አዬነው ጽናቱን የጴጥሮስ ህይወቱን። (ሥርጉተ ሥላሴ)

ሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ ሲዊዘርላንድ)

እንግሊዝ አደባ ቴወድሮስን ሰቶ

የቀድምት ራዕዩን ልጁን አስቀምቶ።

ምድር የተከለ የደሙ ቆይታ

በመርዝ ተጠቅልሎ —– የዘመን ስሞታ።

የታመቀ እርሙን አጥብቶ አሳድጎ

አረምን አብቅሎ አሳምሮ ጉቶ

ጽዋ ተወራርዶ ——— በቋሳ ታግቶ።

ወያኔ ደነፋ የአርሙ መንጋጋ

ጨላማም አውጇል ሊመጣ ሊነጋ።

ውሉ ተዋውሏል ተስፋ ተዚያ ማዶ

መከራን ሊቀበል———- ጀግና ጽላት ወዶ።

የለመደበትን ብረት መዝጊያነቱን

አዬነው ጽናቱን የጴጥሮስ ህይወቱን።

እኔም እለዋለሁ የአንድዬ ትውፊት

ቀራንዮ ሆኖ – ታምር ትሩፋት።

እስኪ ሆዴ ቻለው የተከዘነውን

የአባትህን ቆላ እባክህ ዝገነው።

እዩት ከዛ ማዶ የተከደነውን

እራስን በመስጠት አራሽ የሆነውን።

እልሁ መጥቶ – እኔን ሊያናግረኝ

የአንዳርጋቸው ዶግማ እኔኑ ጋገረኝ።

ጀግንነት የባቱ የዚያ የአንበሳ

ናፍቆቱን አዬነው ነፃነት ሲሳሳ።

ብቃቱ ይህ ነበር የአርበተበታቸው

የጫካን አራዊት የአንተረተራቸው።

ዘመን ይመለሳል እንደወጣ አይቀርም

ሰነብት ይቆጠራል ————————-ጠላቱን ሲቀብር።

የሀገሬ ፋፋ ዱርና ገደሉ

ደም መልሱን ላከው የአርበኛ ዝልሉ።

ይሄውልህ ተዚህ ያነ ማተበኛ

ተስፋ እንደ ጸና ሆነበት መጋኛ።

ጽጌ ትመጫለሽ — እጠብቅሻለሁ

ጉርሻሽን ለማግኘት ፍጹም —- ጓጉቻለሁ።

አታጥፊ ቃልሽን አንቺ የእኔ እመቤት

ዕንባ ተቀበይኝ የጌታዬ አንደበት።

 

ሥጦታ እራሱን ንቆ ለነፃነት ሁለመናውን ለሰጠ የጀግና ጽላት አንዳርጋቸው ጽጌ ይሁንልኝ።

ተጣፈ 11.07.2014 ሲዊዘርላንድ።

 

መፍቻ።

  • ሲሳሳ — ሲናፍቅ፣ ሲፈልግ፣ ሲመኝ፣ ሲማስን፣ ሲባትል፣ ሲደክም፣ ሲሆን፣ ሲገኝ፣ ለማለት ነው

ትርጓሜው አዎንታዊ ነው።

አራሽ —– ሰሙ ጠጋኝ፣ የተጎዳን የሚረዳ ሲሆን ወርቁ ደግሞ የነፃነት ገበሬ ለማለት ነው።

ሰሙም ሆነ ወርቁም አገባባቸው መንፈሳዊ ተዋፆን አምልካች ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተባሿል - አስቻለው ከበደ አበበ

 

 

እግዚአብሄር አምላክ ዘመነ ቋሳን ከሥሩ ነቅሎ ያሰዬን! አሜን!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Share