

/

[jwplayer mediaid=”6117″]

የጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛ ሸዋዬ ለገሰ የዘ-ሐበሻ እና የጤና አዳም ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁን አነጋግራዋለች። ቃለምልልሱ በጀርመን ድምጽ ራድዮ ላይ ተላልፏል። የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች እንድተከታተሉት እዚህ በማምጣት አካፍለናችኋል።

ስለጤና ጉዳይ የሚቀርቡ መረጃዎችን ምን ያህል ህዝብ እንደሚያገኛቸዉ፤ ወይም ለምን ያህል ህዝብ እንደሚደርሱ መገመት ይቸግራል። ነገር ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሰዎች ለጤና ይዞታቸዉ ትኩረት መስጠትን ችላ ሊሉ አይገባም።
ጤና-ነክ ጉዳዮችን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ለማቅረብ መጣር የእኛን ኅብረተሰብ ሊነቃ ይችላል የሚል እምነት ያላቸዉ ወገኖች ራሱን የቻለ የጤና ድረገጽ ከፍተዉ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ወራት ተቆጥረዋል።
ዘመኑ የቴክኒዎሎጂ ነዉ የመረጃ፤ በአንዱ ጓዳ የተከሰተዉን ሌላዉ ባለበት ሆኖ ሊሰማዉ መንገዱ ተመቻችቷል፤ ለብዙሃኑ። በዘመነ ኢንቴርኔት ምስጢር የለም፤ ራዲዮና ቴሌቪዥን ዜናዎችን አልተከታተልኩም፤ የጤና ጉዳይ መረጃዎችን እንደልቤ አላገኝም ከሚባልበት ጊዜ ልንሻገርም ዳርዳር እያልን ይመስላል። አፍሪቃ ዉስጥም ቢሆን ይህ ዛሬ ብዙም የሚወራለት የራቀና ያልተደረሰበት ጉዳይ አይደለም።

ዛሬ ይላል የጤና አዳም ድረገጽ አንቀሳቃሽ፣ ዛሬ ሰዎች ለራዲዮና ቴሌቪዥኑ ጊዜ ቢያጡ እንኳ ከያሉበት በእጅ ስልካቸዉ በየመንገዱም ቢሆን የሚሹትን መረጃ ማንበብ ይችላሉ። የተለያዩ ወቅታዊ ዜናዎችን ከመዘገብ በተጓዳኝ ሄኖክ ዓለማየሁ ለጤና ጉዳይም ትልቅ ትኩረት መስጠቱን የሚያንቀሳቅሰዉ ድረ ገጽ ዘሃበሻ ይናገራል። ለጤና መረጃዎችን የምታጋራዉን ድረገጽም እዚያዉ ላይ ታዝላ ነዉ ያስተዋልኳት። አዘጋጅዋ ለጤና ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት ይገባል በሚል ለኢትዮጵያዉያን አንባቢዎቹ መረጃ በመስጠት ለማበረታታት ታስቦበት የተጀመረ መሆኑን ነዉ የሚናገዉ፤
ጋዜጠኛ ሄኖክ እንደሚለዉ ባላቸዉ መረጃ መሠረት በርካታ የድረገጹ ጎብኚዎች የሚገኙት እዚያዉ ሰሜን አሜሪካ ነዉ። ከኢትዮጵያስ ጎብኚዎች ይኖሩት ይሆን? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኮረና ቫይረስ ወረርሽን አደጋ እና የሀገርና ሕዝብ ደህንነት

(ምንጭ፡ የጀርመን ድምጽ ራድዮ)

Share