የሚዲያ አፈና ትግሉን ያጠናክረወል እንጂ አያቀጭጨውም ! (ከይድነቃቸው ከበደ)

(ይድነቃቸው)

ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራስ ለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ ሰው በመናገሩ አና በመፃፉ ብቻ ለእስር እና ለስደት የሚዳረግበት አገር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዶናት፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በኢትዮጵያ ህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገመንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆይገኛል፡፡
ይሁንእንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አልፎ ተርፎ በአስተሳሰብ ወይም በአመለካከት ላይ ተፅኖ እስከመፍጠር ተደርሶኦል ፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ እንደመሆኑ መጠን የፈጀውን ፈጅቶ ወደ ነበረበት መመለሱ የማይቀር ሃቅ ነው፡፡በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለህዝቡ ተገቢውን መረጃ እያስተላለፉ ያሉ የእትመት ውጤቶችን ከገቢያ ለማውጣትና ፈርጆ ለመክሰስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ሌላው ማሳያ ነው፡፡ ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣ በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡ መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ለእስር የሚዳረግበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
በዲሞክራሳዊ ሥርዓተ ዜጎች የሚኖሩት ግልፅ በሆነ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ የትኛውም አይነት ሃሳብ ከማንም ሊመጣ ይችላል ቁም ነገሩ መሆን ያለበት የሚመጣው ሃሳብ የሚመከተው በምንድነው የሚለው ነው፡፡ ለነፃ ንግግር ችግር የተሻለው መንገድ የበለጠ ነፃ ንግግር ነው፤ አሳብን በመግለፅ መብት ላይ የሚደረግ ማናቸውም ተፅእኖ ሲውልሲያድር በእያንዳንዱ ግለሰብ የመናገር መብት ላይ ስጋት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለዚህም ነው ወደነበረበት መመለሱ የማይቀር ነው ለማለት የሚያስደፍረው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ማንም ሰው በስጋት ውስጥ መኖርን ስለማይፈልግ ነው፡፡
በመሆኑም በአገራችን እየከሰመ ያለው ሃሳብን በነፃ የመግልፅ እና መረጃ የማግኘት መብት በገዥው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረት ወደመሆን ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡ የፈለጉትን መስማት እና ማዳመጥ እንዲሁም በፈለጉት የመገናኛ ብዙሃን መንገድ ሃሳብን መግለፅ እና መረጃን ማግኘት ግለሰብ ከሆነ እንደግለሰቡ፣ ተቋም እንደተቋም እንዲሁም ፓርቲ እንደ ፓርቲ የመምረጥ የራስ መብት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ የዲሞክራሲ መገለጫ ባህሪ ነው፡፡
ሌላው እና አሳሳቢ ሊሆን የሚገባው ሰው የመረጠውን መስማትና ማዳመጥ እንዲሁም ማንበብ መብቱ እንደጠጠበቀ ሆኖ ግለሰብ ወይም ተቋም ሃሳቡን እንዴት የመግለፅ መብት እና ግዴታ አለበት የሚለው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ተቋም ወይም ግለሰብ ሃሳብን ወይም መረጃን በማንኛውም መንገድ የመገልፅ ሙሉ መበት በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡ እንዲኹም የዚህ መብት ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም ነገሮች ተቀባይነት እንደሌላቸው በህገመንግስቱ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት በማናቸውም የመገናኛ ብዙሃንሃ ሳብን መግለፅ እና መረጃን መስጠጥ በራሱ ወንጀል ወይም ጥፋት አይደለም ይህ የሆነው ደግሞ መብት ከመሆኑ አንፃር ነው፡፡ በመሆኑም በኢዲስ ጉዳይ፣ ፋክት፣ ሎሚ፣ .እንቁ እና ጃኖ መፅሔት ላይ መንግሰት ክስ የመሠረተበት ዋንኛ ምክንያት ሃሳብን የመገለፅ እና የሚዲያ ነፃነት በማፈን የለየለት አምባገነናዊ ስርዓት በአገራችን በማስፈን ስልጣንን ለማረዘም የተደረገ መፍጨርጨር ነው፡፡ የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ እና ለዲሞክራሲ ማበብ የሚደረገው ጥረት በይበልጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን እስከድል ጫፍ የምንደርስበት እንጂ ወደኋላ የማንል መሆኑ ወያኔ ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡
ይድነቃቸው ከበደ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ወይንስ የኦሮምያ ንግድ ባንክ? የኦሮምያ ወይንስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ?... ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
Share