August 2, 2014
20 mins read

የጨረቃ ፈስ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

የቀልዱ ጎጆ የድቡሽቱን ህልምን ይደረምሳል።
ሥርጉተ ሥላሴ 02.08.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ክፍል – አንድ።

አዬነው ሰማነው ጉዳችሁን። እንዲህ መንፈስን ማሰራችሁ አልበቃ ብሎ ደግሞ የኤሉሄ ስቃዩን ዓለም እንዲታደምበት ማደረጋችሁ አሳምሮ ገማናችሁን የአደባባይ ሲሳይ አደረገላችሁ —– ጅልነታችሁን ሆነ ጭቃነታችሁን ጫካ እያላችሁ „ማሌሊት ያሸንፋል እያላችሁ“ በአይነ ምድራችሁ የምትጽፉ ገለባዎች መሆናችሁን ስለምናውቅ „ለማያውቅሽ ታጠኝ“ እንላለን – ለእነ አይሁድ። አሪዎሶች!

አሁን በዚህ ሽርክት ዘገባችሁ አንዳርጋቸውን የመሰለ ዕንቁ የነፃነት ፈላስማ ሰብዕናውን ያዋረዳችሁ ሊመስላችሁ ይችል ይሆናል። ይህ ቅንጥብጣቢ ግርድፍ ቅንብር እራሳችሁን ማበሻ ጨርቅ ነው ያደረጋችሁ። አንድ የብዕር ወዳጄ „ወያኔ ለአቅመ አዳም ያልደረስ ድርጅት ነው“ ያለውን ስመረምረው እውነት ነው። አቅማችሁም አቅላችሁም አይፈቅድም። ኢትዮጵያን ያህል ታላቅ ሀገርና ህዝብን ለመምራት እንዴት ትችሉ?  ለነገሩ አቅማችሁን ስላወቃችሁም ነው ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥማችሁ ፈቅ ለማለት የተሳናችሁ። ሰሞኑን ደግሞ የቤት ሥራችሁ ሆኖ ለመቀዬር ካልተንደፋደፋችሁ። አይቻችሁ አለሁ እኮ በሴቶች ጉዳይ ጠንከር ያሉ ወቀሳዎች በ2014 ሲቀርቡ በ2012 እንቅልፍ መዳህኒት ወስዶ ለሽ ያለውን ዬጠ/ሚሩን ወንበር የሸንበቆ ድጋፍ በአምአሳላችሁ ስታወቅሩ ትዝ ሳይላችሁ በ2014 ም/ጠሚር ሴት ለዛውም መቅድም የሆነችውን ስትሉ ተደመጣችሁ። በማግሥቱ በዩንቨርስቲ ተማሪ ሴቶች ላይ፤ በጋዜጠኛ ሴቶች ላይ፤ በብሎገር ጦማርያን አንስት ላይ፤ በፓርቲ አመራር ሴቶች ላይ የለመዳችሁትን የአራዊትነት ተግባር ስትፈጽሙ ም/ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይሰማሉ እልም – እልም – እልም – እያሉ –

እውነት ህዝብን የመምራትና የማስተዳደር ኣቅማችሁ ወርደ ጠባብ ነው። ብናኝ ጸጋው የላችሁም። ከላይኛውም አልተሰጣችሁም። እኔ ከእናንተ ይልቅ „ኢህአድግ“ እያሉ የሚያንቀባርሯችሁን ሆነ „መንግሥት“ እያሉ የተነፋ ባዶ ትቦነታችሁን ለሚዘክሩ ሁሉ አዝንላቸዋለሁ። ምክንያቱም ጫካ በነበራችሁበት ጊዜም ሆነ በሰርጎገቦቻችሁ ባገኛችሁት ዱካ ውንብድናችሁን አሳምሬ ስለማውቅ፤ ተፈጥሯችሁ እስክትከስሙ ድረስ ሆነ ተቃጥላችሁ አመዳችሁ ቢቀበርም „መንግሥት“ „ኢህድግ“ ብዬ አልጠራችሁም። አይገባችሁማ!

ሽፍታ ናችሁ። ኪስም መንፈስም አውላቂ። ወንበዴ ናችሁ – ዘራፊ። „መንግሥት“ አይደላችሁም የማፍያ ቡድን ናችሁ። ስለዚህ መጀመሪያ በነጠረ ቋንቋ የነፃነት ትግሉ አቅም ባለው ጸዕዳ መንፈስ የሚገኘው ወገን፤ ድርጅት ሁሉ ግልጽ የሆነ መስምር ሊከተል ይገባዋል ባይ ነኝ። በተቆርቋሪነት በሚጻፉ – በሚዘገቡ – በሚዘከሩ ልዩ ዝግጅቶች ሁሉ ሊጠነቀቁበት እንደሚገባ አበክሬ በአጽህኖትና በአክብሮት አሳስባለሁ። ማናቸውም የመንፈስ ምርት አዬር ላይ ከመዋሉ በፊት ይፈተሽ ዘንድም በትሁት ሥነ – ምግባር እጠይቃለሁ። በህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የሚወጡ ፖስተሮች ሆኑ በራሪ ጹሑፎች ሁሉ የተገባውን የኤዲትንግ ተግባራቸውን በሚገባ ከጨረሱ በኋላ መሆን ይኖርበታል ለአደባባይ መብቃት ያለባቸው። እንዲያውም እንደ እኔ ማዕከላዊ የሆነ መስመር ቢኖር እመርጣለሁ። ስለምን? እኔ እራሴ የምቆስልበት ስለሆነ። ገንዘቤን – ጊዜዬን – ጉልበቴን እማፈስበት „የሽፍታ አስተዳደሩን ወያኔን እኩይ ኢ-ሰብዕዊ  ተግባርን ተቃውሜ ነው“ ስለዚህ እንደ ደላው ሰው ሁለመናዬን በሞስኮት መበተን አልሻምና። በማያተርፈኝ የግማሽ ጥገና ልስልስ ያለ ዬተቃውሞ ሰልፍና ስብሰባ መገኘት እራሴን የመግደል ያህል ይስማኛል። በዕንባንም መቀለድ።

„ኢህድግ“ ለማለት በእያንዳንዷ ሥነ – ሀገራዊ እንቅስቃሴ አባል ድርጅቶች መምክር መወሰን – ማጽደቅ ሲችሉ ነው። ይህ ደግሞ በወያኔ ቤት አይታሰብም። ለእንጉልቻው የተሰዬሙት ጠ/ሚር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በታሪካችን እኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ምርኩዝ የተዘጋጀላቸው፤ እራሳቸውን ችለው የማይቆሙ ሽባ ጠ/ሚር ብሎ ወያኔ እራሱ ሥም ሰጥቷቸዋል። ቦታው ያስገድድ ስለነበር ወንበር ጠባቂነት ነው የተሰጣቸው። ይሄው ማዕረግ መስሏቸው ፍንጭታቸውን ብልጭ እያደረጉ በዳዴ ይኳትናሉ። መጥኔ!

በተዘጋ አንደበት – በታሰረ መብት – በታፈነ ሃላፊነት ነው በስላቅ ፈገግታ እንዲያረግዱ የሚያደርገው  – ለወያኔ። ስለሆነም አባል ድርጅቶች ጉልቻነታቸው አንደበቱን ከፍቶ መብቱን ማስከብር ሲችል የወልዮሽ መጠሪያ ይገባል።

የሆነ ሆኖ የእስታሁኑ በምህረት ይታረቅና ቢያንስ ከእንግዲህ በድርብ ስለት እጥፍ የበቀል እርምጃ እያዬን – እዬሰማን ስለሆነ ቀጥ ባለ አቋም ለደጋፊ ወይንም ተባባሪ መንግሥታት ሀገራት መሪዎች ሁሉ ኢትዮጵያ በሽፍታ ቡድን እዬተመራች ያለች ስለመሆኗ ውስጣችን አምጦ እንዲወልደው የግድ መታገል አለብን። ወያኔ የተጠቀለለበትን ምስጣዊ ሸንኮፉን ወይንም ክንብንቡን መግፈፍ ያስፈልጋል! እራሱን መለመላውን ገላልጦ እርቃኑን ለህዝብ ዕይታና ፍርድ ማቅረብ የግንባሩ ተግባራችን መሠረታዊ አካል ሊሆን ይገባል።

እራሱ „ወያኔ መራሹ“ የሚለውም የሚያስኬድ አይመስለኝም።  አይመችም። በጣም አሻሚ ትርጉም አለው። ብጣቂ አዎንታዊ አምክንዮች አሉበት። ፍርፋሪ ብናኝ የኢትዮጵያዊነት ጠረን በሌለበት ሁኔታ „ኢትዮጵያን“ „ኢትዮጵያዊነትን“ ለመደርመስ የተሰበሰቡ ድርብ የባንዳ ባለሟሎች ስብስብ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በጠራ መሥመር ትወና ላይ እያለ ይህንን እውነት የምንሸፍንበት ካሊም የሚያስፈልግ በፍጹም አይመስለኝም። ወገኖቻችንም ይህንን ጠንቅቀው እንዲያውቁ ማድረግ አለብን። ጠላትን ሳያውቁ ጥይት መተኮስ ባሩድን ማክሸፍ ይሆናል። ይህ ደግም የመሸነፍ የመጀመሪያው መግቢያ በር ነው። ይህ ከወያኔ ጉያ ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ቀብረው ላሉት ትሎች ሁሉ ማርካሻ መንገዳችን ነው። ጥዝጥዝ ያደርጋቸዋል። ያርመጠምጣቸዋል። እሾኾች የሚፈሩት ነገር ተለባብሳ የኖረችው ቅብ ሽሙንሙን ገማና ደፍረን ስንዘምትባት ያን ጊዜ የድልና የተስፋን ዕለት ቢያንስ ማለም ይቻላል —-

ሌላው „መንግሥት“ የሚለው ነው። መንግሥት ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲካዊ ፍልስፍናዊ ትንታኔውን ትቼ በተለምዶው ትርጓሜ ሲፈታ ለአንድ ህዝብ መንግሥት ማለት እኮ ከፈጣሪ በታች ያለ በፈጣሪው የተቀባ – የተፈቀደለት  ጠበቂ – እረኛ – ወላጅ – ተንከባካቢ – ተቆርቋሪ – የህዝብ ሎሌ – የህዝብ ፍቅር የመረጠው – መንፈስ የፈቀደው ማለት እኮ ነው። አስተውሉ ወገኖቼ የኔዎቹ ፉከራ አይደለም ከልባችሁ ሆናችሁ አዳምጡኝ ማለቴ ነው። ከፈጣሪ አምላክ በታች የጸጋ ስግደት ተፈቅዶና ተወዶ የሚሰገድለት ማለት ነው መንግሥት፤ የሚሰጠው አክብሮትም ከልብ ነው። ጨዋ የሆነ – ሥርዓት ያለው – ፈርሃ እግዚአብሄር ያለው – የህዝብ አገልጋይ – የህዝብ ብሶት ሰሚ – የህዝብ ዕንባ ጠባቂ  – የዜግነት ወታደር – የሀገር ወደር የለሽ ፍጹም አብነታዊ ተቆርቋሪ የልዐላዊነት ሰንደቅ ማለት ነው።

ታዲያ ይህ ዬአራዊት ቡድን በ21ኛው ምዕተ ዓመት ላይ የሰው ልጅን የማናቸውም ዓይነት መርዝ መፈተሻ – መሞከሪያ

እንደ ጥንቸል ሲያደርግ ቃሉ „መንግሥት ወይንም ወያኔ መራሹ“ የሚለውን ደፍሮ ለመናገር እውነት ይቻላልን? ይህ እኮ አሁን የምንሰማው የምናዬው ነገር ሁሉ ከጫካ ጀምሮ ወያኔ ጠላቴ ባላቸው፣ አቅም በነበራቸው፤ ይቀናቀኑኛል ብሎ በሰጋባቸው ወገኖቻችን ሁሉ ሲፈጸም የኖረ የጣር ድምጽ እኮ ሰሞኑን በይፋና በአደባባይ የሰማነው።

ዛሬም የኢትዮጵያ ህዝብ በሚከፍለው ግብር፣ በተሰበሰበው ገንዘብ ሽፍታ ተኮፍሶ ሚሊዮኖች ያለቁበት፤ የተደመሰሱበት ከጠላት እጅ የወደቁ ሥጋና ደሞቻችን ሁሉ እንደ ዘመነ ኦሾትዝ  ወያኔ ሲፈጸም የኖረ በደል – ግፍና ገመና እኮ ነው ያደመጠነው የስቃይ ሲቃ! ይህን እንደ ሰብዕዊ ፍጡር በተደሞ በውስጣችን ሆነን እንፈትሸው። በቀሌንሶ እስር ቤት ይፈስ የነበረው ደም የዚህ ጣር ጭብጥ ነው። እኛ በመናውቃቸው እንጦርጦስ ጉድጓዶችም ….

እጅግ የምትናፍቁኝ ወገኖቼ ዘመን ዋሾ አይደለም። ዘመን ቀጣፊ አይደለም። ዘመን እውነት ነው። ዘመን ዕንባውን እንዲህ እያፈሰሰ ዛሬ ማቄን ጨርቄን ለምንለው ሁሉ ቁርጣችን እንድናውቅ አፍጦ ፍረዱ እያለን ነው። የተከበሩ ዬአቶ አንዳርጋቸው የመከራ ሰከንዶች ሁሉ ሌላ ተጨማሪ የሃቅ ሰነዶችን እያብራራልን ነው። ሌላ ታካይ የቁረጡ ነጋሪት ጎሳሚ ሰቀቀኖችን ሁሉ የአዳባባይ ሲሳይ እያደረገ ነው። መከራን እያነበብን ነው።  ስለዚህ ወያኔን ሚዛን ላይ አስቀምጠን „መንግሥት“ ለማለት የሚያስችለው ምን አምክንዮ አለ? „መራሽ“ ለማለትስ? ይህም ቢሆን የሚሩት በሥሩ ያሉትስ አባል ድርጅቶች ቆራጣ ሥልጣን አላቸው ወይ? ድምፃቸውን ይሰማል ወይ? ይደመጣሉ ወይ? ካለሰጋት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት እርግጠኝነት አላቸው ወይ? ብለን የሂደቱን ሆድ ዕቃ ስንመረምረው ምላሹ ምንም ነው።

ስለዚህ ምንም ላይ ተቀምጠን ምንም ለሆነ ምላሽ፤ በነጠረ ስሙ፤ እሱ በማያፍርበት ስሙ፤ የሽፍታው ዬወያኔ ቡድን ማለት እንጥሽት ውሃውን የሚፈስና አከርካሪውንም የሚያደቅ ስለሚሆን ደፍረን ሚዲያ ላይ አደባባይ እናውለው። እኔ እህታችሁ እንዲህ እንዲህ ማንቆለባበስ አይነካካኝም። ብዕሬም፣ አንደበቴም፣ ካሜራዬም ይጸዬፋዋል። ቆርጫለሁ። ወያኔን ጫካ እያለ ሁሉ በሚገባ አውቀዋለሁ። አጋጣሚው ሲሰጠው ጥፍሩን ከርክሞ ከአጥፊነቱ ይመለስ ይሆን ብዬም ድምጼን አጥፍቼ አዳምጨዋለሁ። ያልተፈጠረበትን ከዬት ያመጣዋል – ወያኔ?

ሰውን ያህል በፖርሳ ጥቅልል አድርገህ የማትይዘውን ግዙፍ ዬፍጥረታት አውራን እኮ ነው በጠራራ ጸሐይ ዬሌላ ሀገርን  የድንበር ክልልና ሰንድቅዓላማ፤ ዬአዬር ወሰን እዬጣሰ የሚዘርፍ – ጭራቅ እኮ ነው። ይህንን ነው ለዓለም ህዝብ በተለያዩ በራሪ ጹሑፎችና ቋንቋዎች በዝርዘር ማስረዳት ያለብን። ከነተባባሪው፣ ከነአጃቢው፣ ከነአልባሹ ማጋለጥ ያለብን። ቀኑ አሁን ነው ዳታ አያስፈልግም። ከመሬት በታች በከርስ ውስጥ ስንት ዕንባ፣ ስንት እሮሮ ተዳፍኖ ይሆን?

እርግጥ ነው  „ኢህድግ/ወያኔ“ እንዲህ በቅንፍ አድርጋችሁ የምትጽፉ ወገኖቼንም  አያለሁ። ትናንት ስላልታያችሁ ወይንም ጫካ እያለ ለማታውቁት አብሮ የሰነበተ ነገር ነው። ዛሬስ? እኮ ዛሬስ? የነፃነት ትግሉ አባወራ ጭንቅላት አንገት በጠላት እጅ ወድቆ እዬታዬ፤ በዘመቻ የነፃነት አርበኞቻችን እዬታፈሱ በገፍ ወደ ወያኔ የፍል – የጋመ ዬበቀል ጉድጓድ እዬተወረወሩ፤ ቀንበጦቻችን አድምጠን ሳንጠግባቸው ወጣቶቻችን፤ እህቶቻችን፤ ዬዕምነት መሪዎቻችን፤ ዬብሄረሰብ፤  ዬእድሜ ዬእውቀት ደረጃ፤ ሳይኖር ኑሮና መኖር እዬተጣሱ ፍቅርና ራዕይ እዬተገረደሱ ገደብ አለቦሽ ግፍ የሚፈጸምባቸው መከራ አለዬንህም አልሰማንህም ማለት እንቸችለላን? የዘመኑ ታዳሚዎች ነን —-

ታዲያ ይህንን እያዬን እንዴት ይሳነን በነጠረ አይሁድ ስሙ ወያኔን ብለን ለመጥራት ////// የሴት እሰረኞች መከራ ደግሞ ብዕርም – አንደበትም – ህሊናም – ባህልም – ትውፊትም – ተመክሮም – ደፍሮ ለመናገር አይችሉትም። ተቀብሮ የሚቀር ሚስጥር ነው። ዘመንና ታሪክም አያወጡትም – እኛ ባልነበርንበትና ባልተፈጠርንበት ውስጥ ሃቁን ለህዝብ አደባባይ አውጥቶ መጻፍ አንችልምና! ለመዳህኒተአለም – ለአውደ ምህረቱ – ለመንበሩ ለመንገርም እንኳን አቅም ያንሳል። እንኳንስ ለሚዲያ ፍጆታ ለማዋል። ሃቅ በሆነ አገላለጽ የወያኔ መሰረተ ተፈጥሮው – ሰብዕናውም ከኢትዮጵያዊነት ጠረን ውጪ ነው — እንዲህ ልከውነው። ትግራይ አኮ ለእምነቱና ለባህሉ የበዛ አክራሪ ነው። እነዚህ ከዬት እንደመጡበት፤ ከዬት እንደፈሉበት አላውቅም። የኔዎቹ በክፍል ሁለት መልሰን እስንገናኝ ድረስ መሸቢያ ሰንበት – ውድድ!

 

  • የጨረቃ ፈስ —የጨረቃ ፈስ በልጅነቴ ነው የማውቀው። መልኩ አፈር ይመስላል። ቅርጹ ድንቡልቡል ነው። መተንፈሻ የለውም። ቆዳው ስስ ነው። ስትነኩት ትንቡክ ትንቡክ ይላል። ስታስተነፍሱት የተቃጠለ ዬአፈር ጢስ ብቻ ነው። ጠረኑም ሥም -የለሽ ነው። የወያኔ ዘመንም እንደዚሁ  ነው።  የወያኔ መረጃው ሆነ ፍጥረተ ነገሩ  የተቃጠለ የአፍር ጢስ ነው።

 

እምዬ ኢትዮጵያን ከዚህ መራራ ዘመን ፈጣሪ ይታደጋት! አሜን!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop